No summary available.
ጥር 27 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት - አልቀረቡም ተጠሪዎች፡- ወ/ሮ ህንደያ እንድሪስ ወኪል አብዲ ዓላ - ቀረበ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርምራ ሲሆን፤ መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዳይ የወጪና ኪሳራ አወሳሰን ሥርዓትን አስመልክቶ በተነሳ ክርክር ምክንያት የቀረበ ነው።
የአሁን አመልካች በቀዳሚነት የወጭና ኪሳራ ዝርዝር ጉዳይ በየትኛው ዓይነት መዝገብ ቀርቦ ላታይ ይገባል? የሚለውን አስመልክቶ ያቀረበውን ክርክር አግባብነት ተመልክተናል።
አመልካች ይህ ብር 10,000.00 እንድንከፍል የተወሰነብን የወጭና ኪሳራ ጉዳይ ላወሰን የሚገባው በአፈፃፀም መዝገብ ሆኖ ሳለ በተዘጋውና ዋናው ጉዳይ የታየበት መዝገብ ተንቀሳቅሶ መወሰኑ ተገቢ አይደለም። የአፈፃፀም መዝገቡ ደግሞ በበላይ ፍ/ቤት ታግዷል። ስለሆነም ይህ የወጭና ኪሳራ ጉዳይ የሚታይበት ሥርዓት ሳይኖር የተወሰነብን አወሳሰን ሥርዓቱን የተከተለ አይደለም በማለት ተከራክሯል።
ይሁን እንጂ በአፈፃፀም ጉዳይ ቀርቦ ላታይ የሚገባው ማናቸውም ጉዳይ አስቀድሞ ፍርድ ያረፈበት ጉዳይ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 378 ተደንግጓል።
ለአፈፃፀም ምክንያት የሆነው ፍርድ ከሚያካትታቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ፍርዱን ለማስወሰን ሲባል በክርክር ምክንያት የወጣው የወጭና ኪሳራ ጉዳይ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 183 በግልፅ ተመልክቷል።
ስለሆነም ወጭና ኪሳራን ግን እንደሚከፍል በዋናው ጉዳይ ተለይቶ ከተወሰነ በኋላ ምን ያህል መክፈል እንዳለበት ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 463 መሰረት የወጭና ኪሳራ ዝርዝር ዋናው ፍርድ ባረፈበት መዝገብ ላይ ቀርቦ ልላኛው ተከራካሪ ወገን ስለቀረበው የወጭና ኪሣራ አስፈላጊነት፤ ስለመጠኑ እና በእርግጥም ወጭና ኪሳራ ስለመውጣቱ የበኩሉን ክርክር ካቀረበ በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 464 እንደተመለከተው የወጭና ኪሳራ ልኩ ይወሰናል።
እንግዲህ የወጭና ኪሳራ አወሳሰን ሥርዓት ይህ ከላይ የተመለከተው በመሆኑ የአሁን አመልካች የወጭና ኪሳራ ጉዳይ ላወሰን የሚገባው በአፈፃፀም መዝገብ ላሆን ይገባል በማለት ያቀረበው ክርክር ህጋዊ መሰረት የልለው፣ የፍርድ አፈፃፀምን ጉዳይ መነሻ ሀሳብ መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ክርክሩ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
በልላ በኩል የስር ፍ/ቤቱ በወጭና ኪሳራ መልክ የቀረበውን እና ለጠበቃ ተከፈለ የተባለውን የጥብቅና አበል በሚመለከት በማስረጃነት የቀረበው የጥብቅና ውል ከጊዜ ቅደም ተከተል አንፃርም ሆነ ከጠበቃው ማንነት አንፃር በአስረጅነቱ ተቀባይነት የልለው መሆኑን ከገለፁ በኋላ በልላ በኩል ጠበቃ ተስፋሁን የተባለ ልላ ጠበቃ በዋናው ጉዳይ ጊዜ የነበረ መሆኑን መታመኑን እና የጥብቅና አበል መጠን ክርክር በተደረገበት የገንዘብ መጠን አስራት መነሻ ተደርጎ የቀረበውን ባለመከተል ጉዳዩን ለመከታተል ወጣ ላባል የሚችለው የጥብቅና አበል መጠን ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ነው ሲል ስለመጠኑም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 462 በፍ/ቤቱ የተሰጠውን ፍቅድ ሥልጣን ከጉዳዩ ጋር በማዛመድ ተመልክቶ የወሰነው በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል ለማለት የሚያስችል ሆኖ ባለመግኘታችን ምክንያት የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የሐረሪ ብ/ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ መስከረም 09 ቀን 2005 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የጥብቅና አበልን አስመልክቶ የሰጠው የመጨረሻ ዳኝነት ፀንቷል።
ቀደም ሲል በመ/ የተጀመረው የአፈፃፀም ክስ ታግዶ እንዲቆይ በሚል በዚህ የሰበር መዝገብ ህዳር 17 ቀን 2005 ዓ.ም. የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በዚህ የሰበር ችሎት ግራ ቀኙ ባደረጉት ክርክር ምክንያት የወጣውን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ በየራሳቸው ይቻሉ።
No topics extracted.