No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 17 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሣ ሙስጠፋ አሕመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ውቢት ሕሩይ ተወካይ ሰብለ ገብሩ ቀረበ ተጠሪ፡- የሀዋሣ ከተማ ፋይናንስ እና ኢኮኖማ ልማት ጽ/ቤት ዐ/ሕግ አቶ ዮሐንስ አሉላ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዳይ በልሎች ወገኖች መካከል ይደረግ በነበረው የአፈፃፀም ክርክር ሶስተኛ ወገን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሰረት በቀረበው መቃወሚያ ላይ የተሰጠ ውሣኔን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በሃዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። የፍ/ባለመበት የነበረው የአሁን ተጠሪ ሲሆን የፍ/ባለእዳ ደግም የሰበር ክርክሩ አካል ያልሆነውና የአሁኗ አመልካች ባለቤት የነበረው አቶ ዝቋላ ሙሉጌታ የተባለ ግለሰብ ነው። አቶ ዝቋላ ሙሉጌታ ከልሎች ተባባሪዎቿ ጋር ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና በመገልገል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀዋሣ ቅርንጫፍ ከሚገኘው የአሁኑ ተጠሪ ሒሣብ ውስጥ ወጪ አድርገው ለወሰዱት ገንዘብ በወንጀል የተቀጡ ከመሆጉም በላይ ከተባባሪዎቹ ጋር በድምሩ ብር 3‚005‚002.03 (ሶስት ሚላዮን አምስት ሺህ ሁለት ብር 03/100) እንዲከፍል በፍ.መ.ቁ.. 09336 በ11/06/03 ውሣኔ የተሰጠበት ሲሆን ገንዘቡን ወጪ አድርገው ወስደዋል የተባሉበት ከ2001 ዓ.ም. መጨረሻ እስከ 2002 ዓ.ም. መጨረሻ አካባቢ ባለው ጊዜ ውስጥ መሆኑን መዝገቡ ያስረዳል።
የአሁኗ አመልካች በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 ድንጋጌ መሰረት በ30/10/03 ዓ.ም. የተፃፈ መቃወሚያ ያቀረበችውም ተጠሪ ከላይ የተጠቀሰውን ፍርድ ለማስፈፀም የሆነ የአፈፃፀም መዝገብ አስከፍቶ ፍ/ባለእዳው ሥም የሚታወቅ አንድ ቤት እና በፍ/ባለዕዳው ባለቤት ማለትም በአሁኗ አመልካች ስም የሚታወቅ ልላ ቤት በሀራጅ ተሽጠው ለአፈፃፀም እንዲውሉ ጥያቄ አቅርቦ ትእዛዝ በመሰጠቱ ሲሆን የመቃወሚያው ይዘትም ባጭሩ እዳው የተጋቢዎች የጋራ እና ለትዳር ጥቅም የዋለ ሣይሆን የፍ/ባለእዳው በግሉ በወንጀል ድርጊት ምክንያት ያመጣው በመሆኑ ምክንያት በፍ/ባለእዳው ስም ከተመዘገበው ቤት ውስጥ ድርሻዬ በሆነው በግማሹ ላይ እና በስሜ በተመዘገበው የግል ንብረቴ በሆነው ቤት ላይ ላፈፀም አይገባምውም የሚል ነው። የአሁኑ ተጠሪ በበኩሉ በ08/11/03 ዓ.ም. በተፃፈ መልስ በክልሉ የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 72(1)እና (2) መሰረት ንብረቱ በእንዳቸው የተመዘገበ ቢሆንም የጋራቸው እንደሆነ እንደሚቆጠር በስሟ የተመዘገበ ቢሆንም የጋራቸው እንደሆነ እንደሚቆጠር በስሟ የተዘመገበው ቤት የግል ንብረቷ ስለመሆኑ ያቀረበችው ማስረጃ እንደልለ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 79(1) እና (2) መሰረት ከተጋቢዎቹ በአንዱ ብቻ የመጣ እዳ ከተጋቢዎቹ የጋራ ሃብትና ከዚያም አልፎ እዳው ባልተሸፈነበት ጊዜ ከተጋቢዎቹ የግል ሀብት ጭምር ላከፈል እንደሚችል በዝርዝር በመግለጽ መቃወሚያው ውድቅ እንዲደረግ ተከራክሯል።
