No summary available.
ታህሳስ 16 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ወይራ እንጨትና ብረታ ብረት ሥራ ኃ/የተ/የሕብረት ሥራ ማህበር ጠበቃ አቶ ወልደሥላሴ ብረቱ ተጠሪ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደርና የንግድ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ነገር ፈጅአቶ ዮሐንስ ይረስህ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፤ መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዳይ የቀረበው በግራ ቀኙ መካከል የተነሣውን ክርክር አይቶ ለመወሰን ሥልጣን ያላቸው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤቶች ናቸው ወይስ የአዲስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ ለይቶ ተገቢውን ዳኝነት ለመስጠት ሲባል ነው።
የአሁን አመልካች ከውል የመነጨን ክስ በአሁኑ ተጠሪ ላይ በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቅርቦ፤ ተጠሪም በልለበት ጉዳዩ ታይቶ የአሁን ተጠሪ በድምሩ ብር 395,026.55 (ሶስት መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ሃያ ስድስት ብር ከ55% ሣንቲም) ለአሁን አመልካች ይከፈል በሚል ተወስኖል።
የአሁን ተጠሪ በቀረበው የይግባኝ አቤቱታ መነሻ ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው ይግባኝ ሰሚው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እና ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩላቸው ለክርክሩ መነሻ የሆነው ውል አስተዳደራዊ ውል ስለሆነ በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41(1)(መ) እንደተደነገገው ተከሣሽ የሆነው መስሪያ ቤት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት አንዱ በመሆኑ ይህ የአስፈፃሚ አካል የገባውን አስተዳደራዊ ውል በሚመለከት የሚነሣው ክርክር የመዳኘት ሥልጣን የተሰጠቸው የአዲስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ናቸው። ስለሆነም የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በልለው ስልጣን የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል በማለት ወስኗል።
ይህ የሰበር ጉዳይ ላቀርብ የቻለውም የአሁን አመልካች በዚህ በፍድራል ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚልበትን ሥነሥርዓታዊ ክርክርና መንስኤ የሆነው ውል አስተዳደራዊ ውል በሚለው ሥር የማይሸፈን መሆኑን መሰረት በማድረግ ጠቅሶ ክርክር በማቅረቡ ሲሆን፤ የአሁን ተጠሪ በበኩሉ ጉዳዩን አይቶ ለመወሰን ሥልጣን ያላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ናቸው መባሉ በህጉ መሰረት መወሰኑን እንጂ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን አያሣይም በማለት የጽሑፍ ክርክሩን አቅርቧል። እንግዲህ የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን፤ እኛም ጉዳዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነውም አመልካች ሥነ-ሥርዓታዊ ክርክሩን በማስቀደም ያቀረበ ሲሆን፤ ይዘቱም የአሁን ተጠሪ በልለበት ጉዳዩ ታይቶ የተወሰነ እስከሆነ ድረስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78 መሰረት እርሱ በልለበት ጉዳዩ ፍርዱን በፈረደው ፍ/ቤት እንደገና እንዲታይለት ከሚያቀርብ በቀር በቀጥታ የይግባኝ ክርክር የማቅረብ መብት የልለው መሆኑ እየታወቀ በዚህ ከሥነሥርዓቱ ውጭ በሆነ አቅራረብ ውሣኔው መሻሩ የህግ መሰረት የልለው ስለሆነ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሣኔ ላታረም ይገባል የሚል ነው።
ይሁን እንጂ በተመሣሣይ የክርክር ነጥብ ከዚህ ቀደም በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ይህ ችሎት በሰበር መ/ በቀረበው ጉዳይ ላይ በ13/2/01 ዓ.ም. ቀን በዋለው ችሎት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78 ድንጋጌ ይዘት የይግባኝ አቤቱታ ለማቅረብ እንደ ቋሚ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠ አለመሆኑ ይልቁንም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 329 የተመለከተው ሥነ -ሰርዓታዊ ገደብ እንደተጠበቀ ሆኖ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 70(ሀ) መሰረት አንድ ጉዳይ ተከሣሹ በልለበት የተሰጠ ከሆነ አዲስ የፍሬ ነገር ክርክር በማቅረብ ለመከራከር መብት የልለው ከመሆኑ በቀር የሥር ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ አግባብነቱ ከህግ አንፃር እንዲታይለት ይግባኝ የመጠየቅና በይግባኝ የማሰማት መብት ያለው መሆኑ በተብራራ አኳኋን ትርጉም የተሰጠበት ጉዳይ ነው።
