No summary available.
የካቲት 29 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ሚ/ር ቺዛኖ ቤነኛ አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ዘውደ ወልደሥላሤ አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሲሚ ችልት የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበውን አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። አመልካች የአሁን ተጠሪ ከፍርድ ባለእዲ ከአቶ ወንድወሰን ካሣ ቤት ገዝተው ያልከፈለት የቤቱ ዋጋ 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ አለ። ይህንንም ለማንም ሣያስተላልፈ ይዘው እንዱቆዩ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጥቶበታል። ስለዚህ ይህንን ገንዘብ ለፍርድ ባለእዲው እዲ መፈፀሚያ እንዱሆን በማለት አቤቱታ አቅርበዋል። ተጠሪ በእኔ እጅ የነበረውን ገንዘብ ለመንግስት መከፈል ላለበት የካፑታል ጌይን ታክስና ላልች እዲዎች ከፍያዋለሁ በማለት መጋቢት 15 ቀን 2002 ዓ.ም የፅሐፍ መቃወሚያ አቀርበዋል።
የከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ በእጃቸው የነበረውን የፍርድ ባለእዲ የቤት ዋጋ ለካፑታል ጌይን ታክስና ለላልች እዲዎች የከፈለ በመሆኑ ገንዘቡ የፍርድ ማስፈፀሚያ ላሆን አይችልም።
የፍርድ ባለመብቱ የፍርድ ባለእዲውን ላላ ንብረት አጣርተው ያቅርቡ በማለት መጋቢት 17 ቀን 2002 ዓ.ም ትእዛዝ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ትእዛዝ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለይግባኝ ሰሚው ችልት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ትእዛዝ አፅንቶአል። አመልካች የካቲት 18 ቀን 2003 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ የያዙት ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ለፍርድ ባለእዲው የሚከፈል ገንዘብ በመሆኑ ተጠሪና የፍርድ ባለእዲው ባደረጉት የቤት ሽያጭ ውል ላይ በግልጽ ተመልክቷል።
ይህን ገንዘብ ተጠሪ ይዞ እንዱቆይና ለላላ ወገን እንዲያስተላልፍ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጥቶበታል። ተጠሪ የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ የፈፀመው ተግባር የሥር ፍርድ ቤት ሉያፀድቀው የሚገባው አይደለም። የካፑታል ጌይን ታክስ የመክፈል ግዳታ የገዥ ሣይሆን የሻጭ ግዳታ ነው። አመልካች በገንዘቡ ላይ ከፍርድ የመነጨ የቀዲሚነት መብት ያለው ሆኖ እያለ ተጠሪ ገንዘቡን ለግል ጉዲዩ ተጠቅመውበታል ስለዚህ የተጠሪ አድራጎት የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 156ን የሚጥስ በመሆኑ ገንዘቡን ለአመልካች ሉከፍል ይገባል በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩላቸው መጋቢት 15 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ መልስ የፍርድ ባለእዲው ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በእኔ እጅ እንዱቆይ ትእዛዝ መሰጠቱ የሚታመን ነው። ገንዘቡ በእኔ እጅ የቆየው የፍርድ ባለእዲ የሸጠለትን ቤት ወደ እኔ ስም ለማዘዋወር ሉከፍለት የሚገባውን የመንግስት ግብር ለመክፈል ነው። ብር 84,580.47 /ሰማንያ አራት ሺህ አምስት መቶ ሰማኒያ ብር ከአርባ ሰባት ሣንቲም/ ከፍዬ ቀሪው ብር 4,085.80 ለቦታ ቅጣት የከፈልኩ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠው ትእዛዝ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክረዋል። አመልካች ገንዘቡ የተከፈለው በፍርድ ባለእዲው በአቶ ወንድወሰን ካሣ መሆኑ የቀረበው ደረሰኝ ያሣያል ተጠሪ ከፍሎል ቢባል እንኳን ገንዘቡ ከፍርድ ባለእዲ ጋር ያደረገውን ውል ማስፈፀሚያ ያደረገው የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ በመጣስ በመሆኑ ህጋዊ እውቅና ሉሰጠው አይገባም በማለት ሰኔ 26 ቀን 2003 ዓ.ም የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን ተጠሪ ለፍርድ ማስፈፀሚያ እንዱሆን ይዘው እንዱቆዩ የታዘዘውን ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ተጠሪ የፍርድ ባለ እዲው የሸጠልኝን ቤት ስም ለማዛወር ለካፑታል ጌይን ታክስና ለላልች እዲዎች ከፍያለሁ በማለት ያቀረቡትን ክርክር የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት መቀበላቸው ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን የሥር አመልካች ተጠሪ ለፍርድ ባለእዲው ያልከፈለትን ብር 100,000 /መቶ ሺህ ብር/ ለፍርድ ማስፈፀሚያ ለማድረግ ያቀረቡትን አቤቱታ፤ ተጠሪ ያቀረቡትን ክርክርና የአፈፃፀሙን ክርክር ያየው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአፈፃፀም መዝገብ በትእዛዝ በማስቀረብ አይቶታል። ከሥር ፍርድ ቤት የአፈፃፀም መዝገብ እንደተረዲነው የፍርድ ባለመብት የሆኑት አመልካች የፍርድ ባለእዲው አቶ ወንድወሰን ካሣ ለተጠሪ /አቶ ዘውደ ወ/ሥላሤ የሸጡት ቤት ንብረትነት ሲዛወር የሚከፈል ብር በገዥው በተጠሪ እጅ ስላለ ገዥው ገንዘቡን ለባለእዲው ሣይከፍለ በእጃቸው ይዘው እንዱቆዩ እና ይህንንም ለመፈፀማቸው ቀርበው እንዱያስረደ ትእዛዝ ይሰጥልኝ በማለት ሐምል 2 ቀን 1996 ዓ.ም አመልክተዋል። የሥር ፍ/ቤትም ተጠሪ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ለባለ እዲው ሣይከፍለ ይዘው እንዱቆዩ አዟል። እንደዚሁም ፍ/ቤቱ የአሁን ተጠሪ በ ትእዛዙ መሰረት የፈፀሙ መሆኑን ወይም የማይፈጽሙበ ምክንያት ካለ በሚቀጥለው ቀጠሮ ቀርበው እንዱያስረደ በማለት ሐምል 2 ቀን 1996 ዓ.ም. ትእዛዝ ሰጥቷል። ለተጠሪም የእግድ ትእዛዙን ከመጥሪያ ጋር ልኳል።
የአሁን ተጠሪ መጥሪያው እና የእግድ ትእዛዙ ከደረሳቸው በኋላ ሐምል 26 ቀን 1996 ዓ.ም ከጠበቃ ጋር ቀርበው ከተባለው ገንዘብ ውስጥ ብር 90,000 /ዘጠና ሺህ ብር/ ለመንግስት ግብር ተከፍሎል በማለት አስረድተዋል። አመልካች የተጠሪ ክርክር ትክክለኛ አይደለም ተጠሪ ገንዘቡን በሞዳል 85 ገቢ እንዱያደርጉ ትእዛዝ ይሰጠልኝ በማለት ተከራክረዋል። ፍርድ ቤቱ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለህዲር 9 ቀን 1997 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል። ህዲር 9 ቀን 1997 ዓ.