No summary available.
ጥር 14 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ረታ ቶለሳ አዳነ ንጉሤ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ጭላሎ ኢንተርፕራይዝ ኃ/የተ/የግል ማህበር ተጠሪ፡- የአዳማ ከተማ የቦኩ ሸነን ቀበል አስተዳደር ጽ/ቤት መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ በአሁኑ የሰበር ተጠሪ ከሳሽነት የተጀመረው በአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ የሰበር አመልካችም ተከሳሽ ነበር። ከሳሽ አሻሽሎ በ01/08/2002 ዓ/ም ያቀረበው ክስ የከተማው አስተዳደር ለከሳሽ ቀበል ለልማት ሥራ ድጋፍ በሚል 400 ካሬ ሜትር ቦታ በመስጠቱ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ቴልቶን ቦታውን በጨረታ ለመሸጥ ጨረታ ተድርጎ ተከሳሽም በጨረታው ተወዳዳሪ በመሆን በብር 370,000.00 ካሸነፈና የቦታውን ካርታ ከተቀበለ በኋላ ገንዘቡን ገቢ እንዲያደርግ ሲጠየቅ የአራት ወር ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ የተሰጠው ቢሆንም ለመክፈል ፈቃደኛ ስላልሆነ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ወጪና ኪሳራ ተጨምሮ እንዲከፍል ይወሰንልን የሚል ነው።
ተከሳሽም ለክሱ በሰጠው መልስ ክስ የቀረበበት መሬት በላዝ ስምምነት የተሸጠ ሲሆን ሽያጩም ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፣ የሽያጭ ውሉ በሚመለከተው አካል ፊት ቀርቦ ያልተረጋገጠ ከመሆኑም ልላ በላዝ ህግና ደንብ መሰረት የተፈረመ የውል ስምምነት የለም፣ገንዘቡን ለመክፈል የ4 ወር ጊዜ ጠይቄ እያለሁ በችኮላ የቀረበ ክስ ነው፣ጨረታው ውድቅ ከሆነ ያስያዝኩት ገንዘብ ቀሪ ከሚሆን በስተቀር ጠቅላላውን ገንዘብ የመክፈል ግድታ የለብኝም ሲሉ ተከራክሯል።
ከፍተኛው ፍርድ ቤትም በሰጠው ውሳኔ በኢ.ፍ.ዲ.ሪ ህገ መንግስትም ሆነ በክልሉ ህገ መንግስት መሬት የማይሸጥ እና የማይለወጥ የመንግስትና የኢትዮጵያ ብሕሮች ብሕረሶቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት መሆኑ የተደነገገ ቢሆንም በስጦታ ወይም በኪራይ የባለይዞታነት መብት ማስተላለፍ የሚቻል ስለመሆኑ ከአዋጅ ቁጥር 456/2005፣272/2002 እና በላዝ ደንብ ቁጥር 1/1987 እንደተሻሻለው ከተደነገገው መገንዘብ የሚቻል ሲሆን በሚያከራክረው ጉዳይም ተከሳሽ ጨረታውን ተወዳድሮ በብር 370,000.00 በማሸነፉ መሬቱ ወደ ተከሳሽ በላዝ ተላልፎለት ወዲያዉኑ ሳይት ፕላን የተሰጠው ስለመሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ ገንዘቡን ለከሳሽ የመክፈል ግድታ አለበት ብሐል።
የስር ተከሳሽም በከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ያቀረቡ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ይግባኙን በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 337 መሰረት በመዝጋት ይግባኝ ባዩን አሰናብቷል። የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎትም የግራ ቀኙን ወገን ካከራከረ በኋላ በዞኑ ከፍተኛው ፍርድ ቤት እና በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለም በማለት አጽንቷል።
አመልካችም በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት የሰበር አቤቱታውን ለዚህ ችሎት ያቀረበ ሲሆን በዋናነት የጠቀሰው የቅሬታ ነጥብም፡- በአመልካች እና በተጠሪው መካከል የተፈረመ የላዝ ውል ሳይኖር ጨረታው የተደረገበትን ዓላማ መሰረት በማድረግ ብቻ የጨረታውን ዋጋ እንድከፍል የሥር ፍርድ ቤቶች የወሰኑት የላዝ አዋጅ ቁጥር 272/1994 አንቀጽ 9(1)(2) እና የፍትሀብሕር ህግ ቁጥር 1723ን የሚቃረን ከመሆኑም ልላ በኢ/ፍ/ዲ/ሪ//ህገ መንግስት አንቀጽ 79(3) ዳኞች ከህግ በስተቀር በልላ ሁኔታ አይመሩም በሚል የተደነገገውን ያላገናዘበ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም የሚል ነው።
ተጠሪው በበኩሉ በሰጠው መልስ የቀበልው አስተዳደር ወደ አዳማ ከተማ ሲጠቃለል አዲስ በመሆኑ ምክንያት የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ለነዋሪው ህዝብ ለሟሟላት ሲባል በተዘጋጀው ቴልቶን 400 ካሬ ሜትር ቦታ አመልካች በጨረታ ተወዳድሮ በማሸነፍ በብር 370,000.00 በመግዛቱ ወዲያውኑ ከከተማው ከንቲባ እጅ የቦታውን ሳይት ፕላን መረከቡ የተረጋጠ ሲሆን የይዞታ ማረጋጫ የምስክር ወረቀትም በከተማው የመሬትና የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ተዘጋጅቶለት እያለ ፎርማላቲውን አሟልቶ መሬቱን እንዲረከብ እየተነገረው እያለ መሬቱ በላዝ አዋጅ መሰረት እንደተላለፈለት በማስመሰል የላዝ አዋጁ ፎርማላቲ ስላልተሟላ በጨረታው አልገደድም ያለው ተገቢነት ስለልለው ገንዘቡን እንዲከፍል የተወሰነበት የሚነቀፍበት ምክንያት የለውም በሚል ተከራክሯል። አመልካችም ተጠሪው ላቀረበው መልስ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክሯል።
