No summary available.
ጥር ዐ4 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- 1- ሳሙኤል ሃይለ - ቀረቡ 2- ሆራይዘን ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግል ማህበር - ጠበቃ እንዲልካቸው ይላቅ ቀረቡ ተጠሪ፡- እነ ወ/ሮ ስምረት አያላው /ዘጠኝ ሰዎች/ 1ኛ. ወ/ሮ ስምረት አያላው 6ኛ. ቤተልሄም አያላው 2ኛ. ወ/ሮ ፅዮን አያላው 7ኛ. አዱስ አያላው 3ኛ. ጳውልስ አያላው 8ኛ. ማህላት አያላው 4ኛ. የማነ አያላው 9ኛ. ሙለጌታ አያላው 5ኛ. ፍሬሕይወት አያላው - የሁለም ጠበቃ ተስፊዬ ቀለመወርቅ -ቀረቡ መዝገቡ ከሰ/መ/ቁጥር 7ዐ38ዐ ከሆነው ጋር አጣምረን በመመርመር የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በቅጅ መብት ሕግ ጥበቃ የሚደረገውን መብት ፣ የመብቱን ተጠቃሚዎችንና መብቱ ተጥሶ ሲገኝ በሕጉ ስላለው መፍትሓ የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋደራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ከሣሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪዎች ሲሆኑ ተከሣሾች የአሁኑ አመልካቾች ነበሩ። የተጠሪዎች የክስ ይዘት ወላጅ አባታቸው አለቃ አያላው ታምሩ በሕይወት ዘመናቸው ብዛት ያላቸው ሐይማኖት ነክ የሆኑ የፈጠራ ስራዎችን መስራታቸውን፣ የተለያዩ ፅሐፍችን ማዘጋጀታቸውን፣ በተለያዩ ሚዱያዎች ላይም በመጣጥፍና በቃለመጠይቅ ዙሪያ ስብከቶችን ማዘጋጀታቸውንና በሕይወት ዘመናቸው የእነኚህ ስራዎች የፈጠራ ባለቤት የነበሩና ከሕልፈተ ሕይወታቸው በኋላም መብቶቹ ለወራሾች መተላለፊቸውን ፣ የአሁኑ 1ኛ አመልካች የባለመብቶችን ፈቃድ ሳያገኝ የሟቹን የፈጠራ ስራ የሆኑትን ፅሐፍች በጋዜጣ እና በመፅሄት ላይ የወጡ ቃለመጠይቆችን ፣ መጣጥፍችን ፣ የሟች የመንፈቅ መታሰቢያ ፕስተር ላይ የወሰደትን የመፅሐፊን የሽፊን ሥእልና የሀዘን መግለጫ ግጥሞችን ጭምር በማሰባሰብ በ2ኛ ተጠሪ ማተሚያ ቤት አማካኝነት “ትምህርተ ሃይማኖት” በሚል ርዕስ ከሕግ ውጪ ማሳተሙን ገልፀው በአዋጅ ቁጥር 41ዐ/1996 መሰረት ህትመቱ እንዱቆም ፣ የታተሙት መፍሐፍችን እንዱወገደ የሞራል ካሣ ብር 1ዐዐ,ዐዐዐ.ዐዐ /አንድ መቶ ሺህ ብር/፣ ሶስት ሺህ መጽሐፍች በገበያ በመሸጣቸው ብር 6ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ /ስልሳ ሺህ/፣ ተጠሪዎች ራሳቸው መጽሐፊን አሳትመው ቢሸጡ ኑሮ ይገኝ የነበረውን ገቢ ብር 250,000.00/ሁለት መቶ ሃምሣ ሺህ ብር/ በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ 1ኛ አመልካች ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርበዋል። አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረቧቸው መከራከሪያ ነጥቦችም ሟች አለቃ አያላው ታምሩ የስራው አመንጪ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ያለመቅረቡን፣ የፅሐፍ ስራው የአለቃ አያላው የግል ስራ ሳይሆን የኢትዮጵያ ኦርቶድከስ ተዋህድ ቤተክርስቲያን ወቅታዊ ሐይማኖት ጥያቄዎችን አስመልክቶ ያላቸውን የእምነት አቋም በተመለከተ የጻፎቸው መሆናቸውን ስራውን ሲያቀርቡ ስራውን ለማሰራጨት