No summary available.
ጥር 14 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- አቶ ልዑል ኪዳነማሪያም - ቀረቡ ተጠሪ፡- እነ ሰብለ ኪዳነ ማሪያም ጠበቃ ሙሉጌታ ፀግዬ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የውርስ ንብረት ይገባኛል ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች አቶ ሚካኤል ኪዳነ ማሪያምና አቶ አለም ገ/መስቀል ኪዳነ ማሪያም ከተባሉ ግለሰቦች ጋር በመሆን የሟች በሻይ ኪዳነ ማሪያምን የውርስ ንብረት በማጣራት የውርስ ንብረቱ ስመ ሀብቱ በወራሾች ስም እንዲዞር አድርገው የወራሽነት ማስረጃ በያዛቸው የአሁኑ ተጠሪዎች ይህ የወራሽነት ማስረጃ ተጠሪዎች በማያውቁት ሁኔታ በ26/07/1964 ዓ.ም.
በስጦታ ባገኙት በአዲግራት ከተማ በ43 ካ.ሜትር ላይ በሰፈረው የንግድ ቤት ጭምር ተደርጎ ይኼው ንብረት ወደ ወራሾች ስም እንዲዞር መደረጉ ያላግባብ ነው በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 አግባብ ባቀረቡት የተቃውሞ አቤቱታ ነው። የአሁኑ አመልካችና ልሎች የወራሽነት ማስረጃውን የወሰዱት ወራሾች ለተጠሪዎች የተቀውሞ አቤቱታ በሰጡት መልስም የተጠሪዎች እናት ከሟች በሻይ ኪዳነ ማሪያም ጋር ትዳር ያልነበራቸው መሆኑን ቀድሞ እስከ ክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት መወሰኑን፣ በወራሽነት ማስረጃውም የሟቹ አስራ ሶስቱ ወራሾች ተጠቅሰው መገኘታቸውን፣አከራካሪው ቤት በስጦታ ተሰጥቶናል የሚሉትም ከእውነት የራቀ መሆኑንና ስጦታ ከሆነም በውልና ማስረጃ ቀርቦ በርስተ መዝገብ ካልተመዘገበ ዋጋ የልለው መሆኑን ፣በቤቱና በቦታው ላይ ከተጠሪዎች እናት ጋር ተከራክረው የተጠሪዎች እናት መብት የልላቸው መሆኑ መረጋገጡንና ውሳኔው ያልተለወጠ መሆኑን ዘርዝረው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል። ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የወረዳው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ለክርክሩ መሰረት የሆነውን ቤት መጋቢት 26 ቀን 1964 ዓ.ም. ለተጠሪዎች ስጦታ ተደርጎ በጥር 08 ቀን 1972 ዓ;ም በቤተዘመድ ሽምግልና ጸድቆ ያለ መሆኑ እንዲሁም በፍርድ ቤት ፀድቆ እስከ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረስ ደርሶ መፅደቁ መረጋገጡን በምክንያት ይዞ አከራካሪው የንግድ ቤት ለተጠሪዎች ላሆን ይገባል ሲል በዚህ ረገድ የተሰጠውን የወራሽነት ማስረጃ ክፍል እንዲሰረዝ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካችና ልሎች ወራሾች ይግባኛቸውን ለአዲግራት ማእ/ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ ክርክሩን ያስነሳው የንግድ ድርጅት ቤት በሟች በሻይ ኪዳነ ማሪያም ስም እስከሆነ ድረስ አመልካችና ልሎች ወራሾች የያዙት የወራሽነት ሰርተፊኬት ተጠሪዎች መብታቸውን ከማስከበር የሚከለክል ምክንያት በልለበት ሁኔታ እንዲሰረዝ መወሰኑ ያላግባብ ነው፣ተጠሪዎች ንብረቱ ላይ ክስ በማቅረብ መብታቸውን ላያስጠብቁ ይችላሉ በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ውድቅ አድርጎታል። ከዚህም በኋላ ተጠሪዎች ይግባኛቸውን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ተሽሮ የወረዳው ፍርድ ቤት ውሳኔ ጸንቷል። አመልካች የሰበር አቤቱታቸው ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ንብረት ላይ ከተጠሪዎች እናት ጋር ቀድሞ ተከራክረው በፍርድ ጉዳዩ አልቆ እያለ ይኼው ታልፎ ንብረቱ የተጠሪዎች ነው ተብሎ መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ነው።አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችሎቱ ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበት ተጠሪዎች እንዲቀርቡ የተደረገ ሲሆን ተጠሪዎች ቀርበውም ግራ ቀኙ በጽሑፍ ተከራክረዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም አመልካች ጉዳዩ ቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነው በማለት ያነሱት ተቃውሞ በበታች ፍርድ ቤቶች መታለፉ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን በጭብጥነት ይዘን ጉዳዩን ተመልክተናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪዎች አመልካችና ልሎች የስር የተቃውሞ አቤቱታ ተጠሪዎች የነበሩት ወራሾች በአከራካሪው ቤት ላይ ያገኙት የወራሽነት ስርተፊኬት ማስረጃ እንዲሰረዝላቸው የሚጠይቁት በአዲግራት ከተማ በ43 ካ/ሜትር ስፋት ባለው ቦታ በሰፈረው የንግድ ቤትን በ1964 ዓ.ም. አባታቸው ሟች ባሻይ ኪዳነ ማሪያም በስጦታ የሰጧቸውና ስጦታውም በሕጉ አግባብ ፀድቆ ያለ መሆኑን ገልፀው መሆኑን፣አመልካች በንብረቱ ላይ ከተጠሪዎች ወላጅ እናት ጋር ተከራክረን ያለቀ ነው ቢሉም ፍሬ ነገሩን ለማጣራትና ማስረጃን ለመመዘን ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች ተጠሪዎች ከአመልካች እናት ጋር ሲከራከሩ የነበሩበት በልላ ንብረት ከመሆኑም በላይ ክርክሩ ተደርጓል ቢባልም ተጠሪዎችን የማይመለከት መሆኑን ጠቅሰው የአመልካችን ክርክር ያለፉት መሆኑን፣አመልካች የስጦታ ውሉ እንዲፈርስ ክስ አቅርበው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር163/1993 ግንቦት 02 ቀን 1993 ዓ.ም.
