No summary available.
ታህሣሥ 04 ቀን 2005 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ሂላላ ሱልማን - ከጠበቃ ወልደስላሴ ብርቱ ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ - ነ/ፈ አሸናፊ ልጃለም ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ ለዳቦ አቅርቦት የተደረገውን የአስተዳደር ውል መሰረት አድርጎ የቀረበውን ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት መደበኛ ችሎት ሐምል 02 ቀን 2000 ዓ.ም.
በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የአመልካች ክስ ይዘት ሲታይም በመጋቢት ወር 2000 ዓ.ም.
በወጣው የዳቦ ግዥ ውስን ጨረታ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከረቢያ በC.P.O ብር 26,035.07 (ሃያ ስድስት ሺህ ሰላሳ አምስት ብር ከዜሮ ሰባት ሳንቲም) በወጋገን ባንክ ጎንደር ቅርንጫፍ አስይዘው የዳቦ አቅርቦት ውል ማሸነፋቸውን፣ በውሉም ከሚያዚያ 08 ቀን 2000 ዓ.ም. እስከ ግንቦት 19 ቀን 2000 ዓ.ም. ድረሰ ክብደቱ 125 ግራም ለሆነ አንድ ዳቦ በብር 0.80 ሂሳብ ለተጠሪ ሶስት ካምፓሶች ለቁርስ፣ ለምሳና ለእራት ለማቅረብ ስምምነት አድርገው በድምሩ 811,363 (ስምንት መቶ አስራ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ስልሳ ሶስት) ዳቦ ማቅረባቸውን፣ በዚህ ሂደት ላይ እያሉም ተጠሪ ግንቦት 07 ቀን 2000 ዓ.ም. ላይ አዲስ የዳቦ ግዥ ውስን ጨረታ አውጥቶና አመልካች በጨረታው ላይ እንዳይሳተፉ በማድረግ ለልላ ግለሰብ የዳቦ አቅርቦት ውሉን በመስጠት አዲሱ አቅራቢ ከግንቦት 20 ቀን 2000 ዓ.ም. ጀምሮ አቅርቦቱን መጀመሩን፣ አመልካች እስከ ግንቦት 19 ቀን 2000 ዓ.ም. ብር 122,534.40 (አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሰላሳ አራት ብር ከአርባ ሳንቲም) ተጠሪ ከፍሐቸው የ658,195. ዳቦ ዋጋ የሆነውን ብር 526,556.00 (አምስት መቶ ሃያ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር) ተጠሪ ያልከፈላቸውና እንዲከፍላቸው ቢጠይቃቸውም የመልካም ስራ አፈፃጸም ዋስትና መያዝ ከነበረበት መጠን በታች ነው በሚል ምክንያት ላከፍላቸው ያልቻለ መሆኑን ዘርዝረው ዳቦ አቅርበው ያልተከፈላቸው ብር 526,556.00 እና ሕጋዊ ወለዱን፣ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 26,035.07 ከክርክሩ ወጪና ኪሳራ ጋር እንዲከፍላቸው በተፋጠነ ስርዓት ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። ለክሳቸውም የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ዘርዝረው አቅርበዋል።
የአሁኑ አመልካችም ለክሱ የመከላከያ ክርክር ለማቅረብ ይፈቅድለት ዘንድ በስርዓቱ መሰረት ጥያቄ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ተቀብሎ ተጠሪ የመካላከያ ክርክርና ማስረጃ እንዲያቀርብ የፈቀደለት ሲሆን ተጠሪ ባቀረበው ክርክር ከአመልካች ጋር ውሉ መደረጉን ሳይክድ የውሉ ጊዜ ከሚያዚያ 08 ቀን 2000 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2000 ዓ.