No summary available.
መጋቢት 12 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡-
ይህ የሰበር ጉዲይ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 የተመለከተውን ድንጋጌ አፈፃፀምና ትርጉም የሚመለከት ሲሆን፤ ዝርዝር ጉዲዩም፣ የአሁን አመልካቾች በሻጭነት ተጠሪ በገዥነት ተሰይመው ጥር 24 ቀን 1999 ዓ.ም አድርገውት በነበረው የቤት ሽያጭ ውል የተነሣ ግራ ቀኙ በመ/ቁ. ዐ55ዐ8 በሆነው መዝገብ ላይ ውለ ይፈርሣል ወይስ አይፈርስም በሚለው ጉዲይ ላይ ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ ክሱን ሲመለከት የነበረው የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሰኔ 23 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በዋለው ችልት በማይንቀሣቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ የሸያጭ ውል ውል ለማዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ፉት ካልተደረገ በቀር የፀና ውል ላሆን አይችልም። ፈራሽ ነው በማለት የፋዳራል ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ.21448 ግንቦት 3ዐ ቀን 1999 ዓ.ም ትርጉም የሰጠበት ስለሆነና ይህም በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው ውል ውል ለማዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ፉት ያልተደረገ ስለሆነ ፈራሽ ነው በማለት በመ/ቁ. ዐ55ዐ8 ላይ ውሣኔ ሰጥቶበታል።
ይህ ውሣኔ ከተሰጠ በኋላ ሻጭ የነበሩት የአሁን አመልካቾች ከዚህ በፉት በግራ ቀኛችን መካከል ተደርጎ የነበረው የቤት ሽያጭ ውል ፈራሽ ነው ተብል የተወሰነ ስለሆነ የሽያጭ ውል ከመደረጉ በፉት ወደነበርንበት ቦታ እንድንመለስ ይወሰንልን በማለት ለዚህ የሰበር ጉዲይ መነሻ የሆነውን ክስ በአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በተጠሪ ላይ ክስ መሥርተዋል።
ገዥ የነበሩትም የአሁን መልስ ሰጭ ውለ ሥልጣን ባለው አካል ፉት እንዱመዘገብ አለመደረጉ የውለን መፍረስ የማያስከትል ስለመሆኑ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ
በታህሣሥ 1ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የተወሰነ ስለሆነ ውለ ሉፈርስ አይገባም፤
የፀና ነው ተብል ይወሰንልኝ የሚል መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም ይህንኑ የግራ ቀኙን ክርክር ተመልክቶ በመ/ቁ. ዐ6799 በ19/9/2ዐዐ2 ዓ.ም በዋለው ችልት ከዚህ በፉት በመ/ቁ. ዐ55ዐ8 በሆነው የግራ ቀኙ ጉዲይ ላይ ውለ ፈራሽ ነው በማለት ሰኔ 23 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ በተመሣሣይ ጉዲይ የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መ/ቁ. 21448 በግንቦት 3ዐ ቀን 1999 ዓ.ም በሰጠው የሕግ ትርጉም መሰረት ነው።
ይህ ውሣኔ በየደረጃው ባለት ፍ/ቤት በይግባኝም የተሻረ አይደለም አሁን ለሁለተኛ ጊዜ የቀረበው ክርክር ደግሞ የሽያጭ ውለ ፈራሽ ነው ተብል የተወሰነውን መሰረት በማድረግ ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት ቦታ እንዱመለሱ ማድረግ ይቻል ዘንድ ታይቶ እንዱወሰን ስለሆነ ውለ ፈራሽ ነው ተብል ከተወሰነ በኋላ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ.36887 በ1ዐ/4/2ዐዐ1 ዓ.ም የተለየ ውሣኔ ወይም ትርጉም መስጠቱ ለዚህ ለተያዘው ወደነበርንበት እንመለስ ጥያቄ ተፈፃሚነት የለውም በማለት ወስኗል።
ሆኖም ይግባኝ ሰሚው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ክርክሩ በይግባኝ ቀርቦለት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ከዚህ በፉት የሥር ፍ/ቤት በመ/ቁ.ዐ55ዐ8 በ23/1ዐ/2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በጊዜው ትክክል የነበረ ቢሆንም በተመሣሣይ ጉዲይ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መ/ቁ. 36887 በታህሣሥ 18 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ውል መኖሩ እስካልተካደ ድረስ ውለ የፀና ነው ተብል ተወስኗል። በዚህ አኳኋን በሰበር ሰሚ ችልት ተስተካክል ከተወሰነ ወይም ከተተረጎመ ይህንኑ ከትርጉም በኋላ የተሰጠን ሁለተኛ ትርጉም መከተል የግድ ስለሆነ ከዚህ በፉት ፈርሷል የተባለው የቤት ሽያጭ ውል የፀና ነው በሚል ተስተካክል ሉወሰን ይገባል። ሉፈርስ አይገባም በማለት ወስኗል። ይህም ውሣኔ በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት እንዱታረም ቀርቦ የሕግ ስህተት የተገኘበት ውሣኔ አይደለም የሚል ዲኝነት በማግኘቱ ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ላቀርብ ችሎል።
