No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 15 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሤ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ጀሽዋ ኤነድ ካልብ ኃ/የተ/የግል/ማህበር ጠበቃ አቶ ሙሉጌተ ገብሩ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ እንቁጣጣሽ አሰፋ ቀረቡ።
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዳይ አንድ ኃ/የተ/የግል ማህበር ስራውን የሚያከናውንበት የንግድ ቦታ መሆኑ በመታወቁ ምክንያት ብቻ በዚህ ቦታ ላይ የኪራይ መብትን እንዳቋቋመ ይቆጠራል ወይስ አይቆጠርም? በዚህ የንግድ ቦታ ላይ የኪራይ መብት የለውም፤ ከተባለ ማህበሩ ፈርሶ ሂሳብ ተጣርቶ እስኪታወቅ ድረስ በዚሁ የንግድ ቦታ ላይ የኪራይ መብት ያለው ወገን በመብቱ ላገለገልበት አይችልም ለማለት ከህግ የመነጨ መብት አለው ወይስ የለውም? የሚሉትን አከራካሪ ነጥቦች ከግራ ቀኙ ክርክርና ስለዚሁ ጉዳይ የሥር ፍ/ቤቶች ከሰጡት ውሳኔ ጋር በማገናዘብ ተመልክቶ ተገቢውን ዳኝነት ለመስጠት ሲባል የቀረበ ነው።
ለጉዳዩ መነሻ የሆነው የአሁን ተጠሪ ከኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት በኪራይ ያገኘሁትን በቂ/ክ/ከ/ቁ/15/16 ከአከራይ ድርጅት ፊት ለፊት የሚገኘውን የመናፈሻ ቦታ የአሁን አመልካች የሆነው ኃ/የተ/የግል ማህበር ያለ አግባብ ይዞ ስለሚገኝ ለቆ እንዲያስረክበኝ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረቡት ክስ ሲሆን፤ የአሁን አመልካችም ለዚህ ለቀረበበት ክስ ማህበሩ ሳይፈርስ ድርጅቱ ያለበትን ቤትና ቦታ ይለቀቅልኝ ማለት አይቻልም፤ ከሳሽ የኪራይ ውሉን ከመፈረም በቀር በቦታው ላይ አንዳችም ነገር ኢንቨስት አላደረጉም። የድርጅቱን የቤት ግንባታና የውስጥ ቁሳቁሶች ያሟሉት ከሳሽ ሳይሆኑ የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ ጃኪ አሰፋ ስለሆኑ ክሱን ያቀረቡት ያለአግባብ ነው በማለት መልስ ሰጥተውበታል።
ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ይህንኑ የግራ ቀኙን ክርክር ተመልክቶ የአሁን ተጠሪ ክርክር ያሰነሳውን የመናፈሻ ቦታ በኪራይ ያገኙት ስለመሆኑ አልተካደም ይህንኑም ከሳሽ አባል ለሆኑበት ማህበር በአይነት መዋጮ አላደረጉም ተከሳሽ በዚሁ ክርክር ባስነሳው የመናፈሻ ቦታ ወጭ አድርጎ የማልማት ሥራ ሰርቶ ከሆነ ይህንኑ ወጭ በህግ አግባብ ከሚጠይቁ በቀር የመናፈሻ ቦታው ባለመብት ላያደርገው አይችልም በማለት ወስኗል።
