No summary available.
የሰ/መ/ ታህሣስ 02 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች:- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ መኰንን ገ/ህይወት አመልካቾች፡-
ለዚህ ሰበር ጉዳይ መነሻ የሆነው በአሁኑ ተጠሪ ከሣሽነት እና በአሁን አመልካቾች ተከሣሽነት የተነሣውን ክርክር ተመልክቶ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 75093 የካቲት 30 ቀን 2003 ዓ.ም የተሰጠው ፍርድ ነው።
የአሁን ተጠሪ በዚህ በከፍተኛ ፍ/ቤት በቀረበው ክስ ላይ የአሁን አመልካቾችን 1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች በማድረግ ያቀረቡት ክስ ፍሬ ቃል በጉለል ክ/ከተማ ቀበል 19 የቤት ቁጥር 423 በተመዘገበው ቤት በ2905 ካ.ሜትር ውስጥ የሚገኘውን ቤት 1ኛ ተከሣሽ ወ/ሮ የሻረግ ከበደ ከሰኔ 14 ቀን 1986 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2002 ዓ.ም ያላግባብ ይዘው እየተገለገሉበት ስለሚገኝ በዚህ በቤት ቁጥር 423 ውስጥ የሚገኘውን ሁለተኛውን ቤት ከእነ ማእድ ቤቱ ደግሞ ሁለተኛ ተከሣሽ ወ/ሮ ሃና አድማሱ ከግንቦት 30 ቀን 1999 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2002 ዓ.ም በኃይል በመያዛቸው ቤቶችን ከኪራይ ክፍያ ጋር ያስረክቡኝ የሚል ነው።
ለዚህም ክስ በማስረጃነት ያቀረቡት ወ/ሮ አለሙሽ አዲሱ ክስ የቀረበበትን ቤት ህዳር 12 ቀን 1966 ዓ.ም በተደረገ የስጦታ ውል ለከሣሽ ያስተላለፉ መሆኑን የሚገልጽውን የስጦታ ውል ቤቱ በወ/ሮ አበበች ወልደዮሐንስ ስም ግብር የተከፈለ መሆኑን የሚያሣይ የግብር ክፍያ ደረሰኝ እንዲሁም በመ/ቁ. 2525/89 እና 0691 በ24/2/98 በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠ ውሣኔ፤ በፍድራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ. 5865 በ11/3/94 ዓ.ም የተሰጠውን ውሣኔ በማያያዝ አቅርበዋል።
1ኛ ተከሣሽ የነበሩት የአሁን 1ኛ አመልካች ወ/ሮ የሻረግ ከበደ በሰጡት መልስና ቤቱን ያላግባብ ይዛለች ከተባለበት ከሰኔ 14 ቀን 1986 ጀምሮ ያለው ጊዜ ሲሰላ ክሱ በይርጋ ላቋረጥ ይገባል። ስጦታው ክርክር የተነሣበትን ቤት የሚያመለክት አይደለም። ክስ የቀረበበትን ሁለት ክፍል ቤቶች ከወ/ሮ አበበች ወ/ዮሐንስ በስጦታ ያገኘሁትን ኩሽና ቤት አፍርሼ የሰራሁት የእራሴ ሀብት ነው ይኸው ክስ የቀረበበት ቤትም የስጦታ አድራጊ የተባሉት የወ/ሮ አለሙሽ ርስት ስለመሆኑም ማስረጃ የለውም በማለት ተከራክረዋል።
ሁለተኛ አመልካች በበኩላቸውም በኃይል ንብረቱን ወስዳለች ከተባለበት ከግንቦት 30 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ ሲታሰብ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው። በህዳር 12 ቀን 1966 ዓ.ም. ተደረገ የተባለው የስጦታ ውል በይርጋ ቀሪ ከመሆኑም በላይ ያልተመዘገበ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም እኔ እራሴ በእርሷ በከሣሽ ላይ ያቀረብኩት ክስ እየታየ ስለሆነ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ የቀረበው ክስ ላሰረዝ ይገባል በማለት የተከራከሩ ሲሆን በማስረጃነትም በፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 80684 የተሰጠ ውሣኔ አቅርበዋል።
ክሱ የቀረበለት ከፍተኛ ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ተመልክቶ 1ኛ ተከሣሽ የአሁን 1ኛ አመልካች ወ/ሮ የሻረግ ከበደ በቤት ቁጥር 423 በተመዘገቡ ሁለት ቤቶች መካከል በስጦታ ከወ/ሮ አበበች ወ/ዮሐንስ በመረከብ አፍርሰው ሁለት ቤቶችን መሥራታቸውን ጠቅሰው ቢከራከሩም የተሰጣቸው የስጦታ ውል በህግ ፊት ተቀባይነት የለውም ተብሎ በውሣኔ የፈረሰና ሰራሁ ስለሚሉትም ለቤቱ የቤት ባለቤትነት ማስረጃ ባለማቅረባቸው ክርክራቸው ተቀባይነት የለውም። በአኳያው ክርክር የተነሣበትን ቤትና ይዞታ ከሣሽ ከእናታቸው ከወ/ሮ ዓለሙሽ አድማሱ በ12/3/66 በስጦታ ያገኙ በመሆኑ የስጦታ ውሉ ቀርቧል። የአሁን ሁለተኛ አመልካች ክስ በቀረበበት ጉዳይ ከከሣሽ ጋር በመከራከር ላይ እገኛለሁ ቢሉም ቤቱን እንዲረከቡ አልተፈረደላቸውም። ቤቱም በወ/ሮ አበበች ወ/ዮሐንስ የተመዘገበና ለጊዜውም በባለቤትነት የምታወቀው እኔ ነኝ በማለት ከመከራከራቸው በቀር ሁለተኛውን ቤት አልያዝኩም በማለት በግልጽ ያቀረቡት ክርክር የለም። ስለሆነም ሁለቱም ተከሣሾች ክስ የቀረበበትን ቤት ለከሣሽ እንዲያስረክቡ ይገደዳሉ፤ ያስረክቡ ሲል ወስኗል።
No topics extracted.