የጉዳዩ አመጣጥ ከዚህ በላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም፡- አመልካች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ የመክፈል ግድታ አለበት? ወይስ የለበትም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
አመልካች በጨረታው ተወዳዳሪ ሆኖ ጨረታውን ማሸነፉን የሚያምነው ጉዳይ ሲሆን በዋናነት ክርክሩን እያቀረበ ያለው ግን ጉዳዩን ከላዝ ህግ ጋር በማገናኘት ነው። በወቅቱ ተፈጻሚ በነበረው የላዝ አዋጅ ቁጥር 272/1994 የላዝ ውሉ በተዋዋዮቹ መፈረም ያለበት ስለመሆኑ ከአዋጁ አንቀጽ 9(1) መገንዘብ የሚቻል ሲሆን የይዞታ ማረጋጫ የምስክር ወረቀትም የሚሰጠው ይሕው የላዝ ውል ስምምነት ከተደረገ በኋላ ስለመሆኑ በዚሁ ድንጋጌ ተመልክቷል። የክፍያ አፈጻጸም ዝርዝር ሁኔታም በላዝ ውሉ ወስጥ መካተት ያለበት ስለመሆኑ ድንጋጌው በንዑስ አንቀጽ 2 ተጠቅሷል። በዚህ በተያዘው ጉዳይ ግን አመልካች ለተጠሪው ቀበል የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ለመዘርጋት በተዘጋጀው ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ቴልቶን በተደረገው ጨረታ ተሳታፊ በመሆን ጨረታውን አሸንፎ የቦታውን ሳይት ፕላን ያገኘ በመሆኑ ለገንዘቡ አከፋፈል የላዝ ውል ስምምነት አልተፈረመም የሚለውን ቅድመ ሁኔታ ላያቀርብ የሚችልበት ሁኔታ አይኖርም። በአመልካች እና አግባብ ባለው አካል መካከል የተፈረመ የላዝ ውል አለመኖሩ ግልጽ ቢሆንም በመካከላቸው የውል ግንኙነት የተመሰረተ መሆኑ የሚያከራክር አይሆንም።
የውል ግድታ መፈጸም የሚጠበቅበት ተዋዋይ ይህንኑ ግድታ ባልፈጸመ ጊዜም በራሱ በኩል ያለውን ግድታ የፈጸመው ተዋዋይ በፍ/ህ/ቁ/1771(1) እንደተደነገገው ልላኛው ተዋዋይ የበኩሉን ግድታ እንዲፈጽም የመጠየቅ መብት ይኖረዋል። እንዲሁም ውሉ ተዋዋዮቹ በአንድነት የሚፈጽሙትን ግድታ (simultaneous performance) የሚጥል ሆኖ ከተገኘም ተዋዋዩ የተዋዋለበትን ግድታ በውሉ እንደተመለከተው እንዲፈጸምለት የሚጠይቀው ወገን ከውሉ ስምምነት የተነሳ እሱም በበኩሉ ያለውን ግድታ ወዲያውኑ መፈጸም ወይም ለመፈጸም የተዘጋጀ መሆኑን ማረጋገጥ የሚገባው መሆኑን የፍ/ህ/ቁ/1757 ያስገነዝባል። በዚሁ መሰረትም አመልካች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ እንደተረጋገጠ በፍ/ህ/ቁ/1688(2) የተደነገገውን በመከተል ተጠሪው ሳይት ፕላኑን ለአመልካች በማስረከብ የበኩሉን ግድታ በመፈጸም ገንዘቡን ገቢ እንዲያደርግ ሲያስታውቅ አመልካችም የክፍያው ጊዜ እንዲያራዘምለት በመጠየቁ በጥያቄው መሰረት የተራዘመለት ቢሆንም ለመክፈል አለመፈለጉን የፍሬ ነገር ጉዳዮችን የሚያጣሩ የሥር ፍርድ ቤቶት ያረጋገጡት ጉዳይ ነው።
በመሆኑም በአመልካች እና በተጠሪው መካከል በተመሰረተው ውል መሰረት በጨረታ ተወዳድሮ ያሸነፈውን ገንዘብ በመክፈል ቀሪውን መሟላት የሚገባቸውን ነገሮች ተጠሪው ወይም አግባብ ያለው አካል እንዲያሟላ አመልካች መጠየቅ ሲገባው ህጋዊ መሰረት የልላቸውን የመከራከሪያ ነጥቦችን በማንሳት ያቀረበውን ክርክር የሥር ፍርድ ቤቶች ውድቅ በማድረግ ያሸነፈበትን የጨረታውን ዋጋ ገንዘብ ገቢ እንዲያደርግ በሚል በሰጡት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ባለማግኘታን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በዋለው ችሎት የሰጠውን ውሳኔ፣የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ10981 በቀን 30/03/2003 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሰጠውን ትዕዛዝ እና የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በ/ቁ/117557 በቀን 28/05/2004 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሰጠውን ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/348(1) መሰረት አጽንተናል።
አመልካች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ብር 370,000 (ሶስት መቶ ሳባ ሺህ ብር) የመክፈል ግድታ አለበት ብለናል።
ከዚህ በፊት በአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/10556 ተጀምሮ የነበረው የአፈጻጸም ክስ ታግዶ እንዲቆይ የተሰጠው ትዕዛዝ ተነስቷል። በመሆኑም እንዲያውቀው ይጻፍ ብለናል።
የዚህን ፍርድ ቤት ወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
No topics extracted.