በአሁን አመልካች ይግባኝ ጠያቂነት ጉዳዩን በይግባኝ የመረመረው የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በበኩሉ፣ ከሳሽ የነበሩት የአሁን ተጠሪ ይህንኑ ማህበር አቋቁመው ማህበሩ በዚህ ቦታ ላይ ሥራውን እንዲሰራ ፈቅደዋል። ይህንኑ መናፈሻ ቦታ የሚፈልጉት ከሆነ መልሰው የግል ለማድረግ የሚችሉበትን ሁኔታ በመተዳደሪያ ደንብ ወይም በመመሥረቻ ፅሑፍ ላይ እንዲካተት አላደረጉም። እንደ ክሳቸው ማህበሩ ሥራውን የሚያከናውንበትን የመናፈሻ ቦታ ያስረክብ ቢባል የማህበሩን ህልውና የሚነካ፤ ጥያቄው ከማህበሩ ትርፍና ኪሣራ ጋር የተያያዘ በመሆኑና የማህበሩን ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ የሚጠይቅ በመሆኑ የእያንዳንዱ ማህበርተኛ ትርፍና ዕዳ ተለየቶ ከመታወቁ በፊት የከሳሽ የኪራይ መብት ይከበር፤ ማህበሩ ለከሳሽ ይልቀቅ በሚል ላወሰን አይገባም። የሚለውን ምክንያት በመስጠት በሥር ፍ/ቤት ከሳሽ ማህበሩ ከቤትና ከቦታው እንዲለቅ ይደረግልኝ በማለት ያቀረቡት ክስ ውድቅ ነው በማለት የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል።
በሁለተኛ ደረጃ ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የይግባኝ ሰሚውን የከፍተኛ ፍ/ቤትን ውሣኔ ሽሮ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትን ወሣኔን ያፀና የመጨረሻ ፍርድ በመስጠቱ የተነሣ ይህ የሰበር ጉዳይ ላቀርብ እንደቻለ የጉዳዩ አመጣጥ አስረጅ ነው።
በዚህ ሰበር ደረጃም በአመልካች የሰበር አቤቱታ መነሻ ክርክር ባስነሣው ቦታ ላይ ሥራውን ሲያከናውን የቆየው ማህበር ፈርሶ ሂሣቡ እንዲጣራ ተወስኖ በጉዳዩም ላይ የመጨረሻ ፍርድ ተሰጥቶበታል። በዚህም መሰረት የማህበሩ ንብረት ተጣርቶ ሳይጠናቀቅ ማህበሩ አከራካሪውን የይዞታ ቦታ ለአሁን ተጠሪ ላያስረክብ ይገባል ወይስ አይገባም? በሚል በተያዘው ነጥብ ላይ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በጽሑፍ አቅርበዋል።
እንግዲህ ጉዳዩ ከላይ ባጭሩ የተመለከተው ሲሆን፤ እኛም ይህንኑ ጉዳይ እንደሚከተለው መርምረናል።
ከላይ ባጭር ባጭሩ እንደተጠቀሰውና በየደረጃው ባሉት የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔዎች ላይ እንደተመለከተው የዚሁ ክርክር ያስነሣው የመናፈሻ ቦታ ከኪራይ ውል በመነጨ የባለይዞታነት መብት ያላቸው የአሁን ተጠሪ ስለመሆናቸው የአሁን አመልካች ክዶ ያቀረበው ክርክር የለም።
በመከላከያ መልሱ ላይ ካቀረባቸው ክርክሮች አንዱ ማህበሩ ሳይፈርስ ድርጅቱ ያለበትን ቤትና ቦታ ለቆ ለተከራይ እንዲያስረክብ ላገደድ አይችልም የሚል ነው። ማህበሩ ከመፍረሱ በፊት እንዳባባሉ የመናፈሻ ቦታውን እንዲያስረክብ ላለመገደድ ከሕግ የመነጨ መብት አለው ወይስ የለውም? የሚለው ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህ ድርጅት ወይም ማህበር በተከራይ ክስ አቅራቢነት በፍርድ ቤት እንዲፈርስ ተወስኖ በዚህ ውሣኔ ላይ ከታች ወደ ላይ ባለው የክርክር መስመር እስከ ፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ጉዳዮች አጣሪ ችሎት ደረሶ ይፍረስ በሚል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም በሚል የመጨረሻ ዳኝነት ያገኘ ጉዳይ ስለመሆኑ የአሁን አመልካች እራሱ ባቀረበው ክርክር ያረጋገጠው ጉዳይ ነው።
No topics extracted.
