No summary available.
ጥቅምት 20 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ መኰንን ገ/ሕይወት አመልካች፡- ሸራተን አዲስ - ጠበቃ ተካ አስፋው ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት የቀረበውን የግል የስራ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች ባሁኑ አመልካች በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የተጠሪዎች ክስ ይዘት ሲታይም በአመልካች ድርጅት በተያለያዩ ጊዜአት ተቀጥረው የተለያዩ የአገልግሎት ዘመን እንዳላቸውና በባንኪቶት እና እስቲዋርዲንግ የስራ ዘርፎች እያገለገሉ እንደሚገኙ፣አመልካች ድርጅት በቅጥር ስርአት ላይ በአሰሪና ሰራተኛ ሕግ ከተደነገገው ውጪ በሰራተኞች መካከል ግልጽ የሆነ ልዩነት በመፍጠር በተመሳሳይ የስራ ሰዓት ርዝመትና ስፋት የክፍያ ልዩነት በመፍጠር ለተጠሪዎች በሕግ የተሰጠውን መብት በመጣስ ከሕግ ጋር የሚጻረር ውል በማዘጋጀት እያስፈረመ በሕግ የተሰጣቸው ተገቢውን ክፍያና ጥቅማ ጥቅም መንፈጉን፣የስራ ሰዓት በወር 208 እንዲሆን በመገደብ በሰዓት ብር 5.50(አምስት ብር ከሃምሳ ሳንቲም) እያሰበ እንደሚከፍላቸውና በቀን ስምንት ሰዓት ለማሰራት በሕጉ የተጣለበትን የአሰሪነት ግድታን ያለመወጣቱን፣ተመሳሳይ የሥራ መደብ ላላቸው ሰራተኞች የክፍያ ልዩነት መፍጠሩንና ለልዩነቱ የቅጥር ሁኔታ አልፎ አልፎ ለሚሰራ ስራ የተቀጠሩ ሰራተኛ እንደቋሚ ሰራተኛ የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ላጠበቁለት አይገባም በማለት በሕግ እውቅና የልለውን ምክንያት መሰረት ማድረጉን ዘርዝረው ተጠሪዎች ለሰሩት ዘመን የተከለከሉትን ሰርቪስ ቻርጅ፣ቲፕ፣ቦነስ በሕግ አግባብ የስድስት ወር እንዲታሰብላቸው፣የአመት ፈቃድ፣የሕክምና አገልግሎት ፣የ24 ሰዓት የሰራተኞች የሕይወት ኢንሹራንስ ሽፋን፣የደመወዝ ጭማሪ፣ፕሮቪደንት ፈንድ የማጠራቀም መብት እንዲጠብቅላቸው እንዲሁም የትርፍ ስራ ሰዓት ሥራ ክፍያ፣የበዓላት እና የእሁድ ቀናት ስራ በመስራት ጥቅም የማግኘት መብት ዘርዝረውና በገንዘብ የሚተመነውን መብት መጠን በገንዘብ ለይተው ጥቅማ ጥቅሞችን የማግኘት መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም ተጠሪዎች የተቀጠሩት አልፎ አልፎ የሚሰራን ሥራ ለመስራት ለተወሰነ ጊዜ በመሆኑ ሰርቪስ ቻርጅ፣ቦነስና ቲፕ የመክፍል፣የፕሮቪደንት ፈንድ መዋጮ የማድረግ፣ኢንሹራንስ የመግባት ግድታ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ወይም በህብረት ስምምነት ወይም ሁለቱም ወገኖች በየግላቸው በተፈራረሟቸው የስራ ቅጥር ውሎች ግድታ ያልተጣለበት መሆኑን ዘርዝሮ ክሱ ተቀባይት የለውም ሲል ተከራክሯል። ጉዳዩ በዚህ መልክ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ተጠሪዎች የተቀጠሩበት ውል የጊዜ ገደብ ያለው ስለመሆኑ በአመልካች በኩል የቀረበው የሰነድ ማስረጃ ቢያስረዳም ተጠሪዎች ሲሰሩ የነበሩት ስራ ተከታታይነት ያለው ስለመሆኑ በማስረጃ መረጋገጡን ገልጾ ተጠሪዎች ላልተወሰነ ጊዜና ስራ የተቀጠሩ ሰራተኞች ናቸው፣እንዲህ ከሆነ በጥቅማ ጥቅም