መብቱ የእሳቸው ብቻ መሆኑን የሚያሳይ ነገር ያለመኖሩን ፣ ጉዲዩ በሽምግልና እየታየ ባለበት ሁኔታ ክሱ ላቀርብ እንደማይገባ የሚገልፁ ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃ ደግሞ ሟች አለቃ አያላው ታምሩ ስራውን የማሰራጨት መብታቸውን ባለመጠበቃቸው ስራው የራሳቸው የፈጠራ ስራ ነው ቢባል እንኳ ላልችን ከማሰራጨት ማገድ እንደማይችለ የሟች አያላው ታምሩ ስራ የኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ቤተክርስቲያን እውቀት መሰረት በማድረጉ የስራ አመንጪ ሉባለ እንደማይችለ ፣ ስራው ወጥ ስራ ያለመሆኑንና በሕግ ጥበቃ ሉያገኝ እንደማይገባ ሟች የጀመሩትን ኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋህድ ትምህርት ለሕዝብ ለማሰራጨታቸው አመልካቹ ሉከሰሱ እንደማይገባ ዘርዝረው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል። የአሁኑ ሁለተኛ አመልካች በበኩለ በሰጠው መከላከያ መልስ አንደኛ አመልካች ለህትመት ባቀረቡት ፅሐፍ ምንጩ አለቃ አያላው ታምሩ መሆናቸውን በመገለፁ የሚያስጠይቀው መሆኑን የወራሾችን ፈቃድ መጠየቅ ያለበት አሳታሚ እንጂ አታሚ ያለመሆኑን ፣ የሟች የፈጠራ ስራ ለመሆኑ ማስረጃ አለመቅረቡን ፣ አታሚዉ በራሱ አነሳሽነት ያለማተሙንና የሟች አለቃ አያላው ታምሩ ስራ ስለመሆኑ የማያውቅ መሆኑን በመዘርዘር ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በሁዋላ ሁለተኛ አመልካችን /አታሚ ድርጅቱን/ ከክሱ ነፃ ሲያደርገው አንደኛውን አመልካች በተመለከተ ግን ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና ፍሬ ነገር ክርክሮችን ውድቅ በማድረግ አመልካችን ለክሱ ኃላፉ በማድረግ ብር 6ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ /ስልሳ ሺህ/ ለቁሳዊ ጉዲት ካሣ፣ ብር 1ዐዐ,ዐዐዐ.ዐዐ /አንድ መቶ ሺህ/ ለሞራል ካሣ ፣ በድምሩ ብር 16ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ /አንድ መቶ ስልሳ ሺህ/ እንዱከፍለ ፣ የሟች አለቃ አያላው ታምሩን ስራ እንዲያሳትሙና መብቱን ከመጣስ ተግባር እንዱቆጠቡ ፣ የታተሙትና ወደፉት የሚታተሙት መፅሐፍት እንዱወገደ በማለት ወስኗል። ከዚህ በኋላ አንደኛ አመልካች ለክሱ ኃላፉ በመባላቸው ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ሁለተኛ አመልካች ከክሱ ነፃ ተብል በመወሰኑ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም የአሁኑ አንደኛ አመልካች ያቀረቡትን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ሲሰርዘው የተጠሪዎችን ይግባኝ ግን ተቀብል ከአሁኑ ሁለተኛ አመልካች ጋር ከአከራከረ በሁዋላ አመልካችን ያለባለቤቱ ፈቃድ የተጠሪዎችን አውራሽ ፍቶ ግራፍ ከእነፈጠራ ስራቸው በመጽሐፍ አትሞ ማውጣቱ ተረጋግጧል በሚል ምክንያትና የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 27 ፣ 29 እና 2ዐ27 ድንጋጌዎችን በዋቢነት በመጥቀስ ለክሱ ኃላፉ አድርጎ ከአንደኛ አመልካች ጋር በአንድነት እና በነጠላ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተወሰነውን ካሣ እንዱከፍል ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነው። አመልካቾች በተናጥል ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አንደኛ አመልካች ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የአመልካች የመከላከያ ማስረጃዎች ሳይሰሙ ውሣኔ መሰጠቱና ስራው የሟቹ ወጥ ስራ ያለመሆኑን ፣ ሟቹ ስራው ለሕዝብ እንዲይሰራጭ ባለደረጉበት ሁኔታ በቅጅ ሕግ ጥበቃ የሚሰጠው መብት ነው ተብል መወሰኑ ያለግባብ መሆኑን ዘርዝረው ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት ተከራክረዋል።
ሁለተኛው አመልካች ደግሞ አታሚ እንደመሆኑ መጠን ሶስተኛ ወገን እንዱታተም ባቀረበው ጽሐፍ የሚጠይቅበት አግባብ የላለ መሆኑንና ለክሱ መሰረት የሆነው ስራም የሟቹ ወጥ ስራ ሳይሆን ሟቹ የኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ በነበሩበት ጊዜ ቤተክርስቲያንን ወክለው መጽሐፍ ቅደስ እየጠቀሱ ሲያስተምሩ የነበሩት የቤተክርስቲያኗ ስራ መሆኑና ሟቹም ያስተማሩትና መግለጫ የሰጡበት ስራቸው ከሃሣቡ አመንጪ ፈቃድ ውጪ ማባዛት ፣ ማሰራጨት ማተም … ወዘተ የሚል ክልከላም ያስቀሙጡት ሁኔታ የላለ መሆኑን ዘርዝሮ አመልካቹ ለክሱ ኃላፉ መደረጉ ከሕግ ውጪ መሆኑን በመግለጽ ተከራክሯል። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካቾች ለክሱ ኃላፉ ተብለው የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎች ጥሪ ተደረጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆኑት ውሣኔዎችና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሕግ ረገድ እንደሚከተለው ተመልክቶታል።
በመሰረቱ አንድን የፈጠራ ስራ በትክክል ስራ ሉስብለው የሚችለውና ለቅጅ መብት ጥበቃ ብቁ የሚያደርገው ስራው የመጀመሪያ ስራ ወይም በባሕርይው ለየት ያለ ስራ ሲሆን መሆኑ የአዋጅ ቁጥር 410/1996 ይዘትና መንፈስን የሚያስገነዝበን ነጥብ ነው። ስራው የመጀመሪያ ስራ / original/ ወይም ባሕርይው ለየት ያለ ስራ ነው ሉያስብለው የሚችለው ደግሞ ውጤቱ የግለሰብ የፈጠራ ጥረት መሆን ያለበት መሆኑ ይታመናል። ሕጉም ጥበቃ የሚያደርገው የግለሰቡን የፈጠራ ውጤት ነው። የፈጠራ ውጤት መኖሩ መረጋገጥ ደግሞ የፈጠራ ስራ ለቅጅ መብት ብቁ ከሚያደርጉት መመዘኛዎች /መለኪያዎች/ አንደ ሲሆን ጥበቃ የሚደረገው ግለሰቡ ሐሳቡን የገለፀበት ቅርፅ እንጂ ሐሳብ ወይም በፈጠራ ስራው ውስጥ ያለው መረጃ አይደለም። ስለሆነም የሃሣብ አገላለፅ ቅርጽ በቅጅ መብት ጥበቃ የሚደረግለት ሲሆን ሃሣቡ በራሱ ብቻ ግን አይሆንም። የሃሣቡን ይዘት ለላልች መግልፅ የፈጠራ ስራ መብት ጥሰትን የሚያስከትል ሲሆን ላልች ሰዎች ሃሣቡንና መረጃውን የራሳቸው ለየት ያለና ነፃ ስራ ተጠቅመው መገኘት የፈጠራ ስራ ውጤትን እንደመጣስ የማይቆጠር መሆኑን ሕጉ ለጥበቃው ካስቀመጠው መለኪያ ይዘት የምንረዲው ነው። የቅጅ መብት አይነተኛ አላማ ለስነ ፅሁፍ ፣ ኪነ ጥበብ እና ስነ ጥበብ ፈጠራዎች ሕጋዊ ጥበቃ ማድረግ ነው። የሕጉ አጠቃላይ ይዘት ሲታይ በቅድሚያ የቅጅ መብት የሚጏናፀፈት የፈጠራ አመንጪዎች መሆናቸውን ያስረዲል። በቅጅ መብት ውስጥ መብት ተብል የሚታወቁት ደግሞ የኢኮኖሚ መብቶችና የሞራል