No summary available.
ሰኔ 22 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፉሳ አዲነ ንጉሴ አመልካቾች፡- ወ/ሮ ሰይዲ ደበላ - ጠበቃ ዕዮብ ገ/ህይወት ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሸሪፍ ሽኩር - በላለበት ታይቷል መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጡት ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የአፈፃፀም ክርክር ነው።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካችንና ተጠሪን በፍርደ መሰረት በስምንት መቶ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያለውን ቤት ተከራካሪዎች የተለያየ ድንበር በማሣያታቸውና ቦታውም ሰነድ አልባ በመሆኑ ለማካፈልም ሆነ ለመሸጥ አስቸጋሪ እንደሆነ የመሬት አስተዲደር ባለስልጣን ጽ/ቤትና ቀበላው የገለፁት መሆኑን ምክንያት በማድረግ አፈፃፀሙን መቀጠል አይቻልም በማለት መዝገቡን ዘግቶታል። አመልካች በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍ/ቤት አቅርበው የከፍተኛው ፍ/ቤት የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ አፅንቶታል።
አመልካች መስከረም 12 ቀን 2004 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በጋብቻ ዘመን በጋራ ያፈራነውን ቤት እኩል እንድንካፈል የተሰጠውን ፍርድ ማስፈፀም አስቸጋሪ ነው በሚል ምክንያት አፈፃፀሙ መዘጋቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክታለች። ተጠሪ መጥሪያ አልቀበልም ስለማለቱ በቃለ መሀላ አረጋግጣ ማመልከቻ አመልካች ስላቀረበች መልስ የመስጠት መብቱን በማለፍ ጉዲዩን በላለበት መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አፈፃፀም ለመቀጠል አስቸጋሪ ነው የተባለው ቤት አመልካችና ተጠሪ በጋብቻ ሲኖሩ ያፈሩት የጋራ ሀብት መሆኑ ቀደም ሲል ፍርድ ተሰጥቶበታል። ቦታውና ቤቱ ግብር ሲከፈልበት የኖረ መሆኑንና አመልካችና ተጠሪ ቦታውን ለረዥም ጊዜ ይዘውት እንደነበሩ አመልካች በሥርና በሰበር ካቀረበችው ክርክር ለመረዲት የሚቻል ሲሆን በፍርደ መሰረት ቦታውና ቤቱን ለማካፈል ወይም በሐራጅ ለመሸጥ አይቻልም በማለት የሥር ፍ/ቤት የአፈፃፀም መዝገቡን የዘጋው ቦታው ሰነድ አልባ መሆኑን የመሬት አስተዲደር ባልስልጣንና የክፍለ ቀበላ አስተዲደር ፅፍልኛል በማለት ነው።
የፍርድ አፈፃፀም ማመልከቻ ፍርደን ለሰጠው ፍ/ቤት በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 378 መሰረት ሲቀርብለት፣ የፍርድ ባለዕዲው የሚያቀርበውን መልስ በመቀበል፣ ፍ/ቤቱ ተገቢ የሆነውን ትዕዛዝ መስጠት እንዲለበት በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 386 ተደንግጓል። የአመልካችና የተጠሪ የጋራ ሀብት በመሆኑ እኩል እንዱከፈል፤ እኩል ማካፈል የማይቻል ከሆነ ተሸጦ ገንዘቡን እኩል እንዱካፈለ ውሳኔ የተሰጠበት ንብረት የማይንቀሳቀስ ንብረት ነው። ይህ ንብረት ካርታ ፔላን ባይኖረውም የማይንቀሳቀሰውን ንብረትና ይዞታ ለመለየት የሚያስችለ ልዩ ምልክቶችንና የንብረቱን አዋሳኞች በመለየትና ግልፅ በማድረግ የማይንቀሳቀሰውን ንብረትና ቦታ ለፍርድ ባለመብትና ለፍርድ ባለዕዲ እኩል እንዱከፍለ ትዕዛዝ ለመስጠት ወይም እኩል ለማካፈል የማይቻል ከሆነ ቤቱና ቦታው ካርታና ፔላን የላለው መሆኑንና የንብረቱን አዋሳኞች በጨረታ ማስታወቂያው ላይ በመግለፅ ንብረቱን በመሸጥ ለማካፈል የሚቻልበት ሁኔታ ያለ መሆኑን ከፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 225 ንዐስ አንቀጽ 2 እና የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 423 ድንጋጌዎች ለመገንዘብ ይቻላል።
የፍርድ አፈፃፀሙን የያዘው ፍ/ቤት በፍርድ አፈፃፀም ሂደት እንደዚህ አይነት ችግሮች ሲያጋጥሙት ለፍርደ አፈፃፀም ተስማሚ መስል የታየውን ትዕዛዝ የመስጠት ሥልጣንና ኃላፉነት ያለበት መሆኑን ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 392 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ ለመገንዘብ ይቻላል። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካችና የተጠሪ የጋራ ሀብት መሆኑ በፍርድ ቀደም ብል የተረጋገጠው ቤት ሰነድ አልባ በመሆኑ ንብረቱን ለማካፈልም ሆነ ለመሸጥ አስቸጋሪ መሆኑን የአስተዲደር አካል ፅፍልኛል በማለት የአፈፃፀም መዝገቡን መዝጋቱ፤ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 371 ንዐስ አንቀጽ 1 የተሰጠውን ፍርድ የማስፈፀም ሥልጣንና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 392 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌዎች የሚቃረን ሆኖ አግኝተነዋል። የከፍተኛ ፍ/ቤትም የስር ፍ/ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ ሣያርም ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጡት ውሳኔ ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን እንደገና በማየት ፍርደን ለማስፈፀም አስፈላጊ የሆነውን ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/392 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት በመስጠት ፍርደን እንዱያስፈፅም ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/343 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት መልሰን ልከንለታል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ
No topics extracted.