No summary available.
ጥር 14 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ/ማ - ነ/ፈጅ ሰለሞን ረታ ቀረበ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 43 ድንጋጌን አፈጻጸም የሚመለከት ሲሆን ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳይ የጀመረው 1ኛ ተጠሪ በአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ላይ በከፋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የመሰረተው ክስ ነው። በክሱም በቁጥር 3-05118 ደሕ በሚል መለያ በራሳቸው ንብረትነት የምትታወቀውንና የህዝብ ማመላለሻ የሆነችን መኪናቸውን ንብረትነቱ የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ የሆነውና በቁጥር UR 666 የሚታወቀው ሩሮ ማሽን በውሽውሽ ከተማ ከሚገኘው የ1ኛ ተጠሪ መኖሪያ ቤት አከባቢ በቆመችበት ሁኔታ ገጭቶ ጉዳት ያደረባት መሆኑን ጠቅሰውና ለተለያዩ ውጪዎች መዳረጋቸውን ጠቅሰው የወጪውን አይነትና መጠን ዘርዝረው በድምሩ .00 (ዘጠና ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ ሶስት ብር) እንዲከፍል ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት ጠይቀዋል።
የአሁኑ 2ኛ ተጠሪም ጉዳት አደረሰ የተባለው መኪና የራሱ መሆኑን አምኖ ተሽከርካሪው በአሁኑ አመልካች የመድን ሽፋን የተገባለት መሆኑን ጠቅሶ በክሱ ውስጥ እንዲገባ ጠይቆ የአሁኑ አመልካችም ወደ ክሱ እንዲገባ ከተደረገ በኋላ በሰጠው መልስ ከአሁኑ አመልካች ጋር ያደረገው የመድን ውል ጉዳዩን የማይሸፍነው፣መድኑ የተገባው የ2ኛ ተጠሪ ተሸከርካሪ በሶስተኛ ወገን ንብረት ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት ሳይሆን ከመንገድ ኮንስትራክሽን ስራ ጋር በተያያዘ ለሚደርስ ጉዳት መሆኑን ጠቅሶ በጉዳዩ ጣልቃ ገብቶ የሚከራከርበት አግባብ የልለ መኑን ገልፆ ለጉዳዩ ተጠያቂነት የለብኝም በማለት የተከራከረ ሲሆን በአማራጭም የጉዳት ከሳ መጠኑ የተጋነነ መሆኑን ገልጾ ተከራክሯል።ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ 2ኛውን ተጠሪ በባለንብረትነቱ በ1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪ ጉዳት አድርሷል በሚል ምክንያት፣አመልካችን ደግሞ ለጉዳዩ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ከመድን ውሉ ይዘት መረዳቱን ገልጾ ለጉዳቱ ሁለቱንም ኃላፊ ያደረጋቸው ሲሆን የጉዳት ካሳ መጠኑንም በርትዕ ወስኖ በድምሩ ብር 41,100.00 (አርባ አንድ ሺህ አንድ መቶ) በማድረግ ይህንኑ የገንዘብ መጠን ለ1ኛ ተጠሪ አመልካችና 2ኛ ተጠሪ እንዲከፍሉ ሲል ወስኗል።የአሁኑ አመልካች በውሳኔው ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለደ/ብ/ብ/ሕ/ብ/ክ/መ/ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎች አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ፀንቷል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል ያለው የመድን ሸፋን ውል ጉዳዩን የማይሸፍን ሁኖ እያለ ጉዳዩን ይሸፍናል ተብሎ አመልካች ካሳውን እንዲከፍል መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ነው።አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችሎቱ ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበት እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በሰጡት መልስ ጉዳዩን በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተገባው የመድን ሽፋን ውል የሚገዛው መሆኑን ዘርዝርው የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላፀና ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።እንደመረመረውም የችሎቱን ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ ሁኖ የተገኘው አመልካች ወደ ክርክሩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 43 መሰረት እንዲገባ ሲደረግ በሰጠው መልስ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ያደረገው ውል ጉዳዩን የማይሸፈን መሆኑን ገልጾ በተከራከረበት ሁኔታ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ በ1ኛ ተጠሪ መዝገብ ላይ ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን የሚመለከት ነው።