ማግኘት ደረጃ ከቋሚ ሰራተኞች የሚለዩበት ምክንያት የለም በማለት ለእየንዳንዳቸው በወር 4,956.70(አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስድስት ብር ከሰባ ሳንቲም) ታስቦ ክሱ ከመቅረቡ በፊት ላለው ስድስት ወራት በድምሩ ብር 1,576,230.60 (አንድ ሚላዩን አምስት መቶ ሰባ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ብር ከስልሳ ሳንቲም) ሰርቪስ ቻርጅ እንዲከፈላቸው፣አመልካች ድርጅት መደበኛ ሰራተኞች ለሚላቸው የሚሰጣቸው ቲፕ (ጉርሻ) ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከሰጠበት ጊዜ ጀምሮ እንዲያዝላቸው፣የአመት ፈቃድ ማግኘት መብታቸው እንደየአገልግሎታቸው እንዲያዝላቸው፣ፕሮቪደነት ፈንድ የማጠራቀም መብት እንዲጠበቅላቸው ሲል ወስኗል። በዚኅ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ የበታች ፍርድ ቤት ሰርቪስ ቻርጁንና ጉርሻን በተመለከተ የሰጠውን የውሳኔ ክፍል ብቻ ሽሮ በልሎች ነጥቦች ላይ የሰጠውን ውሳኔ ግን ሙሉ በሙሉ በማፅናት ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪዎች የተቀጠሩበት ስራ አመልካች ድርጅት በመደበኛነት የሚሰራው ስራ ሳይሆን አልፎ አልፎ የሚሰራ በመሆኑ ግራ ቀኙ ይህንኑ ተገንዝበው ውል ያደረጉ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ የውል ስምምነቱ ታልፎ ተጠሪዎች የሚሰሩት ስራ ተከታታይነት ያለው ስለመሆኑ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት ለመደበኛ ስራተኞች የተጠበቁ መብትና ጥቅማ ጥቅሞች ለተጠሪዎችም ላጠበቁ ይገባል ተብሎ የተወሰነው የአመልካች ድርጅትን የስራ ባህርይ፣የመዋዋል ነፃነትንና በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 9፣10፣14(ረ)፣53(2) እና 134 ድንጋጌዎችንና ይዘትና መንፈስ ውጪ እንዲሁም ከአዋጁ ዓላማ ጋር እና አስገዳጅነት ያላቸውን የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎችን ይዘት ባላገናዘበ መልኩ ነው በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችሎቱ ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖ እንዲቀርብ ከተደረገ በኋላ ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ተጠሪዎች በሰጡት የፅሑፍ መልስ የተጠሪዎች የቅጥር ውል ሕጋዊ ያለመሆኑና ተጠሪዎች ለረዥም አመታት ይሰሩበት የነበረውና አመልካች አልፎ አልፎ የሚሰሩ ስራዎች ናቸው የሚላቸው በተከታታይነት የሚሰሩ መሆኑን የበታች ፍርድ ቤቶች ከአመልካች ማስረጃዎች ጭምር ስለማረጋገጡ በመገንዘብ የሰጡት ውሳኔ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ ከሰጣቸው አስገዳጅ የህግ ትርጉሞች፣ከአለም አቀፍ የሰራተኞች ድርጅት ደንብና አግባብነት ባላቸው የኢ.ፍ.ዲ.