ስለሆነም የመናፈሻ ቦታውን እንዳስረክብ ልገደድ አይገባም ለሚለው ክርክሩ መነሻ አድርጎ ከቀረባቸው ምክንያት አንዱ የሆነው በቅደመ ሁኔታነት ያቀረበው የማህበር መፍረስ ጉዳይ እንደ ክርክሩ በፍርድ ዕልባት ያገኘ ጉዳይ እንደመሆኑ ይህ የመከራከሪያ ነጥብ ማህበሩ ስራውን ሲያከናውን የነበረበትን የይዞታ ቦታ ለቆ ለማስረከብ እንዳይገደድ ለማድረግ የሚያስችል ሳይሆን ቀሪ መሆኑን ስለሚያመለክት ጭብጥ ለመመሰረት በፍሬ ነገር መሰረትነቱ ያከተመ የክርክር ነጥብ ነው። ስለሆነም የማህበሩ ቅድሚያ መፍረስና አለመፍረስ ከሳሽ ለጠየቁት ዳኝነት አግባብነት ያለው ጉዳይ አይደለም።
ማህበሩም በፍርድ ከፈረሰ በኋላ የማህበሩ ሂሣብ በአሁኑ ሰአት አልተጠናቀቀም የሚባል ከሆነም የማህበሩ ሂሣብ ስራ የመጠናቀቁና ያለመጠናቀቁ ጉዳይ አሁን ግራ ቀኙን ካከራከረው ጉዳይ ጋር የሚያገናኘው ምክንያት አይደለም። የሂሣብ ስራው ተጠናቆ ውጤቱ ቢታወቅ ይህንኑ ከኪራይ ውል የመነጨውን የአሁን ተጠሪን መብት ቀሪ የሚያደርግበት ህጋዊ ምክንያት የለም። የሂሣብ ማጣራት ስራ የሚያስከትለው ውጤት እና የዚህ ክርክር ጉዳይ ውጤት በየራሳቸው ችለው የቆሙ እንጂ የመጀመሪያው የክርክር አይነት ለኋለኛው እንደቅድመ ሁኔታ ወይም እንደ መያዣ ሆኖ ላያገለግል የሚችል አይደለም።
ሁለተኛ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት አቅርቦ የነበረው በዚሁ የመናፈሻ ቦታ ላይ ለማስፋፋት ሥራ ከፍተኛ ወጭ አድርገው ያከናወኑት የማህበሩ ሥራ እስኪያጅ የሆኑት ልላዋ የማህበሩ አባል ናቸው እንጂ የድርጅቱ ተከራይ አይደሉም የሚለው ልላው የመከራከሪያ ነጥብ በመሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እንዳለው ይህ አይነት ወጭ ተደርጎ ከሆነ እራሱ በቻለ እኳኋን መብቱን የሚጠበቅበት በመሆኑና በሂሣብ ማጣራት ጉዳይም ተካቶ ላወሰን የሚገባው እንጂ ለዚህ ግራ ቀኙን ካከራከረው ጉዳይ አግባብነት ያለው ሆኖ አይገኝም።
ከዚህም በቀር ማህበሩ ህጋዊ ሰውነት ያለው እንደመሆኑ መጠን የዚህ ማህበር የሚጨበጥና የማይጨበጥ የሚንቀሣቀስና የማይንቀሣቀስ ንብረቶችን መብቶች ምን ምን እንደሆነ በማህበሩ መመሥረቻ ጽሑፍና በመተዳደሪያ ደንቡ የሚወሰኑ እንጂ ማህበሩ ሥራውን የሚያከናውንበት የመናፈሻ ቦታ ላይ ከኪራይ የመነጨ መብት የልለው መሆኑ እየታወቀ ማህበሩ ሥራውን የሚያከናውንበት ልላ ቦታ መኖሩ እስካልተረጋገጠ ድረስ ይህ የሥራ ቦታ ከልለ ማህበሩ ህልውና አለው ማለት አይቻልም የሚለውን ምክንያት በመያዝ ብቻ የማህበሩን መብትና ጥቅም ማቋቋም አይቻልም።
