No summary available.
ህዲር 18 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አመልካች፡- አቶ ዘውደ ግዛው ተጠሪ፡- ወ/ሮ አየለች ደስታ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ህዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የቤት ሽያጭ ውል የሚመለከት ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በወንድገነት ወረዲ ፍ/ቤት ነው። በስር ፍ/ቤት አመልካች ከሣሽ ተጠሪ ተከሣሽ ሆነው ተከራክረዋል። አመልካች በልጁ ስም የገዛው ቤት በገዢ ስም እንዱዛወርለት ክስ አቅርቦ የወረዲው ፍ/ቤት ቤቱ በገዢ ስም እንዱዛወር ሀምላ 6 ቀን 2001 ዓ.ም. ውሣኔ ሲሰጥ ውለ ህጋዊ ነው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። ከዚህ በኋላ የተጠሪ ልጅ ወ/ሮ አይናለም እርቅነው ፍርደን በመቃወም አቤቱታ አቅርባለች። የወረዲው ፍ/ቤት በፉት የሰጠውን ውሣኔ በማጽደቅ ሀምላ 6 ቀን 2002 ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቷል። ተጠሪ በውሣኔው ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለሲዲማ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍ/ቤት በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ይግባኙን ሰርዞታል።
አመልካች በወረዲውና በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ተጠሪ የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበዋል። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ተጠሪን በችልት አስቀርቦ በማየትና ተጠሪ በዕድሜያቸው በጣም የገፈ ማየትም ሆነ ማንበብና መጻፍ የማይችለ አሮጊት መሆናቸውን በማረጋገጥ እንደዚሁም በውለ ላይ ያለው የጣት አሻራ ፊርማ የተጠሪ መሆኑን ለማጣራት በውለ ላይ የተገለጸው ምስክሮች በማጣሪያ ምስክርነት አስቀርቦ በመስማት የሥር ፍ/ቤት ተጠሪ ቀርበው ሣይከራከሩ ቀርበው እንደተከራከሩ በማስመሰል የቤት ሽያጭ ውለ ተፈጻሚነት አለው በማለት የሰጠው ውሣኔ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1728 ንኡስ አንቀጽ 3 ድንጋጌ የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት የወረዲው ፍ/ቤትና የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል።
አመልካች የካቲት 24 ቀን 2002 ዓ.ም ባቀረበው አቤቱታ ውለ በመጀመሪያ ለወረዲው ፍ/ቤት ባቀረብኩት ክስ ክርክር ተደርጏበት ቤቱን የገዛሁት አካለ መጠን ባልደረሰ ልጄ ስም ስለነበር በእኔ በአባቷ ስም እንዱዛወር ውሣኔ ተሰጥቶበታል። የተጠሪ ልጅ ውክልና ሣይኖራት የክስ መቃወሚያ በህግ ከተፈቀደው ሥርዓት ውጭ አቅርባ ተሰርዞባታል። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችልት በተከራካሪዋ ያልተነሳ ነገር ራሱ በዝርዝር በማስፈር የቤት ሽያጭ ውል ስለመኖሩ የተካደበት ነጥብ በላለበት ሁኔታ ከህግ ውጭ የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡትን ውሣኔ መሻሩ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ ጥር 6 ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ መልስ የወረዲው ፍ/ቤት በመጀመሪያ ጉዲዩን አይቶ ሲወስን በፍ/ቤት ቀርቤ በቃል ክርክር እንዲመንኩ ተቆጥሮ በመዝገቡ በላለሁበት ውሣኔ የሰጠ በመሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት ውለ ሀሰተኛ መሆኑን በውለ ላይ ስማቸው የተገለጸውን ምስክሮች በማጣሪያ ምስክርነት በመስማት አረጋግጦ የወሰነው ውሣኔ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ በጽሁፍ ያቀረቡት አቤቱታ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩን የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ከላይ የተገለጸውን ጭብጥ ለመወሰን የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት የተጠሪን ማንበብና መጻፍ አለመቻል ተጠሪ ማየት የማይችለ በእድሜ የገፈ መሆኑንና በውለ ላይ ስማቸው የተገለጹ ምስክሮችን በመስማት ፍሬ ጉዲይ በማጣራት እና ማስረጃ በመመዘን የሰጠው ውሣኔን ተገቢነት ማየት አስፈላጊ ነው። የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበትን በክልል ጉዲዮች የተሰጠ የመጨረሻ ውሣኔ ለማረም በሰበር ችልት የማየት ስልጣን እንዲለውና ዝርዝሩ በህግ እንደሚወሰን በኢ.