No summary available.
ጥር 04 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካቶች፡- 1- አቶ ልኡልሰገድ አጥላባቸው 2- አቶ ሱፉያን አራርሶ 3- አቶ ረመዲን ኢድሪስ ጠበቃ አስፊው ገ/አሉፍ ቀረቡ 4- አቶ አብደላዚዝ ኢብራሂም ተጠሪዎች፡- 1- ፍልራ ኢኮ ፕወር ኃ/የተ/የግል ድርጅት- ነገረ ፈጅ ሽመልስ ሣተናው ቀረቡ 2- የፍልራ ኢኮ ፕወር ሰራተኞች ማህበር-ተወካይ ደሣለኝ ግርማ ቀረቡ መዝገቡን ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የአፈፃፀም ክርክር የሚመለከት ሲሆን አመልካቾች በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ1ኛ ተጠሪ የሆኑ ተሸከርካሪዎች በሀራጅ በሚሸጡበት ወቅት ግዢ የፈጸሙ እና ፍርድ ቤቱም የሀራጅ ሽያጩን በተመለከተ በአግባቡ አልተከናወነም በማለት ሰርዞ አመልካቾቹም የተረከቡትን ማሽኖች እና ተሽከርካሪዎች እንዱመልሱ በመወሰኑ ፣ በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠውም ውሣኔ በክልለ የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በክልለ የሰበር ሰሚ ችልት በመጽናቱ የተፈጸመው መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዱታረምልን በማለት አመልካቾችን በማመልከታቸው የቀረበ ነው።
አመልካቾች ለዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ባቀረቡት ቅሬታ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞባቸዋል ያለትን ነጥቦች ያቀረቡ ሲሆን ሰኔ 2ዐ ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተጻፈ ስድስት ገጽ የአቤቱታ ፍሬ ሃሣብ ፡- የገዛናቸው ተሽከርካሪዎች የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በህጉ አግባብ ባወጣው ሀራጅ መሰረት ሲሆን ፍርድ ቤቱ ራሱ ያዘዘውን በራሱ መልሶ መሻሩ አግባብነት የላለው በመሆኑ ፣ በወጣው ማስታወቂያ መሰረት ጨረታውን ተሳትፈን የገዛነውን ተሽከርካሪዎች እንድንመልስ መወሰኑ አግባብ ባለመሆኑ ፣ በጉዲዩ ላይ ሃሣባችንን እንድናቀርብ ሳይደረግ የተደረገው ሀራጅ መሻሩ አግባብነት ላለው በመሆኑ ፣ ለዚህ ጉዲይ አግባብነት ያለው ተንቀሳቃሽ ንብረት በተመለከተ የሚደረገውን ሀራጅ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 435 መሰረት መታየት ሲገባው የበታች ፍርድ ቤቶች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 445 ን በመጥቀስ ሀራጁ እንዱፈርስ መደረጉ አግባብ ባለመሆኑ ፣ ለተሽከርካሪዎቹ የከፍልነውን ገንዘብ በተመለከተ ምንም ሳይባል መታለፊ አግባብነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዱሻርልን የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ታዞ 1ኛ ተጠሪ በቀን 4/2/2004 ዓ.ም በሶስት ገጽ እና 2ኛ ተጠሪም በቀን 3ዐ/1/2004 ዓ.ም በሶስት ገጽ በተጻፈ የጽሐፍ መልስ የሰጡ ሲሆን ፍሬ ሃሣቡ ፡- የፍርድ ባለዕዲ ግዙፍ እና የተለያዩ አገልግልት ሰጪ ማሽኖችን እና ተሽከርካሪዎችን በቂ ዕውቀት ባለው ባለሙያ ሳይገመት የጨረታው ማስታወቂያ ህጉ በሚያዘው መሰረት ሳይወጣ ፣ የፍርድ ባለመብት በእጅ አዙር የገዛው ስለመሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች ተረጋግጦ ጨረታው እንዱሰረዝ የተደረገ በመሆኑ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክሯል። የአመልካቾች የመልስ መልስም ቀርቧል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር መርምሮታል።
እንደመረመረውም ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ሲባል ተይዞ የነበረው ጭብጥ ለዚህ ጉዲይ ተፈጻሚነት ያለው ድንጋጌ የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን ሽያጭ የሚመለከተው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 435 ሆኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች የማይንቀሳቀስ ንብረቶችን የሚመለከተውን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ 445 መሰረት በማድረግ ጨረታውን የመሰረዛቸውን አግባብነት ለመመርመር ሲባል በመሆኑ ከዚሁ ከነበረው ጭብጥ አኳያ ጉዲዩ ታይቶ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ መሰረት ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አከራካሪ የሆነው የሀራጅ ሽያጭ የተካሄደው በጋዜጣ ማስታወቂያ ሳይወጣ እና በወስጥ ማስታወቂያ ብቻ ሀራጅ መደረጉ ፣ በሀራጅ ሽያጩ ላይ የማጭበርበር ተግባር የተፈጸመ ስለመሆኑ እንደዚሁም ንብረቶቹ ከዋጋቸው በታች የተገመቱ እና የተሸጡ ስለመሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጡ ነጥቦች ናቸው። የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ይዘን አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች ስንመለከት በእርግጥ በበታች ፍርድ ቤቶች የተከናወነው ሀራጅ እንዱፈርስ ሲደረግ የተጠቀሰው የህግ ድንጋጌ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 445 መሆኑን መመልከት ይቻላል። ሆኖም ግን ለዚህ ጉዲይ አግባብነት ያለው ድንጋጌ የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሚመለከቱ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 432 እስከ 438 ድረስ ያለት ድንጋጌዎች እና በተለይም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 435 በመሆኑ ከእነዚህ ድንጋጌዎች አኳያ የተሰጠውን ውሣኔ አግባብነት መመልከት ተገቢነት አለው።
No topics extracted.