በ1ኛ ተጠሪ ደንበኛ መኪና ላይ ጉዳት አደረሰ የተባለው መኪና የ2ኛ ተጠሪ የነበረ ሲሆን ይህ መኪና በአሁኑ አመልካች የመድን ሽፋን የነበረው መሆኑ አልተካደም።አከራከሪው ነጥብ የመድን ሽፋን አድማሱ እስከምን ድረስና በምን ጉዳዮች ነው? የሚለው ጥያቄ ነው።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 43(1) መሰረት ወደ ክርክሩ እንዲገባ የተደረገው ሦስተኛ ወገን በክርክሩ ሂደት ላያነሳ የሚችለው ክርክር ምን ድረስ ነው የሚለውን መሰረታዊ ጥያቄ አስመልክቶ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ የሰጠውና በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀፅ 2(1) መሰረት በየትኛም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድድ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ተገቢ ሆኖ አግኝተናል። በተጠቃሾቹ መዛግብት የክርክሩ ተካፋይ ሦስተኛ ወገን የሚያቀርበው ክርክር ሁለት ፈርጅ ላይዝ የሚችል መሆኑ ተመልክቷል። ይኸውም “1ኛው ከተከሳሽ ጋር ሆኖ ድርሻ ክፍያ ወይም ስለተከሳሽ ሆኖ የካሣ ክፍያ የመክፈል ግድታ ያለበት መሆኑን ተቀብሎ በተከሳሽ እግር በመተካት ተከሳሽ ለከሳሽ ኃላፊነት የማይኖርበት መሆኑን፤
ኃላፊነት አለበት እንኳ ቢባል ላከፈል በሚገባው የካሣ መጠን ላይ ከከሳሽ ጋር ንጽጽር ማድረግ፤ መሟገት የሚችልበት ክርክር ሲሆን ልላው እና ሁለተኛው ደግሞ ድርሻ ወይም ካሣ ለመክፈል ለተከሳሽ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ግድታ የለብኝም በማለት መከራከር የሚችልበት መንገድ ነው።” ስለሆነም የድንጋጌው ይዘት ጣልቃገብ ሦስተኛ ወገን ተከሳሽ በክርክሩ ከገባ በኋላ መሟገት የሚችለው ከተከሳሽ ጋር እንጂ ከከሳሽ ጋር ለመከራከር የሚያስችለው መብት የለውም የሚለው ድምዳሜ የሕግ መሰረት የለውም የሚል ትርጉም ሰጥቷል።የሰበር ሰሚ ችሎቱ በመ/ ላይ ይህንን ትርጉም ለመስጠት መሰረት ያደረገው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ዓላማ እና የሙግት አመራር ውጤታማነት እንዲሁም የድንጋጌ ቁጥር 43(1) እና 76 እንዲሁም የመሰረታዊ ሕጉ ድንጋጌዎች ውስጥ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1896፣ 1897፣ 1908 እና 1909 አፈጻጸም እንዲሁም በንግድ ሕግ ቁጥር 687,688 እና 683 ድንጋጌዎች በክርክር አመራር ረገድ የሚፈፀሙበትን ሁኔታ እና ግብ መነሻ በማድረግ መሆኑ በፍርዱ ሀተታ ተገልጿል። ለማጠቃለል የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 43 አስፈላጊነትም ተከታታይ ክስ ሳይኖር በአንድነት እንዲታይ በማድረግ የኃላፊነት እና መጠኑን እንዲሁም ከፋዩን ወገን በመለየት የመጨረሻ እልባት መስጠት ማስቻል እንደመሆኑ በተለይ ካሣ (indemnity) የመክፈል ግድታ ያለበት አመልካችን መሰል የመድን ድርጅቶች ከከሳሹ እና ተከሳሹ ጋር የሚኖራቸውን አጠቃላይ ክርክር ማቅረብ የሚችሉ ስለመሆኑ በውሳኔው ትርጉም ሰጥቶበታል።ይሁን እንጂ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 43 መሰረት ወደ ክርክሩ እንዲገባ የሚጠራ ጣልቃ ገብ ተከራካሪ ወገን ከመነሻውም ከተከሳሹ ጋር የሕግ ወይም የውል ግንኙነት የለኝም በማለት ክርክር ከአቀረበ የክርክሩ ተሳታፊ የሚሆንበት አግባብ የለም።እንዲህ አይነት ክርክር እልባት ማግኘት ያለበት በተለየ ክስ እና የክርክር መዝገብ እንጂ ከሳሽ ባቀረበው መዝገብ ላሆን አይገባም።የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 43 ድንጋጌ አላማም እንዲህ አይነት ክርክሮችን ሁሉ በአንድ አይነት መዝገብ አጠቃልሎ ለመወሰን ነው ተብሎ አይታሰብም።ይልቁንም ጣልቃ ገብ ከመነሻውም ክዶ በተከራከረበት ጉዳይ የተከሳሽንና የጣልቃ ገብን ክርክርና ማሰረጃ ሰምቶ ውሳኔ መስጠት ከሳሽ ያቀረበው ክስ ያላግባብ ጊዜና ወጪን እንዲጨምር የማድረግ ውጤት የሚኖረው ይሆናል።ስለሆነም አመልካች ከአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ጋር ያለውን የውል ግኙነት የካደ ሁኖ እያለ ክርክሩ እንዲቀጥል ተደርጎ በውጤቱም አመልካች ለካሳው ኃላፊነት አለበት ተብሎ መወሰኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 43 ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘትና ዓላማ ጋር ባልተጣጠመ መልኩ ሁኖ ስለአገኘን በዚህ ረገድ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሥነ ስርዓት ሕግ ግድፈት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወሰነናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.