በማህበሩ መመሥረቻ ጽሑፍም ሆነ በመተዳደሪያ ደንቡ ማህበሩ የንግድ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን የንግድ ሥራውን የሚያከናውንበትን የንግድ ቦታ የመከራየት መብትንም ሁሉ አካቶ ላለመያዙ አከራካሪ ነጥብ ሆኖ አልተገኘም። ይልቁንም ከኪራይ መብት የመነጨ መብት ያላቸው የአሁን ተጠሪ ስለመሆናቸው የሥር ፍ/ቤቶች በማስረጃ ያረጋጡት የፍሬ ነገር ጉዳይም ከመሆኑ በላይ አመልካች እራሱ የካደው አይደለም።
በዚህ ሁሉ ምክንያት የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ማህበሩ የማህበሩ የስራ ቦታ በነበረው የመናፈሻ ቦታ ላይ ማህበሩ እንደማህበር ወይም የማህበሩ አባል ያወጣው ወጭ ካለ የመጠየቅ መብቱን በመጠበቅ ክርክር ያስነሳው መናፈሻ ቦታ ከኪራይ ውል የተነሣ ህጋዊ ባለይዞታ የአሁን ተጠሪ እንጂ የአሁን አመልካች አለመሆኑን አረጋግጦ የአሁን አመልካች ለቆ ለአሁን ተጠሪ ላያስረክብ ይገባል በማለት በሰጠው መጨረሻ ፍርድ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስላላገኘነው የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ/ መጋቢት 27 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው የመጨረሻ ፍርድ ፀንቷል።
በዚሁ ክርክር ባስነሳው የመናፈሻ ቦታ ላይ ማህበሩ ወይም በልላ የማህበሩ አባል አማካኝነት በማስፋፋት ረገድ የወጣ ወጭ ካለ ይህንኑ የመጠየቅ መብቱን በመጠበቅ የመናፈሻ ቦታውን የአሁን አመልካች ለአሁን ተጠሪ ለቆ ያስረክብ መባሉ ተገቢ ነው ብለናል።
በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ግራ ቀኙ ባደረጉት ክርክር ምክንያት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ በየራሳቸው ይቻሉ።
በዚህ የሰበር ጉዳይ ክርክር እስከሚጠናቀቅ በሚል በዚህ የሰበር መዝገብ ሐምል 30 ቀን 2004 ዓ.ም በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ በቀን 22/06/2003 ዓ.ም. እንደዚሁም የፍ/ጠ/ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ/ መጋቢት 27 ቀን 2004 ዓ.ም.
