No summary available.
ጥቅምት 20 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ መኰንን ገ/ህይወት አመልካች፡- አቶ ጐታ ኤጀታ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ ሙደሲር ረዲ - ጠበቃ አቶ መኮንን ኪዳን ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዳዩ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 429 ድንጋጌ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ግራ ቀኙ ያቀረቡትን ክርክር ተመልክቶ ተገቢውን ዳኝነት ለመስጠት በሚል ነው።
የአሁን አመልካች በልላ ጉዳይ የፍርድ ባለእዳ ስለነበሩ ንብረታቸው የሆነውና በአዲስ አበባ አዲስ አዲስ ክ/ከተማ ቀበል 13/15 ክልል የሚገኘው ዲዲስ መድኃኒት መደብር ተሽጦ ለእዳቸው ክፍያ እንዲውል በሐራጅ እንዲሸጥ ገዥዎች ተጋብዘዋል።
በዚህም መሰረት የአሁን ተጠሪ ይህንኑ ንብረት በብር 1,000,000.00 (አንድ ሚላዮን ብር) ለመግዛት በሐራጁ ሽያጭ ተወዳድረው አሸናፊ መሆናቸው ተለይቷል።
ይሁን እንጂ ይህንኑ የግዥ ዋጋ ክፍያ ላፈጽሙ ባለመቻላቸው ሁለተኛ የሐራጅ ሽያጭ ተከናውኖ አቶ አብዱ መሐመድ ይህንኑ ንብረት በብር1,000,000.00 (አንድ ሚላዮን ብር) ለመግዛት የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ተረጋግጧል። እኒህ ሁለተኛ ገዥም እንደ አሸናፊነታቸው ያሸነፉበትን የንብረቱን ዋጋ ከፍለው ላረከቡ ባለመቻላቸው ለሶስተኛ ጊዜ የሐራጅ ሸያጭ ሲደረግ ንብረቱ በብር 265,000.00 (ሁለት መቶ ስልሣ አምስት ሺህ ብር) ተሽጧል። በዚህም የሐራጅ ሽያጭ ዋጋ የንብረቱ ሽያጭ ተከናውኗል።
ከዚህ ከኃላ የአሁን አመልካች በአንደኛ እና ሁለተኛ የሐራጅ ሽያጭ ጊዜ በሐራጅ ሽያጩ ተወዳድረው ንብረቱን በብር 1,000,000.00 (አንድ ሚላዮን ብር) ለመግዛት እንደቅደም ተከተሉ አሸናፊነታቸው ከታወቀ በኃላ በማፈግፈጋቸው ንብረቱ በሶስተኛ ሐራጅ ሽያጭ ጊዜ ባሽቆለቆለ ዋጋ በብር 265,000.00 (ሁለት መቶ ስለሣ አምስት ሺህ ብር) እንዲሸጥ ምክንያት ሆነዋል። ስለሆነም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 429 እንደተደነገገው በሐራጅ ሸያጩ ጊዜ የተከሰተውን የዋጋ ልዩነት 735,000 (ሰባት መቶ ሰላሣ አምስት ሺህ ብር) ሁለቱም በአንድነትና በነጠላ ላከፍሉ ሲገባ በሥር በበየደረጃው ያሉት ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቶች በሁለተኛው ሐራጅ ጊዜ አሸናፊነቱ የታወቀውን ብቻ ኃላፊ አድርገው በመጀመሪያው ሐራጅ ጊዜ ገዥነቱ የታወቀውን ከኃላፊነት ነፃ ማድረጋቸው ይህንኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ድንጋጌ አፈፃፀምን በአግባቡ የተከተለ አይደለም። ስለሆነም ላታረም ይገባል በማለት ባቀረቡት የሰበር ቅሬታ መነሻ ግራ ቀኙ በዚህ ሰበር ችሎት በጉዳዩ ላይ የጽሁፍ ክርክራቸውን አጠናቀው ጉዳዩ ለምርመራ የቀረበ ነው።