በዚሁ መሰረት በበታች ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ይዘን በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠውን ውሣኔ ወይም የተከናወነውን ጨረታ መሰረዛቸው አግባብ ስለመሆን ወይም አለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 435 አኳያ መመርመሩ ተገቢ ይሆናል ማለት ነው። በዚህ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ድንጋጌ ርዕስ እንደሚያሳየው የሽያጩ ስርዓት በትክክል ያለመፈጸም ሽያጩን የሚያፈርስበት ሁኔታ በሚል የተቀመጠ በመሆኑ ፣ ወደ ድንጋጌው ይዘት ስንገባም በእርግጥ ለሽያጩ በወጣው ማስታወቂያ ላይ ጉድለት በመገኘቱ ወይም የሽያጩ ስነስርዓት በትክክል አልተፈጸመም በማለት ብቻ የተከናወነው ጨረታ በሰበብ አስባብ ሉፈርስ እንደማይችል የሚደነግግ ቢሆንም በሂደቱ ላይ ጉዲት አድርሶ ከሆነ ለጉዲቱ ኃላፉ የሆነን ሰው ካሣ እንዱከፍል መወሰን የሚቻል ስለመሆኑ ፈቃጅ በሆነ ሁኔታ የሚደነግግ ከመሆኑም በላይ እንደ ጉዲዩ አግባብ እየታየ የተከናወነው ጨረታ ፈርሶ የተሸጠውም ንብረት እንዱመለስ የሚወሰንበት አግባብ እንዲለ ከድንጋጌው አቀራረጽ ፣ ዓላማ ፣ ይዘት እና መንፈስ መገንዘብ ይቻላል።
በመሆኑም የሚንቀሳቀስ ንብረት በሀራጅ በሚሸጥበት ጊዜ ማንኛውም ዓይነት ስህተት ቢፈጸም ጨረታው የሚሰረዝበት አግባብ የለም በሚል መልኩ በአመልካቾች የሚቀርበው ክርክር የዚህን የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ዓለማ ያላገናዘበ እና በሂደቱ ፍትሐዊነት ላይ ፍርድ ቤቶች ያላቸውን ሚና ያላገናዘበ ነው ብለናል። የበታች ፍርድ ቤቶችም የተረጋገጡትን ፍሬ- ነገሮች በመመልከት የተከናወነው ጨረታ እንዱፈርስ ውሣኔ መስጠታቸው ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 435 አኳያ ሲታይ ተገቢ ነው ከሚባል በስተቀር የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለ የሚያሰኝ አይደለም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔውን ሲያስተላል የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 435ን መጥቀስ ሲገባቸው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ 445. መጥቀሳቸው አግባብነት ያለው ድንጋጌ ባይሆንም ከውጤት አኳያ ግን ተቀባይነት ያለው መደምደሚያ በመሆኑ የተከናወነው ሀራጅ ይፍረስ መባለ የሚነቀፍበት ህጋዊ ምክንያት የለም። በልላ በኩል በዚሁ የሰበር ሰሚ ችልት በመዝ. ላይ የፍርድ ባለመብት የነበሩት ግለሰብ የተከናወነው ጨረታ ሉፈርስ አይገባም በማለት በዚሁ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ላይ በተመሣሣይ ቅሬታቸውን አቅርበው ጉዲዩ ያስቀርባል ተብል ከአሁኖቹ ተጠሪዎች ጋር ተከራክረው የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ የጸና እና በዚሁ ጭብጥ ላይ ንብረቶቹን ገዛን የሚለት የአሁኖቹን አመልካቾች ክርክር ተመልክተን ከላይ በተመለከቱት ነጥቦች ምክንያት ተመሣሣይ መደምደሚያ ላይ ደርሰናል።
ባጠቃላይ የክልለ የዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በተካሄደው የሀራጅ ሂደት ጉልህ ግድፈቶች ስለመከሰታቸው በፍሬ ነገር በተረጋገጠበት ሁኔታ ሀራጁ ተሰርዞ አመልካቾች የገዙትን ንብረት እንዱመልሱ በመባለ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
በሀራጅ ሽያጭ ሂደት ግዙፍ ግድፈቶች በሚኖሩበት ጊዜ የተከናወነው ሀራጅ እንዱሰረዝ መባለ በአግባቡ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።