No summary available.
የሰ/መ/ ህዳር 05 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይምሰል አመልካች፡- ወ/ሮ ዙቤዳ ኑር ኬርሰማ ጠበቃ አቶ ባህሩ መኮንን ቀረበ ተጠሪ፡-
ይህ የሰበር ጉዳይ የቀረበው የወለድ የገንዘብ ብድር የወሰደ ተበዳሪ የብድር ገንዘቡን መመላሻ ጊዜ ካሣለፈ የብድሩን ገንዘብ ብቻ ሣይሆን ከህጋዊ ወለድ ጋር የመክፈል ግድታ አለበት ወይስ የለበትም? የሚለውን ነጥብ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማጣቀስ ለመለየት ነው።
የአሁን አመልካች ከአሁን 1ኛ ተጠሪ ባለቤት እና ከልሎች ተጠሪዎች አባት ከሟች ከአቶ ሐብታሙ ብርሃኑ ታህሣስ 26 ቀን 1995 ዓ.ም በተደረገ የብድር ገንዘብ ብር 237,000.00 /ሁለት መቶ ሰላሣ ሰባት ሺህ ብር/ መበደራቸውና ይህንኑ የብድር ገንዘብ ጥር 30 ቀን 1995 ዓ.ም ለመመለስ ግድታ የገቡ ስለመሆኑ ግራ ቀኙን ያከራከረ ጉዳይ አይደለም።
ተጠሪዎች ሐምል 21 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የክስ አቤቱታ ተበዳሪው ዋናውን የብድር ገንዘብና ይህንኑ የብድር ገንዘብ መክፈል ከነበረበት ጊዜ ከየካቲት 01 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዲከፍሉ ይወሰንልን በማለት ዳኝነት ሲጠይቁ የአሁን አመልካች ወለድ ለመክፈል በብድር ስምምነቱ ላይ ግድታ ያልገባሁ በመሆኑና የመክፈያው ጊዜ እንዳለፈም ገንዘቡን እንድመልስ በማስጠንቀቂያ ያላሣወቁኝ ስለሆነ ወለድ የመክፈል ግድታ የለብኝም በማለት ተከራክረዋል።
ጉዳዩ የቀረበለት የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህንኑ የግራ ቀኙን ክርክር በኮ/መ/ቁ. 97284 ተመልክቶ ሰኔ 14 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችሎት የብድር ውሉ አልተካደም ጥር 30 ቀን 1995 ዓ.ም ለመመለስም ተበዳሪው ግድታ ገብቷል። የብድር መመለሻ ጊዜው በዚህ አኳኋን ቁርጥ ያለ ጊዜ ስለተቀመጠ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1775(ለ) መሰረት ይህ ጊዜ ካለፈ በኋላ ገንዘብ ጠያቂው ማስጠንቀቂያ መስጠት አያስፈልገውም። ስለሆነም ማስጠንቀቂያ ስላልተሰጠኝ ወለድ ልከፍል አይገባም የሚለው ክርክር ተቀባይነት ስለልለው ተበዳሪ ከየካቲት 01 ቀን ጀምሮ ገንዘቡ ተከፍሎ እስከሚያልቅ ድረስ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር ዋናውን የብድር ገንዘብ ይክፈሉ ሲል ወስኗል።
በአሁን አመልካች የይግባኝ አቤቱታ መነሻ ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህ ከላይ የተመለከተው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ በፍሬ ነገርም ሆነ በህግ ረገድ ቅሬታን የሚያስከትል አይደለም። በማለት መልስ ሰጭዎችን ሣይጣራ ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ዘግቶታል።
ይህ የሰበር ጉዳይ የቀረበውም የአሁን አመልካች ይህ በጉዳዩ ላይ የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤትም ሆነ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጡትን ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚሉበትን የመከራከሪያ ነጥብ በመጥቀስ ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መነሻ ነው።
የአሁን ተጠሪዎችም በበኩላቸው ውሣኔው በህግ መሰረት የተሰጠ ነው የሚሉበትን ምክንያቶች በመዘርዘር መልሳቸውን በጽሑፍ አቅርበዋል። ተጠሪም እንደ ሥርዓቱ ለዚሁ መልስ የመልስ መልስ ሰጥተውበታል።
የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን፤ እኛም ጉዳዩን እንደሚከተው ተመልክተናል።
የአሁኗ አመልካች ወለድ እንዲከፍል በገንዘብ ብድር ውሉ ላይ ግድታ ስለመግባቱ ሣይገለጽ፤
እና ማስጠንቀቂያም ሣይደርሰኝ በወለድ ገንዘቡን ትከፍላለህ የሚለው ዳኝነት በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1775 (ለ) የተመለከተው ድንጋጌ በአግባቡ ሣይታይ በመተርጎሙ ምክንያት ነው። ይህ ድንጋጌ ለዚህ ለተያዘው ጉዳይ ተፈፃሚነት የለውም። ይልቁንም በብድር ስምምነቱ ላይ ወለድ የመክፈል ግድታ ባልተጠቀሰ ጊዜ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1478 እንደተደነገገው ወለድ የመክፈል ግድታ እንደልለብኝ ግልጽ ነው። የሚሉትን ነጥቦች በመጥቀስ በሥር በየደረጃው ባሉ ፍ/ቤቶች የተሰጠውን ውሣኔ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ላታረም ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ሆኖም ግራ ቀኙን የሚያከራክረው ጉዳይ የገንዘብ ብድር ጉዳይ እንደመሆኑ መጠን ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚነሣን ክርክር ስለዚሁ ጉዳይ የሚገዛው ልዩ የህጉ ክፍል ተፈፃሚ በማድረግ ምላሽ የሚሰጠው ሆኖ ከተገኘ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1676 እንደተመለከተው ጉዳዩ በዚህ ለጉዳዩ በቀጥታ ተፈፃሚነት ባለው የህጉ ክፍል መሰረት የሚታይ እንጂ ስለውሎች በጠቅላለው በሚለው የህግ ክፍል የተቀመጡት ድንጋጌዎች አግባብነት አይኖራቸውም። ከዚህ አንፃር ይህንኑ በግራ ቀኙ መካከል የተነሣውን አከራካሪ ነጥብ ለይቶ ለመወሰን ለጉዳዩ አግባብነት ያለውን በፍ/ብሕር ህጉ የሚያልቅ ነገር ብድርን አስመልክቶ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ጋር ተገናዝቦ ላታይ ይገባል።
No topics extracted.
በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2478 ላይ ተበዳሪው ወለድ እንዲከፍል የውል ቃል ከልላ በቀር ለአበዳሪው ወለድ መክፈል የለበትም በሚል የተቀመጠው ድንጋጌ ተዋዋይ ወገኖች ባላቸው የመዋዋል ነፃነት ተጠቅመው በገንዘብ ብድሩ ውል ስለወለዱ አከፋፈል የጠቀሱት ጉዳይ ባይኖር ይህ መሰል የገንዘብ ብድር ውል ስምምነት የወለድ ክፍያ ግድታን ያስከትላል ወይስ አያስከትልም? የሚል ክርክር እንዳያስነሣ ህጉ ክፍተቱን ለመሙላት ማስቀመጡ እንጂ ተበዳሪው በገባው ግድታ መሰረት የብድር ገንዘቡን በመመላሻው ጊዜ አለመክፈሉ ቢረጋገጥ ይህ የመክፈያ ጊዜው ላለፈበት ጊዜ ወለድ የማይከፈል መሆኑን ሁሉ የሚሸፍን አይደለም።
ይህም በመሆኑ ነው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2489(1) ተበዳሪው የተበደረውን ነገር ከመመለስ ወይም ከመክፈል የዘገየ እንደሆነ ስለውሎች በጠቅላላው በሚለውና አግባብነት ባለው ህግ መሰረት ጊዜ በማሣለፍ የሚከፈለውን ወለድ የመክፈል ግድታ አለበት በሚል የተደነገገው። ይህ ድንጋጌ ተፈፃሚነቱ የወለድ ግድታን ላካተተም ላላካተተም ጭምር እንደሆነ ከይዘቱ መረዳት ይቻላል።
ይህም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2489(1) የተመለከተው ስለውሎች በጠቅላላው የህግ ክፍል አፈፃፀም እንደብደሩ ዓይነት እያታየ ተግባራዊ የሚሆኑ እንጂ ለማናቸውም የብድር ገንዘብ መቼም ቢሆን ተፈፃሚ ላሆን እንደማይቻል የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2482 እና 2483 ድንጋጌ ንባብ አስረጂ ነው።
በመሆኑም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2482 እንደተደነገገው ይህ ክርክር ያስነሣው የብድር ስምምነት የብድር ገንዘቡን መመለሻ ጊዜ አስቀድሞ ወስኖ ያስቀመጠ በመሆኑ እና ወለድ የመክፈል ግድታም ያላስቀመጠ በመሆኑም እንደዚህ ያለ የብድር መመለሻ ጊዜ ተወስኖ ከሆነ የብድር ገንዘቡን ከዚህ መመለሻ ጊዜ በፊት የመክፈል ግድታውን በተበዳሪው ላይ የሚጣል እንጂ ይህ የመክፈያ ጊዜ ካለፈ በኃላ አበዳሪው ለተበዳሪው ጊዜው እልፏልና ክፈለኝ በማለት ማስጠንቀቂያ የመስጠት ግድታ የለበትም። አበዳሪ የማስታወቅ ግድታ የሚኖርበት በብድር ውሉ ላይ የብድሩን ገንዘብ መመለሻ ጊዜው በውሉ ያልተወሰነ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ ተከታይ በሆነው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2483 ተመልክቷል።
ስለሆነም አመልካች የወሰዱትን የብድር ገንዘብ ብቻ እንጂ ወለዱንም ጨምረው ለመክፈል ግድታ ያልገቡበት ስምምነት በመሆኑ እና የመክፈያ ጊዜው በወሉ ላይ ተወስኖ የተቀመጠ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2482(2) እና (3) መሰረት በመመላሽ ጊዜው የመክፈል ግድታ ያለበት መሆኑን ተረድቶ ጊዜው ከማለፉ በፊት አለመክፈሉ እስከተረጋገጠ ድረስ የብድር ገንዘቡን ከህጋዊ ወለድ ጋር የመክፈል ግድታ አለበት። በዚህ ሁሉ ምክንያት የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዳኝነት በውጤት ደረጃ ሲታይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አላገኘነውም።
ው ሣ ኔ
በጉዳዩ ላይ የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በይ/መ/ቁ. 71668 ነሐሴ 09 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው የመጨረሻ ትእዛዝ ፀንቷል።
ተጠሪ የብድር ገንዘቡን ከ