No summary available.
ሐምል 19 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኢትዮጵያ- ጠበቆች 1. ማርሻል ፍቅረ ማርቆስ ቀረቡ 2. ሰለሞን እምሩ ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ከሉዝ ውል አፈጻጸም ጋር የተያያዘ ሲሆን የተጀመረውም በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁኖ በአመልካች ከሳሽነት ነው። የአመልካች ክስ ይዘትም፡- በየካቲት 11 ቀን 1997 ዓ.ም የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የሉዝ ቦርድ ባሳለፈው ውሳኔ በቀድሞው ዞን 3፣ ወረዲ 28 መር ቀበላ ገበሬ ማህበር ክልል ውስጥ (ባሁኑ አጠራር በአዱስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ቀበላ 20/21 ክልል ውስጥ የሚገኝ 303,000 ካ.ሜትር ቦታ በሉዝ እንዱሰጠው ተወስኖለት በከተማ ቦታ የምስክር ወረቀት ሴሪ ቁጥር 0710 እና በካርታ ቁጥር ሉዝ 0236 ተረክቦ ቦታው በአመልካች ይዞታ ስር እንደሚገኝ፣ ሆኖም የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመሬት አስተዲደር የግንባታ ፈቃድ ባለስልጣን ቁጥር መአግፈባ/502/03 በ8/02/2003 ዓ.ም. በጻፈው ደብዲቤ የመሬት ልማትና አስተዲደር ቦርድ በ22/11/2002 በቃለ ጉባኤ ቁጥር 16/2002 አሳለፈ ያለውን ውሳኔ በመጥቀስ አመልካች ከክፍያ ነጻ በተሰጠው ቦታ ላይ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ግንባታ ሳያከናውን ቆይቶ የቦታ አገልግልት ለውጥ ጥያቄ በማቅረቡ የሉዝ ውለ ተሰርዞ ካርታው መክኖ ቦታው እንዱመለስ መወሰኑን፣ ይህም ከሕግና ከሉዝ ውል ስምምነቱ ውጪ መሆኑን፣ ግንባታው በጊዜ ገደቡ ውስጥ ካልጀመረ ውለ እንደሚሰረዝ ግልፅ ስምምነት የላለ መሆኑንና ግንባታው ሉዘገይ የቻለውም የካቲት 2002 ዓ.ም. ድረስ የቆየው አስተዲደሩ በውለ አንቀፅ 3.1 በገባው ግዳታ መሰረት ቦታው ላይ የሰፈሩትን ሰዎች ካሳ ከፍል ባለማሰናበቱና ለውጥን በተመለከተም አመልካች የፔሮጀክት ለውጥ እንዱደረግለት በውለ እና በሕግ መሰረት ጥያቄ ማቅረብ ስለሚችል ለውለ መሰረዝ ምክንያት ላሆን እንደማይችል ዘርዝሮ ውለ መሰረዙ ያላግባብ ነው ተብል የሉዝ ውለ ጸንቶ በይዞታው የመጠቀም መብቱ እንዱጠበቅለት ይወሰን ዘንድ ዲኝነት ጠይቋል። የአሁኑ ተጠሪዎች ለክሱ በሰጡት መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክሮችን አቅርበዋል። ተጠሪዎች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የሚያነሱት ክርክር ጉዲዩ መታየት ያለበት በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች እንጂ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አይደለም የሚል ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃ ደግሞ የሉዝ ውለ የተሰረዘውና ካርታው የመከነው በውለ እና በሕጉ መሰረት መሆኑን ዘርዝረው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ነው። ጉዲዩ በዚህ መልክ የቀረበለት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ክሱ የቀረበው በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር አካላት ላይ መሆኑና የክሱ መሰረትም የሉዝ ውል መሆኑን ጠቅሶና የአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀፅ 41(1(ሀ) ድንጋጌን ዋቢ በማድረጉ ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን ያላቸው የአዱስ አበባ ከተማ መስተዲደር ፍርድ ቤቶች ናቸው በማለት ክሱን ውድቅ አድርጎታል። ከዚህም በኋላ አመልካች ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ጉዲዩ ከሉዝ ውል አፈጻጸም ጋር የተያያዘ ሁኖ ከከተማው መሪ ፔላን ጋር የተያያዘ ባልሆነበት ሁኔታ ግንኙነት የላለው