No summary available.
ጥር 13 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ፍሬ ሕይወት መብራህቱ ገ/መድህን ጠበቃ ኃይሉ ደቤሣ ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ አንድ የልላ ሰው የማይንቀሳቀስ ንብረትን ይዞ ሲጠቀም የነበረ ሰው ቤቱን ለማደስ ወጪ ማውጣቱ ቢረጋገጥ ውጪውን የቤቱ ሕጋዊ ባለቤት የሆነው ሰው የሚተካበት ሕጋዊ አግባብ መኖር ያለመኖሩንና በሕጉ ላሟሉ ስለሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችን የሚመለከት ነው።ክርክሩ በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲጀመር ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች ሲሆኑ ተከሳሾች ደግሞ የአሁኑ ተጠሪዎች ናቸው።የአመልካች ክስ ተጠሪዎች ወደ አሜሪካን አገር ሲሄዱ ንብረትነቱ የተጠሪዎች የሆነውንና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለል ክፍለ ከተማ ቀበል 01/02 ክልል ውስጥ የሚገኘውን በቁጥሩ 593 የሚታወቀውን ቤት ይዘው ሲኖሩ የእድሳትና የማሻሻያ ፈቃድ በማውጣት የቤቱን ይዞታ በማሻሻል ከፍተኛ ወጪ ማውጣታቸውን ገልፀውና ወጪ የወጣባቸውን ምክንያቶችን አይነትና የወጪውን መጠን በመዘርዘር በድምሩ ብር 265,812.92(ሁለት መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ስምንት መቶ አስራ ሁለት ብር ከዘጠና ሁለት ሳንቲም) ማውጣታቸውን ጠቅሰው ከቤቱ ግምት ጋር ተቻችሎ የቤቱ ስመ ሃብቱ እንዲዞርላቸውና ከቤቱ ግምት የሚተርፈውን ወጪ ደግሞ ተጠሪዎች እንዲተኩላቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት ጠይቀዋል።የአሁኑ ተጠሪዎች ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስም የአመልካች የወጪ ይተካልኝ ጥያቄ የህግ መሰረት የልለው መሆኑንና ወጪውም የተጋነነ መሆኑን ጠቅሰው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል። ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር በመስማትና ተገቢ ነው ያለውን ማጣራትም አድርጎ ጉዳዩን በመመርመር አመልካች ቤቱን ይዘው እድሳት አደረግሁ በሚሉበት ጊዜ ተጠሪዎች በቤቱ ላይ ህጋዊ መብት እንደነበራቸውና ቤቱን የመመለስ ህጋዊ ግድታ ያለባቸው መሆኑን እያወቁ እድሳት ማድረጋቸውና እድሳቱም አስፈላጊነቱ ታምኖበት የተደረገ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ያለመቅረቡን በምክንያትነት ይዞ ሁሉንም የወጪ ድምር ለአመልካች እንዲከፈል መወሰን ተገቢነት የልለው መሆኑን ገልጾና የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2169፣2170 እና 2174 ድንጋጌዎችን በዋቢነት ጠቅሶ በርትዕ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ለአመልካች እንዲተካላቸው ሲል ወስኗል።በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ጸንቷል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የተጠሪዎችን ቤት ለማደሳቸው ተረጋግጦ የወጪው መጠንም በሁለት አካላት ተጣርቶ በአንደኛው አካል ብር 42,338.80፣በልላኛው የመንግስት አካል ደግሞ ብር 63,942.43 መሆኑ ተረጋግጦ እያለ የስር ፍርድ ቤት አነስተኛውን የወጪ ግምት እንኳን ሳይዝ በመቅረት በርትዕ ብር 15,000.00(አስራ አምስት ሺህ ብር) ብቻ ለወጪ እንዲታሰብ ማድረጉ ያላግባብ ስለሆነ ውሳኔው ተሽሮ አመልካች በስር ፍርድ ቤት በጠየቁት መሰረት እንዲወሰንላቸው ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም አመልካች አወጣሁ የሚሉት ወጪ በሁለት አካላት ተገምቶ በቀረበበት ሁኔታ አነስተኛው ግምት ሳይያዝ ታልፎ በርትዕ ብር 15,000.00 ብቻ እንዲከፈላቸው ተብሎ መወሰኑ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎችም ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በጽሑፍ በሰጡት መልስ የአመልካች ቅሬታ የመሰረታዊ ሕግ ስህተት ያለበት ያለመሆኑና የሕግ መሰረትም የልለው መሆኑን ዘርዝረው የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እንዲፃናላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል።አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባበነት ካላቸው ድንጋጌዎች አንፃር ጉዳዩን ለሰበር ሰሚ ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር ብቻ በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች በተጠሪዎቸ ላይ ክስ ላመሰርት የቻለው ተጠሪዎች አሜሪካን አገር ሲሄዱ የተጠሪዎች ንብረት የሆነውን ቤት ይዘው ሲጠቀሙ በቆዩበት ጊዜ ቤቱን ለማደስና ለማሻሻል ወጪ በማውጣታቸው ወጪው እንዲተካላቸው፣ ከቤቱ ግምትና አመልካች ከአወጡት ወጪ አንጻርም ሲታይ ወጪው ከፍተኛ በመሆኑ ስም ሃብቱ ለአመልካች ላዛወር ይገባል በሚል ምክንያት ነው።ተጠሪዎች የአመልካችን ወጪ የሕግ መሰረት የልለው መሆኑን ጠቅሰው ተከራክረውም ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት በጉዳዩ ላይ የቀረቡትን የግራ ቀኙን ክርክሮችንና ማስረጃዎችን እንዲሁም ፍርድ ቤቱ በራሱ ተነሳሽነት የወጪው መጠን በሚመለከታቸው አካላት ተገምቶ እንዲቀርብለት በማድረግና ከሕግ ጋር በማገናዘብ የአመልካችን አብዛኛውን ጥያቄ ውድቅ አድርጎ በተጠሪዎች ላተካላቸው የሚገባውን የወጪ መጠን በርትዕ የወሰነ መሆኑን ከውሳኔው ይዘት ተመልክተናል።የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን የወጪ ይተካልኝ ጥያቄ ውድቅ ያደረገው አመልካች ወጪ ያወጡት ቤቱ ለተጠሪዎች የሚመለስ መሆኑን በሚያውቁበት ወቅት መሆኑንና ወጪውም አስፈላጊ የነበረ ስለመሆኑ ያለመረጋገጡን በምክንያትነት ይዞ ሲሆን ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው ፍርድ ቤትም ቤቱ ባይታደስ ኑሮ በጠቅላላ በቤቱ ይዘት ላይ ጉዳት ይደርስበት የነበረ ስለመሆኑ አመልካች ያቀረቡት ማስረጃ ያለመኖሩንና ቤቱ ስለተጎዳ የቤቱን ህልውና ለማቆየት በቅን ልቦና አድሼአለሁ የሚል ክርክርም አመልካች ያላቀረቡ መሆኑን በምክንያትነት ይዞ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቶታል።
በመስረቱ ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች ያሉት ያላግባብ ስለመበልጸግ ጉዳይን በሚገዙት ደንቦች ስር ሲሆን ለጉዳዩ ቀጥተኛ አግባብት ያለው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2168 ድንጋጌ ይዘት ሲታይም አንድ ሰው ለተወሰነ ጊዜ በእጁ ያቆየውን እቃ እንዲመለስ የተገደደ እንደሆነ ለሕግ ወይም ለውል ተቃራኒ የሚሆን ድንጋጌ ከልለ በቀር የተባለውን እቃ ከመለዋወጥ የተነሳ ያሉት መብቶችና ግድታዎች ከድንጋጌው ቀጥለው ባሉት ደንቦች መሰረት የሚወሰን መሆኑን የሚያስገነዝብ ሲሆን በዚሁ ድንጋጌ ስር ከሰፈሩት ደንቦች መካከል አንዱ የሆነው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2169 ስር የተቀመጠው ደግሞ የያዘውን እቃ እንዲመልስ የተገደደ ሰው በእቃው ላይ ያደረገው ወጪ ላመለስለት የሚገባው ወጪው የግድ አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ ስለመሆኑና ወጪው አስፈላጊ ሳይሆን ከቀረ ወይም ወጪው እቃውን እንዲመለስ በተገደደው ሰው ወይም ተገዳጁ ኃላፊ በሚሆንበት ሰው ጥፋት ምክንያት ከሆነ ወጪው ላመለስ የማይችል መሆኑን ያሳያል።ሕጉ በአንቀጽ 2171(1) ስርም ለእቃው የተደረገው ወጪ የእቃውን ዋጋ ግምት ከፍ አድርጎት እንደሆነም እቃውን ለመመለስ የተገደደው ሰው ስለዚሁ ጉዳይ ያወጣው ገንዘብ ላመልስለት እንደሚገባ የደነገገ ሲሆን ይህ ወጪ በክፉ ልቦና ስለመደረጉ የተረጋገጠ ወይም ርትዕም የሚያስገድድ ከሆነ ደግሞ ዳኞች ወጪውን ለመቀነስ ወይም ጭራሹን ለማስቀረት የሚችሉበት አግባብ መኖሩንን የተጠቃሹ ድንጋጌ ቀጣይ የሆነው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2172((1) ይዘት ያሳያል።