በሰጠው ውሳኔ መሰረት አፈፃፀም እንዳይቀጥል በሚል ተሰጥቶ የነበረው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። የዕግድ ትዕዛዙ ለተላለፈላቸው ክፍሎች ይፃፍ። መዝገቡ ተዘግቷል። ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
ት/ዘ ቤተሰብ
ህዳር 20 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሤ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ትዕግስት ሽባባው - ጠበቃቸው አቶ ኃ/ማርያም ኢትቻ ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ በአሁን የሰበር ተጠሪዎች ከሳሽነት የተጀመረው በአምቦ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁን የሰበር አመልካችም 3ኛ ተከሳሽ ነበሩ። ክሱም ሟች አባታችን ያደረጉት ኑዛዜ እኛን ህጋዊ ወራሾች የነቀለን ከመሆኑም ልላ ጉድለት ያለበት ስለሆነ ይሻርልን የሚል ነው።
3ኛ ተከሳሽም በሰጡት መልስ ሟች አባታችን ባደረጉት ኑዛዜ ያላቸውን ንብረት ለከሳሾችም ሆነ ለተከሳሾች የተናዘዙ ስለሆነ ኑዛዜው ከሳሾችን የሚነቅል ካለመሆኑም በላይ ጉድለት የልለበት በመሆኑ ላሻር አይገባም ብለዋል።
የወረዳው ፍርድ ቤትም ክርክሩ የውርስ ሀብት የሚመለከት በመሆኑ ክሱ ከመቅረቡ በፊት የውርስ ሀብቱ ተጣርቶ ድርሻ ሳይታወቅ ከሳሾች ባለመብት ሆነው ክስ ላያቀርቡ ስለማይገባ ክሱ ተቀባይነት የለውም ብሐል።
በወረዳው ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት የስር ከሳሾችም ይግባኝ ለምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ወገን በማከራከር በሰጠው ውሳኔ መልስ ሰጪዋ በወረዳ ፍርድ ቤት ደረጃ በሰጡት መልስ ውርስ ማጣራትን በተመለከተ ያቀረቡት ክርክር ሳይኖር ፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነት ከሳሾች በመጀመሪያ የሚደርሳቸውን የውርስ ንብረት ማጣራት ስለሚገባቸው ይሕው ሁኔታ በቅድሚያ ሳይፈጸም ክስ ላያቀርቡ አይገባም ያለው ተቀባይነት የለውም፣ የግራ ቀኙን ወገን የሚያከራክረው በ23/07/1996 ዓ.ም. በጽሁፍ ተደርጓል የተባለው ኑዛዜም በህጉ መሰረት በሰው ማስረጃዎች ተሟልቶ ያልቀረበ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም ሲል ውድቅ በማድረግ 1ኛ እና 2ኛ መልስ ሰጪዎች የአቶ ወርቁ ደስታ ወራሾች ስለመሆናቸው የቀረበውን የወራሽነት ማስረጃ ይግባኝ ባዮች ክደው ያልተከራከሩ በመሆኑ ይግባኝ ባዮችና 1ኛ እና 2ኛ መልስ ሰጪዎች በፍ/ህ/ቁ/842 መሰረት የሟች አባታቸውን ሀብትና ንብረት እኩል የመውረስ መብት አላቸው በሚል የወረዳውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ሽሯል።
በሥር 3ኛ ተከሳሽ ይግባኝ ጠያቂነት የግራ ቀኙን ወገን ያከራከረው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በበኩሉ መልስ ሰጪዎች እንዲሻር የጠየቁት ኑዛዜ በፍ/ህ/ቁ/882 መሰረት ሥልጣን ባለው አካል የተመዘገበ ከመሆኑም በላይ ሟች በፍላጎታቸው ያደረጉትና ወራሾችን ከውርስ የሚነቅል ባለመሆኑ ላሻር አይገባም በሚል የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ሽሯል።
