No summary available.
የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሤ አመልካች፡ የኢትዮጵያ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ነ/ፈጅ አቶ አብርሃም አሻ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- በኢትዮጵያ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን የሐዋሳ ቁጥር 2 ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን የቦርድ አባላት፡-
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ክስ በአሁን ተጠሪዎች ከሳሽነት የተጀመረው በሐዋሳ ከተማ ከፍ/ፍ/ቤት ሲሆን ተከሳሽ ደግሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ስራ መስክ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ነው። የክሱ ፍሬ ቃልም የሐዋሳ ቁጥር 2 የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ህገ ደንብና መመሪያ መሰረት የተቋቋመች የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ስትሆን ቤተክርስትያኗ ከ300 እስከ 400 የሚደርሱ መዕመናንን አቅፊ በአድቬንቲስት ቤተክርስቲያን መሰረተ እምነትና የአምልኮ ስርዓት እየሰራች እያለ በ1967 ዓ.ም. ከወጣውና እስካሁን በስራ ላይ ካለው የአድቬንቲስት ቤተክርስቲያን መተዲደሪያ ደንብ ምዕራፍ 14 የተጠቀሰውን አብያተ ክርስቲያናት የሚቋቋሙበት፣ የሚዋሀደበትና የሚፈርሱበት ሁኔታን ባልተከተለ መልኩ እንዱሁም አጥቢያ ቤተክርስቲያኗ እንድትዘጋ፣እንድትፍርስ የሚያደርግ አንድም ምክንያት ሳይኖር በታህሳስ 8-9/2001 ዓ/ም የሰበካው ጉባኤ ባደረገው ስብሰባ በሀሰትና በፈጠራ ብቻ የአጥቢያ ቤተክርስቲያኗ እንድትፈርስ ጉባኤው የወሰነ ስለሆነ ውሳኔው ይሻርልን የሚል ነው።
ተከሳሽ በበኩሎ በሰጠችው መልስ ቤተክርስቲያኗ እንድትዘጋ የተወሰነው በአመጽና በክህደት ተግባር ሲሆን ከሳሾችም ከተጠቀሱት ድርጊቶች እንዱታቀቡ የተሀድሶ ሰበካ ተደርጎ እንዱሁም ከስህተታቸው ተመልሰው ለመተዲደሪያ ደንቡ ተገዢ ሆነው እንዱቀጥለ በመንፈሳዊ ርህራሓ ቢለመኑም በእምቢተኝነት ስለጸኑ እርምጃው ተወስዶል ብላለች።
የስር ከፍተኛው ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ምስክሮች ከሰማና የጽሁፍ ማስረጃዎችን ከመረመረ በኋላ በሰጠው ፍርድ እንድትዘጋ ውሳኔ የተሰጠባት ቤተክርስቲያን የአመጽም ሆነ የክህደት ተግባር ስለመፈጸሟ አልተረጋገጠም፣ ቤተክርስቲያኗ የፈጸመቻቸው ድርጊቶችም ቢሆኑ ከኢትዮጵያ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን መተዲደሪያ ደንብና በተዘጋጀው ማኑዋል መሰረት በመሆኑና የሰበካው ጉባኤ ውሳኔም ይሓንኑ የመተዲደሪያ ደንብና ማኑዋል የጣሰ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም ሲል ሰርዟል።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በበኩለ ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 337 መሰረት በመዝጋት ይግባኝ ባይዋን አሰናብቷል።
በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት አመልካች አቤቱታዋን ለዚህ ችልት ያቀረበች ስትሆን በዋናነት የጠቀሰቻቸው የቅሬታ ነጥቦችም፡ተጠሪዎች ከእናት ቤተክርስቲያን የተሰጣቸው ውክልና ሳይኖር በስማቸው የመክሰስም ሆነ የመከሰስ መብት የላቸውም ፣ ቤተክርስቲያኗ የተመዘገበችው በአዱስ አበባ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች ጉዲዩን አከራክረው የመወሰን ስልጣን የላቸውም በሚል የቀረቡትን የመቃወሚያ ነጥቦችን አለመቀበላቸው ህግ ስህተት ነው፣ አመልካች ሀይማኖታዊ ተልዕኮዋን ለማሳካት ቅርንጫፍ ቤተክርስቲያናትን የማስፊፊትና እንደአስፈላጊነቱ የአሰራር ስርዓቷን ተከትላ የመዝጋት ሙለ መብት ያላት በመሆኑ የሐዋሳ ቁጥር 2 ቤተክርስቲያንን በመበተኗ ምክንያት ተጠሪዎች አንድም ያጡትን መብት ወይም ጥቅም ባላስረደበት የተወሰነው ከፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 33 ዓላማ ውጪ ነው፣ የስር ፍ/ቤቶች በማስረጃነት ከቀረበው የመተዲደሪያ ደንብ ገጽ 156 ቁጥር(3) መንፈስ ውጪ ደንቡን በመተረጎም ጥፊቶቹ እንደክህደት ወይም አመጽ የሚፈረጁ አይደለም ሲለ ቤተክርስቲያኗ እንድትበተን የተሰጠውን ውሳኔ መሻራቸው ያለ አግባብ ነው፣የሚለ ናቸው።
ተጠሪዎች በበኩላቸው በሰጡት መልስ፡በፍ/ህ/ቁ/448(1) መሰረት ተጠሪዎች በቤተክርስቲያኒቱ አባልነታችን ያልተቀበልናቸውንና የቤተክርስቲያኒቱ መተዲደሪያ ደንብ የሚጥሱትን የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎችን ለማሻር ክስ የማቅረብ መብት አለን፣ የስር ፍ/ቤቶችም ጉዲዩን ተቀብለው አከራክረው የመወሰን ስልጣን የላቸውም በሚል አመልካች ያቀረበችው መቃወሚያም ቢሆን የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ህጉን ያልተከተለ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፣ አመልካች ሀይማኖታዊ ተልዕኮን ለማሳካት ቅርንጫፍ ቤተክርስቲያን የማስፊፊትና እንደአስፈላጊነቱም የአሰራር ስርዓቷን ተከትላ የመዝጋት ሙለ መብት እንደአላት ብትገልጽም ይህ መብትና ነጻነት ገደብ የለሽ ባለመሆኑ በሀይማኖት ነጻነት መብቷ ሽፊን የራሷን ደንብ በመጣስ ለጥቂት ግለሰቦች ፍላጎት በሚል በብዙሀኑ ፍላጎት ላይ መጫን አይገባትም በሚል በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለም ሲለ ተከራክረዋል።
የክርክሩ ሂደት ጠቅለል ባለ መልኩ ከዚህ በላይ የቀረበ ሲሆን እኛም ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ በፍርድ ቤት የሚወሰን ጉዲይ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
የሰበካው ጉባኤ ቤተክርስቲያኗ እንድትፈርስ ውሳኔ ያስተላለፈው ቤተክርስቲያኗ በራሷ ስልጣን እንድያገለግሎት የተመደቡላትን ፒስተር እና ወንጌላዊ አባርራለች፣ ለፒስተር የቅስና ማዕረግ ሰጥታለች፣ አስራትና መባ ለዋናው መስሪያ ቤት አትልክም፣ የተሰጣት ፈቃድ ሳይኖር ለላልች የአጥቢያ አድቬንቲስት ቤተክርስቲናት አገልግልት በመስጠት የክህደትና የአመጽ ተግባር በመፈጸሟ ምክንያት ከድርጊቷ እንድትታቀብ የተሀድሶ ትምህርት ቢሰጣትም ልትመለስ አልቻለችም በሚል ነው። የተጠሪዋ ቤተክርስቲያን የቦርድ አባላት በበኩላቸው የክህደት እና የአመጽ ተግባር አለመፈጸማቸውንና በአድቬንቲስት መሰረተ እምነትና የአምልኮ ስርዓት የሚሰሩ ስለመሆናቸው ተከራክረዋል። የስር ከፍተኛ ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ማስረጃዎች በመመርመርና በ1967 ዓ/ም የወጣውን የኢትጵያ አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን መመሪያ በምዕራፍ 14 አብያተ ክርስቲያናትን ስለማቋቋም፣ማዋሃድ እና ስለማፍረስ በተደነገገው ስር በገጽ 156 በቁጥር 3 ክህደት የሚለው ቃል በመመሪያው ያልተብራራ መሆኑን ጠቅሶ የክህደት እና አመጽ ድርጊቶች ናቸው ተብለው በአመልካች በኩል የተነገሩትን ከምስክሮች ቃል አንጻር ሲታይ ተቀባይነት የለውም፣ በከሳሾች በኩል የተፈጸሙ ድርጊቶችም ቢሆኑ በመመሪያው መሰረት በቤተክርስቲያኗ ማኑዋል መሰረት የተፈጸሙ ናቸው ብሎል።