መብቶች ሲሆኑ በአዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 7 እንደተደነገገው ከኢኮኖሚያዊ መብቶች አንደ ተጥሶ በተገኘ ጊዜ የሞራል ጉዲት ጥሰት የሚኖር መሆኑ ተመልክቷል። አዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 7 የተመለከቱት ኢኮኖሚያዊ መብቶች ደግሞ ከአዋጅ አንቀፅ 9 እስከ 19 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የሥራ አመንጪ ወይም የአንድ ሥራ ባለቤት፡- ሀ/ ሥራን የማባዛት ፣ ለ/ ሥራን የመተርጏም ፣ ሐ/ ሥራን የማመሳሰል ፣ የማቀናበር ወይም ወደ ላላ አይነት የመቀየር መ/ በሽያጭ ወይም በኪራይ ኦርጅናል ሥራን ወይም ቅጂውን የማከፊፈል ሰ/ ኦርጅናል ሥራን ወይም ቅጂውን ከውጭ ሀገር የማስገባት ረ/ ኦርጅናል ሥራን ወይም ቅጂውን ለሕዝብ የማሣየት ሰ/ ሥራን በይፊ የመከወን ሸ/ ሥራን ብሮድካስት የማድረግ ቀ/ ሥራን በልላ መንገድ የማሰራጨት መብቶችን ራሱ ሉፈጽም ወይም ላላ ሰው እንዱፈፅማቸው ለመፍቀድ ብቸኛ መብት ይኖረዋል ተብል አስገዲጅነት ባለው መልኩ ተቀምጧል።
በተያዘው ጉዲይ የ1ኛ አመልካች የተጠሪዎች አባት የፈጠራ ስራ የሆኑትን ፅሐፍች በጋዜጣ እና በመፅሄት ላይ የውጡ ቃለመጠይቆችን ፣ መጣጥፍችን ፣ የሟች የመንፈቅ መታሰቢያ ፕስተር ላይ የወሰደትን የመፅሐፈን የሽፊን ሥእልና የሀዘን መግለጫ ግጥሞችን ጭምር በማሰባሰብ በ2ኛ ተጠሪ ማተሚያ ቤት አማካኝነት “ ትምህርተ ሃይማኖት ” በሚል ርዕስ 1ኛ አመልካች ማሳተሙን ሳይክደ የታተሙት ስራዎች የሟቹ ወጥ ስራዎች ሳይሆኑ ሟቹ በኦርቶድክስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ሁነው ሲሰሩ በቤተክስቲያን ሐይማኖት የነበራቸውን አቋም የገለፁበት እንጂ የራሳቸው ወጥ ስራ አይደለም ፣ 1ኛ አመልካችም ለሕዝብ ከማሰራጨት በሟቹ አልተከለከለም በማለት ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክርክርም ሆነ በዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ባቀረቡት ክርክር የመጽሐፍ ገቢ ለሟች ቤተሰቦች እንዱሆን በማለት በመፅሐፊ መፃፊቸው የተረጋገጠ መሆኑ ሲታይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 83 እና 235 ድንጋጌዎች መሰረት የስራው ፈጠራ ባለቤት የተጠሪዎች አባት መሆናቸውን ማመናቸውን የሚያስረዲ ነው። ስለሆነም 1ኛ አመልካችም ሆነ 2ኛ አመልካች የስራው የፈጠራ ባለቤት የተጠሪዎች አባት መሆናቸውን በግልፅ ሳይክደ መቅረታቸው የተረጋገጠ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ መከላከያ ማስረጃ ያለመሰማቱ የአመልካቾችን የመከላከያ ማስረጃ ማሰማት መብት ያጣበበ ነው ለማለት ስላልተቻል በዚህ ረገድ የቀረበውን ክርክር የምንቀበለው ሁኖ አልተገኘም።
