No summary available.
የካቲት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ድፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ዲሽን ባንክ (አ/ማ) ነገረ ፈጅ አቶ ካላብ ተስፊዬ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረም በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ በአፈፃፀም ክርክር ጣልቃ መግባትን የሚመለከት ነው። አመልካች አንደኛ ተጠሪና ሁለተኛ ተጠሪ የነበራቸው ጋብቻ በፍች ከፈረሰ በኋላ የጋራ ንብረት ክፍፍልን በተመለከተ አንደኛ ተጠሪ የፍርድ ባለመብት ሁለተኛ ተጠሪ የፍርድ ባለዕዲ ወይም በአፈፃፀም የሚከራከሩባቸው ንብረቶች ተጠሪዎች በጋብቻ በነበሩበት ወቅት ለወሰደት ብር 12,835,838.26 (አሥራ ሁለት ሚሉዮን ስምንት መቶ ሰላሣ አምስት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሣ ስምንት ብር ከሀያ ስድስት ሣንቲም) በመያዣነት የተያዙ በመሆናቸው በአፈፃፀሙ ክርክር ጣልቃ እንድገባ ይፈቀድልኝ በማለት ያቀረበውን ማመልከቻ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንብረቶቹ ፍርድ ያረፈባቸው በመሆኑ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም በማለት በአፈፃፀም መዝገብ ታህሣሥ 5 ቀን 2003 ዓ.ም ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አመልካች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርቧል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኙን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ግንቦት 24 ቀን 2003 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪዎች ለወሰደት ብድር በመያዣነት የያዛቸውን ቁጥራቸው አስራ ሁለት የሚሆኑ የማይንቀሣቀሱ እና የሚንቀሣቀሱ ንብረቶች በመዘርዘር አንደኛ ተጠሪና ሁለተኛ ተጠሪ ባላቸው ክርክር መነሻ ንብረቶቹ በሀራጅ እንዱሸጡ የአፈፃፀም ትዕዛዝ ሰጥቶ ውክልና ለደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰጥቷል።
አመልካች ዕዲው የተጠሪዎች የጋራ ዕዲ ንብረቶቹም የተመዘገቡ የብድር መያዣዎች መሆናቸውን በማስረዲት የቀዲሚነት መብት ለማስከበር በአፈፃፀም ክርክሩ ጣልቃ ለመግባት ያቀረብኩት ጥያቄ ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ይታረምልኝ በማለት አመልከቷል። አንደኛ ተጠሪ አመልካች በአፈፃፀሙ ክርክር ጣልቃ እንድገባ ቢደረግ ተቃውሞ የለኝም በማለት መልስ የሰጠ ሲሆን ሁለተኛ ተጠሪ ንብረቶቹ የጋራ ንብረት መሆናቸው ፍርድ ያረፈባቸው ስለሆነ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ትዕዛዝ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥታለች። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች በክርክሩ ጣልቃ ለመግባት ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አንደኛ ተጠሪና ሁለተኛ ተጠሪ በጋብቻ ተሣሥረው የኖሩና ጋብቻቸው በፍች እንዱፈርስ የተደረገ መሆኑንና ሁለተኛ ተጠሪ የፍርድ ባለመብት አንደኛ ተጠሪ የፍርድ ባለዕዲ በመሆን በአፈፃፀም የሚከራከሩት በጋብቻ ወቅት የገኙትን የጋራ ሀብት እንዱከፊፈለ የተሰጠን ውሣኔ ለማስፈፀም በተከፈተው መዘገብ ነው።
አመልካች አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪ የጋራ ሀብት ለመከፊፈል በሚያደርጉት የአፈፃፀም ክርክር ጣልቃ ለመግባት የሚጠይቀው አመልካችና ተጠሪ የፀና ጋብቻ ላይ በነበሩበት ወቅት ቁጥራቸው አስራ ሁለት የሚሆኑ የማይንቀሣቀሱና የሚንቀሣቀሱ ንብረቶች በመያዝ ብር 12,835,838.26 ብድር የሰጠሁ በመሆኑ በንብረቶቹ ላይ የቀዲሚነት መብት አለኝ በማለት ነው። ከባል ወይም ከሚስት አንደኛው ወይም ሁለቱም በፍርድ የተረጋገጠባቸው ወይም ሁለቱም ያመኑት ዕዲ መኖሩ የታወቀ እንደሆነ ይኸው ዕዲ የባልና የሚስት ሀብት ከመከፊፈለ በፉት ተቀንሶ የሚከፈል ስለመሆኑ የተሻሻለው የፋዳራል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 89 ይደነግጋል። አመልካች ላበደረው ብድር በመያዣነት የያዛቸውን ንብረቶች ሸጦ የብድሩ መክፈያ ለማድረግ ፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ የማያስፈልገው መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንደተሻሻለ ህግ አውጭው አውጥቷል።
እንደዚሁም በፍርድ አፈፃፀም ምክንያት ንብረት እንዲይያዝ፣ ወይም እንዲይከበር የመቃወም አቤቱታ ሲቀርብ ወይም በቡዙ ንብረት ላይ ቀዲሚ መብት አለኝ የሚል ተቃዋሚ አቤቱታ ያቀረበ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ መቀወሚያ ያቀረቡት ወይም እንዱያዝ በታዘዘው ንብረት ላይ ተቀዲሚ መብት አለን የሚለ ወገኖች በመጀመሪያው ክርክር ላይ ተካፊይ ባይሆኑም በሚያዘው ንብረት ላይ መብት እንዲላቸው በመቁጠር የሚያቀርቡትን አቤቱታ ተቀብል መመርመር እንዲለበት፣ አቤቱታውንና ማስረጃውን መርምሮ ውሣኔ መሰጠት እንደሚገባው በፍታብሓር የሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 418 እና ከፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 419 ድንጋጌዎች በማየት ለመገንዘብ ይቻላል።
አመልካች የተሻሻለውን የቤተሰብ ህግና የፍታብሓር ህጉን ድንጋጌዎችና ላልች የህግ ማዕቀፍች መሰረት በማድረግ አመልካችና ተጠሪ በአፈፃፀም እንዱከፊፈለአቸው ትዕዛዝ በተሰጠባቸው ንብረቶች ላይ ያለውን የቀዲሚነት መብት ለማሣየት ያቀረበውን ጥያቄ በመቀበል ወደ ክርክሩ እንዱገባ መፍቀድ ሲገባቸው ንብረቶቹ ውሣኔ ስለተሰጠባቸው በአፈፃፀም ጣልቃ መግባት አይፈቀድም በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ትዕዛዝ ከላይ የጠቀስናቸውን የህግ ድንጋጌዎች ይዘት መንፈስና ዓላማ ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ትዕዛዝ ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች በአፈፃፀሙ ጣልቃ ለመግባት ያቀረበውን አቤቱታና ማስረጃ በመቀበልና የተጠሪዎችን ክርክርና ማስረጃ በመቀበልና በመመርመር ውሣኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቀጥር 341 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት መልስን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.