No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 29 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ አመልካች፡- አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ/ማህበር ነገረ ፈጅ ብርሃኑ ሚልካሳ ቀረበ ተጠሪዎች፡-
ይህ የሰበር ጉዳይ አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ በይርጋ የተቋረጠ ነው በሚል በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ዳኝነት በሙግት ሂደት የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች መነሻ በማድረግ ለጉዳዩ አግባብነት ካለው ድንጋጌ ጋር በማዛመድ በአግባቡ ታይቶ የተሰጠ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ለይቶ ለመወሰን ሲባል የቀረበ ነው።
ለጉዳዩ መነሻ የሆነው የአሁን አመልካች በዚህ የሰበር መዝገብ 1ኛ ተጠሪ በሚል የተሰየመው በአቶ ዋቅቶል አብደላ በብድር የወሰደውን ገንዘብ እንደውሉ መልሶ ለመክፈል የተሳነውና ያልቻለ በመሆኑ ቀሪ የብድር ገንዘብ እስከ መጋቢት 13/2ዐዐ3 የታሰበ ወለድና የወለድ ቅጣት ብር 1ዐዐ,240.74 /አንድ መቶ ሺህ ሁለት መቶ አርባ ብር ከ74/100/ በአጠቃላይ ብር 146,994.44 /አንድ መቶ አርባ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አራት ብር ከ74/100/ እንዲሁም ይኸው ዕዳ ተከፍሎ እስከሚያልቅ ድረስ ከሚታሰብ 14% ወለድ ጋር ይክፈለን 2ኛ ተጠሪ ደግሞ ተበዳሪው በብድር ለወለደው ገንዘብ አመላለስ ዋስትና ይሆን ዘንድ በዚሁ ተበዳሪ ስም በካርታ ቁጥር ዐ33/ዐዐ/88 የተመዘገበውንና በግምቢ ከተማ ቀበል ዐ3 ውስጥ የሚገኘውን ቁጥሩ 667 የሆነውን መኖሪያ ቤት የግምቢ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ከዕዳና እገዳ ነጻ መሆኑን በማረጋገጥ እና ለዚሁ ብድር የእኛ መያዣ መሆኑን መዝግቦ በማረጋገጡ ይህንኑ መያዣ ይዘን የብድር ገንዘቡን ለተበዳሪው ሰጥተናል። ሆኖም ይኸው ቤት በተበዳሪው ባለቤት በወ/ሮ ደሼ ተረፈ ስም በግምቢ ማዘጋጃ ቤት አማካኝነት ልላ ካርታ ቁጥሩ 5ዐ2/89 የሆነ ተዘጋጅቶ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሰጠው ብድር መያዣ ሆኖ በመገኘቱ ምክንያት የልማት ባንኩ በሰጠው ብድር ምክንያት ይህንኑ ቤት የተረከበው መሆኑን አረጋግጠናል። ስለሆነም ማዘጋጃ ቤቱ በፈፀመው ጥፋት ምክንያት ጉዳት እንዲደርስብን ያደረገ ስለሆነ ለዕዳው ተጠያቂ በመሆኑ ከዋናው ተበዳሪ ጋር በአንድነትና በነጠላ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ እንዲከፍል ይወሰንልን በማለት ያቀረበው ክስ ነው።
በዚህ ክስ መነሻ 1ኛ ተከሳሽ የነበረው ዋናው ተበዳሪ አሁን በ1ኛ ተራ ቁጥር በተጠሪነት የተጠቀሰው ተከራካሪ ለክሱ ምክንያት የሆነው ነገር ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ 1ዐ ዓመት ካለፈው በኋላ ክሱ የቀረበ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 መሰረት በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ሲከራከር የአሁን 2ኛ ተጠሪ በሁለተኛ ተከሳሽነቱ በሰጠው መልስ ላይ ባንኩ በእኛ ላይ ክስ ለማቀረብ አይችልም ንብረቱን መውሰድ ይቻላል በማለት በፍሬ ነገሩ ረገድ ከመከራከሩ በቀር እንደተከሰሰ የይርጋ ክርክርን ጠቅሶ ያቀረበው ክርክር እንዳልነበረ የስር ፍ/ቤቶች በሰጡት ውሣኔ ላይ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው።
ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የምዕራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በሁለቱም ተከሳሾች ላይ የቀረበው ክስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 እና 3058 መሰረት በይርጋ ውድቅ ነው በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሣኔ መነሻ የአሁን አመልካች ክሱ በይርጋ ቀሪ ላሆን እንደማይገባ ገልፆ ከታች ወደ ላይ በተዋቀሩት ፍ/ቤቶች ያቀረበው ክርክር ተቀባይነትን