No summary available.
ጥቅምት 06 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ አብደላ ኢብራሂም ተጠሪ፡- አቶ ኡሶ አብዲ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለዚህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የተጀመረው በኮምቦልቻ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ የሰበር ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ። ከሳሽ ያቀረቡት ክስ ፍሬ ቃሉ:- ከተከሳሽ ከአምስት ዓመት በፊት ብር 500 ተበድሬ ገንዘቡን እስከምመልስ ድረስ ተከሳሽ መሬቴን ይዞ እንዲቆይ በመያዣ ሰጥቼው ከሁለት ዓመት በኋላ ገንዘቡን በሽማግልዎች ፊት ሰጥቼው ከለቀቀልኝ በኋላ የተቀበለውን ገንዘብ ለሽማግልዎች መልሶ እንደገና መሬቴን በመያዝ ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለቆ እንዲወጣ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
ተከሳሽ በበኩላቸው በሰጡት መልስ፡- ከሳሽን በወንድምነት ድሬው መሬቱን በስጦታ የሰጠኝ ሲሆን ለመሬቱም ከተከሳሽ የተቀበልኩት ገንዘብ የለም። በዚሁ መሬት በ1992 ዓ.ም. ጫት ተክየበት ከሁለተኛ ሚስቴ ጋር ስንጋባ የሰጠኋት በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም በሚል ተከራክረዋል።
የወረዳው ፍርድ ቤትም በሰጠው ውሳኔ፡- ከሳሽ መሬቱን በመያዣ ስለመስጠታቸው በፍ/ህ/ቁ/2005 መሰረት በጽሁፍ ማስረጃ ያላረጋገጡ ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለውም ብሐል።
የስር ከሳሽም በወረዳው ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የይግባኝ ባዩን ይግባኝ በፍብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት በመዝጋቱ የሰበር አቤቱታቸውን ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርበው ችሎቱም የግራ ቀኙን ወገን ካራከረ በኋላ በሰጠው ውሳኔ አመልካች ለጊዜው በመቸገሩ ምክንያት ብር 500 ተበድረው ይዞታቸውን ለዕዳ ማስያዛቸውን በግራቀኙ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ሲሆን በክልሉ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 130/1999 መሰረት የገጠር መሬት ይዞታን አርሶ አደር በዕዳ ለማያስዝ አይችልም፣ በስጦታም ቢሆን በአዋጁ መሰረት የገጠር መሬትን ከቤተሰብ አባል ውጪ አሳልፎ መስጠት የሚቻል አይሆንም በሚል ተጠሪ ከአመልካች የተቀበሉትን ገንዘብ እንዲመልሱና አመልካችም መሬቱን ለተጠሪ እንዲያስረክቡ ወስኗል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ ህግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን አመልካች በዋናነት የጠቀሱአቸው የቅሬታ ነጥቦችም፡የሚያከራክረውን ይዞታ አመልካች ለ11 ዓመት ይዤ የቆየሁ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም በሚል ያቀረብኩት የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ የተደረገው ተገቢ አይደለም፣ተጠሪው መሬቱን በ1992 ዓ/ም በስጦታ ያስተላለፈልኝ ስለመሆኑ ከማመኑም ልላ የቀበል ኮሚቴዎችና የአካባቢ ሽማግልዎች አረጋግጠው እያሉ እንድለቅለት የተወሰነው አግባብ አይደለም የሚሉ ናቸው።
ተጠሪውም በሰጡት መልስ፡- አመልካች ይዞታውን በስጦታ አግኝቻለሁ ይበል እንጂ የተደረገለት ስጦታ የለም፣ ብር 500 ያበደረኝ ገንዘቡን እስከምመልስ ድረስ መሬቴን በመያዣነት ይዞ ነው። የገጠር መሬትን በዕዳ ማስያዝም ሆነ ከቤተሰብ አባል ውጪ በስጦታ ማስተላለፍ እንደማይቻል በክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 የተደነገገ በመሆኑ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ ከዚህ በላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም፡- አመልካች ክስ የቀረበበትን መሬት ለቅቀው እንዲወጡ የተወሰነው በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
በወረዳ ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክርና ከቀረቡት የግራ ቀኙ ምስክሮች አመሰካከር የተረጋገጠው ፍሬ ነገር አመልካች ለተጠሪው ብር 500 በማበደር ለዚሁም የብድር ዕዳ የተጠሪውን መሬት መያዛቸውን ነው። አንድ ውል የሚጸና ውል ነው ለማለት ሶስት መሰረታዊ የሆኑ ሁኔታዎች እንደሚያስፈልጉ የፍ/ህ/ቁ.1678 የሚደነግግ ሲሆን እነዚህም ሁኔታዎች በድንጋጌው- (ሀ-ሐ) የተመለከቱት፡- ውል ለመዋዋል ችሎታ ባላቸው ሰዎች መካከል ጉድለት የልለው ስምምነት መኖር ፣ በቂ የሆነ እርግጠኛነት ያለውና ህጋዊ የሆነ ጉዳይ መሆንና፣ የውሉ አጻጻፍ ፎርም በህግ በታዘዘ ጊዜ ይህኑ ልዩ ፎርም አሟልቶ መገኘት ናቸው። ውሉ በቂ የሆነ እርግጠኛነት ያለውና ሕጋዊ የሆነ ጉዳይ ላይ መደረግ እንደሚገባው የሚያስገነዝበው በፊደል (ለ) ስር ሲሆን በህግ እንዲደረግ ያልተፈቀደ የህግ ክልከላ ባለበት ጉዳይ ላይ የተደረገ ውል ደግሞ ህገ ወጥ ውል (unlawful contract) ይሆናል። አንድ ውል የተደረገበት መሰረታዊ ጉዳይ ( object of contract) በህግ ክልከላ የተደረገበት በሆነ ጊዜ ውሉ በህግ ፊት ምንም ዓይነት ህጋዊ ውጤት የማያስከትል (void contract) ይሆናል።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስ አመልካችና ተጠሪ ባደረጉት ውል ተጠሪው የገጠር መሬት ይዞታውን በመያዣ በመስጠት ገንዘብ የተበደሩ ሲሆን መያዣ በተሰጠበት በ1992 ዓ.ም.
