No summary available.
ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሣ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ወ/ሪት ሚስጢር ሰለሞን በእራሱ ቀረበ መልስ ሰጪ፡- 1ኛ. አቶ ፍቃዱ ካሣሁን ቀረቡ 2ኛ. አቶ አላ ካሣሁን አልቀረቡም 3ኛ. አቶ ሙላለም ካሣሁን አልቀረቡም 4ኛ. አቶ በላይ ካሳሁን ቀረቡ 5ኛ. አቶ አባተ ካሳሁን አልቀረቡም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መረምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዳይ የቀረበው ክርክርን ለማስረዳት ሲባል የቀረበን ማስረጃ ህጋዊነት አስመልክቶ ክርክር በቀረበ ጊዜ ይኸው ክርክር ታይቶ ላወሰን የሚገባው ክርክሩ በቀረበበት ፍ/ቤት ወይስ በልላ የተለየ ፍ/ቤት የሚለውን አከራካሪ ነጥብ ከግራ ቀኙ ጉዳይ አንፃር ተመልክቶ ተገቢውን ዳኝነት ለመስጠት በሚል ነው።
ለዚህ ጉዳይ መነሻ የሆነው የአሁን አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረቡት ክስ ሲሆን የክሱም ይዘት ከአባቴ በውርስ ላገኝ የሚገባውን በአባቴ በአቶ ሰለሞን ካሳሁን ስም ተመዝግበው የሚታወቁትን በየካ ክ/ከተማ ቀበል 06/02 በቁጥር 020 የሚታወቀውን ቤት እና የሰልዳ ቁጥሩ 01-4142 አ.አ የሆነውን መኪና ይዘው ስለሚገኙ እነዚህ ንብረቶች ላይ መብት የልላቸው ስለሆነ እንዲያስረክቡን ቢጠየቁ አባቴ መጋቢት 10 ቀን 1986 ዓ.ም አድርጎታል ባሉት የቁም ስጦታ ለእናታቸው ያስተላለፉና እነሱም የእናታቸው ወራሽ ስለሆኑ በንብረቱ ላይ መብት እንደላቸው ገልፀው ለማስረክብ እምቢተኛ ሆነዋል። ይሁን እንጂ ይኸው የቁም ኑዛዜ ስጦታ በአባቴ ያልተፈረመ እና በአደራረግም ረገድ በህግ ተቀባይነት የለውም የሚሉበትን ምክንያት በመጥቀስ በንብረቱ ላይ መብት አያሰጥም። ስለሆነም የዚሁኑ ንብረቶች ካስገኙት የኪራይ ጥቅም ጋር እንዲያስረክቡ ይወስንልኝ የሚል ነው።
ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም በዚህ ክስ መነሻ የአሁኑ ተጠሪዎች ያላቸውን ክርክር እንዲያቀርቡ ካደረገና የመልሳቸውንም ዝርዝር ይዘት ሳይመለከት መልሳቸውን በጥቅል ከጠቀሰ በኃላ በፍ/ብ/መ/ በሆነው መዝገብ ሐምል 07 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጉዳዩን መርምሮ፡- ተደረገ የተባለውን የቁም ስጦታ ህጋዊ ነው? አይደለም? ላፈርስ ይገባል አይገባም? የሚለውን አይቶ ለመወሰን ስልጣን ያለው ልላ ፍ/ቤት ነው። ከሳሽ ሰነዱ በህግ ፊት ተቀባይነት የለውም ከሚሉት በቀር ስልጣን ባለው ፍ/ቤት አቅርበው ፈራሽ ነው በሚል የተወሰነበትን ውሳኔ አላቀረቡም በዚህም ግራ ቀኙ በሚከራከሩበት ፍ/ቤት ይኸው የቁም ስጦታ እንዲፈርስ ይደረግልን በማለት አልጠየቁም ስለሆነም በዚህ ሰነድ አማካኝነት ለሶስተኛ ወገን የተላለፈን ንብረት የአውራሽ አባቴ ስለሆነ ለእኔ ይገባል በማለት ያቀረቡት ክስ ተገቢነትም ሆነ የህግ መሰረት የለውም በማለት ወስኗል።
ይህም ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 በተመለከተው መሰረት በፍሬ ነገርም ሆነ በህግ ረገድ ግድፈት ያለበት ባለመሆኑ ሰርዘለሁ በማለት ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ዳኝነት በመስጠቱ የተነሳ የአሁን አመልካች ለዚህ የሰበር ምክንያት የሆነውን፡ የሰበር አቤቱታ አቅረበዋል። በዚህ ሰበር ደረጃም ክርክር ባስነሳው “የቁም ስጦታ ላይ ክርክር ቀርቦበት እያለ ከሳሽ አላስፈረሰቺውም በሚል የአሁን አመልካች ክስ ውድቅ መድረጉ አግባብ ነው? አይደለም? በሚለው ጭብጥ ላይ ግራ ቀኙ ያላቸውን ክርክር በፅሁፍ አቀርበዋል።
እንግዲህ የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ ባጭሩ የተመለከተው ሲሆን እኛም ጉዳዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