ሪፐብላክ ሕግ መንግስት ድንጋጌዎች መሰረት የተሰጠ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክረዋል። አመልካች በበኩሉ አስገዳጅነት ያላቸው የሰበር ችሎት ውሳኔዎች ለጉዳዩ አግባብነት የልላቸው መሆኑን በመዘርዘር የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን አቅርቧል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የችሎቱን ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዳዩ ላይ ውሳኔ የሰጡት ተገቢውን ማጣራት አድርገው ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪዎች አመልካችን ላከሱት የቻሉት ቅጥሩ አልፎ አልፎ ለሚሰራ ስራ የተደረገ ነው በሚል ምክንያት በሕጉ ላጠበቁ የሚገባቸውን ጥቅማ ጥቅሞችን አልጠበቀልንም፤ከልክሎናል በሚል ምክንያት ሲሆን አመልካች ተጠሪዎች ይገባናል የሚሐቸውን መብቶች የከለከላቸው መሆኑን ሳይክድ እርምጃውን ሕጋዊ በማለት ነው የሚከራከረው የተጠሪዎች ቅጥር አመልካች በመደበኛነት የሚሰራቸውን ስራዎች ለማሰራት የተደረገ ሳይሆን አልፎ አልፎ የሚያጋጥሙት ስራዎች እንደ ስብሰባ ዝግጅት፣የሰርግ ፣የፍስቴቫል እና የምርቃት ፓርቲ፣ከክብረ በዓላት እና ኢዩቤልዩ ሲከበር የሚሰሩትን ስራዎች ለመስራት አውቀውና ወደው በውል በመተሳሰር ተጠሪዎች ስራዎቹን ሲሰሩ የቆዩ በመሆኑ ለመደበኛ ስራ ሰራተኞች የተጠበቁት ጥቅማ ጥቅሞች ላጠበቅላቸው አይገባም፣ከውል ወይም ከህግ የመነጨ ግድታ የለብኝም በማለት መሆኑን ነው። የበታች ፍርድ ቤቶች በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካችን ክርክር ውድቅ ያደረጉት ተጠሪዎች አመልካች አልፎ አልፎ የሚሰሩ ስራዎች ናቸው የሚላቸውን በተከታታይ ፕሮግራም እየወጣላቸው ሲሰሩ የነበሩ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ መረጋገጡ ስራዎቹ ቀጣይነት ያላቸው መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው በሚል ምክንያት መሆኑንም ከውሳኔዎቹ ግልባጮች ተመልክተናል።
በመሰረቱ ማንኛውም የስራ ውል ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ ሕግ ግምት የሚወስድበት ጉዳይ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 9 ድንጋጌ በግልፅ ያሳያል። ይህ የሕግ ግምት ላስተባበል የሚችለው በተጠቀሰው አዋጅ አንቀፅ 10 በተመለከቱት ሁኔታዎች መሰረት ነው።
አሰሪው በዚህ አንቀጽ ስር በተመለከቱት ሁኔታዎች ቅጥሩ መፈፀሙን ካስረዳ በአዋጁ አንቀጽ 9 ስር የተመለከተውን የሕግ ግምት እንዳስተባበለ የሚቆጠር ሲሆን እርምጃውም ከዚሁ አንጻር ላታይ የሚገባው ነው። የሥራው ባህርይ ቀጣይነት ያለው መሆኑ እየታወቀ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ጊዜን በመቁረጥ የሚደረግ የቅጥር ውል ስምምነት ሕጋዊ ጥበቃ የማይደረግለት ስለመሆኑ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም በሰ/መ/፣25526 እና በልሎች በርካታ መዛግብት የሰጠበት ጉዳይ ነው።