እንድትፈርስ የተወሰነባት ቤተክርስቲያን ማለትም የሐዋሳ ቁጥር 2 አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ከክርክሩ መገንዝብ እንደሚቻለው የአመልካች ቤተክርስቲያን አንድ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ስትሆን በአጥቢያው ቤተክርስቲያኑዋና በሰበካው ጉባኤ እንዱሁም በኢትዮጵያ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን መካከል ሉኖሩ የሚችለትን ከአምልኮና ከቤተክርስቲያኗ የውስጥ አስታዲደራዊ ሁኔታዎች ጋር የተያያዙ ጉዲዮችን በፍ/ቤት በመወሰን እልባት መስጠት የሚቻል መሆን አለመሆኑን መመርመር ተገቢ ነው። ለዚህም የኢ/ፋ/ዱ/ሪ/ ህገ መንግስት አንቀጽ 37 (1)ን መመልከት ተገቢነት አለው። በዚሁ ድንጋጌ መሰረት ማንኛውም ሰው (የተፈጥሮም ሆነ በህግ የሰውነት መብት ያለው ድርጅት) በፍርድ ቤት ሉወሰን የሚገባውን ጉዲይ (justiciable matter) ለፍርድ ቤት ወይም ለላላ በህግ የዲኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት አለው። በዚሁ አነጋገር በፍርድ ቤት ወይም በልላ በህግ የዲኝነት ስልጣን የተሰጠው አካል ተቀብል አከራክሮ ውሳኔ ወይም ፍርድ ላሰጥ የሚችለው ዲኝነት የተጠየቀበት ጉዲይ በፍርድ ቤት ሉወሰን የሚችል ሲሆን ብቻ ነው። በሀገራችን ኢትዮጵያ መንግስትና ሀይማኖት የተለያዩ መሆናቸውንና መንግስት በሀይማኖት ጉዲይ ጣልቃ እንዲይገባ፣ሀይማኖትም በመንግስት ጉዲይ ጣልቃ እንዲይገባ በኢ/ፋ/ዱ/ሪ/ህገ መንግስት አንቀጽ 11(1) እና (3) በግልጽ ተደንግጓል። በመሆኑም በኢትዮጵያ መንግስትና ሀይማኖት በህገ መንግስቱ የተለያዩ ናቸው። ይህ እስከሆነ ድረስ የመንግስት አንደ ክፍል የሆነው ፍርድ ቤት አመልካች እና ተጠሪዎች ባላቸው ሀይማኖታዊ በሆነ አለመግባባት ወይም በአምልኮ ስርዓት ጣልቃ ገብቶ ህገ ደንቡን በመተርጎም የሚወስንበት የህግ መሰረት የለውም።
በመሆኑም የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪዎች ያቀረቡትን በፍርድ ሉወሰን የማይችለውን ጉዲይ ተቀብል አከራክሮ መወሰኑም ሆነ የክልለ ጠ/ፍ/ቤት በይግባኝ ተቀብል ማጽናቱ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በማግኘታችን የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የሐዋሳ ከተማ ከፍ/ቤት በመዝገብ በቀን 09/02/2003 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠውን ፍርድ እንዱሁም የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በቀን 19/5/2003 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠውን ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/348(1) መሰረት ሽረናል።
ተጠሪዎች ያቀረቡት ጉዲይ በሚከተለት ሀይማኖታዊ ስርዓት እና በሚመሩበት ደንብ መሰረት እልባት ከሚያገኝ በቀር በፍርድ ቤት የሚወሰን ጉዲይ አይደለም ብለናል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.