ያላገኘ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰጠው የመጨረሻ ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ላታረም ይገባል በማለትና ምክንያቱን በመዘርዘር ባቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ ጉዳዩ ግራ ቀኙ ባሉበት በሰበር ሰሚ ችሎት ላታይ የሚገባ መሆኑ ተጠቅሶ መጥሪያ ለ1ኛው ተጠሪ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ የተሰጠው ቢሆንም ይህንኑ የሰበር ሰሚ ችሎቱን መጥሪያ በእራሱ ቸልተኝነት ወጭ አድርጎ ያለመውሰዱና ይህም ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 7ዐ/መ/ አንጻር ታይቶ ጥቅምት 28 ቀን 2ዐዐ5ዓ.ም በዋለው ችሎት በአሁን 1ኛ ተጠሪ ላይ ያቀረበው የሰበረ ክርክር ተሰርዞ ቀሪ ነው በሚል በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠውን ዳኝነት አግባብነት በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ላታይ የሚችል ሆኖ አላገኘነውም።
በልላ በኩል አመልካች የአሁኑን ሁለተኛ ተጠሪ አስመልክቶ ይኸው 2ኛ ተጠሪ ይርጋን በሚመለከት በስር የከፍተኛ ፍ/ቤት በነበረው ክርክር ጊዜ በማንሳት ያልተከራከረበት ስለሆነ ክርክር ባልቀረበበት ጉዳይ በዚሁ ተከራካሪ ወገን ላይ ያቀረብነው ክስ በይርጋ ውድቅ ነው መባሉ አግባብ አይደለም በማለት ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በይግባኝ የመከራከሪያ ነጥብነቱ ሲያቀርብ የአሁን 2ኛ ተጠሪ ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በሰጠው መልስ ስለይርጋ ጉዳይ 1ኛ ተከሣሽ የነበረው በማንሳት የተከራከረበት ስለሆነ እኛም እንድናነሳ አይጠበቅብንም በማለት ተከራክሯል።
No topics extracted.
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤትም በስር ከፍተኛው ፍ/ቤት ከሳሽ የነበረው የአሁን አመልካች በሁለቱም ወገኖች ላይ በመሰረተው ክስ ሁለቱም ተከሳሾች በአንድነትና በነጠላ ኃላፊነት አለባቸው በሚል ሁለቱንም የከሰሳቸው ስለሆነ 1ኛው ተከሳሽ የነበረው ያነሳው የይርጋ ጊዜ ለሁለተኛ ተከሳሽም የሚጠቅም ይሆናል። ስለሆነም የብድር ውሉ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ መብቱን ለማስጠበቅ እንቅስቃሴ እስካደረገበት ጊዜ ድረስ 1ዐ ዓመት ያለፈው ስለሆነ በብድር ምክንያት ንብረት በመያዥነት ከተመዘገበና ይኸው የመያዣ ጉዳይ ውጤት የሚኖረው ለ1ዐ ዓመት ብቻ በመሆኑ ይህ የ1ዐ ዓመት ጊዜ ከመሙላቱ በፊት የመያዣ ውሉ እንዲታደሰ ካልተደረገ በቀር ውጤት የሚያስከትለው ለ1ዐ ዓመት ብቻ ሰለሆነ እንዲሁም ማስጠንቀቂያ ሰጠሁ የሚለው በዚሁ 1ዐ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሆኖ ስላለተገኘ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው በሚል በስር ፍ/ቤት መወሰኑ አግባብ ነው በማለት ውሣኔውን አጽንቶ ወስኗል።
ለዚህ የሰበር ጉዳይ መነሻ የሆነውም ከዚህ በላይ በተገለፀው አኳኋን የስር ፍ/ቤቶች በሰጡት ውሣኔ ላይ የአሁን አመልካች ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ነው።
እኛም በየደረጃው ያሉት ፍ/ቤቶች የሰጡትን ውስጥ ግራ ቀኙ በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት በጽሑፍ ካቀረቡት ክርክር ጋር በማገናዘብ ለጉዳዩ አወሳሰን አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች አንጻር ጉዳዩን እንደሚከተለው ተመልክተናል።
እንደተመለከትነውም የአሁን 2ኛ ተጠሪ በአንደኛ ተጠሪነት በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ከተሰየመው ጋር ተጣምሮ በተከሰሰ ጊዜ የይርጋ ክርክርን በማንሳት ያልተከራከረ ለመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች በሰጡት ውሣኔ የተረጋገጠ የፍሬ ነገር ጉዳይ ነው።
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ይኸው ተጠሪ ይርጋን ጠቅሶ ክርክር አለማቅረቡ ቢታወቅም የአንድነትና የነጠላ ኃላፊነት አለበት በሚል ከ1ኛው ተጠሪ ጋር ተጣምሮ የተከሰሰ በመሆኑ 1ኛው ተጠሪ ባነሳው የይርጋ ክርክር ተጠቃሚ መሆኑ አይቀርም የሚለውን ምክንያት በመጥቀሰ ነው ይህንኑ ተከሳሽም አስመልክቶ የቀረበው ክስ በ1ዐ ዓመት የይርጋ ጊዜ ቀሪ ነው የሚለውን ውሣኔ ላሰጥ የቻለው።
