No summary available.
ሕዲር 18 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ቴላኮሙኒኬሸን ኮርፕሬሽን - ተጠሪ፡- አቶ ማርቆስ አበበ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአዱስ አበባ ከተማ ማህበራዊ ፍ/ቤቶች አመልካች የኢትዮጵያ ቴላኮሙኒኬሽን ኮርፕሬሽን ተከራካሪ የሆነበትን ጉዲይ ተመልክተው ለመወሰን የሚያስችል ሥልጣን ያላቸው መሆን ያለመሆኑን የሚመለከት ነው።
የጉዲዩም መነሻ የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ የመሰረተው የጉዲት ካሳ ይከፈለኝ ጥያቄ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡-ንብረትነቱ የተጠሪ የሆነው የሰ/ቁ/ 2-61006 አ.አ ተሽከርካሪ በስር 2ኛ ተከሳሽ በነበሩት ግለሰብ ሲሽከረከር ግንቦት 07 ቀን 1999 ዓ.ም. የአመልካች ንብረት የሆነውን የሰ/ቁጥር 4-06809 ኢ.ት. መኪና በመግጨት ጉዲት በማድረሱ መኪናውን ወደ ነበረበት ለመመለስ የወጣውን ወጪ ብር 4,537.50 (አራት ሺህ አምስት መቶ ሰላሳ ሰባት ብር ከሃምሳ ሳንቲም) ተከሳሾች በአንድነት እና በነጠላ እንዱከፍለ ይወሰንልኝ የሚል ነው። የአሁኑ ተጠሪም በአመልካች መኪና ላይ ጉዲት አደረሰ የተባለው የሰ/ቁጥር 2-61006 የሆነውን መኪና ከሕዲር 15 ቀን 1998 ዓ.ም. ጀምሮ ለአቶ ሄኖክ ታደሰ በሽያጭ ውል ያስተላለፍኩ ስለሆነ ግጭቱ በደረሰበት ጊዜ የመኪናው ባለንብረት ስላልሆንኩ ልከሰስ አይገባም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃም ግጭቱን አደረሰ የተባለውን መኪና በግጭቱ ወቅት በይዞታቸው ስር አድርገው ሲጠቀሙ ያልነበሩ በመሆኑ ተጠያቂነት የላለባቸው መሆኑን ጠቅሰው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል።
ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት በጉዲዩ ላይ ሁለቱንም ወገኖች ካከራከረ በኋላ ተጠያቂ የሚሆነው መኪናውን የገዛው ሰው እንጂ ተጠሪ አይደለም በማለት የወሰነ ሲሆን በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለከተማው መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ይኸው ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የመኪና ባለቤት የሚታወቀው በሉብሬ ስለመሆኑ የአዋጅ ቁጥር 256/60 አንቀፅ 6(1) እና የደንብ ቁጥር 360/69 አንቀፅ 4 ድንጋጌዎች ያሳያለ በማለት ተጠሪን ለጉዲቱ ኃላፉ ያደረጋቸው ሲሆን ተጠሪ ይህን ውሳኔ በመቃወም የሰበር አቤቱታቸውን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበዋል። ይኸው ሰበር ሰሚው ችልትም ወደ ጉዲዩ ዘልቆ ከመግባቱ በፉት ክሱ በአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ቀርቦ ላታይ የሚገባው ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው የሥልጣን ጉዲይ በቅድሚያ ሉመረመር የሚገባው ነጥብ መሆኑን በጭብጥነት ይዞ የአሁን አመልካች በፋዳራል መንግሥቱ የተመዘገበ አካል ነው፣ይህን መሰል ወገን ተከራካሪ የሆነበትን ጉዲይ ተመልክተው የመዲኘት ሥልጣን ያላቸው የፋዳራል ፍ/ቤቶች ስለመሆናቸው በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5/1/ ሥር ተመልክቷል።
ስለሆነም የፋዳራል የሆነውን ጉዲይ የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ተመልክተው ለመወሰን ከሕግ የመነጨ ሥልጣን የላቸውም በማለት በየደረጃው የተሰጠውን ውሣኔ ሽሮ ግራ ቀኙን አሰናብቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህ ከላይ የተጠቀሰው ትርጉም በአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀፅ 50(1) ስለማኀበራዊ ፍ/ቤቶች የተሰጣቸውን ሥልጣን ያገናዘበ አይደለም፣በሁለቱም አዋጆች ላይ ሥልጣንን በሚመለከት ግጭት አለ እንኳ ቢባል አግባብነት ያለውን አተረጓጎም ልንከተል ይገባል፣ ከዚህ ቅደም ተከተል አንፃር ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለው አዋጅ ቁጥር 361/1995 እንጂ አዋጅ ቁጥር 25/1988 አይደለም፣ ስለሆነም የሕግ ስህተቱ ይታረምልን በማለት አመልካች በማመልከቱ ነው። ጉዲዩ በሰበር ችልት ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበትም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል። ይህ ችልትም ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