ም. ድረስ ሆኖ ተጠሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ዳቦውን ላያቀርቡና የዳቦውን ዋጋ 10% የሆነው ብር 245,036.00 (ሁለት መቶ አርባ አምስት ሺህ ከሰላሳ ስድስት ብር) ለመልካም ስራ አፈፃጸም ዋስትና ማስከበሪያ ላያስይዙ የውል ግድታ ገብተው የዳቦ ዱቄት ዋጋ ጨመረ በሚል ምክንያት አቅርቦቱን መቀጠል እንደማይችሉ ታውቆ የሰሩበት ገንዘብ ታስቦ እንዲሰጣቸው ለተጠሪ ፕሬዝዳንት በአድራሻ ግንቦት 05 ቀን 2000 ዓ.ም. መጻፋቸውን፣ ለአመልካች ሥራ አፈፃጸም ዋስትና አመልካች ላያስይዙ ይገባ የነበረው ብር 245,036.00 ሆኖ ያላስያዙና ቢያስይዙ ኑሮ በዩኒቨርሲቲው ላይ የደረሰውን ኪሳራ መተኪያ ላሆን ይችል እንደነበርና ይህ ኪሳራውን ይተካል ባይባልም ውሉ ስለሚሽር የመልካም ስራ አፈፃጸም ተቀንሶ ልላው የሰሩበት ገንዘብ ቢከፈላቸው ተቃውሞ የልለው መሆኑ የተነገራቸው መሆኑን ዘርዝሮ ይኼው ተፈፅሞ ወጪና ኪሳራ እንዲከፈል እንዲወሰንለት ገልፆ ተከራክሯል። ከዚህም በተጨማሪ ተጠሪ የተከሳሽ ከሳሽነት አቅርቧል። በዚህም ክሱ የአሁኗ አመልካች ለአርባ አንድ ቀናት ብቻ የዳቦ አቅርቦት ውሉን ፈፅመው አቅርቦቱ ለአፍታም ያህል ላቋረጥ እንደማይገባው እየታወቀ በውሉ የገቡትን ቀሪውን 114 ቀናት ዳቦውን ላለማቅረብ ግንቦት 05 ቀን 2000 ዓ/ም በጻፉት ደብዳቤ የአሁኗ አመልካች በማረጋገጣቸው ምክንያት ተጠሪ ሁለተኛ ጨረታ አውጥቶ ወ/ሮ ታደለች ጌታሁን የተባሉት ግለሰብ አንዱን ዳቦ በብር 1.31 ለማቅረብ ተጫርተው በማሸነፋቸው አመልካች አቀርባለሁ ካሉት ዋጋ በብር 0.51 ብልጫ እንዲያቀርቡ መደረጉን፣ በዚህም ምክንያት ተጠሪ ላይ ለአንድ መቶ አስራ አራት ቀሪ ቀናት የብር 0.51 ጉዳት በአንድ ዳቦ የደረሰበት ሁኖ በድምሩ ብር 1,148,846.40(አንድ ሚላዩን አንድ መቶ አርባ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ አርባ ስድስት ብር ከአርባ ሳንቲም) ኪሳራ የደረሰበት መሆኑን ዝርዝሮ ይኼው ገንዘብ እንዲከፈለው ዳኝነት ጠይቋል። የአሁኗ አመልካች ለተጠሪ የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ በሰጡት መልስም የውሉ ጊዜ ከ08/08/2000 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 19/09/2000 ዓ.ም. ድረስ እንጂ እስከ ጳጉሜ 05 ቀን 2000 ዓ.ም. ድረስ ያለመሆኑንና ከ19/09/2000 ዓ.ም. በኋለ ዳቦ ያላቀረቡበት ምክንያት ዩኒቨርሲቲው በ07/09/2000 ጨረታ አውጥቶና አመልካች በጨረታው ላይ እንዳይሳተፉ በማድረግ ከ20/09/2000 ጀምሮ ለልላ ሰው ዳቦ አቅርቦት ውሉን በመስጠቱ ሆኖ ኪሳራው የደረሰው ከአመልካች ጋር የነበረውን ውል እንዲቀጥል ተጠሪ ባለማስቻሉ ምክንያት በመሆኑ አመልካች የፈፀሙት ጥፋት ሳይኖር ለኪሳራው ኃላፊ የሚሆኑበት ሕጋዊ አግባብ የልለ መሆኑን፣ ተጠሪ በውሉ በገባው ግድታ መሰረት አመልካች ለአቀረቡት ዳቦ ዋጋውን በወቅቱ ባለመክፈሉ ምክንያትም በወቅቱ ከተከሰተው የዳቦ ዱቄት ዋጋ መናር ጋር ተዳምሮ አመልካች ግድታቸውን እንዳይወጡ የራሱን አስተዋጽኦ ማድረጉን ዘርዝረው የተጠሪ ክስ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል።
ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው ውል ጊዜው ከሚያዚያ 08 ቀን 2000 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 05 ቀን 2000 ዓ.