ይሁን እንጂ በተለያዩ የመሰረታዊ ህጐች ክፍል ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ወገኖች ለገንዘብ ጠያቂው ወይም ከሳሽ በመሆን ለሚሰየመው ወገን የአንድነትና የነጠላ ግድታ አለባቸው በሚል የተቀመጡት የህግ ድንጋጌዎች መብትና ግድታን በማቋቋም ረገድ ምክንያታቸውና መነሻ ሀሳባቸው ሁልጊዜም ተመሳሳይ መሆናቸው ታይቶ አይደለም የአንድነትና የነጠላው ኃላፊነት ከተለያዩ የህግ ክፍል እና ከተለያዩ ምክንያት ላመነጭ ይችላልና።
በዚህ በተያዘው ጉዳይ የአንደኛ ተጠሪ ኃላፊ ነው በሚል የቀረበው ክስ ከውል ህግ የመነጨ ሁለተኛው ተጠሪ ደግሞ ስለ ጉዳዩ ከአንደኛው ተጠሪ ጋር የአንድነትና የነጠላ ኃላፊነት አለበት በሚል የቀረበበት ክስ ከሚጠበቅበት የስራ ግድታ አንጻር የፈፀመው ድርጊት ጥፋት ነው በሚል ውል ሳይኖር በሚደረግ ኃላፊነት ህግ በሚገዛው ክፍል እንደሆነ ከግራ ቀኙ ክርክር መረዳት የምንችለው ጉዳይ ነው።
የሁለቱም ዓይነት የኃላፊነት ምንጭ ከተለያዩ የህግ ክፍል የሚነሳ እንደመሆኑ እንደቅደም ተከተሉ የይርጋ ክርክር በተነሣ ጊዜ የይርጋ ዘመናቸው ጉዳዩን እንደሚሸፍነው የህግ ክፍሉ በተቀመጠው የይርጋ ዘመን መሰረት እየታዩ የሚወሰን በመሆኑ አንዱ ያነሳው የይርጋ ክርክር ለልላውም ይጠቅመዋል ብሎ ለመተርጎም የሚቻል አይደለም። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 36 እንደተመለከተው የአንድነትና የነጠላ ኃላፊነት ያለባቸውን ወገኖች አጣምሮ መክሰስ እንደሚቻል መደንገጉም ሁለቱንም ወገኖች ለየብቻ ከመክሰስ ይልቅ በአንድ መዝገብ አጣምሮ መክሰሱ በአጭር ጊዜ እና በአነስተኛ ወጭ ጉዳዮችን ለመቋጨት ያስችላል በሚል እንጂ አንዱ ተከሳሽ የሚያቀርበው ክርክር ያለቅድመ ሁኔታ ለልላውም ተጣምሮ ለተከሰሰው ተከሳሽ ተፈጻሚነት ያለው መሆኑ ታይቶ አይደለም።
ስለሆነም በዚህ ጉዳይ 1ኛው ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ያነሳው የይርጋ ክርክር በዚሁ አቅራቢ ላይ ብቻ የሚወሰን እንጂ የአሁን 2ኛ ተጠሪም እንዳቀረበው አድርጎ ለመቁጠርና ለመውሰድ የሚያስችል ህግ ባለመኖሩ 2ኛ ተጠሪ የይርጋ ክርክርን አስመልክቶ ክርክር አቅርቧል ማለት አይቻልም። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244 እንደተመለከተው የይርጋ ክርክር መቅረብ በሚገባው ጊዜ ካልቀረበ እንዳተተው ክርክር ተደርጎ ላወስድ እንደሚገባው በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 244/3/ እና በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1852 የተደነገገ ሆኖ እያለ የስር ፍ/ቤቶች የተሳሳተ የትርጉም መነሻ በመየዝ 1ኛው ተጠሪ ያቀረበው የይርጋ ጊዜ ለአሁን 2ኛ ተጠሪም የሚጠቅም ነው በማለት ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው ሲሉ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 13/ዐ7/ዐ4ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እንዲሁም የምዕራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 7866ዐ በቀን 16/ዐ9/2ዐዐ3ዓ.ም የሰጠው ብይን ሁሉ ተሽሯል።
በአሁን ሁለተኛ ተጠሪ ላይ የቀረበው ክስ በይርጋ ላታገድ ይገባል በሚል እንደ ስርአቱ ክርክር ያልቀረበበት በመሆኑ በይርጋ ቀሪ ላሆን አይገባም ብለናል።
በይርጋ ቀሪ ነው በሚል የተዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ የአሁን አመልካች ከአሁን 2ኛ ተጠሪ ከግምቢ ማዘጋጃ ቤት ጋር ያቀረበው ክርክር እና ማስረጃ ታይቶ ተገቢው ዳኝነት ይሰጥበት ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 341 መሰረት ጉዳዩን ወደ ምዕራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት መልሰናል።
የዚህ የሰበር ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ መዝገቡ ተዘግቷል።
ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።