No summary available.
ጥር 29 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሤ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- አቶ መሐመድ ሲራጅ ቀረቡ ተጠሪ፡- የአወላያ ዋና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ነ/ፈጅ አቶ አሕመድ ሙዲ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
አመልካች በዚህ መዝገብ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት የፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት የሥራ ክርክር ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 2(1) መሰረት የስራ መሪ በመሆናቸው ያቀረቡት ክስ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት የሚዳኝ አይደለም የሥራ ክርክር ችሎቱም ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም በማለት የሰጠው ውሣኔ እና በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የቀረበለትን ይግባኝ ዘግቶ በማሰናበት የፍ/ከ/ፍ/ቤት ስራ ክርክር ችሎት የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመባቸው በመሆኑ ላታረሙ ይገባል በማለት ሲሆን አቤቱታው ተመርመሮ አመልካች በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 3 እና በማሻሻያው አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 2/1/ መሰረት በሰራተኛ ውስጥ የሚካተት ሳይሆን የስራ መሪ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 ላስተናገድ አይገባም የመባሉን አግባብነት ለማጣራት ጉዳዩ ለሰበር ክርክር ያስቀርባል በመባሉ ግራ ቀኙ የጽሑፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።
የጉዳዩ አመጣጥና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አመልካች ያቀረቡት ክስ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት የሚስተናገድ አይደለም በማለት በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሐግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን መርምረናል።
በዚህም መሰረት አመልካች በ07/03/04 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ያቀረቡት ክስ ይዘት ተጠሪው ድርጅት በሕግ አማካሪነት ቀጠሮ ሲያስራኝ ከቆየ በኋላ አላግባብ ከስራ ያሰናበተኝ በመሆኑ የስራ ውሉ መቋረጥ ሕገወጥ ነው ተብሎ ተጠሪው የካሣ ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ፣የስራ ስንብት ክፍያ በሕብረት ስምምነቱ መሰረት ያደረጉት ክፍያ ለጠቅላላ ሰራተኛ የተሰጠውን የ40% የደመወዝ ጭማሪ እና መሰል ክፍያዎችን እንዲከፍለኝ ውሳኔ ይሰጠኝ የሚል እና የአዋጅ ቁጥር 377/96 ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያስረዳል። የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ የሰጡት አመልካች የስራ መሪ በመሆናቸው ጉዳዩ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 የሚዳኝ አይደለም በማለት ቢሆንም በበኩላችን ግን በመዝገቡ ከቀረበው ክርክር አንፃር ምላሽ ማግኘት የሚገባው ጭብጥ በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ግንኙነት የቅጥር ውል ነው ወይስ የእውቀት ሥራ ውል ነው?
የሚል መሆኑን በመገንዘብ ከዚሁ ጭብጥ አንፃር ጉዳዩን መርምረናል። በዚህም መሰረት አመልካች ከተጠሪ ጋር የስራ ውል ከመሰረቱበት ጊዜ በፊት ጀምሮ የሰራ ግንኙነቱ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ፈቃድ አውጥተው የጥብቅና አገልግሎት በመስጠት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ መሆኑንን ተጠሪው በሰበር መልሱ ላይ የገለፀ ሲሆን አመልካችም የተጠሪው ስራ ብዙ በመሆኑ በጥብቅና ፈቃድ ልላ ስራ ልሰራ አልቻልኩም ከማለት በስተቀር በጥብቅና ስራ አገልግሎት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ መሆኑን አላስተባበሉም። እንደዚህ ዓይነቱ የስራ ግንኙነት ደግሞ በፍ/ሕ/ቁ.2632-2638 በተመለከተው መሰረት በእውቀት ስራ ውል ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንጂ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 3(1) እና (2) መሰረት በቅጥር ላይ የተመሰረተ የስራ ግንኙነት ባለመሆኑ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/96 እና 494/98 መሰረት ሰራተኛም ሆነ የሰራ መሪ ላባሉ የሚችሉ አይደሉም። የግራ ቀኙ መብትና ግድታም የሚወሰነው ከላይ በተጠቀሱትና አግባብነት የሚኖራቸው ልሎች የፍ/ብሕር ህጉ ድንጋጌዎች መሰረት በመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 በግራ ቀኙ መካከል ላለው ግንኙነት ተፈፃሚነት ላኖረው አይችልም። በዚህም ሁኔታ የስር ፍ/ቤቶች ለውሣኔያቸው የሰጡት ምክንያት የተሳሳተ ቢሆንም በውጤት ደረጃ ግን ውሳኔው ተገቢ መሆኑን በመገንዘብ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል፡
348/1/ መሰረት በውጤት ደረጃ ፀንተዋል።
በሰበር ደረጃ የደረሰውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራቸውን ይቻሉ።
ክርክሩ ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል። ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡
No topics extracted.