የሥር ከሳሾችም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል የሰበር አቤቱታቸውን ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡ ሲሆን ችሎቱም ኑዛዜው የህጉን መስፈርት የሚያሟላ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ የግራ ቀኙን ወገን በማከራከር በሰጠው ውሳኔ ኑዛዜው በኮምፕዩተር ተጻፈ እንጂ ማን እንደጻፈው አይገልጽም፣ በፍ/ህ/ቁ/881 መሰረት በኑዛዜው አራት ምስክሮች መፈረም ያለባቸው ሲሆን በሚያከራክረው ኑዛዜ ያሉትና የፈረሙት ምስክሮች 3 ብቻ ሲሆን 4ኛው ምስክር ሆኖ የተመዘገበው የፈረመው 4ኛ ተጠሪ ነው። እንዲሁም ከፍ/ህ/ቁ 882 አንጻር ሲታይም ኑዛዜው በሬጅስትራር ወይም አንድ ምስክር ባለበት ውል ለመመዝገብ ሥልጣን ባለው ሰው ፊት ያልተደረገ እና በ23/07/1996 ልላ ቦታ ተደርጎ በ26/08/1996 ዓ.ም. የውል ምዝገባ ጽ/ቤት ማህተም የተመታበት በመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ. 881-882 የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟላ ባለመሆኑ የሚሻር ነው ሲል የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ አጽንቷል።
የሰበር አመልካችም በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል የሰበር አቤቱታቸውን ለዚህ ችሎት ያቀረቡ ሲሆን በዋናነት የጠቀሱት የቅሬታ ነጥብም፡- ለክርክሩ ምክንያት የሆነው በ23/07/1996 ዓ/ም የተደረገው ኑዛዜ በፍ/ህ/ቁ/882 ስር በተደነገገው መሰረት ለምዕራብ ሸዋ ዞን ውል ምዝገባ ጽ/ቤት ቀርቦ በ26/08/1996 ዓ.ም. ተመዝግቦ በማህተም የተረጋገጠ ህጋዊ ኑዛዜ ሆኖ እያለና ተጠሪዎችም ከውርስ ሀብት ስለመነቀላቸው ባላስረዱበት ኑዛዜው ይፈርሳል ሲል የወሰነው ተገቢ አይደለም የሚል ነው።
ተጠሪዎች በበኩላቸው በሰጡት መልስ፡- በፍ/ህ/ቁ/881 መሰረት ኑዛዜ ሲደረግ ተናዛዡ እየተናገረ ልላ ሰው ወይም ተናዛዡ ራሱ እየጻፈ በአራት ምስክሮች ፊት ተነቦ መፈረም ያለበት ሲሆን የሚያከራክረው ኑዛዜ ግን ተናዛዡ እየተናገረ ማን እንደጻፈው የሚገልጽ ካለመሆኑም ልላ ምስክሮቹም ሶስት ብቻ ሲሆኑ ከእነርሱ ውስጥም አንዱ ኑዛዜ የተደረገለት ሰው ነው፣ ኑዛዜው በፍ/ህ/ቁ/882 መሰረት የተፈጸመ ነው ለማለት ደግሞ አንድ ውል ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ሰው ሥራውን በሚያካሂድበት ክፍል ውስጥ ተደርጎ በዚያው ቀን በኑዛዜው ላይ ሁለት ምስክሮች መፈረም ያለባቸው ሲሆን የሚያከራክረው ኑዛዜ ግን በ23/07/1996 ዓ.ም.
ተደርጎ በ26/08/1996 ዓ/ም በባለሥልጣኑ ሳይፈረም ማህተም ብቻ የተደረገበት በመሆኑ ጉድለት ያለበት ነው፣ እንዲሁም ኑዛዜው ተወላጆችን (ተጠሪዎችን) የሚነቅል በመሆኑ ፈራሽ ላሆን የሚገባ ነው ሲሉ ተከራክረዋል።
አመልካች በመልስ መልሳቸው ኑዛዜው የተደረገው በፍ/ህ/ቁ/881 ሳይሆን በቁጥር 882 መሰረት በመሆኑና የተደረገውም ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ሰው ፊት ሆኖ ሶስት ምስክሮች የፈሩመበት በመሆኑ ተጠሪዎች በኑዛዜው አራት ምስክሮች ላፈርሙበት ያስፈልጋል ያሉት ተቀባይነት የለውም፣ ኑዛዜው ተጠሪዎችን ከውርስ የሚነቅላቸው አይደለም ሲሉ ክርክራቸውን አጠናክረዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ ከዚህ በላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም፡- የግራ ቀኙን ወገኖች የሚያከራክረው በ23/07/1996 ዓ.ም. ሟች ያደረጉት ኑዛዜ ላሻር የሚገባ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
