No summary available.
ሰኔ 22 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፉሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የዱላ ዩንቨርስቲ - ነገረፈጅ ተዘራ ገዲሙ ቀረቡ ተጠሪ፡- 1ኛ. አቶ የትናየት ጣፊ - የቀረበ የለም 2ኛ. አቶ ዲግም ጫላ - ቀረቡ 3ኛ. አቶ ነጌሳ ጥላሁን - የቀረበ የለም መዝገቡ ያደረው ለውሳኔ ሲሆን ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ተጠሪዎች በዱላ ዩንቨርስቲ በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ክፍል ከTA || ወደ GA || የደረጃ እድገት እንዱሰጠን በተለያዩ የስራ ክፍልች የተወሰነ ሆኖ ያልተፈጸመ ስለመሆኑ በማመላከት የደረጃ እድገቱ እንዱሰጣቸው እና ክፍያውም ከተወሰነላቸው ቀን ጀምሮ እንዱከፈለን በማለት የቀረበውን ክስ ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የደቡብ ክልል የጌድኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክር በመስማት የደረጃ እድገቱም እንዱሰጣቸው እና ክፍያውም እንዱፈጸምላቸው ውሳኔ ሰጥቷል፣ ይሄው ውሳኔ በክልለ የጠቅላይ ፍርድ ቤትም በመጽናቱ አመልካች የተፈጸመው መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዱታረምልን በማለት በማመልከቱ የቀረበ ነው፡ አመልካች ባቀረበው የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞባቸዋል ያላቸውን ነጥቦች ያነሳ ሲሆን ፍሬ ሃሳቡ፡- ተጠሪዎች በክሳቸው የተመለከተውን የደረጃ እድገት እንዱያገኙ በትምህርት ክፍላቸው አማካኝነት ለፊኩልቲው ቀርቦ እና ፊኩልቲውም ለተቋሙ ኘሬዚዲንት አስተላልፍታል፣ ሆኖም ይሄ የደረጃ ዕድገት ሉተገበር የሚችለው የፋ/ሲቪል ሰርቪስ ውክልና ያለው የፋ/ትምህርት ሚንስቴር የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ ሲያጸድቀው በመሆኑ እና ይሄንን በማጽደቅ ያልመለሰ በመሆኑ የምፈጽመው የእድገት ጥያቄ የላለ በመሆኑ በኋላ ላይ በትምህርት ሚንስቴር በተላለፈው ሰርኩላር መሰረት ዩንቨርስቲው የሚያያቸው የእድገት ጥያቄዎች ሉታዩ የሚችለ ሁነው አሁን በፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ግን ከመመሪያ ውጭ እንድንሰራ የሚያደርግ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው አይደለም። ቀደም ሲል በዩንቨርስቲው የተጻፈው ደብዲቤም ቢሆን ተጠሪዎች ወደ ደረጃ GA-| እንዱያድጉ እንጂ ወደ ደረጃ GA-|| ባለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጠት ውሳኔ አግባብነት የላለው በመሆኑ እንድታረምልን የሚል ነው።
ጉዲዩ ለዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ሲባል የስር ፍርድ ቤቶች ይሄንን ጉዲይ አይተው ለመወሰን የስረ ነገር ስልጣን ያላቸው መሆን አለመሆንን ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.9 አንጻር ለመመርመር በሚል ጭብጥ ተይዞ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት በመታዘዙ መልሳቸውን ሰጥተውበታል። የተሰጠውም የመልስ ፍሬ ሃሳብ፡- ለፍርድ ቤቱ ያቀረብነው ክስ በመካከላችን ያለውን ውል ይፈጸም እንጂ ያቀረብነው የደረጃ እድገት ባለመሆኑ ፍርድ ቤቱ ይሄንን የፍታብሓር ክስ መመልከት ይችላል፡ አስፈላጊውን ሰነድች ፍርድ ቤቱ ከስራ ክፍላችን በማስመጣት መመልከት የሚችል በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶችም የሰጡት ውሳኔ በአግባቡ በመሆኑ እንዱጸናልን በማለት ተከራክሯል። አመልካችም ባቀረበው የመልስ መልስ አመልካች የመንግስት መስሪያ ቤት እንደመሆኑ መጠን የሚተዲደረው በፋ/የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 515/99 መሰረት በመሆኑ ፍርድ ቤቶች ይሄንን ክስ የማስተናገድ ስልጣን የላቸውም በሚል ቅሬታውን በማጠናከር ተከራክሯል።
በግራቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ ከተያዘው ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