በዚህም ጉዳይ ያሁን ተጠሪ ያደረገውና ያቀረበው ክርክር ቢኖር ተከሣሸ ቀረበም አልቀረበም አንድን ጉዳይ ተቀብሎ ለማየትና ለመዳኝት ሥልጣን ያለው በየትኛው ደረጃ የተደራጀ፤
(የተቋቋመ) ፍ/ቤት ነው? የሚለውን ነጥብ ከህገ መንግስቱ አንቀጽ 37፣ ከፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
23(1)(ለ)፣ 244(3) አንፃር ተመልክቶ የጉዳዩ ባለቤት መሆኑንና አለመሆኑን ለይቶ መወሰን የዳኝነት ሥራ ተግባር የሚያስገድደው ሆኖ እያለ ይህንኑ በህግ የተመለከተ የዳኝነት ተግባር አልተወጣም፤ ይህ ከህጉ ጋር ተገናዝቦ ይታይ በማለት ማቅረቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሐ/ቁ. 329 የተመለከተውን ሥነ- ሥርዓታዊ ድንጋጌ አፈፃፀም የጣሰ መሆኑን አያመለክትም።
በልላ በኩል የአሁን አመልካች ክርክር ያስነሣው ጉዳይ የአስተዳደር ውል ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ለመለየት በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3132 ላይ በህግ ተለይቶ በተደረገ ጊዜ ነው የሚለውን ድንጋጌ መነሻ በማድረግ አንድ ውል የአስተዳደር ውል ነው ብሎ ህግ ተነግሯል የሚባለው ደግሞ በንብረት ህግ አንቀጽ 1444(2)፣ 1446 እና 1447(1) የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመከተል ነው ሲሉ ያቀረቡት ክርክር እጅግ የጠበበ ከመሆኑም በላይ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.3132(ለ) የተመለከተውን ድንጋጌ ይዘት እና ዓላማ የተከተለ የትርጉም መስመር አይደለም ይልቁም በፍ/ህ/ቁ. 3132 እንደተመለከተው አንድ ውል “የአስተዳደር ውል” ነው በሚለው ማእቀፍ ሥር ይወድቃል ወይስ አይወድቅም ብሎ ለመወሰን መመዘኛ ተደርገው የተያዙት በህግ ወይም በተዋዋዮቹ ግልጽ የሆነ ቃል የአስተዳደር መ/ቤት ውል ነው የተባለ እነደሆነና፤ ከህዝብ አገልግሎት ሥራ ጋር ተያያዥና ለሥራ ውል አፈፃፀም የአስተዳደር ፍ/ቤቱን ተካፋይነት ያለማቋረጥ የሚጠይቅ መሆኑን ሁሉ የሚጨምር ነው። ከእነዚህም መስፈርቶች አንፃር አንድ ውል የአስተዳደር ውል ነው ለማለት የግድ በውሉ ላይ በግልጽ መነገር ብቻ ሣይሆን የውሉን ዓይነት የውለታውን ጉዳይ እንዲሁም የተዋዋዮችን ማንነት በማየት መለየት እንደሚገባ በዚሁ ህግ የተደነገገ በመሆኑ በዚሁ መሰረት የሚለይ እንጂ የአሁን አመልካች ከጠቀሷቸው የንብረት ህግ ድንጋጌዎች አንፃር ብቻ ታይቶ ላወሰን ይገባል የሚለውን ትርጉም የሚሰጥ አይደለም።
ከዚህም አንፃር ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በተለይ ከአሁን አመልካች ጋር ውለታ የገባው ማን ነው የሚለውንና የውለታውን ጉዳይ በማየት ውሉ የአስተዳደራዊ ውል ነው። ይህንኑ አስተዳደራዊ ውልም የገባው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር ከሚገኙት አስፈፃሚ አካላት መካከል አንዱ የሆነው ተጠሪ የመሆኑን ፍሬ ጉዳዮች መነሻ አድርጎ ጉዳዩን አይቶ ለመወሰን ሥልጣን ያላቸው ፍ/ቤቶች የአዲስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ናቸው በማለት የሰጡት ውሣኔ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3132(ለ) እና በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41(1)(መ) ላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በአግባቡ ተመልክቶና ተርጉሞ መሆኑን እንጂ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አላገኘነውም።
ው ሣ ኔ
የፍድራሉ ይግባኝ ሰሚ ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 115093 በቀን 12/04/2004 ዓ.ም የሰጠው ብይን እና ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. 76951 በቀን 25/08/2004 ዓ.ም. የሰጠው ትእዛዝ ሁሉ ፀንቷል።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 176341 በቀን 10/10/2003 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ ተሽሯል።
በግራ ቀኙ መካከል የተነሣውን የክርክር ጉዳይ ተመልክቶ ዳኝነት ለመስጠት ሥልጣን ያላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ናቸው ብለናል።
በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት የተደረገው ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ።
No topics extracted.