ኑዛዜ በህግ ፊት የጸና የሚሆነው ህጉ ያስቀመጣቸውን መለኪያዎች አሟልቶ ሲገኝ ስለመሆኑ ይህ ችሎት በሰበር መ/ቁ/17058 የሰጠው ፍርድ ያስገነዝባል። ኑዛዜ የሚሰጥበት ሥርዓት እንደ ኑዛዜው ዓይነት የሚለያይ ነው። በዚህ ጉዳይም የግራ ቀኙን ወገኖች የሚያከራክረውን ኑዛዜ በፍ/ህ/ቁ 881 ግልጽ ኑዛዜን በተመለከተ ከተቀመጡት መስፈርቶች እና ተያያዥነት ካለው ከፍ/ህ/ቁ/882 ጋር በማገናዘብ ላመረመር የሚገባ ነው።
በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ ተናዛዡ እየተናገረ ማናቸውም ልላ ሰው ወይም ተናዛዡ የሚጽፈው ሲሆን ኑዛዜው ተናዛዡና አራት ምስክሮች ፊት መነበብ የሚገባው ነው። ይህም ስርዓት መፈፀሙና የተፃፈበት ጊዜ በኑዛዜው ላይ መጠቀስ ይኖርበታል። እንዲሁም ተናዛዡና ምስክሮቹ በኑዛዜው ላይ ወዲያውኑ ፊርማቸውን ወይም ያውራ ጣት ምልክታቸውን ማድረጋቸውን ማረጋገጡ አስፈላጊ ነው። ኑዛዜው እነዚህን መስፈርቶች አሟልቶ ካልተገኘም ፈራሽ ነው። ሆኖም በግልጽ ኑዛዜ በፍ/ህ/ቁ 881 የምስክሮች ቁጥር አራት መሆን እንደሚገባ የተደነገገ ቢሆንም በፍ/ህ/ቁ 882 በተነገረው ዓይነት የተደረገ ኑዛዜ ከሆነ ደግሞ የምስክሮቹ ቁጥር ሁለት ከደረሰ በቂ እንደሚሆን ተመልክቷል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ከምስክሮቹ መካከል አንዱ ዳኛ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ሰው ሆኖ ኑዛዜው የተደረገው ዳኛው ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ሰው ሥራቸውን በሚያካሂዱበት ክፍል ውስጥ የሆነ እንደሆነ ነው። በዚህ በተያዘው ጉዳይ ግን ኑዛዜው በፍ/ህ/ቁ 881 በተነገረው መሰረት አራት ምስክሮች ተሟልተው በተገኙበት የተደረገ ካለመሆኑም ልላ በፍ/ህ/ቁ 882 መሰረት ተደርጓል ለማለትም ውል ለመመዝገብ ሥልጣን ባለው አካል ፊት የተደረገ አይደለም። ምክንያቱም ኑዛዜው በ23/07/1996 ዓ.ም. ልላ ቦታ ተደርጎ 26/08/1996 ዓ/ም ወደ ውል ለመመዝገብ ሥልጣን ወደአለው አካል ቀርቦ ማህተም የተመታበት በመሆኑ ነው።
በህጉ ኑዛዜው ዳኛ ፊት ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ሰው ሥራውን በሚያካሂድበት ክፍል ውስጥ መደረግ አለበት ሲል በግልጽ የተደነገገውን ባለመከተል ልላ ቦታ የተደረገውን ኑዛዜ ከቆይታ በኋላ ውል ለሚመዘግበው አካል አቅርቦ ማስመዝገብ ኑዛዜው በህግ ፊት ዋጋ ያለው እንዲሆን የሚያደርግ አይሆንም። በመሆኑም ኑዛዜው ከፍ/ብ/ህ/ቁ. 881
በዋለው ችሎት የሰጠውን ውሳኔና የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/108978 በቀን 20/02/2004 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሰጠውን ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/348(1) መሰረት አጽንተናል።
ሟች በ23/07/1997 ዓ.ም. ያደረጉት ኑዛዜ የህጉን መስፈርት የሚያሟላ አይደለም በሚል የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት እና የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ውድቅ ያደረጉት በአግባቡ ነው ብለናል።
የዚህን ፍርድ ቤት ወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።