ም የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ብር 90,000 /ዘጠና ሺህ ብር/ ለመንግስት ግብር የከፈለ መሆኑን የሚያሣየው ማስረጃ ያልቀረበለት መሆኑን ገልጾ ይህ ፍ/ቤት ገንዘቡ ታግድ እንዱቆይ የሰጠው ትእዛዝ እንደተጠበቀ ሆኖ ተጠሪ ለመንግስት ግብር የከፈለ መሆኑን የሚያሣየውን ህጋዊ ደረሰኝ ያቅርቡ በማለት ትእዛዝ ሰጥቶ ተጠሪ ደረሰኝ የሚያቅርቡ ቢሆን ለመጠባበቅ ለህዲር 17 ቀን 1997 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል። ህዲር 17 ቀን 1997 ዓ.ም. የተጠሪ ጠበቃ ቀርበው ባለፈው ቀጠሮ ደንበኛቸው ብር 90,000 /ዘጠና ሺህ ብር/ ለመንግስት ግብር ከፍያለሁ ያለት በስህተት ነው ገንዘቡ ገና አልተከፈለም ወደ ፉት የቤቱ ንብረትነት ከሻጭ ወደ ገዥ ሲዛወር የሚከፈል በመሆኑ ልንጠየቅ የሚገባው ክፍያ አይደለም በማለት አመልክቷል። ፍርድ ቤቱ ተጠሪ የፍርድ ባለእዲውን ገንዘብ ለማንም ሣይከፍለ በእጃቸው ይዘው እንዱቆዩ በማለት ህዲር 17 ቀን 1997 ዓ.ም ትእዛዝ ሰጥቷል። ተጠሪ በእኔ እጅ የነበረውን ገንዘብ የፍርድ ባለእዲው መክፈል የሚገባቸውን የካፑታል ጌይን ታክስና ለትርፍ ቦታ ቅጣት ከፍያለው የሚለት መጋቢት 26 ቀን 1997 ዓ.ም. መሆኑን ለሥር ፍ/ቤት ያቀረቧቸው የሆኑ ደረሰኞች ያሳያለ። ከላይ ይዘታቸውን የገለጽናቸው የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጣቸው ትዕዛዞች ተጠሪ አከራካሪውን ብር 100,000 /መቶ ሺህ ብር/ የፍርድ ባለ ዕዲው ሉከፍለው ለሚገባው የግብር ዕዲም ሆነ በልላ ምክንያት ወጭ ሳያደርግ ባለበት ሁኔታ ይዞ እንዱቆይ ግልጽና የማያሻማ ትዕዛዝ ሰጥቶ እያለና ተጠሪም ይህንን የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ እያወቀ ገንዘቡን ለካፑታል ጌይን ታክስና በትርፍ ቦታ ቅጣት የከፈለ መሆኑን ነው።
የፍርድ ባለእዲ የሆነ ሰው በእጁ ያልገባ ከላላ ሰው የሚጠይቀው በሚተላለፍ ሰነድ ያልተደገፈ ገንዘብ ያለው መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ገንዘቡን የመያዝ ወይም የማስከበሩ ሥርዓት የሚፈፀመው ፍርድ ቤት ግልጽ የሆነ ትእዛዛ እስከሚሰጥ ድረስ ለፍርድ ባለእዲው ገንዘብ መክፈል የሚገባው ሰው ይህንን የሚከፈለውን ገንዘብ ለማንም ሰው ሣይሰጥ በእጅ እንዱቆይ በማድረግ እንደሆነ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 409 ንዐስ አንቀጽ 1 በግልጽ ተደንግጓል። የከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀምላ 2 ቀን 1996 ዓ.ም፣ ህዲር 9 ቀን 1997 ዓ.ም. እና ህዲር 17 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ተጠሪ ገንዘቡ አንድ ጊዜ ለግብር እዲ ተከፍሎል። ላላጊዜ ደግሞ ወደፉት ለግብር እዲ የሚከፈልና ጊዜ የማይሰጥ ነው በማለት የተከራከሩ ቢሆንም ገንዘቡን ለማንም ሣይሰጥ በእጃቸው ይዘው እንዱቆዩ ግልፅና የማያሻማ ተደጋጋሚ ትእዛዝ የሰጠ መሆኑንና ትእዛዙም በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 409 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት ያደረገ መሆኑን ነው።
የከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪ እጅ ተይዞ እንዱቆይ ትእዛዝ የሰጠበት ብር 100,000 /መቶ ሺህ ብር/ ለአመልካች የእዲ መክፈያነት መዋል አለበት ወይስ ተጠሪ ከፍርድ ባለእዲው የገዙትን ቤት ስም ለማዛወር መከፈለ አስፈላጊ ለሆነው የካፑታል ጌይን ታክስ ክፍያ መዋል አለበት?