ከክርክሩ ይዘት እንደተረዳነው የአሁን አመልካች ክሱን ለፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረቡት ለክሱ ምክንያት የሆነው ቤትና መኪና ግምት መነሻው በማድረግ ክርክሩ በያዘው የገንዘብ መጠን ላይ የተወሰነን የስልጣን ዓይነት መሰረት ነው። በዚህም መሰረት ከሳሽ የክስ አቀራረብ ሥርዓት ከአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 14(1) አንፃር ሲታይ በእርግጥ ክሱ የቀረበው ጉዳዩን አይቶ ለመወሰን የስረ ነገር ስልጣን ባለው ፍ/ቤት በመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 16 ፣ 9 ፣231(1)(ለ) አንፃር ሲታይ ከስልጣን አንፃር ሥርዓቱን ጠብቆ የቀረበ ሲሆን፣ በዚህ ረገድም ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት ክሱን አልነቀፈውም፤ የአሁን ተጠሪዎችም ክርክር አላነሱበትም።
ከላይ በተገለፀው አኳኋን አንድን ጉዳይ ተቀብሎ ለማየትና ለመወሰን የስረ-ነገር ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት የቀረበን ክርክር ለማስረዳት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223 የቀረበን የሰነድ ማስረጃ ህጋዊነትን አስመልክቶ የሚቀርብን ክርክር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 246 ፣ 247 ፣ 248 እንደተደነገገው አከራካሪ ነጥብ ያስረዳ መሆኑ ታውቆ ክርክሩ በሚሰማበት የክርክር ደረጃ (at the trail stage) በግራ ቀኙ የቀረበውን ክርክር እና ለክርክሩ አግባብነት ያለውን ህግ ተፈፃሚ በማድረግ በዚያው ክሱ በቀረበለት ፍ/ቤት የሚወሰን እንጂ ክርክርን በማስረዳት የቀረበን ማስረጃ ብቻ በመነጠል የዚህን ያለአግባብ የተነጠለውን የማስረጃ ህጋዊነት በሚመለከት በልላ ፍ/ቤት ቀርቦ እንዲታይ በማድረግ የሚያስችል ሥርዓት አልተዘረጋም።
No topics extracted.
ግራ ቀኙ በየፊናቸው ያቀረቡት ክርክር ተመልክቶ ለመወሰን ይኸው የቁም ስጦታ ህጋዊነት (validity) ከማስረጃ አቀራረብ ሥርዓት አንፃር አይቶ እና ለይቶ በመወሰን ላይ የተመረኮዘ እንደመሆኑ መጠን የአሁን አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ በቀረቡት ክስ ውስጥ ይኸው የቁም ሥጦታ ሰነድ እንዲፈርስ ይወሰንልን በማለት የተለየ ዳኝነት እንደጠየቁ የሚያስገድድ የክርክር አቀራረብ ሥርዓትም የለም።
በዚህ ሁሉ ምክንያት አከራካሪ ሆኖ የተገኘውን የቁም ኑዛዜ ሰነድ ህጋዊነት አስመልክቶ የአሁን አመልካች ለዚህ የሰበር ጉዳይ ምክንያት በሆነው ክስ ላይ ማቅረብ አይችሉም፤
ላያቀርቡ የሚችሉት እራሱን በቻለ የዳኝነት ጥያቄ በልላ ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት ላሆን ይገባል በሚል የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍድራልየመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 07/11/2003 ዓ.ም. የሰጠው ብይን፤ እና ይህ ብይን በአግባቡ የተሰጠ ነው በሚል ይግባኝ ሰሚው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/ ህዳር 18 ቀን 2004 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
ክርክር ያስነሳው የቁም ስጦታ ሰነድ ህጋዊ መሆንና አለመሆኑ ክሱ በቀረበለት ፍ/ቤት የሙግት ደረጃውን ጠብቆ ከግራ ቀኙ ክርክርና ለጉዳዩ አግባብነት ካለው ህግ ጋር ተገናዝቦ ላወሰን የሚገባ ስለሆነ በዚሁ መሰረት የዘጋውን መዝገብ አንቀሳቅሶ ጉዳዩን ተመልክቶ ተገቢውን ዳኝነት ይሰጥበት ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343(1) መሰረት ጉዳዩን ወደ ፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መልሰናል።
በዚህ የሰበር ደረጃ የቀረበውን ክርክር ለመከታተል ግራ ቀኙ ያወጡት ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።