የከተማው ከፍተኛ ፍ/ቤትም የመቃወሚያ ክርክሩን ከመረመረ በኃላ ተቃዋሚዋ በስሟ የተመዘገበው ቤት የግሐ መሆኑን ስላለስረዳች ሁለቱም ቤቶች የተጋቢዎች የጋራ ሃብት ናቸው በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 79(2) መሰረተ እዳው ለጋራ ጥቅም የዋለ መሆኑን የፍርድ ባለመብቱ ስላስረዱ ተቃዋሚዋ ከሁለቱም ቤቶች ያላት ድርሻ ለእዳው መክፈያነት ላውል አይገባም በማለት ብይን ሰጥቶአል። በፍ/ባለመብቱ ጠያቂነት የቀረበለትን ይግባኝ የተመለከተው የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት በበኩሉ ክርክሩን ከሰማ በኃላ ከተጋቢዎቹ ከአንዳቸው በግል የሚጠይቀው እዳ የሚከፈለው ከባለእዳው ተጋቢ የግል ሀብት መሆኑ የግል ሃብቱ እዳውን ለመሸፈን በቂ በማይሆንበት ጊዜ በጋራ ሃብታቸው መሆኑ በክልሉ የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 79(1) ተደንግጐ የሚገኝ መሆኑን ገልፆ ግማሽ ድርሻዋ ላጠበቅላት ይገባል ሲል የሥር ፍ/ቤት ግማሽ ድርሻዋ ላጠበቅላት ይገባል ሲል የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ብይን በማሻሻል የፍ/ባለዕዳውን ንብረት እዳውን የማይሸፍን ከሆነ የጋራ ሃብታቸው ተሸጦ ለአፈፃፀም ላውል ይገባል በማለት ውሣኔ የሰጠ ሲሆን የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ሰበር ችሎትም ይህንኑ ውሣኔ አጽንቶታል።
የአሁኗ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበችው የጠቅላይ ፍ/ቤት ይ/ሰሚ እና ሰበር ችሎቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመባቸው በመሆኑ ላሻሩ ይገባል በማለት ሲሆን በ25/03/04 ዓ.ም. ተዘጋጅቶ የቀረበው የሰበር አቤቱታ ይዘትም ባጭሩ እዳው በአንዱ ተጋቢ የወንጀል ድርጊት የመጣ መሆኑ እንዳልተካደ፣ ከፍ/ባለእዳው ጋር ተጣልተው በ1999 ዓ.ም ጠፍታ ወደ ዱባይ እንደሄደች የፍ/ባለዕዳ በ2001 ዓ.ም. የመጥፋት ውሣኔ እንደተሰጠባት የመጥፋት ውሣኔ በክልሉ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 84(ሀ) መሰረት ጋብቻውን የሚያፈርስ ምክንያት እንደሆነ፣ ድጋሚ እንዳልተጋቡ፣ እዳው የመጣው ከመጥፋት ውሣኔው በኃላ ጋብቻው በፈረሰበት ጊዜ እንደሆነ እና በፍ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ.ቁ. 39837 የተሰጠው ውሣኔ ለጉዳዩ አግባብነት እንዳለው የሚከራከር ነው። ተጠሪው በበኩሉ በ08/05/04 ዓ.ም.