በተያዘው ጉዳይ ተጠሪ ከአመልካች ጋር የመሰረቱት የስራ ውል በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 10(ሐ) መሰረት ተደርጎ የተመሰረተ መሆኑ ያልተካደ ጉዳይ ነው። ሆኖም የበታች ፍርድ ቤቶች በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካችን ክርክርና በክርክሩ ሂደት የተረጋጠውን ፍሬ ነገር ተጠሪዎች የሚሰሩት ስራ ቀጣይነት ያለውና አመልካች ድርጅት መደበኛ ስራ ላይም ተጠሪዎችን ማሰራቱ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት ሳይቀበሉት ቀርተዋል። በእርግጥ ከላይ የተጠቀሱት አስገዳጅነት ያላቸው የዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች የስራው ባሕርይ ቀጣይነት ያለው መሆኑ ከተረጋገጠ አሰሪ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 10 መሰረት የስራ ውሉ ተደርጓል በማለት የሚያቀርበው ክርከር ተቀባይነት ላሰጠው እንደማይገባ ያስገነዝባል። ይሁን እንጂ ይህ የሰበር ሰሚ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም መንፈሱ በጥንቃቄ ታይቶ ግንዛቤ ካልተወሰደበት ከሕጉ ዓላማና መንፈስ ጋር የማይሄድ ውጤትን ማስከተሉ የማይቀር መሆኑ እሙን ነው። ስለሆነም የስራው ባሕርይ ቀጣይነት ያለው ነው ለማለት መታያት ያለበት ነጥብ ስራው ለተከታታይ ሳምንታት፣ወራት ወይም አመታት በገበያው አመቺነት ምክንያት መቀጠሉን ነው ወይስ ከገበያው ምቹነት ሳይሆን ስራው ራሱ ብቻውን ሲታይ ቀጣይነት ያለው መሆኑን ለማሳየት ነው? ከሚለው ጥያቄ ጋር ላለይ የሚገባው ነው። በዚህም አግባብ ጉዳዩ ሲታይ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 10 መሰረት ተደረገ ተብሎ የሚቀርበውን የቅጥር ውል ውድቅ ለማድረግ የስራው ቀጣይነት የሚለው መለኪያ መሰረት ማድረግ ያለበት ስራው በገበያው አመቺነት ረዘም ላሉ ጊዜያት መሰራቱን ብቻ ሳይሆን ስራውን በባህርው እና ከድርጅቱ መሰረታዊ አላማ ጋር ተዛምዶ ሲታይ ቀጣይነት ያለው መሆኑ መረጋገጥን ጭምር የሚጠይቅ ላሆን ይገባል። ከዚህ ድምዳሜ ውጪ የሚያዘው ድምዳሜ በአንድ ድርጅት ላይ ተገቢ ያልሆነ የሰው ኃይል እንዲኖር የሚያደርግ እና የድርጅቱን ተወዳዳሪነት በመፈታተን ለአገር ኢኮኖሚ ላጫወተው የሚገባውን ሚና ሁሉ የሚገድብ ነው። የአንድን ድርጅት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ለአገር ኢኮኖሚ የሚያበርክተውን አስተዋጽኦ የሚገድብ እርምጃ ደግሞ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ዓላማን የሚጻርረ ነው። በመሆኑም አንድ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይን አከራክሮ ለመወሰን ስልጣን የተሰጠው አካል አንድን ስራ በባሕርይው ቀጣይነት ያለው ነው ብሎ ለመደምደም ስራው ረዘም ላለ ጊዜ መሰራቱን ብቻ ሳይሆን የስራው ባህርይ ከድርጅቱ አይነተኛ ስራ ጋር የሚሄድና ቀጣይነት ያለው መሆኑን ላያረጋግጥ ይገባል። ይህ ድምዳሜ ሲያዝም የድርጅቱ አጠቃላይ ተቋማዊ ሁኔታው በውል ላታወቅ ይገባል። ይኼውም ድርጅቱ የተቋቋመበት ዓላማ፣ላሸከመው የሚገባው የሰራተኛ ቁጥርና ልሎች ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች በተገቢው መንገድ ተጣርተው ላታወቁ ይገባል።