No summary available.
ጥር 18 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ አክሉለ ገብሬ - ጠበቃ ኪሩቤል ኃ/ማርያም ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡- አቶ መለኮት ክንፈሚካኤል - ጠበቃ ፍስሐ ሐጏስ ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በአደራ የተሰጠ የንግድ ድርጅት ልረከብ ጥያቄን መሰረት ያደረገ ሲሆን ጉዲዩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። አመልካች ያቀረቡት የክስ ማመልከቻ የካቲት 22 ቀን 2002 ዓ.ም. የተጻፈ ሆኖ ይዘቱ በአራዲ ክፍለ ከተማ ቀበላ 01/02 የሚገኝ የቤት ቁጥር 164 የሆነ ንግድ ቤት በባለቤታቸው በአቶ ወልደማሪያም ወልደሚካኤል ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መሆኑን፣ ባለቤታቸው ከሞቱ በኋላም ሚስትነታቸውን አረጋግጠው የቤቱ ኪራይ በስማቸው መዛወሩን፣ ከተጠሪ ጋር በነበራቸው ቤተሰባዊ ቅርርብም ድርጅቱን እንዱሰሩበት በአደራ ሰጥተዋቸው ሲሰሩበት ከቆዩ በሁዋላ ድርጅቱን እንዱያስረክቧቸው ቢጠይቋቸው ፈቃደኛ ያለመሆናቸውን ገልጸው ተጠሪ የንግድ ድርጅቱን ለቀው ቤቱን እንዱያስረክቡ፣ እስከሚያስረክቡ ድረስ ደግሞ በወር ብር 3,000.00 እየታሰበ እንዱከፈላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስም ከአመልካች በአደራ የወሰደት የንግድ ድርጅት ቤት የላለ መሆኑን ገልጸው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ክርክሩ መሰረት ያደረገው የአደራ ውለን መሆኑን በመገንዘብ የንግድ ድርጅቱ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የተደረገ በመሆኑ በዚህ ድርጅት ላይ የአደራ ውል ስለመኖሩ መረጋገጥ ያለበት በፍ/ሕ/ቁጥር 1723(1) በተመለከተው ሕጋዊ መስፈርት ነው በማለት እና አመልካች ደግሞ በፍ/ሕ/ቁጥር 1723(1) መሰረት የተደረገ የአደራ ውል ስለመኖሩ ያቀረቡት ማስረጃ የለም በማለት ክሳቸውን ውድቅ አድርጎታል። በዚህም አመልካች ይግባኛቸውን ለከተማው ይግባኝ ሰሚ፣ የሰበር አቤቱታቸውን ደግሞ ለከተማው ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም በንግድ ድርጅት ቤት ላይ የሚደረገው የአደራ ውል በፍ/ሕ/ቁጥር 1723(1) ድንጋጌ መሰረት መደረግ ያለበት ነው ተብል የተወሰነው ያላግባብ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ ለተጠሪም ጥሪ ተድርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደረመረመረውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ ጉዲዩ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የከተማ ፍርድ ቤቶች የስረ ነገር ሥልጣን ስር የሚወድቅ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች በክሱ የጠየቁት ዲኝነት ቀበላው በባለቤትነት የሚያስተዲድረውን ቤት የተከራይነት መብት ያላቸው መሆኑንና ይኸው መብት እያላቸው ድርጅቱን ተጠሪ እንዱሰሩበት በአደራ ሰጥተው ተጠሪ ሲሰሩበት ከቆዩ በኋላ እንዱያስረክቧቸው ሲጠየቁ ፈቃደኛ አልሆኑም በሚል መሆኑን፣ ተጠሪ ደግሞ ከአመልካች ጋር ያደረጉት የአደራ ውል የለም ሲለ በመከራከራቸው የስር ፍርድ ቤት የአደራ ውል አለ? ወይስ የለም? የሚለውን ጭብጥ ይዞ ይህንኑ ጭብጥ ለመመለስም አግባብነት አላቸው ያላቸውን የፍ/ብ/ሕግ ድንጋጌዎችን በመመመርመር ውሳኔ መስጠቱን ነው።