በተፃፈ መልስ የመጥፋት ውሣኔ ከተሰጠ በኃላ አመልካቿ ቀርባ የመጥፋት ውሣኔውን ከነ ውጤት ያሻረች በመሆኑ ምክንያት ፍቺ እንዳልተፈፀመና እዳውም የመጣው በጋብቻ ጊዜ እንደሆነ የሚቆጠረ መሆኑን ጋብቻው መፍረሱን አመልካች ያላስረዳች መሆኑን በፍ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ.ቁ. 39837 የተሰጠው ውሣኔ ጋብቻ ፀንቶ ባለበት ጊዜ በአንዱ ተጋቢ የመጣ እዳ አከፋፈልን የሚመለከት በመሆኑ ምክንያት የሚደግፈው የአመልካችን ሣይሆን የተጠራን የክርክር አቋም መሆኑን እና በነዚህም ምክንያቶች አቤቱታው የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት አለመሆኑን ገልፆ የተከራከረ ሲሆን አመልካችም በ25/05/04 የተፃፈ የመልስ መልስ ሰጥታለች።
የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን መርምረናል።
በዚህም መሰረት ለክርክሩ ምክንያት የሆነው እዳ የሥር የፍ/ባለእዳ በወንጀል ድርጊት ጭምር ጥፋተኛ በተባለበት ሁኔታ የመጣ የግል እዳ መሆኑ በተጠሪ ያልተካደና በማስረጃም የተረጋገጠ ሲሆን በአንድ በኩል በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሰረት መቃወሚያው የቀረበለት የሃዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት እና በልላ በኩል ደግሞ ጉዳዩን ቀጥለው የተመለከቱት የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችሎቶች በጉዳዩ ላይ የተለያየ ውሣኔ የሰጡት ከባል ወይም ከሚስት በግል የሚጠየቅ እዳ ላፈፀም ስለሚችልበት ሃብት በክልሉ የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 79 የተመለከተውን ድንጋጌ በተለየየ ሁኔታ በመተርጐም መሆኑን ተገንዝበናል። በመሰረቱ በድንጋጌው ውስጥ ”…..ከባል ወይም ከሚስት……..” በሚል የተቀመጠው ሐረግ መነሻ የሚያደርገው የጋብቻ መኖርን በመሆኑ ድንጋጌው ተፈፃሚነት ላኖረው የሚችለው እዳው የመጣው ጋብቻው ፀንቶ ባለበት ጊዜ መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ነው።
በተያዘው ጉዳይ አመልካች በሰበር አቤቱታ በሥር ከፍ/ባለእዳ ጋር ተጣልታ በ1999 ዓ.ም ጠፍታ ወደ ዱባይ ሃገር መሄዷን የፍ/ባለእዳው በ2001 ዓ.ም የመጥፋት ውሣኔ እንደሰጠበት፣ የመጥፋት ውሣኔው በክልሉ የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 84(ሀ) መሰረት ጋብቻን የማፍረስ ውጤት እንደሚያስከትል ከዚህ በኃላ ተመልሰው እንዳልተጋቡ እና እዳው የመጣው ከመጥፋት ወሣኔው በኋላ ጋብቻው በፈረሰበት ጊዜ እንደሆነ በዝርዝር በመግለጽ የተከራከረች ሲሆን ተጠሪውም በሰጠው መልስ እነዚህን ፍሬ ነገሮች ሣይክድ ነገር ግን አመልካች የመጥፋት ውሣኔውን ያሻረችው በመሆኑና የመጥፋት ወሣኔው መሻር ደግሞ የጋብቻ መፍረስን ጨምሮ የመጥፋት ውሣኔው ያስከተላቸውን ውጤቶች የሚሽር በመሆኑ ምክንያት ወንጀሉ የተደረገውም ሆነ እዳው የመጣው ጋብቻው ፀንቶ ባለበት ጊዜ እንደሆነ ግምት ስለሚወሰድበት እና ጋብቻው በሕጉ አግባብ የፈረሰ ስለመሆኑ ያቀረባቸው ማስረጃ ስለልለ የአመልካች ክርክር ተቀባይነት ላኖረው አይገባም በማለት ተከራክሮአል። ይሁን እንጂ የመጥፋት ውሣኔ ውጤት ማስከተል የሚያቆምባቸው ሁኔታዎች እና ጠፋ የተባለው ሰው መመለስ የሚያስከትለው ውጤት በፍ/ሕ/ቁ. 170 እና 