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመጣ አመልካች የተቋቋመበት መደበኛ የመኝታ፣የምግብና የመጠጥ አገልግሎቶችን መስጠት መሆኑን ጠቅሶ ተጠሪዎች ይሰሩበት የነበረውን ስራ አልፎ አልፎ የሚሰራና የአመልካች ድርጅት መደበኛ ስራ ያለመሆኑን ገልጾ ተከራክሯል። ይሁን እንጂ አመልካች የሚሰራቸው መደበኛ ስራዎች አይነት እና ብዛት፣በእነዚህ መደበኛ ስራዎች የሚይዛቸው የሰራተኞች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ፣አመልካች አልፎ አልፎ የሚሰራቸው ስራዎች አመልካች በቀጣይነት የሚሰራቸው መሆን ያለመሆኑ፣ስራዎቹ በቀጣይነት የሚሰሩበት ሁኔታ እንድት ላከሰት እንደሚችልና የሚያስፈልገው የሰው ኃይልና ስራውን ለመስራት በቀን ወይም በወር ለአንድ ሰራተኛ ላመደብ የሚችለው የስራ ሰዓት ምን ያህል እንደሆነ በአመልካች ማስረጃም ሆነ በተጠሪዎች ማስረጃ ነጥረው የወጡ ነጥቦች አይደሉም። ፍርድ ቤቱም የሚመለከታቸውን አካላት እንዲያጣሩለት ያደረገበት የክርክር አመራር ደረጃ ያለመኖሩን የክርክሩ ሂደት ያሳያል። በክርክሩ ሂደት የተነሱትና ለጉዳዩ አወሳሰን ወሳኝ የሆኑት ፍሬ ነገሮች በማስረጃ ሳይነጥሩ ትክክለኛና ፍትሃዊ ዳኝነት መስጠት የማይቻል መሆኑን የዳኝነት አሰጣጥ ስርዓታችን ያስገነዝበናል። ዳኝነት ሰጪ አካል የሆነው ፍርድ ቤት በሕጉ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት የተከራካሪ ወገኖችን ማስረጃ አስቀርቦ ሣይመለከት፤ሳይሰማና ከተያዘው ጭብጥ ጋር አገናዝቦ ሣይመረምር በሕግ ባልተመለከተ ምክንያት የማስረጃ መሰማት መብትን በማለፍ ወይም ፍርድ ቤቱ ራሱ ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ ሲባል ላነጥር የሚገባውን ፍሬ ነገር ራሱ በሚያስቀርበው ማስረጃ ሳያነጥር ፍርድ የሚሰጥበት አካሄድ የዳኝነት አሰጣጥ ስርኣታችን የሚቀበለው ጉዳይ አይደለም። በግልጽ የቀረበን ክርክር በተቆጠረው ማስረጃ ወይም አግባብነት ባለው መንገድ ሣያጣሩ መወሰን ደግሞ መሰረታዊ የሆነ የፍርድ አካሄድ ጉድለት ነው። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 136፣137፣145፣264፣272፣345 እና ልሎች ስለማስረጃ አቀራረብና አቀባበል የተደነገጉት ድንጋጌዎች የሚያስገነዝቡን ሐቅም ይኼው ነው። በመሆኑም ከላይ የተመለከቱት ፍሬ ነገሮች በተከራካሪ ወገኖች ማስረጃዎች ወይም በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በሚቀርቡ የሚመለከታቸው አካላት ወይም የባለሙያ ማስረጃዎች ባልነጠሩበት ሁኔታ የተጠሪዎች ስራ አልፎ አልፎ የሚሰራ አይደለም ተብሎ በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ባልተሟላ የፍርድ አካሄድ የተሰጠና በአመልካች ድርጅት ላይም ተገቢ ያልሆነ የሰራተኛ ኃይል የመጫን ውጤት ያለው በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆኖ ስለአገኘን የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል። በአጠቃላይ ከላይ በተመለከቱት ሕጋዊ ምክንያቶች ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.