ሁለቱም ወገኖች በዚህ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያደረጉት የጽሐፍ ክርክር ከዚህ በፉት በሥር ፍ/ቤቶች ያቀረቡትን ክርክር የደገመ እና ያብራራ ከመሆኑ በቀር በይዘቱ የተለየ ባለመሆኑ በድጋሚ ማስፈሩ አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የሰፈረው ሲሆን እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
በኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 8ዐ/3/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 መሰረት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ትርጉም ያለባቸው ውሣኔዎች የሰበር ሥርዓት መዘርጋት እንዲስፈለገበት ዓላማ በሀገሪቱ ሕጏች ወጥ የሆነ አተረጓጎምና የሕግ አፈፃፀም ይኖራቸው ዘንድ ተከታይ በሆነው አዋጅ ቁጥር 454/97 እንደተደነገገው ይኸው ሰበር ሰሚ ችልት የሕግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች በየትኛውም ደረጃ በሚገኙ የሀገሪቱ ፍ/ቤቶችና የዲኝነት አካላት በተመሣሣይ ተፈፃሚነት እንዲላቸው ከዚሁ አዋጅ አንቀጽ 2 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ተመልክቷል። በሀገሪቱ በየደረጃው የሚገኙት ፍ/ቤቶችና ላልች አካላት ሰበር ሰሚው ችልት በሰጠው ትርጓሜ መሰረት ተመሣሣይ ጉዲዬችን በማየት መወሰን የሚችለት ተመሣሣይ የሆነው ጉዲይ ክርክር ተደርጎበት ለውሣኔ በደረሰበት ጊዜ ሰበር ሰሚው ችልት ትርጉም የሰጠበት ሆኖ ከተገኘ ነው። በዚህም መሰረት በእጅ የተያዘውን ጉዲይ ስንመለከት በመ/ቁ. ዐ55ዐ8 በሆነው መዝገብ ላይ በግራ ቀኙ መካከል የተነሣው ጉዲይ ክርክር ተደርጎበት ለውሣኔ በደረሰበት ጊዜ በተመሣሣይ ጉዲይ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ትርጉም የሰጠበት ጉዲይ መሆኑን የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ተገንዝቦ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 መሰረት ይህንኑ የሰበር ሰሚ ችልት የሰጠውን የሕግ ትርጉም በመከተል ወስኗል።
ከዘህ በኋላ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 እንደተመለከተው የሰበር ሰሚ ችልቱ ትርጉም የሰጠበት ጉዲይ ቢሆንም በልላ ጊዜ የተለየ ትርጉም ለመስጠት ሥልጣን ያለው በመሆኑ ሙለ በሙለ ተመሣሣይ በሆነው ጉዲይ በልላ ጊዜ የተለየ ትርጉም መስጠቱ ቢታወቅ እንኳ የዚሁ በልላ ጊዜ የሰጠው ትርጉም ተፈፃሚነት ወሰን የሕጉ ትርጉም ከተሰጠ በኋላ በመጀመሪያ ደረጃም ሆነ ሳይወሰን ለሚነሱ ክርክሮችና ክርክሮች ተደርገው ለውሣኔ በደረሱ ጉዲዮች ላይ የሚገደብ እንጂ በየደረጃው ያለት ፍ/ቤቶችም ሆኑ ላልች የዲኝነት አካላት በጎንዮሽም ሆነ በላይኛው የክርክር እርከን ክርክር ተደርጎ በውሣኔ የተቋጨን ጉዲይ ሁለ እየቀሰቀሱ እንደገና ለማየት በሚያስችል አኳኋን የተቀመጠ ሥልጣን ሰጭ ድንጋጌ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አልተደነገገም የሕጉ ዓላማም ውሣኔ የሚያሻቸው ጉዲዮች ዓይነት ከዚህ በፉት በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት ቀርበው ትርጉም ተሰጥቶባቸው ከሆነ በሀገሪቱ ወጥ የሆነ የሕግ አተረጓጏምና አፈፃፀም ማስፈን እንዱቻል በተመሣሣይ ታይተው እንዱወሰኑ ለማድረግ እንጂ ሥርዓቱን አሟጦ በውሣኔ የተቋጩን ጉዲይ ሁለ እንደገና እየቀሰቀሱ የተረጋጋውን ሁኔታ ለማናጋት ወይም ተከራካሪ ወገኖችን ተገማች ላልሆነ የዲኝነት ሥርዓት ለመጋበዝ ተፈልጏ አይደለም። ስለሆነም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጡት ዲኝነት ከላይ በዝርዝር እንደሰፈረው በአዋጅ ቁጥር 454/97 የተፈፃሚነት አግባብ ላይ የሰጡት ትርጓሜ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው በሕገ - መንግሥቱ አንቀጽ 8ዐ/3/ሀ/ እና 25/88 አንቀጽ 1ዐ መሰረት በማረም የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ 1/ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 1ዐ634ዐ ጥር 1ዐ ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ፤ እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 124793 በ14/7/2ዐዐ3 ዓ.ም. የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
3/ በመ/ቁ. ዐ55ዐ8 በሰኔ 23 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 በተመለከተው ድንጋጌ መሰረት ታየቶ የመጨረሻ ዲኝነት ያገኘ ጉዲይ ስለሆነ እንደገና ውሣኔውን ከአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 አንፃር አይቶ ለማረም የሚያስችል ሥርዓት የለም ብለናል።
በዚህ ሰበር ችልት የተደረገው ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሣራ ሁለቱም ወገኖች የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.