No topics extracted.
በ26/07/1964 ዓ.ም. የተደረገው ስጦታ ላፈርስ አይገባም በማለት መወሰኑን፣ከዚህ ጊዜ በፊትም በ1972 ዓ.ም. ስጦታው በሕጉ አግባብ የፀደቀ ስለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ጉዳይ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ አንድ ወራሽ ከሕግ ውጪ፤ ወራሽነት በልለው መብት ላይ የወራሽነት ሰርቲፊኬት ማስረጃ መያዙ ከተረጋገጠ ይኼው ማስረጃ ላሰረዝ እንደሚገባ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 998 ድንጋጌ ይዘት የምንገነዘበው ጉዳይ ነው። በልላ በኩል አንድ ክርክር ዳግም ክስ ላቀርብበት የማይገባው በተመሳሳይ ተከራካሪ ወገኖች በተመሳሳይ ፍሬ ነገሮችና የህግ ነጥቦች ላይ ክርክር ተደርጎ እልባት ማግኘቱ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁጥር 5(1) ድንጋጌ ይዘት ያሳያል። ከዚህ አንጻር ጉዳዩን ስንመለከተው አመልካች አከራካሪውን ቤት በተመለከተ ከተጠሪዎች እናት ጋር ክርክር አድርገው የመጨረሻ እልባት የተሰጠበት ካለመሆኑ በላይ በቤቱ ላይ ሟቹ ስጦታ ያደረጉት ልጆቻቸው ስለመሆናቸው የተረጋገጠው ለተጠሪዎች በመሆኑ የተጠሪዎች እናት በንብረቱ ላይ መብት የላቸውም ተብሎ መወሰኑ ተጠሪዎች የሚያነሱትን የሕግ ክርክር ዋጋ የሚያሳጣበት ሕጋዊ አግባብ የለም። ይልቁንም ተጠሪዎቸ አለን የሚሉት የስጦታ ውል በተለያዩ ጊዜያአትና ፍርድ ቤቶች ጸድቆ ተጠሪዎች በአከራካሪው ንብረት ላይ መብት ያላቸው መሆኑ መረጋገጡ አመልካች እና ልሎች ወራሾች በንብረቱ ላይ የወሰዱትን የወራሽነት ማስረጃ ለመሻር ሕጋዊ ምክንያት ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 998(1) ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው። ስለሆነም አመልካች በንብረቱ ላይ በ1984 ዓ.ም. በተሰጠው ውሳኔ ተረክቤአለሁ የሚሉት የመከራከሪያ ነጥብ የክርክሩን ሂደትና ይዘት ያላገናዘበና በበታች ፍርድ ቤቶችም በዚህ ረገድ ግልፅ የሆነ መከራከሪያ ሳያቀርቡ በዚህ የሰበር ደረጃ ያነሱት አዲስ ክርክር በመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 329(1) ድንጋጌ አንጻር ተቀባይነት ላሰጠው የሚገባ ክርክር ሁኖ አላገኘነውም። ሲጠቃለልም በጉዳዩ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት የሚቻልበትን ሕጋዊ ምክንያት ስላላገኘን ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በትግራይ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ ሚያዚያ 10 ቀን 2003 ዓ.ም. ተሰጥቶ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ ሐምል 11 ቀን 2003 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
አመልካች በአከራካሪው የንግድ ድርጅት ቤት ላይ የወሰዱት የወራሽነት ሰርቲፊኬት ማስረጃ እንዲሰረዝ ተብሎ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለም ብለናል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።