ም. ድረስ መሆኑ መረጋገጡን፣ ለውሉ ያለመፈጸም ምክንያት የሆኑት የአሁኗ አመልካች መሆናቸውን፣ ለውሉ ያለመፈፀምም በቂና ሕጋዊ ምክንያት በአመልካች በኩል ያለመቅረቡንና ዩኒቨርሲቲው ከልላ ሰው ጋር ውል ማድረጉን ያለበትን ኃላፊነትን ለመወጣት የፈፀመው ተግባር ነው ከሚባል በስተቀር ውል ማፍረሱን እንደማያሳይ ገልፆ አመልካችን ለውሉ መፍረስ ኃላፊ ያደረጋቸው ሲሆን በተጠሪ ላይ የደረሰው ጉዳት መጠን በተመለከተም ብር 1,068,225.60 መሆኑና ከዚሁ ገንዘብ ውስጥ አመልካች ዳቦ አቅርበው በተጠሪ ያልተከፈላቸው ገንዘብ ለጨረታው ማስከበሪያና ለመልካም ስራ አፈፃጸም የተያዘባቸው ገንዘብ ሲቀናነስ ብር 797,153.93 (ሰባት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ ሶስት ብር ከዘጠና ሶስት ሳንቲም) መሆኑን ለይቶ ይህንኑ ገንዘብ ለተጠሪ ላከፍሉ ይገባል በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ሰኔ 08 ቀን 2003 ዓ.ም. በፃፉት አራት ገፅ የሰበር አቤቱታ በጉዳዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት የሚሉባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም የስር ፍርድ ቤት የውሉን ጊዜ በተመለከተ ሚያዚያ 08 ቀን 2000 ዓ/ም በቁጥር ጥበ/01/568/08/2000 የተጸፈውን ደብዳቤ መነሻ በማድረግ እስከ ጳጉሜ 05 ቀን 2000 ዓ.ም. ድረስ ነው በማለት ድምዳሜ ላይ የደረሰው የደብዳቤውን አርዕትና ይዘት ባግባቡ ሳይመለከትና የተዋዋይ ወገኖችን ሐሳብ ሳያገናዘብ መሆኑን፣ ለውሉ አለመፈፀም ምክንያቱ አመልካች ናቸው መባሉም የውሉን አንቀፅ 5.1 አና 6.2 ድንጋጌዎችን ያላገናዘበና ተጠሪ አመልካች ለአቀረቡት ዳቦ ክፍያውን በወቅቱ ያለመክፈሉን ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ መሆኑን፣በመንግስት ደረጃ እውቅና ያለው የዋጋ ግሽበት ስለመኖሩና የውሉን ሚዛን ስለማናወጡ ተረጋግጦ እያለ ይኼው ግምት ውስጥ ካለመግባቱም በላይ በውሉ አንቀጽ 8.2 እና 8.4 ድንጋጌዎች መሰረት ችግሩን ከተጠሪ ጋር በጋራ ለመፍታት አመልካች ጥያቄ አቅርበው እያለ ፈቃደኛ ያልሆነውና በውሉ ቃል መሰረት አመልካች ልፈፀም እያሉ ውሉ ሳይፈርስ በግንቦት 07 ቀን 2000 ዓ.ም. ጨረታ ያወጣው ተጠሪ መሆኑም ለውሉ መፍረስ ምክንያት የሆነውን ወገን በትክክል በመለየት ረገድ ስህተት መፈፀሙን እንደሚያመላክት፣ ውሉ ሲደረግ የዳቦ ዱቄት ዋጋ ለውጥ ይኖረዋል ተብሎ ያልተገመተ ሲሆን ውሉ የአስተዳደር ውል እንደመሆኑ መጠን በዚህ ረገድ በተደነገጉት ድንጋጌዎች እና በጠቅላላ ውል ደንቦች የሚመራ በመሆኑ ለውሉ አለመፈፀም ምክንያት የሆነውን ተግባር የፈፀመው ተጠሪ በመሆኑ ኪሳራ መክፈል የነበረባቸው አመልካች ሁነው እያለ መታለፉ ያላግባብ መሆኑንና የውሉ ማፍረሻ ምክንያት የሆኑት ጉዳዮች በውሉ ተገልፀው እያለ በአግባቡ ሳይታዩ መታለፋቸውን፣ አመልካች በሕጉ መሰረት ተጠሪን ሳያስጠነቅቅ የውሉን መሻር መብት ላሰራበት የሚችልበት ሕጋዊ አግባብ ያለመኖሩንና የኪሳራው ልክ ሲሰላም በበታች ፍርድ ቤቶች ስህተት መፈፀሙን ገልፀው የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እንዲሻርላቸው ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችሎቱ እንዲታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርቦ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበውን የክርክር ይዘት በአጭሩ ያስቀመጠ ሲሆን አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ከመስጠታቸውም በላይ ይህ ችሎትም ግራ ቀኙን ሚያዚያ 25 ቀን 2004 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በቃል አከራክሯል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችሎት ምላሽ የሚፈልጉ አበይት ጭብጦች፡-
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ፡- አመልካች ውሉ አልፈረሰም፣ ፈረሰ ከተባለም ምክንያቱ ተጠሪ ነው በማለት የሚከራከሩት የውሉ ጊዜ ከሚያዚያ 08 ቀን 2000 ዓ.ም. እስከ ግንቦት 19 ቀን 2000 ዓ.ም. እንጂ እስከ ጳጉሜ 05 ቀን 2000 ዓ.ም. ድረስ አይደለም፣ በትክክለኛው የውሉ ጊዜ የዳቦ አቅርቦት ግድታዬን ተወጥቼአለሁ፣ የዳቦ ዱቄት ዋጋ በመጨመሩ ምክንያትም ተጠሪ ጋር ለመነጋገር ተደጋጋሚ ጥረት አድርጌ ተጠሪ ጥያቄዬን በውሉ አግባብ ሳያስተናግድና በሁለተኛው ጨረታም እንዳልሳተፍ ከልክሎኛል በሚሉት ምክንያቶች ስለመሆኑ ከክርክሩ ሂደት ተገንዝበናል። ተጠሪ በበኩሉ የውሉ ዘመን ከሚያዚያ 08 ቀን 2000 ዓ.ም.
እስከ ጳጉሜ 05 ቀን 2000 ዓ.ም. ሆኖ አመልካች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ላያቀርቡ የተዋዋሉትን የዳቦ አቅርቦት የዳቦ ዱቄት ዋጋ ጨምሯል በሚል ምክንያት ከግንቦት 19 ቀን 2000 ዓ/ም በኋላ ማቅረብ እንደማይፈልጉ ግንቦት 05 ቀን 2000 ዓ.ም. ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በፃፉት ደብዳቤ በግልፅ ያሳወቁና ውሉንም ያፈረሱት አመልካች በመሆናቸው ለውሉ መፍረስ ምክንያት አመልካች ናቸው በማለት ተከራክሯል። ፍሬ ነገርንና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያለው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መደበኛ ችሎት ግን ውሉ ስለመኖሩ ሳይካድ በውሉ ጊዜ ላይ ግራ ቀኙ መካካዳቸውን ገልፆና ሚያዚያ 08 ቀን 2000 ዓ.ም. በቁጥር ጥበ/01/586/2000 በተጻፈ ደብዳቤ አቅርቦቱ እስከ ጳጉሜ 05 ቀን 2000 ዓ.ም.
ለአመልካች ተጠሪ ማሳወቁን፣ ሶስት እማኞች ባሉበት ይኼው ውል መገባቱን አረጋግጧል።
ይህ የስር ፍርድ ቤት የፍሬ ነገርና የማስረጃ ምዘና ድምዳሜ በፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትም ተመሳሳይ ድምዳሜ የተያዘበት ጉዳይ ነው። እንዲህ ከሆነ አመልካች የበታች ፍርድ ቤቶች የደብዳቤውን ይዘት በተዛባ መንገድ መመዝገባቸውና ከውል አመሰራረት ደንቦች ጋር ያለማገናዘባቸውን መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡት ክርክር የደብዳቤው ይዘት አመልካች በሚከራከሩት መልኩ ሆኖ ባለመገኘቱ ተቀባይነት የሚሰጠው አይደለም።ይልቁንም ሚያዚያ 08 ቀን 2000 ዓ.ም. የተደረገው ውል አንቀፅ 8.5 ውሉ የጨረታ ሰነዱ አካል ሆኖ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1731 እና 2005 መሰረት በሕግ ፊት የጸና ስለመሆኑ በግልፅ የሚያሳይ ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ደግሞ የውሉ ጊዜ ከሚያዚያ 08 ቀን 2000 ዓ.ም. እስከ ጳጉሜ 05 ቀን 2000 ዓ.ም. ድረስ ስለመሆኑ የተጠቀሰ በመሆኑ አመልካች የውሉን ጊዜ እስከ ግንቦት 19 ቀን 2000 ዓ.ም. ድረስ ነው በማለት የሚያቀርቡት ክርክር በ08/08/2000 ዓ.ም. የተፈረመውን የውሉን ይዘት ባግባቡ ያገናዘበ አይደለም። አመልካች በግልጽ በተደረገው ጨረታ በሚሳተፉበት ጊዜ የውሉን ጊዜ በግልጽ አውቀው የነበረ ስለመሆኑ ከውሉ ይዘት የምንገነዘበው ከመሆኑም በላይ ግንቦት 05 ቀን 2000 ዓ.