171 የተመለከተ ሲሆን በተለይ ለተያዘው ጉዳይ ቀጥኛ አግባብነት ያለው የፍ/ሕ/ቁ. 171 የመጥፋት ውሣኔ ከተሰጠበት በኃላ የሚመለስ ሰው በንብረቶቿ ላይ የነበረውን መብት መልሶ እንደሚጐናፀፍ የሚገልጽ ከመሆኑ በስተቀር ቀደም ሲል ጋብቻ የነበረው ከሆነ ጠፋ በመባሉ ምክንያት ፈርሶ የነበረው ጋብቻው ተመልሶ ሕይወት የሚዘራ ስለመሆኑ የሚጠቁመው ነገር የለም። እንዲህ ከሆነ ደግሞ አመልካች የመጥፋት ውሣኔውን ማሻሯ የፈረሰውን ጋብቻ ከፈረሰበት ቀን ጀምሮም ሆነ ከተመለሰችበት ቀን ጀምሮ መልሶ የሚያቋቁመው ባለመሆኑ እዳው የመጣው ጋብቻው ፀንቶ ባለበት ጊዜ እንደሆነ ይገመታል በማለት ተጠሪው ያቀረበው ክርክር የሕግ መሰረት ያለው ሆኖ አልተገኘም። ጋብቻው በሕጉ አግባብ የፈረሰ ስለመሆኑ አመልካች ያቀረበው ማስረጃ የለም በማለት ከተጠሪ የቀረበውን የክርክር ነጥብ በተመለከተ ከላይ እንደተገለፀው የመጥፋት ውሣኔ የሚያስከትለው የጋብቻ መፍረስ ውጤት ዘላቂነት ያለው እንጂ ጠፋ የተባለውን ሰው መመለስ ተከትሎ የሚሰረዝ ባለመሆኑ አመልካች ማቅረብ የሚጠበቅበት ማስረጃ አይኖርም። ይልቁንም አመልካች ከተመለሰች በኃላ የቀድሞ ባለቤቷ ከሆነው የሥር የፍ/ባለእዳ ጋር አዲስ ጋብቻ ፈጽመዋል ወይም በቀድሞው ሁኔታ በትዳር መኖር ቀጥለዋል ጠማል ከሆነ ይህንን ማስረዳት የሚጠበቅበት ተጠሪው ሲሆን በዚህ ረገድ ያቀረበው ክርክርና ማስረጃ የለም።
በዚህም ሁኔታ እዳው ጋብቻው ከፈረሰ በኋላ በሥር የፍ/ባለእዳ በግል የመጣ መሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ የክልሉ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 79 ድንጋጌ ለጉዳዩ አገባብነት ላኖረው የሚችልበትም ሆነ ካልተከፍፈለው የጋራ ሃብት ውስጥ አመልካች ያላት ግማሽ ድርሻ ለእዳው ማስፈፀሚያ ላሆን የሚችልበትን የሕግ አግባብ ባለመኖሩ የሀዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ሆነ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችሎቶች ጉዳዩን ከክልሉ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 79 አፈፃፀም ጋር ያላግባብ በማያያዝ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በልላ በኩል የሐዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሥር ተቃዋሚ ከሁለቱም ቤቶች ያላት ድርሻ ለእዳው መክፈያ ላውል አይገባም በማለት ለሰጠው ውሣኔ የቤተሰብ ሕጉን አንቀጽ 79 ድንጋጌ በምክንያትነት መጥቀሱ ስህተት ቢሆንም በውጤት ደረጃ ግን ውሣኔው ተገቢ መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም የሚከተለው ውሣኔ ተሰጥቷል።
ው ሣ ኔ
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 55591 በ22/03/04 ዓ.ም. ያፀናው ውሣኔ በፍ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የሀዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 10106 በ27/11/03 ዓ.ም. የሰጠው ብይን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት በውጤት ደረጃ ፀንቷል።
መዝገቡ ተዘግቷል። ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.