እኛም ጉዳዩን እንደሚከተለው ተመልክተናል። እንደተመለከትነውም በአፈፃፀም እንዲሸጥ በሐራጅ ማስታወቂያ መሰረት በሁለት ተከታታይ የሐራጅ ሽያጭ ጊዜ ሁለት ተወዳዳሪዎች ተመሣሣይ የሐራጅ መግዣ ዋጋ ካቀረቡ በኃላ ሁለቱም ይህንኑ ያሸነፉበትን ዋጋ ላከፍሉ ባለመቻላቸው ሶስተኛ ሐራጅ ተደርጎ ንብረቱ እነርሱ ካቀረቡት ባነሰ የመግዣ ዋጋ ከተሸጠ ይህንኑ የሽያጭ ዋጋ ልዩነቱን መክፈል ያለባቸው ሁለቱ ናቸው ወይስ በሁለተኛው ሐራጅ ጊዜ ተወዳድሮ ከመጀመሪያው የሐራጅ ጨረታ አሸናፊ ከሆነው ጋር ተመሣሣይ የመግዣ ዋጋ ያቀረበው ብቻ ነው? ለሚለው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 429 ድንጋጌ ቀጥተኛ ምላሽ የሚሰጥ አይደለም።
ያም ሆኖ የዚህ ድንጋጌ ግብ እና ዓላማ በሐራጅ ሽያጭ ጊዜ ተወዳድሮ አሸናፊ መሆኑ ከተረጋገጠ በኃላ እንደአሸናፊነቱ የሽያጭ ዋጋውን ባለመክፈሉ የተነሣ ለልላ ለሁለተኛ ሐራጅ መንስኤ ከሆነና በዚህም ልላ (ሁለተኛ) ሐራጅ ጊዜ ንብረቱ ከመጀመሪያው የሐራጅ ሽያጭ ዋጋ አንሶ ከተገኘ ይህን የዋጋ ልዩነት በካሣ መልክ የፍርድ ባለእዳው አዲያገኝ በማድረግ ነው።
በዚህ ጉዳይ የአሁን ተጠሪ በመጀመሪያው የሐራጅ ሽያጭ ጊዜ ለንብረቱ ብር 1,000,000.00 /አንድ ሚላዮን ብር/ የመግዣ ዋጋ አቅርቦ አሸናፊነቱ ከተለየ በኃላ ዋጋውን አለመከፈሉ እና ለሁለተኛ ሐራጅ ሽያጭ መንስኤ መሆኑ ቢረጋገጥም፤ ሁለተኛው የሐራጅ ሸያጭ ተደርጎ በዚህ ሁለተኛ የሐራጅ ሸያጭ አሸናፊ ሆኖ የተገኘው ገዥ ያቀረበው የመግዣ ዋጋ የአሁን ተጠሪ አቅርቦት ከነበረው የብር1,000,000.00 /አንድ ሚላዮን ብር/ የግዥ ዋጋ ጋር ተመሣሣይ እንጂ ያነሰ ሆኖ አልተገኘም። በዚህም የተነሣ የአሁን ተጠሪ ገዥነቱ ከታወቀ በኃላ የመግዣ ዋጋውን አለማቅረቡ በፍርድ ባለእዳው ላይ ያስከተለው ጉዳት የለም።
ከዚህም አንፃር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቶች የግራ ቀኙን ክርክር ጉዳዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 429 የተመለከተው ድንጋጌ ቀጥተኛ ምላሽ የሚሰጥ ባይሆንም ክፍተቱን ለመሙላት የአሁን ተጠሪ በመጀመሪያው ሐራጅ ጊዜ ገዥነቱን ካረጋገጠ በኋላ የግዥ ዋጋውን ባለመክፈሉ እና ለሁለተኛ ሐራጅ ሸያጭ ምክንያት መሆኑ ቢታወቅም ይህ መሆኑ በእራሱ በፍርድ ባለእዳው ላይ ያስከተለው ጉዳት እስከልለ ድረስ በሁለተኛው ሐራጅ ሽያጭ ጊዜ አሸናፊነቱ ተለይቶ ካፈገፈገውና ለሶስተኛ ሐራጅ ሽያጭ ምክንያት ሆነው ንብረቱ ባነሰ ዋጋ እንዲሸጥ ቀጥተኛ ምክንያት ከሆነው እና ለልዩነቱ ብር 735,000.00 /ሰባት መቶ ሰላሣ አምስት ሺህ ብር/ ኃላፊ ከሆነው ከአቶ አብዱ መሐመድ ጋር የአንድነትና የነጠላ ኃላፊነት የለበትም በሚል የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አላገኘነውም።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. 69945 ሐምል 08 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
በተለያዩ የሐራጅ ሸያጮች ጊዜ ለተከሰተው የዋጋ ልዩነት የአሁን ተጠሪ ለአሁን አመልካች ለመክፈል የአንድነትና የነጠላ ኃላፊነት የለበትም መባሉ በአግባብ ነው።
ብለናል።
በዚህ የሰበር መዝገብ በሰበር መ/ቁ. 72017 ጥቅምት 17 ቀን 2004 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተጠሪ ቤት ላይ ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል። ትእዛዙ ለተላፈላቸው ክፍሎች ይፃፍ።
የዚህ ሰበር ጉዳይ ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ ብለናል።