ም. ለዩኒቪርሲቲው በፃፉት ደብዳቤም ለሰባት ቀናት ብቻ ኣቅርቦቱን መቀጠል እንደሚችሉ፣ ከዚያ በኋላ መቀጠል እንደማይችሉ ያሳወቁ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ተዋዋይ ወገኖች በውሉ ጊዜም ሆነ በውሉ ወቅት ያደረጓቸውን ተግባራት መነሻ በማድረግ ስለውሉ ጊዜ የነበራቸውን ሐሳብ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1734 ይዘትና መንፈስ አንፃር ሲታይ የውሉ ጊዜ እስከ ጳጉሜ 05 ቀን 2000 ዓ.ም. ድረስ ነው ብሎ ለመደምደም የሚያስችል ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች የውሉን ጊዜ ከሚያዚያ 08 ቀን 2000 ዓ.ም. እስከ ጳጉሜ 05 ቀን 2000 ዓ.ም. ድረስ ነው በማለት መወሰናቸው ከውሉ ሙሉ ይዘት፣ አመልካች ለተጠሪ ግንቦት 05 ቀን 2000 ዓ.ም. ከፃፉት ደብዳቤና ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1732፣1734 እና ስለውል አቀራረብና አቀባበል የተደነገጉትን ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ ያገናዘበ እንጂ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስላላገኘን አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረቡትን ክርክር አልተቀበልነውም።
ለውሉ መፍረስ ምክንያት ማን ነው የሚለውን ጥያቄ ስንመለከት ደግሞ አመልካች እና ተጠሪ በመካካለቸው ከሚያዚያ 08 ቀን 2000 ዓ.ም. እስከ ጳጉሜ 05 ቀን 2000 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ የዳቦ አቅርቦት ውል ማድረጋቸውና አመልካች አቅርቦቱን የቀጠሉት እስከ ግንቦት 19 ቀን 2000 ዓ.ም. ድረስ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። አመልካች ከግንቦት 19 ቀን 2000 ዓ.ም በኋላ አቅርቦቱን ያልቀጠሉት የዳቦ ዱቄት ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት ይህንኑ ችግር ተጠሪ ከአመልካች ጋር ተወያይቶ ላፈታ ባለመቻሉ ምክንያት መሆኑን ጠቅሰው ሲከራከሩ ተጠሪ በበኩሉ የዳቦ ዱቄት ዋጋ መጨመር ለውሉ መፍረስ በምክንያትነት ላጠቀስ እንደማይችልና አመልካችም አቅርቦቱን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለማቅረብ አውቀውና ወደው ግድታ መግባታቸውን ገልፆ ለውሉ መፍረስ ምክንያት አመልካች ናቸው በማለት ተከራከሯል። የበታች ፍርድ ቤቶችም አመልካች ግንቦት 05 ቀን 2000 ዓ.ም. የጻፉት ደብዳቤ ውሉን መቀጠል እንደማይችሉ በግልጽ ለዩኒቨርሲቲው ያሳወቁበት ስለመሆኑ ያረጋገጡበት ሲሆን አመልካችም ቢሆኑ ይህንኑ ደብዳቤ ይዘቱ ልላ ስለመሆኑ ሳይጠቅሱ ደብዳቤውን የጻፉበት ምክንያት ዩኒቨርሲቲው ችግሩን በጋራ ለመፍታት ዝግጁ ሁኖ ባለመገኘቱ ስለመሆኑ ገልጸው ተከራክረዋል። በእርግጥ በውሉ አንቀጽ 8 ስር ልዩ ልዩ የጋራ ሁኔታዎችን የሚገዙ ንዑስ ድንጋጌዎች የተካተቱ ሲሆን የውሉ መሻሻል በተዋዋይ ወገኖች የጋራ ስምምነት ላሆን እንደሚችል በንኡስ ቁጥር 4 ስር በግልጽ ተቀምጧል። የድንጋጌው ሙሉ ይዘት ሲታይ ይህ ውል ማሻሻያ ይደረግ ጥያቄ ቢቀርብ የሁለቱ ወገኖች ስምምነት ተጠይቆ ፈቃደኛነታቸው ከታወቀ ላሻሻል ይችላል በሚል የተቀመጠ ሲሆን ድንጋጌው ፈቃደኝነት ባለው መልኩ የተቀመጠ በመሆኑ በተዋዋይ ወገኖች የሚቀርብ የውል ይሻሻል ጥያቄ ሁል ጊዜ ተቀባይነት እንደሚኖረው ወይም ይህ ጥያቄ ቀርቦ ባለበት ሁኔታ ልላኛው ተዋዋይ ወገን በውሉ መሰረት እንዲፈፀም ቢፈልግ ይህንኑ ከማድረግ የማይከለክለው ወይም ውሉን ለማፍረስ በቅድመ ሁኔታነት መፈፀም ያለበት ጉዳይ ስለመሆኑ አስገዳጅነት ባለው መልኩ የሚያሳይ አይደለም።
