No summary available.
ታህሳስ 02 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ቤተልሄም ፋርማሲ ቲዩካል ኃ/የተ/የግል/ማህበር አልቀረበም ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነገረ ፈጅ ምህረት ኃ/የሱስ ቀረበ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዳይ የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፈል በድሀ ደንብ መሰረት የሚቀርብበትን አግባብነት የሚመለከት ነው።
የአሁን አመልካች በተጠሪ ላይ ለማቅርበው የ47,705.069 ብር (የአርባ ሰባት ሚላዮን ሰባት መቶ አምስት ሺህ ስድሳ ዘጠኝ ብር) ክስ ላከፈል የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብ ብር 429,900.69 (አራት መቶ ሃያ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር ከ69%) የሆነውን ገንዘብ ለመክፈል የገንዘብ አቅም ስለልለኝ ክሱን በድሀ ደንብ እንዳቀርብ እንዲፈቀድ ያቀረብኩት ጥያቄ ውድቅ የተደረገው ስለድህነቴ የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ሳይሰሙ ስለሆነ በዚህ ረገድ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዳኝነት ላታረም ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ተጠሪ በበኩሉ ዳኝነቱ በሕግ አግባብ የተሰጠ ስለሆነ በሰበር ላታረም የሚችል የሕግ ስህተት የለም የሚለውን ክርክሩን አቅርቧል።
እኛም ጉዳዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
ክስ ለማቅረብ የፈለገ ወገን ከፍርዱ ለሚያገኘው የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችል የገንዘብ አቅም የልለው ከሆነ ክሱን ያለዳኝነት ገንዘብ በደሀ ደንብ መሰረት የማቅረብ መብት እንዳለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 215 ተደንግጓል።
ክሱን የሚያቀርበው ወገን ድሀ በመሆኑ ምክንያት የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፈል ክሱን አቅርቦ እንዲያሰማ ላፈቅድለት ይገባል? የሚለው ጉዳይ ላለይ የሚችልበት ዝርዝር አፈፃፀም ደንቡም ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 467 እና ተከታዩ ድንጋጌዎች ተመልክቷል።
እነዚህ ደንቦች ተፈፃሚነታቸው ክስ ለማቅረብ በፈለገ የተፈጥሮ ሰውም ሆነ በሕግ ሰውነት ያላቸው ወገኖችም ጭምር ነው።
በዚህም መሰረት ድሀ ነኝ፤ መብቴን ለማስከበር ያለኝ ፍላጐቴ በዳኝነት ገንዘብ እንቅፋት ምክንያት ላሰናከል አይገባም። ስለሆነም በድሀ ደንብ መሰረት ክሱን በነፃ እንዳሰማ ይፈቀድልኝ የሚል ማናቸውም ከሳሽ ድሀ መሆኑን ላያመለክት የሚችል የሚገኝበትን የገንዘብ አቋም ማረጋገጥ ይገባዋል። ይህም ከሳሹ የሚገኝበት የገንዘብ አቋም ከተረጋገጠ በኋላ ለክሱ ላከፈል የሚገባው የዳኝነት ገንዘብ መጠን ከሳሹ ከሚገኝበት የገንዘብ አቋም አኳያ ተገናዝቦ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 467 መሰረት ድሀ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ላለይ ይገባል።
በዚህ በተያዘው ጉዳይ አመልካች የሕግ ሰውነት የተሰጠው ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ነው። ከላይ እንደተገለፀው በሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረት ድሀ መሆኑንና አለመሆኑን በመለየት በመነሻነት ላረዳ የሚችለውን ከሳሹ የሚገኝበትን የገንዘብ አቋም በቅድሚያ ላያረጋግጥ ይገባል።
ይህ ዓይነት ከሳሽም የሚገኝበትን የገንዘብ አቋም ለመረዳት በምን የገንዘብ አቋም ደረጃ ላይ ይገኛል የሚለውን ለመወሰን የሚገባው አግባብነት ባለው የንግድ ሕግ መሰረት ካልሆነ በስተቀር በሰው ማስረጃ መለየት የሚቻል አይደለም። ስለሆነም ከሳሹ የሚገኝበትን ደረጃ ለመለየት ለጉዳዩ ተቀባይነት ያለው የማስረጃ ዓይነት በንግድ ሕጉ ስለገንዘብ አቋሙ/ደረጃው ለማረጋገጥ ያስችላል ተብሎ የሚቀርበው የሰነድ ማስረጃ ነው። የሰው ማስረጃዎች ስለጉዳዩ የሚሰጡት የምስክርነት ቃል በሕግ ዓይን ተቀባይነት ያለው አይደለም።
አመልካችም ስለምገኝበት የገንዘብ አቋም ላያረጋግጥ ይችላል በሚል የኦዲት ማረጋገጫ እንዳቀረበ ገልፆ ቢከራከርም ይህ ማረጋገጫ ክሱ ከመቅረቡ 8 እና 7 ዓመት በፊት የነበረውን ሁኔታ የሚጠቅሱ በመሆኑ አሁን ያለበትን ደረጃ ላያመለክት የሚችል አይደለም።
በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 37 እንደተመለከተው የአንድ ሰው ፍትሕ የማግኘት መብቱ ላከበር የሚችለው ይህንኑ ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ ለማስፈፀም ሲባል የተቀመጡትን ዝርዝር የክስ አቀራረብ ደንብም ጭምር ተሟልቶ ከተገኘ እንደሆነ ስለጉዳዩ የተዘረጋው የሕግ ማዕቀፍ አስረጂ ነው።
በዚህ ሁሉ ምክንያት የሥር ፍ/ቤቶች ከከሳሹ ማንነት አንፃር በማየት አመልካች ድሀ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ከመለየት አንፃር የሰጡት ዳኝነት የማስረጃ አቀባበል ሥርዓትን የተከተለ ነው ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አላገኘነውም።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ በፍድራል ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍ/ቤት በጉዳዩ ላይ በፍ/ብ/ይ/መ/ ሚያዝያ 26 ቀን 2004 ዓ.ም የተሰጠው ትዕዛዝ ፀንቷል።