No summary available.
የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ሀብቱ ሀጋዚ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1- የኮምቦልቻ ግብርና ሙያ ማሰልጠኛ ኮላጅ - አበበ ዘውደ ቀረቡ 2- አቶ ዐመር የሱፍ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የአንደኛ ተጠሪ ንብረት የሆነችውን ኮድ 4-00242 የሆነች መኪና በሁለተኛው ተጠሪ በመሽከርከር ላይ እያለ የአካል ጉዲት የደረሰበት መሆኑን ገልፆ ያቀረበውን የካሣ ጥያቄ በመቀበል ፣ ለደረሰው ጉዲት ሙለ በሙለ ኃላፉዎች ተጠሪዎች ናቸው።
ተጠሪዎች ለአመልካች ብር 63,ዐዐዐ /ስልሣ ሶስት ሺህ ብር/ ካሣና ለህክምና የወጣውን ብር 11,277.90/አሥራ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሰባት ብር ከዘጠና ሣንቲም/ ይክፈለ በማለት የሐረሪ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሰኔ 29 ቀን 2002 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ አንደኛ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አንደኛ ተጠሪና አመልካች ያቀረቡትን ክርክር ከሰማ በኋላ ለደረሰው ጉዲት አመልካች በከፉል ኃላፉነት አለበት በማለት አንደኛ ተጠሪ አመልካች ለህክምና ወጭ ያደረገውን ብር 11,277.90 /አሥራ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሰባት ብር ከዘጠና ሣንቲም/ ብቻ ይክፈል በማለት በመዝገብ ጥቅምት 3ዐ ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠውን ውሣኔ በሰበር ታይቶ እንዱታረም ነው።
አመልካች ጥር 23 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የሐረሪ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በከፉል በመሻር የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት መሆኑን በመዘርዘር አመልክተዋል። ጉዲዩ በሰበር የሚጣራ ነጥብ ያለው መሆኑ ተገልፆ ጭብጥ ተመርቶ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት መጥሪያ በመላኩ ተጠሪ መልስ ሰጥቷል። አመልካች በፅሐፍ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
እኛም በመጀመሪያ በሰበር የተያዘውን ጭብጥ ከመወሰናችን በፉት ጉዲዩ የይግባኝ ደረጃውን የጨረሰና በሰበር ለመታየት የሚችል ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ማየቱ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው በሐረሪ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተከራከሩት ተከራካሪ ወገኖች የሁለት ክልል ኗሪዎች ናቸው። አመልካች የሐረሪ ክልል ነዋሪ ሲሆን ተጠሪ የኦሮሚያ ክልል የተቋቋመ የግብርና ሙያ ማሰልጠኛ ኮላጅ ነው። ይህም በመሆኑ የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በመቀበል አከራከሮ የወሰነው በህገ መንግስቱ አንቀፅ 8ዐ ንዐስ አንቀፅ 4 በተሰጠው የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የውክልና ሥልጣኑ ነው። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በይግባኝ በማየት የወሰነው በህገመንግስቱ አንቀፅ 80 ንዐስ አንቀፅ 2 በተሰጠው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የውክልና ሥልጣን ነው።
ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 5 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት የፍደራል ጉዲይ ከሆነና የሐረሪ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የውክልና ሥልጣኑ አይቶ የሰጠውን ውሣኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውክልና በተሰጠው ሥልጣን አይቶ ከለወጠው አመልካች ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ማቅረብ እንዲለበት አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 9 ንዐስ አንቀፅ 2 በግልፅ ይደነግጋል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበው በመጀመሪያ ውሣኔው በይግባኝ እንዱታይለት ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ጉዲዩን ሣያቀርብና ይግባኝ ሰሚው ችልት የመጨረሻ ውሣኔ ሣይሰጥበት ነው። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት በዲኝነት አይቶ ውሣኔ የሚሰጠው በይግባኝ ታይተው የመጨረሻ ውሣኔ ባገኙ ጉዲዮች ላይ እንደሆነ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 8ዐ ንዐስ አንቀፅ 3/ሀ/ ተደንግጓል።
ስለሆነም አመልካች የይግባኝ ደረጃውን ሣይጨርስ ጉዲዩ በሰበር ታይቶ እንዱወሰንለት ያቀረበው አቤቱታ የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
ው ሣ ኔ አመልካች ይግባኝ ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በማቅረብ ጉዲዩ የመጨረሻ ውሣኔ እንዱያገኝ ሣያመለክት በሰበር ችልት ያቀረበውን አቤቱታ ለማስተናገድ የሚችልበት የህግ መሰረት የላለ በመሆኑ አልተቀበልነውም።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.