በመሆኑም ተጠሪ ውሉን ያቋረጠው አመልካች የዳቦ አቅርቦቱን የሚቀጥሉበትን የጊዜ ገደብ በግልጽ አስቀምጠው ደብዳቤ በመጻፋቸው ምክንያት በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው አመልካች ያስቀመጡት የጊዜ ገደብ ከማለቁ በፊት ውስን ጨረታ አውጥቶ ልላ ግለሰብ ዳቦ አቅርቦቱን እንዲቀጥል ማድረጉ ከዩኒቨርሲቲው ኃላፊነትና ግድታ አንፃር ሲታይ የሚነቀፍበት ምክንያት ካለመኖሩም በላይ በውሉ አንቀፅ 8.2 ስር ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥም ጉዳዩ በአገሪቱ የፍትሃብሕር ሕግ እንደሚፈታ ስለመሆኑ የተመለከተ በመሆኑ በዚሁ ረገድ አመልካች ያቀረቡት ክርክር የዳቦ ዱቄት ዋጋ መናር የሚለውና በመንግስት የታወቀው የዋጋ ግሽበት ነው። ይሁን እንጂ አመልካች የሚያቀርቡት ለተማሪዎች ቁርስ፣ ምሳ እና እራት የሚሆን ዳቦ እንደመሆኑ መጠን የአቅርቦቱ ባህርይ ሲታይ ለአፍታ ጊዜ ያህል ላቋረጥ የማይችል በመሆኑ በመንግስት የታወቀ የዋጋ ግሽበት ቢኖር እንኳ አቅርቦቱን ቀጥለው ኪሳራውን በፍ/ሕ/ቁጥር 3183(2) እና 3188(1) ድንጋጌዎች አግባብ ተጠሪ በከፊል እንዲችል የሚደረግበት ሕጋዊ መፍትሕ የነበረ በመሆኑ የዋጋ ግሽበቱ አመልካች አቅርቦቱን ወዲያውኑና ሙሉ በሙሉ እንዲያቋርጡ የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት ነው ለማለት የሚቻል አይደለም። አመልካች ለአቀረቡት ዳቦ ተጠሪ ዋጋውን በውሉ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ አልከፈለም በማለት የሚያቀርቡት ክርክርም በአመልካች የዳቦ አቅርቦት ስራ ላይ የራሱ የሆነ ተጽእኖ የሚኖረው መሆኑ ቢታመንም አመልካች ውሉን ለማቋረጥ ለተጠሪ ግንቦት 05 ቀን 2000 ዓ.ም. በፃፉት ደብዳቤ ይህንኑ ምክንያት በመጥቀስ ውሉን ለማቋረጥ ስለመገደዳቸው ያልፃፉ ስለመሆኑ የክርክሩ ሂደት የሚያሳይ በመሆኑ በዚህ ምክንያት ውሉን ያፈረሰው ተጠሪ ነው ብሎ ለመደምደም የሚቻል ሁኖ አልተገኘም።አመልካች በተለያዩ ጊዜያት ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ጋር ለመወያየት ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ስለመሆኑ ጠቅሰው የሚያቀርቡት ክርክር ሲታይም ግንቦት 05 ቀን 2000 ዓ.ም. በግልፅ ከፃፉት ደብዳቤ ይዘትና ከአቅርቦቱ ልዩ ባህርይ ሲታይ ለውሉ መፈረስ ምክንያቱ ተጠሪ ነው ለማለት የሚያስችል ባለመሆኑ ተቀባይነት የሚሰጠው ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም ውሉ የፈረሰና ለመፍረሱም ምክንያት አመልካች ናቸው ተብሎ በበታች ፍርድ ቤቶች መወሰኑ የሚነቀፍበትን ሕጋዊ ምክንያት አላገኘንም።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡- አመልካች ከተጠሪ ጋር ባደረጉት ውል አንዱን ዳቦ በብር 0.80 ለማቅረብ ተዋውለው እስከ ግንቦት 19 ቀን 2000 ዓ.ም. 811,363 ዳቦ ያቀረቡ መሆኑና ከግንቦት 20 ቀን 2000 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 05 ቀን 2000 ዓ.