No summary available.
ህዲር 21 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ኢስላሚክ ሪሉፍ ኢትዮጵያ - ጠበቃ ቃሲም መሐመድ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ መሐመድ ሰይድ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በግራ ቀኙ መካከል በነበረው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ክርክር በፍርድ ባለቀና የአፈጻጸም መዝገቡ ላይ የተሰጠው የአፈጻጸም ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች ባቀረበው አቤቱታ መሰረት የቀረበ ነው። በአሁኑ ተጠሪ ቀርቦ የነበረው የአሰራና ሰራተኛ ጉዲይ ክስ በአፊር ብሓ/ክልላዊ መንግስት በዞን 4 እዋ ወረዲ ፍ/ቤት ውሣኔ ያገኘ ሲሆን ይዘቱ በተጠሪ ላይ የተፈጸመው የስንብት እርምጃ ህገ ወጥ ነው በማለት ሉከፍለ የሚገባቸውንም ተያያዥ ክፍያዎች በማመላከት የተሰጠ ነው። በዚህ ውሣኔ ተከሣሽ የነበረው የአሁኑ አመልካች ለክልለ የዞን 4 ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን በማከራከር በተጠሪ ላይ የተወሰደው እርምጃ ህገ ወጥ ስንብት መሆኑን በማጽናት ተያያዥ ክፍያዎችን በተመለከተ የወረዲው ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በማሻሻል የወሰነ ስለመሆኑ መረዲት ይቻላል። አሁን አከራካሪ የሆነውና ለዚህ ቅሬታ መሰረት የሆነው የአሁን ተጠሪ ለዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበው የአፈጻጸም ማመልከቻ እና ፍ/ቤቱም የቀረበለትን ማመልከቻ በመቀበል ግራ ቀኙን በማከራከር ታህሣስ 20 ቀን 2000 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ ነው።
አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው የክልለ የዞን 4 ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ የተመለከተውን ጉዲይ ማስፈጸም ያለበት ቀድሞውኑ በወረዲው ፍ/ቤት ላይ ተከፍቶ በነበረው የአፈጻጸም መዝገብ የወረዲው ፍ/ቤት እንጂ የዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አይደለም። ስልጣኑ ካለመሆኑም በላይ የይግባኝ መብታችንን የሚያጣብብ በመሆኑ አግባብነት የለውም የሚል ሲሆን በልላ በኩል የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በአፈጻጸም መዝገቡ ላይ ትዕዛዝ ሲሰጥ ቀድሞ ፍርድ ያላረፈበትን ክፍያዎች ሁለ በመጨመር በመሆኑ ተቀባይነት የለውም የሚል ነው። ተጠሪ በበኩለ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በይግባኝ አይቶ ውሣኔ የሰጠበት በመሆኑ የአፈጻጸም ጉዲዩን ተመልክቶ ማስፈጸም ይችላል ከፍርድ ዉጪ ተጨምረዋል የተባለትን ክፍያዎች በተመለከተ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የወሰናቸው በመሆኑ የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የለውም በሚል ተከራክሯል።
ጉዲዩ ለዚህ ችልት ያስቀርባል ሲባል ተይዞ የነበረው ጭብጥ የተጠሪ የሥራ ውል ከህግ ውጪ ተቋርጧል ተብል የካሣ ክፍያ የ85 ቀናት ደመወዝ ይከፈለው ተብል የተሰጠው ፍርድ እያለ በአፈጻጸም ውሣኔው ላይ የ180 ቀናት ደመወዝ ይከፈለው የመባለን አግባብነት የነበረ ቢሆንም አሁን ችልቱ ጉዲዩን ሲመለከተው ከተያዘው ጭብጥ በፉት የዞኑ ፍ/ቤት ያለውን ስልጣን መመልከት ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ መሰረት የክልለ የዞን 4 ከፍተኛ ፍ/ቤት የአፈጻጸም መዝገቡን ተመልክቶ ትዕዛዝ መስጠቱ በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ ተይዞ የተያዘው ጉዲይ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
በዚሁ መሰረት በግራ ቀኙ መካከል የነበረው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ክርክር በክልለ የዞን አራት የእዋ ወረዲ ፍ/ቤት ውሣኔ ያገኘ ስለመሆኑ ይሄ የወረዲ ፍ/ቤት በተጠሪ ላይ የተወሰደው የስንብት እርምጃ ህገ ወጥ ስለመሆኑ የዞኑ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም በተመሳሳይ የተቀበለውና ያጸናው ሲሆን የአሁን አመልካች ባቀረበው ቅሬታ መሰረት የክፍያውን መጠን በተመለከተ ብቻ የወረዲውን ውሣኔ ያሻሻለው ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል። አንድን ፍርድ ማስፈጸም ያለበት ጉዲዩን በመጀመሪያ ተመልክቶት ፍርደን የሰጠው ፍርድ ቤት ስለመሆኑ የአፈጻጸም ሥርዓት የሚመራበትን አግባብ የሚያመለክተው የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ በተለይም በህጉ ከቁጥር 371- እስከ 385 ድረስ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ዓላማ ይዘትና መንፈስ የሚያስገነዝቡን ናቸው። ይሄ አሰራር ደግሞ በየደረጃው ያለት ፍ/ቤቶች በበታች ፍ/ቤቶች የተሰጡትን ውሣኔዎች ሉያሻሽለ የሚችለበት በርካታ አጋጣሚዎች ሉኖሩ ቢችለም አፈጻጸሙ ግን አንድ ላይ ተጠቃል ጉዲዩን በመጀመሪያ በተመለከተው ፍ/ቤት እልባት ማግኘቱ ለተከራካሪዎች ወጪ ቆጣቢ ከመሆኑም በላይ በአፈጻጸም ሂደት በሚሰጡት ትዕዛዞች ላይ ቅሬታ ቢኖር እንኳ የይግባኝ መብት የማያጣብብ በመሆኑ ጠቀሜታው የጏላ ነው። በተጨማሪም ቀድሞ በወረዲው ፍ/ቤት ፍርድ መሰረት የአፈጻጸም መዝገብ በወረዲው ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ያስከፈቱ ስለመሆኑ ግራ ቀኙን አላከራከረም። በወረዲው ፍ/ቤት የተሰጠውም ውሣኔ በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሻሻለ ቢሆንም አፈጻጸሙ መቀጠል ያለበት በመጀመሪያ ደረጃ ጉዲዩን አይቶ ፍርድ በሰጠው የወረዲ ፍ/ቤት መሆን ሲገባው የክልለ የዞን 4 ከፍተኛ ፍ/ቤት የእዋ ወረዲ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በማሻሻለ ብቻ የአፈጻጸም መዝገቡን አስከፍቶ ውሣኔ መስጠቱ አግባብነት የለውም ብለናል። ባጠቃላይ የአፈጻጸም ክስ መስተናገድ ያለበት በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ የሰጠው ፍ/ቤት ሆኖ እያለ የክልለ የዞን ፍ/ቤት ጉዲዩን ተመልክቶ ውሣኔ መስጠቱ መሰረታዊ የአፈጻጸም ሥነ ሥርዓቶችን የጣሰና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል።
No topics extracted.
በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
በመዝ.ቁ. 00039 ላይ የተሰጠው የአፈጻጸም ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፍርድ ባለመብት በፍርደ መሰረት ሉፈጸምለት የሚገባቸውን ነጥቦች በተመለከተ በወረዲው ፍ/ቤት ከመጠየቅ የሚከለክለው ነገር የለም ብለናል።