ከዚህ አንፃር ስንመረምረው የአዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች ስልጣንና ኃላፉነት ከፋዳራል ፍርድ ቤቶች ስልጣንና ኃላፉነት በአዋጅ ቁጥር 361/1995 እና በአዋጅ ቁጥር 408/1996 ተቆርሶ የተሰጠ ሲሆን በአዋጁ 361/1995 በአንቀጽ 41 ስር ደግሞ የስረ ነገር ስልጣናቸው በዝርዝር ተለይቶ ተሰጥቷል። በሕጉ ተለይተው ከተሰጡት የስረ ነገር ስልጣኖች መካከል ንብረትነቱ የከተማው አስተዲደር የሆነ ቤት ላይ የሚነሱ ክርክሮችን አይቶ የመወሰን ስልጣን አንደ ስለመሆኑ በአዋጅ አንቀጽ 41(1)(ረ) በግልጽ ተደንግጓል። የዚህ ድንጋጌ ይዘትም የከተማው ፍርድ ቤቶች ንብረትነታቸው የከተማው አስተዲደር ስለመሆናቸው ክርክር በማይቀርብባቸው ቤቶች ላይ የሚነሱ የይዞታ፣ የኪራይ እና ላልች ክርክሮችን አይተው የመወሰን ስልጣን ያላቸው መሆኑን ነው። በመሆኑም ክርክሩ መሰረት ያደረገው የከተማው አስተዲደር የሚያስተዲድረውን ቤት የሚመለከት መሆኑ ብቻውን ሁለንም ቤቱን መሰረት አድርገው የሚቀርቡትን ክርክሮች የከተማው አስተዲደር ፍርድ ቤቶች ለማስተናገድ ስልጣን የሚሰጣቸው አይደለም።
በመሆኑም ክርክር የተነሳበት ቤት የከተማው አስተዲደር ነው? ወይስ የላላ ግለሰብ? ወይም ድርጅት? የሚል መሰረታዊ ክርክር ያለበት ከሆነ የከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች ይህንን የቤት ወይም የድርጅት ባለቤትነት ጥያቄ አስመልክቶ በከተማው አስተዲደርና በላልች ሰዎች መካከል የሚደረግ ክርክር በዲኝነት አይተው ለመወሰን የሚያስችል የሥረ ነገር ስልጣን የላላቸው መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41 (1) (ረ) ድንጋጌ ለመረዲት ይቻላል። በያዝነው ጉዲይ የቤቱን ሕጋዊ ባለቤትነትን አስመልክቶ በአመልካች በኩል ክርክር የቀረበበት ሳይሆን የንግድ ድርጅቱ የሚገኝበት ቤት ባለቤት የሆነው ቀበላም የክርክሩ ተካፊይ አልሆነም። የክርክሩ መሰረት የአደራ ውል ሆኖ ተካራካሪ ወገኖች ደግሞ ግለሰቦች ሲሆኑ የጉዲዩ መሰረታዊ ጭብጥም በአመልካችና በተጠሪ መካከል የአደራ ውል አለ? ወይስ የለም? የሚል ነው። ጉዲዩ የቤት ይዞታ ወይም ከባለቤትነት በመለስ ያለ ላልች መብቶች ክርክር ባለመሆኑ የከተማው አስተዲደር ፍርድ ቤቶች የቤት የይዞታ ክርክርንና ከባለቤትነት መብት በመለስ ያለትንና ላልች ክርክሮችን በተመለከተ የዲኝነት ስልጣን በሕጉ የተሰጣቸው አደራ ውልንም የሚጨምር ነው ልባል የሚችል አይደለም። ስለሆነም የአደራ ውልን መሰረት አድርጎ የሚቀርብ ክርክር በከተማው ፍርድ ቤቶች የስረ ነገር ስልጣን ስር የሚወድቅ ስለመሆኑም አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41 እንዱሁም አዋጅ ቁጥር 408/1996 ድንጋጌዎች የሚያሳዩት ጉዲይ አይደለም። አንድ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ከማየቱ በፉት የስረ ነገር የዲኝነት ስልጣን ያለው መሆኑን ማረጋገጥ ያለበት ሲሆን የስረ ነገር የዲኝነት ስልጣን በተከራካሪ ወገኖች ባይነሳም በማናቸውም የክርክር ደረጃ ፍርድ ቤቱ በራሱ ሉያነሳው የሚገባው ጉዲይ መሆኑን ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 9 እና 231 (1(ለ)) ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። ስለሆነም በየደረጃው ያለ የአዱስ አበባ አስተዲደር ከተማ ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን ሣይኖራቸው ጉዲዩን ሰምተውና አከራክረው የሰጡት ውሣኔ ህጋዊ አስገዲጅነት የላለውና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ሆኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.