ይህ ድንጋጌ አንድን ወጪ በክፉ ልቦና የተደረገ ነው ለማለት የሚቻልበት አግባብም ወጪው በተደረገበት ጊዜ ወጪውን የሚጠይቅ ሰው እቃውን ለመመለስ ግድታ ያለበት መሆኑን ያውቅ እንደነበረ ወይም ማወቅ ይገባው የነበረና ርትዕም ሲያስገድድ መሆኑን በመለኪያነት አስቀምጧል። ስለሆነም እነዚህ ድንጋጌዎች ሲታዩ አንድ ሰው የልላ ሰው ንብረት ይዞ ሲጠቀም ከቆየና ንብረቱን በሚጠቀምበት ጊዜ ንብረቱን ከጥፋት ወይም ከብልሽት ለማዳን ሲል ተገቢውን ወጪ ቢያወጣ ይኼው ወጪ በሕጋዊ ባለሃብቱ እንዲተካለት መጠየቅ የሚችልበት አግባብ የሚኖረው ወጪው የግድ አስፈላጊ ከሆነና በቅን ልቦና የተደረገ መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የሚያስገነዝቡ ሲሆን በክፉ ልቦና የተደረገ ስለመሆኑ የተረጋገጠውን ወጪ ግን እቃውን እንዲመለስ የተደረገ ሰው ላቀነስበት ወይም ጭራሹንም ዳኞች ላያስቀሩት የሚችሉ ስለመሆኑ ሕግ ስልጣን የሰጣቸው መሆኑን ድንጋጌዎች ያስረዳሉ።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስም አመልካች የተጠሪዎችን ቤት ይዘው ሲኖሩ ወጪውን ያወጡት ቤቱን ለተጠሪዎች የመመለስ ግድታ ያለባቸው መሆኑን በሚያውቁበት ወይም ማወቅ ይገባቸው በነበረ ጊዜ መሆኑና ወጪውንም በክፉ ልቦና ያደረጉት መሆኑን ፍሬ ነገሩን ለማጣራትና ማስረጃን ለመመዘን ስልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ጉዳይ ሲሆን ይህ ችሎትም በኢ.ፍ.ዲ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀፅ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 10 አግባብ ከተሰጠው ስልጣን አንጻር በበታች ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮችን እንዳሉ የሚቀበላቸው ሁኖ አግኝቷል።ከዚህ አንጻር በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡን ፍሬ ነገሮችን ይዘን ጉዳዩን ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2169፣2171 እና 2172 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ጋር አገናዝበን ስንመለከተው አመልካች አወጣሁ የሚሉት ወጪ ሙሉ በሙሉ ላተካላቸው ይገባ የነበረ ወይም ፍርድ ቤት በሕጉ በተሰጠው ስልጣን መሰረት መቀነስ የማይችልበት ሁኖ አላገኘነውም።የስር ፍርድ ቤት በሁለት አካላት ተረጋግጦ የቀረበለት የወጪ ግምት እያለ አነስተኛ የተባለውን ብር 42,338.92 እንኳን መሰረት አድርጎ ውሳኔ ሳይሰጥ የወጪ መጠኑ ብር 15,000.00(አስራ አምስት ሺህ ብር) ብቻ እንዲሆን መወሰኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2171 እና 2172(1) ድንጋጌ መሰረት የተሰጠውን ስልጣን በመጠቀም ነው ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት የሚቻልበት ሕጋዊ ምክንያት ያለ ሁኖ አላገኘነውም።ሲጠቃለልም በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
ተሰጥቶ በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 16 ቀን 2004 ዓ.ም.
የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
አመልካች የተጠሪዎች ሕጋዊ ሃብት የሆነውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ይዘው ሲጠቀሙ አወጣሁ የሚሉት ወጪ የግድ አስፈላጊ የነበረ በመሆኑ ወይም በቅን ልቦና ያደረጉት ስለመሆኑ ያለማስረዳታቸውን መሰረት አድርገውና ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2169፣2171 እና 2172(1) ድንጋጌዎች አንጻር በመመልከት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የልለበት ነው ብለናል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
በዚህ ችሎት ህዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል። ለሚመለከታቸው አካላት ይፃፍ ብለናል።
No topics extracted.