የፋዳራል ፍርድ ቤቶች የወል የፍትሐብሕር ሥልጣንን በሚደነግገው በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 5 (1) እና (6) መሰረት በጉዲዩ የተካተተው የገንዘብ መጠን ምንም ይሁን ምን የፋዳራል መንግሥቱ አካል ወይም በፋዳራል መንግስት የተመዘገበ የንግድ ድርጅት ወይም ማህበር ተከራካሪ የሆነበትን ማናቸውም ጉዲይ ተቀብለው ለማስተናገድ ብቸኛ ሥልጣን ያላቸው የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ናቸው። ይህ አዋጅ በፋዳራለ መንግስት የወጣ ሲሆን በልላ በኩል ተመሳሳይ በሆነ አካል (በፋዳራለ የሕግ አውጪ) የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶችን ለማደራጀት በወጣው አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 5ዐ ላይ ደግሞ ተከራካሪ ወገን ማንም ይሁን ማን እስከ ብር 5ዐዐዐ.00 ሉደርስ የሚችለውን የገንዘብ ክርክር ጉዲይ በአዱስ አበባ ሥር እስከተነሣ ድረስ የአዱስ አበባ ከተማ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ተቀብለው ለመወሰን ሥልጣን የተሰጣቸው ስለመሆኑ የተጠቃሹ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ያሳያል። እንዱህ ከሆነ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 5(1) እና (6) ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ከአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 50 ይዘትና መንፈስ ጋር ጋር ተገናዝቦ ላታይ የሚገባው ነው። ይህን ለማድረግም ተገቢውን የሕግ አተረጓጎም ዘዳ መከተል የግድ ይላል። ከእነዚህም የአተረጓጎም ዘዳዎች ልንከተለው የሚገባው አንደ፤አንድን ክርክር ያስነሳውን ጉዲይ ተቀብል ለመወሰን ሥልጣን ያላቸው የትኞቹ ፍ/ቤቶች ናቸው? የሚለውን አስመልክቶ በእኩል ደረጃ የሚገኙ ሕጎች /አዋጆች/ በተለያየ ሁኔታ ደንግገው ከተገኙ ከጊዜ ቅደም ተከተል አንፃር በኋላ የወጣው ሕግ ከፍተኛና በልጦ ተፈፃሚነት ይኖረዋል የሚለው የትርጉም መርህ ነው። በመሆኑም አዋጁ ቁጥር 361/1995 ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 ጋር እኩል ደረጃ ላይ የሚገኝ ሕግ ሲሆን አዋጅ ቁጥር 361/1995 በኋላ የወጣ በመሆኑ ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 ቅድሚያ ተፈጻሚነት ይኖረዋል። በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5/1እና 6/ ድንጋጌ መሰረት ይህ መሰል ጉዲይ በፋዳራል ፍ/ቤቶች ሥር እንደሚወድቅ እየታወቀ ሕግ አውጪው ዘግይቶ ሥልጣንን በገንዘብ መጠን ወሰን አበጅቶ በልላ አነስተኛ የፍርድ መድረክ ሥር ቀርቦ እንዱታይ ማድረጉ በክርክር ምክንያት የሚሰጠው ወጪና የሚባክነው ጊዜ ክርክሮች ከያዙት የገንዘብ መጠን ጋር የተመጣጠነ ላሆን እንደሚገባው ታሳቢ በማድረግ የፋዳራል ፍ/ቤቶችን ሥልጣን ቀንሶ ለመስጠት ሲባል የወጣ ሕግ መሆኑን ያመለክታል። በተለይም ይህንኑ የትርጉም መስመር ይበልጥ የሚያጠናክረው የፋዳራል ፍ/ቤቶች ሥልጣን ተፈፃሚ ከሚሆንበት ከድሬዲዋ ከተማ ጋር በተያያዘ የድሬዲዋ ከተማ ቻርተር ለማቋቋም በወጣው በአዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀጽ 41 ሥር ስለ ቀበላ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ሥልጣን ሲደነግግ ከተላላፉ የገንዘብ ሰነድች እና ከኢንሹራንስ ጉዲይ በቀር ላልች ግምታቸው እስከ ብር 25ዐዐ.00 ድረስ ያለትን ገንዘብ ነክ ክርክሮች ለማየት ሥልጣን ያላቸው የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ናቸው በማለት ከዚህ ቀድሞ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 5 ሥር የፋዳራል ጉዲይ መሆኑን ለመለየት መነሻ ከሆኑት 1ዐ ንዐስ ጉዲዮች መካከል ተላላፉ የገንዘብ ሰነድና የኢንሹራንስ ጉዲዮች ሉያስነሱ ከሚችለት የተወሳሰበ የሕግ ጥያቄ አንፃር ሁለቱን ብቻ በመለየት የፋዳራል ሆነው እንዱቀሩ፣ ከላልች ጉዲዮች የሚነሳው ክርክር ግን ግምቱ እስከ 25ዐዐ.00 እስካልበጠ ድረስ ከፋዳራል ፍርድ ቤቶች ወጥተው በድሬዲዋ ከተማ ቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤቶች እንዱታዩ መደረግ በገንዘቡ መጠን ትይዩ የሚታይበትን ፍርድ ቤት እና የክርክር ደረጃ ለመለየት ሆን ተብል የወጣ ሕግ መሆኑን የሚያስገነዝበን ነው። ይህም የሕግ አውጪው ሐሳብ ምን ነበር? የሚለውን የአተረጓጎም መርህ በመከተል ልንደርስበት የምንችለው ድምዲሜ ነው። ስለሆነም በተመሳሳይ አካል የወጡት ሕጎች ስለፍርድ ቤቶቹ ስልጣን ያስቀመጧቸውን ድንጋጌዎች ከሕጎች አወጣጥ ቅደም ተከተልና ሕጎችን እርስ በራሳቸው አጣጥሞ ከሕግ አውጪው ሐሳብ ጋር በማዛመድ ከመተርጎም የሕግ አተረጓጎም ደንቦች አንፃር ስንመለከተው የአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 5ዐ ይዘት ከዚሁ ተለይቶ የሚታይ ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም ከሥልጣን አደላደል አንፃር የሕግ ጥበቃ የተደረገለት የአሁን አመልካች የፋዳራል መንግስት አካል ወይም በፋዳራል መንግስት የተመዘገበ መሆኑ ብቻ ጉዲዩን የፋዳራል ጉዲይ የማያደርገው ሲሆን ተለይቶ መታወቅ ያለበት ክስ የቀረበበት ጉዲይ በባሕርይው ሲታይ ውስብስብ የሕግ ጥያቄ የሚያስነሳ መሆን ያለመሆኑ ነው። በመሰረቱ ለአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ስልጣን የተሰጠው ከፋዳራል ፍርድ ቤቶች ስልጣን ተቆርሶ መሆኑ ግልፅ ነው። ስለሆነም ጉዲዩ በቀበላ ማህበራዊ ፍርድ ቤት ስልጣን ስር የሚወድቅ የገንዘብ መጠንን መያዙ ብቻ ስልጣኑን ለቀበላ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች እንዱሆን የማያደርገው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 50(1) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ከአዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀፅ 41 ስር ከተመለከተው ድንጋጌ ጋር በማስተሳሰር ልንገነዘበው የምንችለው ነው። ስለሆነም ጉዲዩ የሚያስነሳው የሕግ ጥያቄና የጉዲዩ ልዩ ባህርይ ትኩረት ሉሰጣቸው ይገባል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች ለክሱ መሰረት ያደረገው የገንዘብ መጠን በአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 50 መሰረት የሚወድቀው በቀበላ ማህበራዊ ፍርድ ቤት የስረ ነገር ሥልጣን ስር ነው። ይሁን እንጂ አመልካች ክስ ያቀረበው ንብረቱ የሆነው ተሽከርካሪ በተጠሪ መኪና በመገጨት ጉዲት ስለደረሰበት የጉዲቱን ግምት ተጠሪ እንዱተኩለት ነው። ተጠሪ ደግሞ ግጭቱን ያደረሰው መኪና የራሳቸው ንብረት የነበረ ሁኖ ግጭቱን አደረሰ በተባለት ጊዜ ደግሞ በሽያጭ ወደላላ ሰው የተላለፈና ገዥው ሲጠቀሙበት በነበረበት ጊዜ በአመልካች መኪና ላይ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት የለብኝም በማለት ተከራክረዋል። ስለዚህ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነቱ የማን ነው?፣የሻጩ ወይስ የገዥው?፣አንድ ሰው ከአዋጅ ቁጥር 256/60 እና ከደንብ ቁጥር 360/1969 እና ላልች አግባብነት ካላቸው ሕጎች አንፃር ሲታይ የመኪና ባለንብረት ነው የሚባለው መቼ ነው?