የሚለውን ጭብጥ ያልወሰነውና ወደፉት መርምሮ ትእዛዝ የሚሰጥበት መሆኑን ህዲር 9 ቀን 1997 ዓ.ም በሰጠው የአፈፃፀም ትእዛዝ በግልጽ አስፍሮታል። ተጠሪ ገንዘቡን ይዞ እንዱቆይ ትእዛዝ የተሰጠበት ገንዘብ ለአመልካች እዲ መክፈያነት ይውላል ወይም ተጠሪ ከፍርድ ባለእዲ የገዛውን ቤት ስመሀብት ለመዛወር ሻጭ (የፍርድ ባለእዲው) ለሚከፍለት የካፑታል ጌይን ታክስ መክፈያነት ይዋል የሚለውን የሥር ፍርድ ቤት ሣይወሰንና ግልጽ ትእዛዝ ከመስጠቱ በፉት አመልካች ከፍርድ ባለእዲው ጋር አድርጌዋለሁ የሚለትን የቤት ሽያጭ በውለ መሰረት የቤቱን ስመሀብት ሻጭ (የፍርድ ባለእዲው) ወደ ገዥ (ተጠሪ) ለማዛወር በህግ እንደ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠው የካፑታል ጌይን ታክስ ለመክፈል የሥር ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ የሰጠውን የእግድ ትእዛዝ በመጣስ ገንዘቡን ወጭ ያደረግሁ መሆኑን ያሳዩልኛል የሚሎቸውን ደረሰኞች በማያያዝ ለዚህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነውን ትእዛዝ ለሰጠው ችልት ክርክር አቅርበዋል። ይኸው ተጠሪ አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤት ሐምል 2 ቀን 1996 ዓ.ም፤ ህዲር 9 ቀን 1997 ዓ.ም ተጠሪ ገንዘቡን ለማንም ሣይሰጡ በእጃቸው ይዘው እንዱቆዩ የሰጠው የእግድ ትእዛዝ እዱነሣላቸው የሥነ ሥርዓት ህጉን መሰረት በማድረግ አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 409 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት የሰጠው የእግድ ትእዛዝ እንዱነሳ ሣያደርግ፣ ገንዘቡን በራሳቸው ፍላጎትና ግላዊ ውሣኔ የእሳቸውን መብትና ጥቅም ለሚያስከብር ተግባር /ክፍያ/ ወጭ ያደረጉት መሆኑን የሚያሣይ መሆኑን ተረድተናል።
ፍርድ የሚያስፈፀመው ፍርድ ቤት አንድ ሰው የተወሰነ ነገር ከመፈፀሙ እንዱታገድ ትእዛዝ ሰጥቶ እያለ ትእዘዝ የተሰጠው ሰው በትእዛዙ መሰረት ሉፈፀም ሲችል ሆነ ብል ሳይፈፀም የቀረ እንደሆነ ወይም እንዲይፈፀም የተከለከለውን ነገር የፈፀም እንደሆነ ፍርድ ቤቱ የእንቢተኛውን ንብረት እንዱያዝና እንዱሸጥ አድርጎ የተወሰነበትን ግዳታ እንዱፈፀም ለማዘዝና ተገቢ መስል ከታየውም ከንብረቱ ሽያጭ ለፍርድ ባለገንዘብ ካሣ ወይም ኪሣራ እንዱከፈል እንደሚወስን በፍታብሓር ህግ 400 በግልጽ ተደንግጓል። የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 156 ንዐስ አንቀጽ 2 የፍርድ ቤትን የእግድ ትእዛዝ ያላከበረው ሰው ንብረት ለፍርድ ባለገንዘቡ ገንዘብ መክፈያ በመሸጥ ለማስከፈል ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እንደሚሰጥ የሚደነግግ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ እግድን ያላከበረውን ሰው የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ በመጋፊቱ በችልት መድፈር ወንጀል የወንጀል ቅጣት ሉወሰንበት እንደሚችል የፍታብሓር የሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 156 ንዐስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል።
በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ አመልካች ለፍርድ ማስፈፀሚያ እንዱሆን ይከበርልኝ በማለት የፍርድ ባለእዲው ሀብት የሆነ ብር 100,000 /መቶ ሺህ ብር/ ለማንም ሰው ሣይሰጥ በእጁ ይዞ እንዱቆይ የፋዳራል ከፍትኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ተደጋጋሚና ግልጽ ትእዛዝ እያወቀና ገንዘቡ የእግድ ትእዛዝ ላሰጥበት አይገባም የሚል መቃወሚያ ሲያቀርብና በችልት ሲከራከር ቆይቶ ፍርድ ቤቱ የሰጠው የእግድ ትእዛዝ ሣይነሣና ተጠሪ ገንዘቡን የፍርድ ባለእዲ የሸጠውን ቤት ስመሀብቱ ለማዛወር ቅድመ ሁኔታ የሆነውን የካፑታል ጌይን ታክስና የትርፍ ቦታ ቅጣት መክፈያነት አውየዋለሁ በማለት ያቀረበውን ክርክር የሥር ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት መቀበላቸው ተገቢነት የላለውና ከላይ የጠቀስናቸው የህግ ድንጋጌዎችን መሰረት ያላደረገ ሆኖ አግኝተነዋል።
ማንም ሰው ህጉን በእጁ አድርጏ እንዱጠቀምና በራሱ ጉዲይ ዲኛ ሆኖ እንዱወሰን አይፈቀድለትም። ተጠሪ የፍርድ ባለእዲው ብር 100,000 /መቶ ሺህ ብር/ በእሱ እጅ የነበረ መሆኑን በመጠቀም ገንዘቡን ለማንም ሰው አሳልፍ እንዲይሰጥ ወይም እንዲይከፈል ፍርድን የሚያስፈጽመው ፍርድ ቤት የሰጠውን ግልጽ የእግድ ትእዛዝ እያወቀ ሆነ ብል ገንዘቡን የፍርድ ባለእዲው ከእኔ ጋር ላደረገው የቤት ሽያጭ ውል ለሚፈለግበት የካፑታል ጌይን ታክስ እና የትርፍ ቦታ ቅጣት እጠየቃለሁ በማለት የሚያቀርበው ክርክር የፍታብሓር ህግ ቁጥር 409 ንዐስ አንቀጽ 1፣ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 400 እና የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 156 ድንጋጌዎችን የሚጥስና የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ተግባር ሆኖ እያለ ተጠሪ አመልካች ላቀረበው የፍርድ አፈፃፀም ጥያቄ ተጠያቂነት የለበትም በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ስለሆነም አመልካች ለማንም ሰው ሳይሰጥ ወይም ክፍያ ሣይፈጽም ፍርደን በሚያስፈፀመው ፍርድ ቤት የተሰጠውን ተደጋጋሚ ግልጽ ትእዛዝ በመጣስ የፍርድ ባለእዲው ከእኔ ጋር ባደረገው ውል ምክንያት ለነበረበት የካፑታል ጌይን ታክስና ለትርፍ ቦታ መቀጫ ክፍየዋለሁ የሚለውን ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ለፍርድ ባለመብት (አመልካች) የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 409(1) የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 400 የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 156(2) መሰረት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍትኛ ፍርድ ቤት መጋቢት 17 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ህዲር 22 ቀን 2003 ዓ.ም. የሰጠው ትእዛዝ ተሽሯል።
ተጠሪ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ለአመልካች የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ውጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ
No topics extracted.