ይህንን ውሣኔ በ1ኛ አመልካች አቤቱታ መሰረት በይግባኝ የተመለከተው ይግባኝ ሰሚው የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በይ/መ/ቁ. 68052 ሰኔ 06 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችሎት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 እንደተደነገገው መዝገቡን ዘግቷል። እንዲሁም በሁለተኛው አመልካች ይግባኝ ባይነት በይ/መ/ቁ. 67759 ሰኔ 03 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተመሣሣይ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥረ 337 መሰረት በመዝጋቱ የአሁን ሁለቱም አመልካቾች በየፊናቸው እንደቅደም ተከተሉ ለዚህ የሰበር ጉዳይ ማለትም በሰበር መ/ቁ. 71537 አና በሰበር መ/ቁ. 72381 ምክንያት የሆነውን የሰበር ቅሬታ በማቅረባቸው በእነዚሁም የሰበር መዛግብት ላይ ሁሉም ያላቸውን የጽሑፍ ክርክር አቅርበዋል።
የሰበር አመልካቾችም ሆነ ተጠሪ በዚህ ሰበር ደረጃ ያቀረቡት የጽሑፍ ክርክር በይዘቱ በሥር ፍ/ቤት አንስተው የተከራከሩባቸውን ነጥቦች የሚያብራሩ ሆነው ተገኝተዋል።
የዚህ የሰበር ጉዳይ አመጣጥ ከላይ ባጭሩ የተመለከተው ሲሆን፤ እኛም ጉዳዩን እንደሚከተውን መርምረናል። እንደመረመርነው እንደ ጉዳዩ አነሣስና ይዘት በዚህ ጉዳይ በቅድሚያ ምላሽ ላሰጠው የሚገባው አከራካሪ ነጥብ የአሁን አመልካቾች የቀረበብን ክስ በይርጋ ቀሪ ላሆን ይገባል በማለት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ካነሱት ነጥብ አንፃር ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ሆኖ ተገኝቷል።
ይህንን አከራካሪ ነጥብ አስመልክቶ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ የካቲት 28 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችሎት ከሳሽ ክስ ያቀረቡበት ጉዳይ የባለቤትነት መብትን የሚመለከት በመሆኑ በይርጋ ላታገድ አይችልም የሚል ትርጉም ሰጥቶ ክሱ በይርጋ አይታገድም የሚል ዳኝነት እንደሰጠበት ከመዝገቡ ግልባጭ ተገንዝበናል።
በንብረት ላይ ያለን የመፋለም ክስ አስመልክቶ ይህ የፍድራል ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መ/ ጥር 05 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት በይርጋ ቀሪ ላሆን እንደማይገባ ተንትኖ ትርጉም የሰጠበት ጉዳይ ስለመሆኑም ተገንዝበናል። ይሁን እንጂ በዚሁ ትርጉም በተሰጠበት ውሣኔ ላይ ይኸው ሰበር ሰሚ ችሎት ከውርስ ከሽያጭ እና ከስጦታ ውል የመነጨን የባለቤትነት መብት አስመልክቶ በሚነሳ የንብረት ክርክር የይርጋ ጉዳይ በተነሣ ጊዜ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ ለጉዳዩቹ አግባብነትና ተፈፃሚነት ባለው የህግ ክፍል እና የህግ ይዘት ታይቶ ላወሰን እንደሚገባ በተለይ አኳኋን ተመልክቶ ትንታኔ የሰጠበት እንጂ ማናቸውም በንብረት ላይ ያለን የባለቤትነት መብት ጥያቄ በይርጋ ላታገድ የሚችል አይደለም በሚል አልወሰነም።
ይህም አሁን በግራ ቀኙ የተነሣውን ክርክር እንዳየነው የአሁን ተጠሪ በስጦታ ውል ከወ/ሮ አለሙሽ አድማሴ የተላለፈልኝን ቤት ተከሣሾ /የአሁን አመልካቾች/ ያለአግባብ ይዘውብኛል በሚል መነሻ የቀረበ የንብረት መብት ማስከበር ጥያቄ እንደመሆኑ ከስጦታ ውል የመነጨውን የንብረት መብት ለማስከበር የሚቀርበው የዳኝነት ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ላሆን ይገባል ወይስ አይገባም? የይርጋ ክርክርን ላጋብዝ የሚችል ከሆነስ የይርጋ ዘመኑ ምን ያህል ነው?