ፋ.ዳ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80 ንኡስ አንቀጽ 3/ለ/ ተደንግጓል። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችልት በክልል ጉዲዮች በተሰጠ የመጨረሻ ውሣኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበትን ውሣኔ በሰበር አይቶ የማረም ስልጣን እንዲለው በክልለ ህገ መንግስትና በክልለ ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ድንጋጌዎች መኖሩን ለመገንዘብ ይቻላል።
ከላይ በዝርዝር ከገለጽናቸው የህግ ማዕቀፍች የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት ፍሬ ጉዲይ የማጣራት ተጨማሪ ምስክር መስማትና ተጨማሪ ማስረጃ በመቀበል ማስረጃን በመመዘንና በመመርመር ውሣኔ መስጠቱ በክልለ ጉዲይ በተሰጠ የመጨረሻ ውሣኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ከማረም ስልጣኑ ውጭ በመውጣት ውሣኔ የሰጠ መሆኑን የሚያሣዩ ናቸው። የሰበር ሥርዓት በመሰረታዊ ባህሪው ከይግባኝ ሥርዓት የተለየ ነው። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችልት በዚህ መዝገብ ተጨማሪ ምስክሮችን በመስማትና ላልች ፍሬ ጉዲዮችን በማጣራት ማስረጃ በመመዘን የሰጠው ውሣኔ የአመልካቹን የመከላከያ ማስረጃ የማቅረብና የመስማት መብት የሚያጣብብ ነው። አመልካች በፍሬ ጉዲይና በማስረጃ ምዘና ሂደት ተፈጽሟል የሚለውን ስህተት በይግባኝ የማሣየት መብቱን የሚያሳጣ ነው።
በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ጉዲዩን ባየበትና ተጠሪን አስቀርቦ በአካል በአየበት ወቅት ሣይሆን ወለን በተዋዋለበት ጊዜ ማየት የተሣናቸው ነበሩ ወይስ አልነበሩም? ተጠሪዋ በወቅቱ ማሀይም ማንበብና መጻፍ የሚችለ ነበሩ ወይስ አይደለም? የሚለት ነጥቦች ግራ ቀኙ በስር ፍ/ቤት ያልተከራከሩበትንና ማስረጃቸውን አቅርበው ያላሰሙበት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ውለ ላይ ተጠሪ ስለመፈረማቸው ወይም አለመፈረማቸውና ስለውል አፈራረም የግራ ቀኙ ማስረጃ አቅርበው ማሰማትና መከራከር ካለባቸው በስር ፍ/ቤት እንጂ በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችልት ላሆን እንደማይገባ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80 ንኡስ አንቀጽ 3 /ለ/ ና ከላልች የክልለ የህግ ማዕቀፍች እንደዚሁም ከፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343/1/ ድንጋጌዎች ይዘት መንፈስና ዓላማ ለመገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት ተጠሪ በአሁኑ ወቅት ማየት የተሳናትና ማሀይም ናት በማለት በፍሬ ጉዲይ ደረጃ መደምደሚያ ላይ የደረሰው ተጠሪ ውለ ከአመልካች ጋር ተዋዋለች በተባለበት ወቅት ስለነበረው ሁኔታ አመልካች የበኩለን ማስረጃ እንዱያቀርብ እድል ያልሰጠና ከላይ የተጠቀሱትን የህግ ድንጋጌዎች የጣሰ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ህዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የወንድገነት ወረዲ ፍ/ቤት ተጠሪ ውለን ከአመልካች ጋር በተዋዋለበት ጊዜ ማየት የተሣናቸው ነበሩ ወይስ አልነበሩም? ተጠሪ ውለን በሚዋዋለበት ጊዜ ማንበብና መጻፍ የማይችለ ነበሩ ወይስ አልነበሩም? ተጠሪ ውለን ከአመልካች ጋር ተዋውለዋል ወይስ አልተዋዋለም? በሚለት ነጥቦች ላይ የአመልካችንና የተጠሪን ምስክሮቻቸውን እንዱያቀርቡ በማድረግና በውለ ላይ በምስክርነት ተገኝተው ፈርመዋል የተባለትን ምስክሮች ቃል በመስማት አመልካች ከተጠሪ ጋር አድርጌዋለሁ የሚለው ውል ፈራሽ ነው ወይስ አይደለም? ውለ ፈራሽ ነው የሚባል ቢሆን ውጤቱ ምን ይሆናል በሚለት ጭብጦች ላይ ውሣኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍ/ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.