ም. ድረስ አቅርቦቱ በልላ ግለሰብ እንዲቀጥል በተደረገው ውል ግን የአንድ ዳቦ ዋጋ ብር 1.31 ሁኖ ተጠሪ ለአንድ ዳቦ ብር 0.51 ብልጫ ለሁለተኛ ጨረታ አሸናፊ እንዲከፍል የተገደደ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋገጧል። በክርክሩ ሂደት አመልካች ከተጠሪ ጋር ያደረጉት ውል በውሉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያለመከናወኑና ለልላ ሰው ጨረታው ተላልፎ ሲሰጥም ተጠሪ ለዋጋ ጭማሪ መዳረጉ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። ተጠሪ የጉዳት ካሳ ጥያቄን መሰረት ያደረገውም ስራው በውሉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ሙሉ በሙሉ ያለመተግበሩንና ድጋሚ ጨረታ ያስከተለውን ተጨማሪ ወጪ ነው። ግራ ቀኙ ባደረጉት ውል ውስጥ የውል ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 10% ብር 245,036.00 (ሁለት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሰላሳ ስድስት ብር) አመልካች ለተጠሪ ማስያዝ እንደአለባቸው በአመልካች ግድታነት በአንቀፅ 5.7 ስር በግልጽ የተቀመጠ ሲሆን ከዚህ የገንዘብ መጠን ውጪ ለውሉ መዘግዬት ተብሎ የተጠቀሰው ለእንያንዳዱ ቀን የውሉን ዋጋ ብር 1/1000ኛ ታስቦ እንዲከፈል ውል ተቀባይ ግድታ ያለው መሆኑን የሚሳይ የውሉ ድንጋጌ በውሉ አንቀፅ 5.10 ስር ተቀምጧል።
የግራ ቀኙ ውል ከላይ የተቀመጡትን ድንጋጌዎችን ከመያዙ ውጪ አንዱ ወገን በውሉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ በሙሉ ወይም በከፊል ግድታውን ካልተወጣ ልላው ወገን የጉዳት ካሳ የመጠየቅ መብት ያለው መሆኑንና ላጠየቅ የሚገባውን የጉዳት መጠን ምን ያህል እንደሆነ አይገልጽም። ይሁን እንጂ ተጠሪ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ የመልካም ሥራ አፈጻጸም /ቦንድ/ ሰነድ መሆኑንና ይህም ከተጠሪ ላይ ላደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመካስ ተብሎ የተገባ ግድታ መሆኑን ተጠሪ ከስር ፍርድ ቤት ጀምሮ የሚከራከርበት ነጥብ ነው። የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ወይም የመልካም ስራ አፈጻጸም ቦንድ የውል አፈፃፀምን ለማረጋገጥ የሚሰጥ የዋስትና ሰነድ መሆኑን፣ ይህም በባለገንዘብ እና በባለ እዳ መካከል የተደረገን ውል አፈፃፀም ለመጠበቅ የሚገባ ግድታ መሆኑን ከሰነዱ አይነተኛ ዓላማ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው። የመልካም ስራ አፈጸጻም ቦንድ መሰረታዊ አላማ ስራው በውሉ መሰረት ስለመሰራቱ ለማረጋገጥ የሚገባ ግድታ መሆኑ እሙን ነው። በአመልካችና በተጠሪ መካከል ሚያዚያ 08 ቀን 2000 ዓ.ም. የተደረገው ውል በአንቀፅ 5.7 ስር ይህንኑ የሚያስገነዝብ ሲሆን አመልካች በወቅቱ ብር 245,036.00 ሙሉ በሙሉ ባያስይዙም ብር 26,035.07 አስይዘው ጨረታውን ማሸነፋቸው ተረጋግጧል። ይህ ሲታይ የመልካም ስራ አፈፃፀም ቦንድ ስራው በስኬታማ ሁኔታ ባይጠናቀቅ በተጠሪ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማካካስ ጭምር ታስቦ የተገባ ግድታ መሆኑን ያስገነዝባል። ይህም አመልካችና ተጠሪ ስለጉዳት ካሳ ቀደም ብለው በውላቸው የገለፁት መጠን መኖሩን የሚያስረዳ ነው። ግራ ቀኙ ባደረጉት ውል አመልካች እንደ ውሉ ላፈጽሙ ባለመቻላቸው የተነሣ ላደርስ የሚችለው ጉዳት መጠኑን አስቀድመው ተምነው በውላቸው ላይ አስቀምጠዋል። ይህም ዓይነት ስምምነት በህግ የተፈቀደ እና ለተፈፃሚነቱ ለማናቸውም ጉድለት ነፃ ስለመሆኑ ያከራከረ ባለመሆኑ ይህም ከሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1731 እና 1889 እንደተደነገገው እንደውሉ ባለመፈፀሙ ምክንያት ላደርስ የሚችለውን ጉዳት ለማካካስ የጉዳት ኪሣራ ገንዘብ መጠኑ በብር 245,036.00 (ሁለት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሰላሳ ስድስት ብር) ብቻ እንዲወሰን በማድረግ ባደረጉት ስምምነት መሰረት በቃላቸው ላታሰሩ እንደሚገባ የሚያስገነዝብ ሆኖ አግኝተናል።