የክልሎች የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ባለመውጣቱ ተፈጻሚ የነበረው የአዋጅ ቁጥር 89/1989 ነው። በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 2(3) በተሰጠው ትርጉም መሰረት ‹‹ የይዞታ ባለመብት ›› ማለት ማንኛውም አርሶ አደር የገጠር መሬትን ለግብርና ሥራ ለማዋል ፣ለማከራየት እና ይዞታው ጸንቶ ባለበት ጊዜ ለቤተሰብ አባሉ ለማውረስ የሚኖረው መብት ሲሆን ይህም አርሶ አደሩ በጉልበቱ ወይም በገንዘቡ ንብረት ማፍራትና ይህንኑ ንብረት መሸጥ፣መለወጥና ማውረስ እንደማይጨምር የተጠቀሰ ሲሆን አርሶ አደሩ የይዞታ መሬቱን በዕዳ እንዲያስይዝ በህግ መብት አልተሰጠውም። አዋጅ ቁጥር 89/1989 ከተሻረ በኋላ በሥራ ላይ ባለው አዋጅ ቁጥር 456/97 በአንቀጽ 8(2) የገጠር መሬት መብትን አርሶ አደሮች በከፊል አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች እነርሱን በማያፈናቅል መልኩ ልላ አርሶ አደር ወይም ባለሀብት በክልሎች የገጠር መሬት አስተዳደር በሚወጣው አዋጅ የጊዜ ገደብ ከይዞታቸው ላይ ለተፈላጊው ልማት በቂ የሆነ መሬት የማከራየት መብት የሰጣቸው ሲሆን በዚሁ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ 5 ደግሞ ማንኛውም ባለይዞታ የገጠር መሬት የመጠቀም መብቱን ለቤተሰብ አባል የማውረስ መብት እንዳለው ተደንግጓል። በዚህ በተጠቀሰው አዋጅም ቢሆን ባለይዞታ የሆነ አርሶ አደር ይዞታውን ላለበት ዕዳ በመያዣነት እንዲያስይዝ ወይም በስጦታ ለቤተሰብ አባል ላልሆነ ሰው ለማስተላለፍ መብት አልተሰጠውም። አሁን በስራ ላይ ባለው የክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999ም ቢሆን የገጠር መሬትን በመያዣነት መስጠትም ሆነ ከቤተሰብ አባል ወጪ በስጦታ ማስተላለፍ የማይቻል መሆኑን ይደነግጋል። በመሆኑም አመልካች ለተጠሪው ገንዘብ ሰጥተው መሬቱን በመያዣ ከያዙ በኋላ በስጦታ አግኝቻለሁ በሚል ያቀረቡት ክርክር የቤተሰብ አባል መሆናቸውን ባላረጋገጡበት ከመሆኑም ልላ በህግ ባልተሰጠ መብት የገጠር መሬትን መያዣ በማድረግ ገንዘቡን ያበደሩ ስለሆነ ውሉ ህገ ወጥ ( unlawful contract) ነው። ህገ ወጥ ውል ደግሞ በፍ/ህ/ቁ/1716 መሰረት በህግ ፊት ውጤት የማይኖረው ፈራሽ ውል ነው።
ልላው ከዚህ ጋር ተያይዞ ምላሽ ማግኘት ያለበት አመልካች ያቀረቡት የይርጋ ክርክር ነው።
አመልካች ይርጋውን መቃወሚያ ያደረጉት ይዞታውን በ1992 ዓ.ም. ይዤ ለ11 ዓመት የጫት ተክል በመትከል የምገለገልበት ነው በሚል ነው። በእርግጥ የመሬት ይዞታውን ከ1992 ዓ.ም.
ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት ድረስ መያዛቸውን ክርክሩ ያመለክታል። ይሁን እንጂ ይህ ችሎት በሰበር መ/ቁ/ 43226
No topics extracted.