የሚሉትና ተያያዥነት ያላቸው ክርክሮች ስለስጦታ ውል አመሰራረት ውጤት እና የመሳሰሉትን ዝርዝር ጉዳዮች በሚገዛው የህግ ክፍል እና የአፈፃፀም ወሰን መሰረት ታይቶ ላወሰን እንደሚገባ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ጉዳይ በሰበር መ/ መጋቢት 22 ቀን 2002ዓ.ም በዋለው ችሎት ትርጉም የሰጠበት በመሆኑ ይህም ጉዳይ በዚሁ ትርጉም መሰረት ላታይ የሚገባው እንጂ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እንደሰጠው ትርጉም በይርጋ የሚታገድ የክርክር ዓይነት ሆኖ አልተገኘም።
ከዚህም አንፃር የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካቾች ላይ ላቀረቡት ቤት ይመለስልን የዳኝነት ጥያቄ መሰረት አድርገው ያቀረቡት ክርክር እና ማስረጃ የቤት ቁጥር 423 ባለንብረት የነበሩት እና ወ/ሮ አለሙሽ አድማሱ ህዳር 12 ቀን 1966 ዓ.ም በተደረገ የስጦታ ውል አስተላልፈውልኛል በሚል እንደሆነ በፍሬ ረገድ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። ይህ ለክርክሩ መሰረት ያደረጉት የስጦታ ውል ህዳር 12 ቀን 1966 ዓ.ም የተደረገ ሆኖ የተሻሻለ ክስ እስከ መሰረቱበት እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2002 ዓ.ም ሆነ ንብረቱን ተከሳሾች ያለአግባብ ይዘዋል እስከተባለበት እስከ ሰኔ 14 ቀን 1986 እስከ ግንቦት 30 ቀን 1999 ድረስ ያለው ጊዜ ሲታሰብ እንኳ ከ20 ዓመት በላይ ነው። በዚህ ስጦታ ተደረገ በተባለበት በህዳር 1966 ዓ.ም እና ንብረቱ ያለአግባብ ተይዟል እስከተባለበት ጊዜ ድረስ የስጦታ ውሉ ውጤት ይኖረው ዘንድ መብትን ለማስከበር የቀረበ እንቅስቃሴም ሆነ ለአፈፃፀም የቀረበ አለመሆኑን ክርክሩ አስረጅ ነው።
ይህም ከሆነ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መ/ እንደሰጠው ትርጉም የስጦታ ጉዳዩን የሚገዛው የህግ ክፍል ሰለይርጋ በተለየ መንገድ የደነገገው ጉዳይ ባይኖርም ስጦታ ውል እንደመሆኑ መጠን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1676/1/ እና 1845 ድንጋጌዎች መሰረት ከስጦታ ላመነጨ የሚችል የግድታ አይነት በ10 ዓመት የጊዜ ገደብ ላገደብ የሚገባው ነው። የአሁን ተጠሪ ንብረቱን በስጦታ እግኝቻለሁ ካለበት ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ ንብረቱን ተከሳሾች ያዙብኝ እስካሉበት ጊዜ ድረስ ከ20 ዓመት በላይ በሆነው ጊዜ ውስጥ በስጦታ ውሉ መሰረት ንብረቱን በእጅ ስለማድረጋቸው ወይም ክርክር ያስነሳውን ቤት በስጦታ ውሉ መሰረት በይዞታቸው ስር እንዲሆን በውሉ መሰረት እንዲፈፀሙላቸው ያቀረቡት ጥያቄ እንደልለ በክርክርም ሆነ በማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬ ጉዳይ ነው። የስጦታ ውሉ ተደረገ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ስጦታ ውሉ ለማስፈፀም ክስ እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ ደግሞ ከ10 ዓመት /ከአስር ዓመት/ በላይ የሆነ ጊዜ አልፎታል። በመሆኑም ጉዳዩ ከስጦታ ውል የመነጨ የንብረት ጥያቄ በመሆኑና ጥያቄውም የቀረበው ለጉዳዩ አግባብነት ባለው የህግ ክፍል የተቀመጠው የይርጋ ጊዜ ካለፈ በኋላ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ የአሁን አመልካቾች ያቀረቡትን የይርጋ ክርክር ውድቅ ያደረጉበት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