No summary available.
ጥር 13 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- አቶ አብዱልቃድር ጁሐር - ጠበቃ ገ/እግዚአብሕር ተስፋዬ ቀረቡ ተጠሪ፡- አምባሰል የንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማ - ጠበቃ አረጋ ፀጋ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ የተያዘው ክርክር የተጀመረው በአ/ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሲሆን ክሱን የመሰረተው የአሁኑ ተጠሪ ነው። የአሁኑ አመልካችም ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። የክሱ ይዘት ባጭሩ ግራ ቀኙ በ30/03/89 እና በ04/04/89 ባደረጓቸው የሰላጥ ሽያጭ ውሎች መሰረት ተከሳሽ ሰላጡን ተረክበው እያለ ዋጋውን ያልከፈሉ በመሆኑ በገቡት የውል ግድታ መሰረት ገንዘቡን መክፈል ከነበረባቸውን ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ 14% ወለድ ጋር እንዲከፍሉ ይወሰንልን የሚል ሲሆን ተከሳሹም የበኩላቸውን የመቃወሚያና የፍሬ ጉዳይ ነጥቦች በማቅረብ ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ከሳሽ አንዱን ኩንታል በብር 299.65 ሂሳብ በድምሩ 4,143.55 ኩንታል ሰላጥ ለተከሳሽ ማስረከቡና ተከሳሹም ክፍያውን መፈፀም ይገባቸው የነበረው በ10/05/89 ዓ.ም መሆኑ መረጋገጡን፣ ተከሳሽ ወለዱ በ14% የታሰበው ከፍ.ሕ.ቁ. 2479(3) ውጪ ነው ቢሉም የወለድ ምጣኔው ተከሳሽ በውል ግድታ የገቡበት ከመሆኑም በላይ ገንዘቡ የብድር ውልን የሚመለከት ባለመሆኑ ምክንያት ለጉዳዩ ተፈፃሚነት ያለው የፍ.ሕ.ቁ 2479(3) ሳይሆን 1803(2) መሆኑን እና ተከሳሽ ያቀረቧቸው የመቃወሚያና ልሎች የፍሬ ነገር የክርክር ነጥቦች ተቀባይነት የልላቸው መሆኑን በዝርዝር በመግለፅ ተከሳሽ ብር 1,241,641.75 ከ10/05/89 ዓ/ም ጀምሮ ክስ እስከቀረበበት 24/05/99 ዓ.ም ድረስ ከሚታሰብ 14% ወለድ ጋር እንዲሁም በዋናው ገንዘብ ላይ ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ተከፍሎ እስከሚያልቅ ድረስ የሚታሰብ 9% ወለድ ከወጪና ኪሳራ ጋር ለከሳሽ እንዲከፍሉ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የቀረበለትን ይግባኝ ሰርዞ አሰናብቷል።
አመልካች የሰበር አቤቱታውን ያቀረቡት የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ሲሆን በዋናው የገንዘብ ዕዳ ላይ የ14% ወለድ እንዲታሰብ የመወሰኑን አግባብነት ከፍ/ሕ/ቁጥር 2479(3) ድንጋጌ አንፃር ለመመርመር አቤቱታው በዚህ ነጥብ ላይ ብቻ ለሰበር ችሎት ላቀርብ ይገባዋል በመባሉ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።
የጉዳዩ አመጣጥና የክርክሩ ይዘት ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን ከላይ ከተጠቀሰው ጭብጥ አንፃር መርምረናል።
በዚህም መሰረት የፍ/ሕ/ቁ 2479 የሚናገረው በብድር በሚሰጥ ገንዘብ ላይ ተዋዋይ ወገኖች ላያቋቋሙ ስለሚችሉት የወለድ ምጣኔ ጣሪያ እና ብድሩ በውሉ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ የሚከፈል ከሆነ በብድር ገንዘብ ላይ ላታሰብ ስለሚገባው የወለድ ምጣኔ ጣሪያ ሲሆን የፍ/ሕ/ቁ 1803(2) ድንጋጌ ደግሞ በውሉ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ሳይከፈል በቀረ የገንዘብ ዕዳ ላይ የሚታሰበው የወለድ ምጣኔ ተዋዋዮቹ የተስማሙበት መጠን እንደሆነ የሚደነግግ ነው። ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው ሁለቱ ድንጋጌዎች ሁለት የተለያዩ የውል ግንኙነትና አፈፃፀም ሁኔታዎችን የሚመለከቱ መሆኑን ነው። በውሉ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ሳይከፈል የቀረን የገንዘብ ዕዳ የሚመለከተው የፍ/ሕ/ቁ 1803 ድንጋጌ በፍ/ሕ/ቁ 2479 መሰረት ተቋቁሞ ነገር ግን በውሉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ያልተከፈለ የብድር ገንዘብን ጭምር የሚመለከት መሆኑን ከፍ/ሕ/ቁ 2488 እና 2489 ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
በተያዘው ጉዳይ የስር ተከሳሽ ኃላፊ የተደረጉበት ገንዘብ ከብድር ውል የመነጨ ካለመሆኑም በላይ የውል ግድታ ገብተውለት የነበረው የገንዘብ ዕዳ የመክፈያ ጊዜ ካለፈ አስር ዓመታት ያህል ማስቆጠሩ በክርክሩ ተረጋግጧል። ይህ ከሆነ ደግሞ ለክርክሩ አወሳሰን አግባብነት የሚኖረው አመልካች እንደሚከራከሩት የፍ/ሕ/ቁ 2479(3) ሳይሆን የስር ፍ/ቤት ለውሳኔው መሰረት ያደረገው የቁጥር 1803 (2) ድንጋጌ ነው።
በልላ በኩል የውል ግድታውን ያልፈፀመ ወይም ያዘገየ ወገን ለልላኛው ተዋዋይ የሚከፍለው የኪሳራ መጠን የግድታው አለመፈፀም ወይም መዘግየት ካስከተለው ጉዳት ጋር ተመጣጣኝ መሆን እንደሚገባው በፍ/ሕ/ቁ 1790(2) እና ተከታይ ድንጋጌዎች ተመልክቷል። በተያዘው ጉዳይ የግራ ቀኙን ውል መሰረት በማድረግ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ የሰጡበት የ14% የወለድ መጠን በተጠሪ ላይ ከደረሰው የጉዳት መጠን የበለጠ ነው ለማለት የሚያስችል ሁኔታ ካለመገኘቱም በላይ በተጠሪ የተጠየቀው የወለድ መጠን ከደረሰበት ጉዳት በላይ ስለመሆኑ አመልካች በፍ/ሕ/ቁ 1800 መሰረት ያቀረቡት ክርክርና ማስረጃ የለም።
ሲጠቃለል የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የአ/ብ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በ19/09/03 የሰጠው ውሳኔ እና የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ በ24/08/04 የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት በአብላጫ ድምፅ ፀንቷል።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸው ይቻሉ።
ክርክሩ ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.