ድንጋጌ ተጠቅሶ ጉዲዩን የማየት ስልጣን ያላቸው የአዱስ አበባ ከተማ መስተዲደር ፍርድ ቤቶች ናቸው ተብል የተወሰነው አግባብነት ካለው ህግ ይዘትና በሰ/መ/ ከተሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ውጪ ነው በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበት ለዚህ ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በሰጡት መልስ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ናቸው ተብል መወሰኑ በተሻሻለው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀፅ 41(1(መ)) ድንጋጌና በሰ/መ/ ከተሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም አንጻር ሕጋዊ ነው በማለት የተከራከሩ ሲሆን አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙ ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደረመረውም ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ናቸው? ወይስ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ናቸው? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ሐምል 14 ቀን 1990 ዓ.ም በተፈረመ የከተማ ቦታ ሉዝ ውል ጠቅላላ ስፊቱ 303,000 (ሶስት መቶ ሶስት ሺህ) ካሬ ሜትር ቦታ በየካ ክፍለ ከተማ ቀበላ 20/21 ክልል ውስጥ ለዘጠና አመታት መውሰደንና ተጠሪዎች አመልካች ቦታውን በጊዜ ገደቡ ሳያለማ ለአስራ ሶስት አመታት ይዞ በመቆየቱና የፔሮጀክት ለውጥ ለማድረግ ጥያቄ አቅርቧል በሚል ምክንያት የሉዝ ውለን በመሰረዝ ካርታውን ያመከኑ መሆኑንና አመልካች የሚጠይቀው ዲኝነትም የሉዝ ውለ እንዱጸናና በይዞታው የመጠቀም መብቱ እንዱጠበቅለት መሆኑን ነው።
በመሰረቱ ከኢ.ፋ.ድ.ሪ ሪፐብላክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 37/1/፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 4፣ 9፣ 231 እና ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 እንዱሁም ተሻሽል በወጣው ከአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው ፍርድ ቤቶች አንድን ጉዲይ ማየት እና ውሳኔ መስጠት የሚችለት በሕግ በግልጽ ተለይተው በተሰጧቸው ጉዲዮች መሆኑን ነው። በመሆኑም ለእያንዲንደ ፍርድ ቤት በሕግ የተሰጠው ስልጣንም መጠበቅ ያለበት ከመሆኑም በላይ በአስተዲደራዊ ውሣኔ የመጨረሻ እልባት እንዱያገኙ በሕግ ተለይተው የተቀመጡ ጉዲዮችን ፍርድ ቤቶች የመዲኘት ስልጣን የላላቸው መሆኑ ሉስተዋል የሚገባው ጉዲይ ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ /ክርክር/ መሰረት ያደረገው ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ባደረገው የሉዝ ውል የተሰጠውን ቦታ በጊዜ ገደቡ አልለማም፣ የፔሮጀክት ለውጥ ተደርጎአል ተብል የሉዝ ውለ መሰረዙና ካርታው መምከኑ ከሕግ ውጪ ነው የሚል ነው።
ስለሆነም ጉዲዩ ከሉዝ ውል አፈፃፀም ጋር የተያያዘ ሲሆን የሉዝ ውል መሰረዝን ሕጋዊነት በተመለከተ ስራ ላይ ባለው የሉዝ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሰረት የሚቀርበውን የዲኝነት ጥያቄ የከተማው አስተዲደር በሚሰጠው አስተዲደራዊ ውሣኔ የመጨረሻ እልባት የሚሰጥበት መሆኑን ወይም ጉዲዩ በመደበኛ ፍርድ ቤት ላታይ የማይገባው መሆኑን የሚደነግግ ሕግ የለም። የከተማው አስተዲደር ካርታ የመስጠት የመሰረዝ፣ የማሻሻል፣ የማምከን፣ የማገድ እና አሻሽል የመስጠት ሙለ ስልጣን ያለው ቢሆንም የሉዝ ውልን መሰረት አድርጎ የተሰጠውን ካርታ መልሶ ከሕግ ውጪ ሰርዞ ሲገኝ በእርምጃው ላይ ቅሬታ ያለው ወገን ጉዲዩን ለፍርድ ቤት እንዲያቀርብ የሚከለከልበት ስርዓት የላለ ስለመሆኑ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግልት አካላት ስልጣንና ኃላፉነትን ለመደንገግ የወጣውና፣ ክርክሩ ሲጀመርም ሆነ ከተጀመረ በኋላ በስራ ላይ ያለው ሕግ ያሣያል። ይልቁንም የተሻሻለው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41/1/ሀ/ እና /መ/ ድንጋጌዎች አንድ ላይ ተጣምረው ሲታዩ የተያዘውን ጉዲይ አይነት የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ተቀብለውና አከራክረው ለመወሰን የስረ ነገር ሥልጣን ያላቸው ስለመሆኑ ያስገነዝባለ። የአዋጁ አንቀፅ 41(1(መ)) በተለይ ሲታይም የከተማው አስተዲደር አስፈፃሚ አካላት ወይም በከተማው አስተዲደር ባለቤትነት ስር ያለ ተቋማት የሚገቧቸውን አስተዲደራዊ ውልች በተመለከተ የሚነሱ ጉዲዮችን የማየት የስረ ነገር ስልጣን ለከተማው ፍርድ ቤቶች የተሰጠ ስለመሆኑ ተመልክቷል።
ክርክሩ በተነሳበት ጊዜ ተፈፃሚነት ካላቸው ሕጎች ስንነሳም የሉዝ ውለም ከደንብ ቁጥር 29/2002 አንቀፅ 15 እና ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 3132 ድንጋጌዎች አንፃር ሲታይ በአስተዲደራዊ ውልች ስር የሚሸፈን ሁኖ ተገኝቷል።
አመልካች ይህ ሰበር ችልት አስገዲጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጠ በማለት የሚጠቅሱት መ/ ሲሆን በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ ግን በሉዝ ውል በተገኘው ቦታ ሁከት ተፈጠረብኝ በሚል ምክንያት ሁከቱ እንዱወገድ ዲኝነት የተጠየቀበት በመሆኑና እንዱህ አይነት ክርክር ከከተማው መሪ ፔላን አፈፃፀም ጋር የተያያዘ ካልሆነ በስተቀር በአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ስረ ነገር ስልጣን ስር አይወድቅም በሚል ምክንያትና የአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀፅ 41(1(ሀ)) ድንጋጌ በዋቢነት ተጠቅሶ ሲሆን በመዝገቡ ያለት መሰረታዊ ፍሬ ነገሮችና ለውሳኔው መሰረት የሆነው አብይ ምክንያት አሁን ከተያዘው ጉዲይ ጋር በፍሬ ነገር እና የሕግ ክርክር ሙለ በሙለ ግንኙነት አለው ልባል የሚችል አይደለም። ይልቁንም በሰ/መ/ በቀረበው ጉዲይ ሰበር ሰሚ ችልቱ ከሉዝ ውል አፈፃፀም ጋር በተያያዘ የከተማው አስተዲደር አካላት ተከራካሪ ወገኖች ሲሆኑ ጉዲዩ መታየት ያለበት በአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች እንጂ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አይደለም በማለት የአዋጁ ቁጥር 361/1995 አንቀፅ 41(1(መ)) ድንጋጌን ትርጉም ሰጥቶበታል። ይህ የሕግ ትርጉም በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) አግባብም በሰ/መ/ በቀረበው ጉዲይ ላይ በግልጽ ተለውጧል ለማለትም የሚቻል አይደለም። በመሆኑም በዚህ ረገድ የቀረበው የአመልካች ክርክር ተቀባይነት ያለው ሁኖ አልተገኘም።
ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካች በፋዳራል ፍርድ ቤቶች ሳይሆን በአዱስ አበባ ፍርድ ቤቶች ስልጣን ስር የሚወድቅ ነው በማለት የሰጡት ብይን ከአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41/1/ሀ/ እና /መ/ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ አንፃር ሕጋዊ ሆኖ አግኝተናል። በዚህ ምክንያት በውሣኔው ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 10 ቀን 2004 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 08 ቀን 2004 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር አስፈጻሚ አካላት ወይም በከተማው አስተዲደር ባለቤትነት ስር ያለ ተቋማት የሚገቧቸውን የሉዝ ውልን መሰረት አድርጎ የሚቀርበውን የውል አፈፃጸምና ተያያዥ ጉዲዮችን የማየት የስረ ነገር ስልጣን የከተማው ፍርድ ቤቶች የስረ ስልጣን ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.