፣የመኪና ባለንብረት መኪናው ለሚያደርሰው ጉዲት ኃላፉ የሚሆንበት የሕግ አግባብ ምንድነው? የሚለትና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከካሳ መጠኑ ጋር ተዛምደው የሚነሱት ክርክሮች በባሕርያቸው ሲታዩ ውስብስብ የሕግ ጥያቄ የሚያስነሱ መሆኑ ግልጽ ነው። ስለሆነም በእጃችን ያለው ጉዲይ ከራሱ ልዩ ባህርይ አንፃር ሲታይ ውስብስብ የሕግ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ በመሆኑ በቀበላ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ስልጣን ሥር የሚወድቅ ሁኖ አልተገኘም። በአዱስ አበባ ከተማ ስር የሚገኙ የቀበላ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች የገንዘብ መጠኑ ከብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) በታች የሆነውን ማንኛውንም የፍትሐብሕር ክርክር ለመመልከት ስልጣን አላቸው ተብል በአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀፅ 50(1) ስር የተመለከተው ድንጋጌ ተግባራዊ መሆን ያለበት ተከራካሪው ወገን የፋዳራል መንግስት አካል ወይም በፋዳራል መንግስት የተመዘገበ ድርጅት ያለመሆኑ ሲረጋገጥ ሳይሆን የተከራካሪ ወገኖች በፋዳራል መንግስት አካልነት ወይም የተመዘገቡ መሆኑ ግንዛቤ ውስጥ ሳይገባ የጉዲዩ ልዩ ባሕርይ እየታየ በጉዲዩ ላይ የሚነሳው የሕግ ጥያቄ ውስብስብነት በመመዘኛነት(መለኪያነት) ተይዞ ነው።
በአጠቃላይ በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር ላይ ያለት ተከራካሪ ወገኖች ማንነት እና በክርክሩ የሚነሳው የሕግ ጥያቄን መሰረት በማድረግ ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 እና ከአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀፅ 50(1) አንፃር ተመልክቶ ባለው አግባብ ሉስተናገድ የሚገባው ሆኖ ሳለ የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የአመልካችን የፋዳራል መንግስት አካል መሆኑን ብቻ በመመልከት ጉዲዩ በአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የስረ ነገር ስልጣን ስር አይውድቅም ያለው የምክንያት ክፍል ተገቢነት የላለው ቢሆንም የተያዘው ጉዲይ በተለይ ሲታይ ግን ባሕርይው ውስብስብ የሕግ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ በመሆኑ የአዱስ አበባ ከተማ ማህበራዊ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የላለው ሁኖ አግኝተናል። ስለሆነም የማህበራዊ ፍርድ ቤቱ ይህንኑ ተገንዝቦ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 9 እና 231/1/ለ/ መሰረት መዝገቡን መዝጋት ሲገባው በጉዲዩ ላይ ውሣኔ መስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል።
በዚህም መሰረት አመልካች በቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤት የቀረበው ጉዲይ በፋዳራል ፍ/ቤቶች ስልጣን ሥር የሚወድቅ እንጂ በአዱስ አበባ ፍ/ቤቶች ሥልጣን ሥር የሚወድቅ አይደለም በሚል የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ትርጓሜ ሕጎቹ ከወጡበት ዘመን አንፃርም ሆነ የሕግ አውጪውን ሃሣብ ከመፈለግ አንፃር ላሰጥ የሚገባውን የሕግ አተረጓጎም ዘይቤ ያልተከተለ ስለሆነ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት የምክንያት ክፍል ቢሆንም በውጤት ደረጃ ግን ተገቢ ሆኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲዲር ፍ/ቤቶች ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 12394 በ21/05/2ዐዐ2 ዓ.ም. የተሰጠውን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 342 ምክንያቱን ለውጠን ውጤቱን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት አፅንተነዋል።
ክርክር ያስነሳው ጉዲይ ከአመልካች ማንነትና ከገንዘቡ መጠን አንፃር ሲታይ በመጀመሪያ ደረጃ ከአዱስ አበባ የቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤት ሥልጣን የሚጀምር ቢሆንም የጉዲዩ ልዩ ባሕርይ ሲታይ ግን በቀበላ ማህበራዊ ፍርድ ቤት ስልጣን ስር የሚወድቅ አይደለም ብለናል። የተያዘውን ጉዲይ አይነት የማየት የስረ ነገር ስልጣን ያላቸው የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ናቸው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.