ስለሆነም የአሁን አመልካች ለውሉ አለመፈፀም ምክንያት በመሆናቸውና በዚህም የተነሣ በአሁን ተጠሪ ላይ ጉዳት መድረሱ ቢታወቅም ለውሉ አለመፈፀም ኃላፊ የሆኑት የአሁን አመልካች በውሉ ከተመለከተው የጉዳት ኪሣራ ገንዘብ ጣሪያ በላይ ተጠሪን እንዲክሱ ላገደዱ የሚቻልበት የህግ ምክንያት የልለ በመሆኑ ለተጠሪ ላከፍል በሚገባው የኪሣራ መጠን ላይ የተሰጠው የውሣኔ ክፍል መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ አግኘተናል። አመልካች ለተጠሪ ላከፍሉ የሚገባው የጉዳት ኪሳራ መጠን ከብር 245,036.00 ላበልጥ አይችልም ከተባለ አመልካች ለተጠሪ ዳቦ አቅርበው ያልተከፈላቸው ብር 526,556.00 (አምስት መቶ ሃያ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ስድሰት ብር) መኖሩ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠና ተጠሪም ያልካደው ጉዳይ ነው።አመልካች ይኼው ገንዘብ እንዲከፈላቸው በስር ፍርድ ቤትም ክስ የመሰረቱ በመሆኑ ተጠሪ ይህንኑ ገንዘብ የሚያስቀሩበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። በመሆኑም አመልካች ለተጠሪ በመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ማስያዝ ከሚገባቸው ገንዘብ ብር 245,036.00 ውስጥ ብር 26,035.07 ብር ያስያዙ በመሆኑ ማስያዝ ከሚገባቸው ገንዘብ ውሰጥ ብር 219,000.00 ያላስያዙ በመሆኑ ይሕው ገንዘብ ከብር 526,556.00 ላቀነስ የሚገባው ሆኖ ስለአገኝን ገንዘቡ ተቀንሶ የሚመጣው ውጤት ብር 307,555.07 (ሶስት መቶ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ አምስት ብር ከዜሮ ሰባት ሳንቲም) ለአመልካች ተጠሪ ላከፍል የሚገባው ገንዘብ ሁኖ ተገኝቷል። ሲጠቃለልም ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላሻሻል የሚገባው ሁኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት መደበኛ ችሎት በመ/ ታህሳስ 25 ቀን 2003 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ ግንቦት 22 ቀን 2004 ዓ.ም. የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሐል።
አመልካች ለውሉ አለመፈፀም ምክንያት በመሆናቸውና በዚህም የተነሣ በአሁን ተጠሪ ላይ ጉዳት መድረሱ ቢታወቅም ለውሉ አለመፈፀም ኃላፊ የሆኑት የአሁን አመልካች በውሉ ከተመለከተው የጉዳት ኪሣራ ገንዘብ ጣሪያ በላይ ተጠሪን እንዲክሱ ላገደዱ የሚቻልበት የህግ ምክንያት የለም ብለናል። አመልካች ብር 245,036.00 ላያገኙ አይገባም ብለናል።
አመልካች ለተጠሪ ዳቦ አቅርበው ካልተከፈላቸው ገንዘብ ውስጥ ብር 307,555.07 (ሶስት መቶ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ አምስት ብር ከዜሮ ሰባት ሳንቲም) ተጠሪ ላከፍላቸው ይገባል ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ማናቸውንም ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቷ፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ብለናል።
No topics extracted.