እንደመረመረውም ይሄንን ጉዲይ መደበኛ ፍርድ ቤቶች በቀጥታ ክሱን ተመልክተው ውሳኔ ሉሰጡበት የሚያስችል የስረ ነገር ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ ወይም ስላለመሆኑ በመመልከት ለተያዘው ጉዲይ እልባት መስጠት ተገቢነት ይኖረዋል።
በዚሁ መሰረት ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪዎች የደረጃ እድገት እንዱያገኙ በዩንቨርሲቲው የተለያዩ የስራ ክፍልች የውሳኔ ሃሳብ የተጻጻፈ ስለመሆኑ፣ ሁኖም ግን በስተመጨረሻ ለትምህርት ሚንስቴር የተጻፈ የውሳኔ ሃሳብ ስለመኖሩ እና የትምህርት ሚንስተር የቀረበለትን የደረጃ እድገት በማጽደቅ ያልመለሰ ስለመሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች ናቸው፣ ሆኖም ግን የክልለ የከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች የተጠየቀውን የደረጃ እድገት ጥያቄ የትምህርት ሚንስተር በማጽደቅ አልመለሰልኝም በማለት እጁን አጣጣፍ መቀመጥ የለበትም በማለት የደረጃ እድገቱም ሆነ ክፍያው እንዱፈጸምላቸው ውሳኔ የሰጠ ስለመሆኑ መመልከት ይቻላል።
ከዚህ ሁለ ክርክር እና በታች ፍርድ ቤቶች ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር መገንዘብ የሚቻለው አከራካሪው ጉዲይ የደረጃ እድገት የሚሰጥበትን አግባብ የሚመለከት እንጂ ተጠሪዎች እንደሚለት የውል ግንኙነትን መሰረት ያደረገ የፍትሐብሕር ክርክር አለመሆኑን ነው። ይሄ ከሆነ ደግሞ ይሄንን የደረጃ እድገት ጥያቄ ፍርድ ቤቶች በቀጥታ ተቀብለው ማስተናገድ የሚችለ ስለመሆኑ ወይም ስላለመሆኑ በመመልከት ለተያዘው ጉዲይ እልባት መስጠት ተገቢነት ይኖረዋል ማለት ነው። በዚሁ መሰረት ጉዲዩን ስንመለከት ተጠሪዎች የዱላ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ክፍል ውስጥ የሚሰሩ ስለመሆኑ እና መስሪያ ቤቱም የመንግስት መስሪያ ቤት ስለመሆኑ ግራቀኙን አላከራከረም። ይሄ ከሆነ ደግሞ ለዚህ ጉዲይ ተፈጻሚነት ያለው የህግ ማዕቀፍ እንዲግባብነቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መመልከት ይቻላል። ከእነዚህ የህግ ማዕቀፍች አጠቃላይ ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ የፋዳራል የመንግስት ተቋም ባጠቃላይ እና የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በተለይ የራሱ የሆነ የእድገት አሰጣጥ፣ የቅሬታ አፈታት እና አጠቃላይ አስተዲደራዊ ስራዎችን የሚያከናውኑበትን አግባብ ያስቀመጡ ስለመሆኑ መመልከት ይቻላል።
ይሄ ከሆነ ደግሞ የተጠሪዎች የደረጃ እድገት ክርክር በእነዚሁ አዋጆች በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ታይቶ እልባት ከሚያገኝ በስተቀር በቀጥታ ለመደበኛ ፍርድ ቤት የሚቀርብበት እና ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን በቀጥታ አይተው ውሳኔ የሚሰጡበት አግባብ አይኖርም። የበታች ፍርድ ቤቶችም ጏዲዩ ሲቀርብላቸው ስልጣን እንደላላቸው በመገንዘብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.
9፣231/1/ለ/ ፣244/2/ሀ/ መሰረት መመለስ ሲገባቸው ክሱን በመቀበልና በማከራከር ውሳኔ መስጠታቸው አግባብነት የላለው ሁኖ አግኝተናል። ባጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ባቀረቡት የደረጃ እድገት ጥያቄ ላይ ስልጣን ሳይኖራቸው የሰጡት ውሳኔ አግባብነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሳኔ ሰጥቷል።
በዋለው ችልት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.348(1) መሰረት ተሽሯል።
የመደበኛ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ያቀረቡትን የደረጃ እድገት ጥያቄ በመመልከት ውሳኔ ለመስጠት የስረ ነገር ስልጣን የለውም ብለናል። ይህ ማለት ግን ተጠሪዎች መብታቸውን በህጉ በተቀመጠው ስርዓት መሰረት መብታቸውን ከመጠየቅ ይሄ ውሳኔ አያግዲቸውም።
በዚህ ችልት በተደረገው ክርክር በግራቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.