የተጠሪዎች አባት የኦርቶድክስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ በነበሩበት ጊዜ ስለሐይማኖቱ የሰጡትን አስተያየት ማንም ሰው ለማሳተም የሚችልበት አግባብ አለ? ወይስ የለም? የሚለውን ጥያቄ ስንመለከት ደግሞ ሐሳቡ የኦርቶድክስ ቤተክርስቲያን ሐይማኖታዊ ትምህርት ነው ቢባል እንኳ ሟቹ ሐሳቡን የገለፁበት ቅርፅ ግን የራሳቸው የፈጠራ ስራ በመሆኑ በሕጉ ጥበቃ ለማግኘት የሚያስችለውን መመዘኛን ማሟላቱን የክርክሩ ፍሬ ነገሮች የሚያስረደ ስለመሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። ከላይ እንደተገለጸው ሕጉ በዋነኛነት ጥበቃ የሚያደርገው የሐሳቡ አገላለፅ ቅርፅ እንጂ ሃሣቡን ራሱን አይደለም። 1ኛ አመልካች የተጠሪዎች አባት ስለሃይማኖቱ የገለፁበትን የሐሳብ አገለላጽ ቅርጽ ሳይለውጡ ሐሳቡ የተገለፀበትን መንገድ እንዲለ መውሰድና “ ትምህርተ ሐይማኖት ” የሚል ርዕስ በመስጠት ማሳተማቸውና ማሰራጨታቸው አልተካደም።
ይህ ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 410/1996 አንቀጽ 7 የተመለከተውን መብት መጣስ ነው።
አመልካቾች የአዋጁን አንቀጽ 13 በመጥቀስ የሚያቀርቡት ክርክርም ሲታይ ሕጉ ለሕዝብ ስለማሰራጨት እና ማባዛት እንደቅደም ተከተላቸው በአንቀፅ 2/6/ እና 2/25/ ስር የተመለከቱትን ትርጓሜዎችን የሚያሟላ አይደለም። በልላ አገላለጽ የፈጠራ ባለቤት የፈጠራ ስራዎቹን እንዲይሰራጩ አልከለከለም ተብል አንድን የፈጠራ ስራ በመፅሐፍ መልክ ባልታተመበት ሁኔታ በሕግ አግባብ መብት ያላገኘ ሰው ለሕዝብ ትምህርት ነው ብል ማሰራጨት ወይም ማባዛት በአዋጅ አንቀጽ 13/1/ መሰረት የቅጅ መብት ጥሰት አይደለም ልባል የሚችል አይደለም።
በአዋጅ ቁጥር 41ዐ/1996 አንቀጽ 2/6/ እንደተመለከተው ለሕዝብ ማሰራጨት ማለት የአንድ ስራ ክወና ፣ የድምፅ ሪከርድ ወይም ብሮድካስት ምስል ፣ ድምጽ ወይም ሁለቱን በሽቦ ወይም ያለሽቦ ማሰራጨትን የሚመለከት ሲሆን ማባዛት ማለት ደግሞ አንድን ስራ ወይም የድምጽ ሪከርዱንግ በጊዜያዊነት ወይም በቋሚነት የኤላክትሮኒክ ማከማቻን ጨምሮ በማንኛውም አኳኋን ወይም መልክ ስራውን ወይም የድምጽ ሪከርደን በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ቅጅዎች መገልበጥ መሆኑን ደግሞ የአዋጅ አንቀፅ 2/25/ ድንጋጌ በግልፅ ያሳያል።
ከእነዚህ ድንጋጌዎች ጋር ተያይዞ የሚነሳው ድንጋጌ በአዋጅ አንቀፅ 13/1/ የሰፈረ ሲሆን ይዘቱም በዚህ አዋጅ ቁጥር 7/1/ሀ/ ፣ /ሸ/ እና /ቀ/ የተደነገገው ቢኖርም እስከተቻለ ድረስ የስራውን ምንጭና የስራ አመንጪውን ስም መጥቀስ እንደተጠበቀ ሆኖ የቅጅ መብት ባለቤቱ፣ የማባዛት ፣ ብሮድካስት የማድረግ ወይም ለህዝብ የማሰራጨት መብቱ የስራው አመንጪ ወይም የቅጅ ባለመብቱ መሆኑን በቅጅው ላይ በግልጽ የተጠቀሰ ነገር ከላለ በወቅታዊ የኢኮኖሚ ፣ የፕለቲካ ወይም የሃይማኖት ጉዲዮች ላይ በጋዜጣ ፣ በመፅሓት የወጡ ወይም ተመሳሳይ ባህሪ ኖሯቸው ብድሮድካስት የተደረጉ መጣጥፍችን በልላ ጋዜጣ መጽሄት ማባዛት ፣ በብሮድካስቲንግ ወይም በልላ የመገናኛ ብዙሃን ለሕዝብ ማድረሱን ሉከለከል አይችልም ተብል በግልፅ ተደንግጓል።
የተጠሪዎች አባት በሕይወት ዘመናቸው ብዛት ያላቸውን ሐይማኖትን ነክ የሆኑ የፈጠራ ስራዎችን መስራታቸው ፤ የተለያዩ ፅሐፍችን ማዘጋጀታቸውን ፣ በተለያዩ ሚዱያዎች ላይም በመጣጥፍና በቃለመጠይቅ ዙሪያ ስብከቶችን ማዘጋጀታቸውንና የሟቹን የፈጠራ ስራ የሆኑትን ፅሐፍችን በጋዜጣ እና በመፅሄት ላይ ወጡ ቃለመጠይቆችን ፣ መጣጥፍችን ፣ ከሟች የመንፈቅ ዓመት መታሰቢያ ፕስተር ላይ የወሰደትን የመፅሐፍን የሽፊን ሥእልና የሀዘን መግለጫ ግጥሞችን ጭምር በማሰባሰብ በ2ኛ ተጠሪ ማተሚያ ቤት አማካኝነት “ ትምህርት ሃይማኖት ” በሚል ርዕስ ታትሞ መውጣቱ ተረጋግጧል። ከዚህም በግልፅ መረዲት የሚቻለው እነዚህ ስራዎች ለህዝብ መረጃ አገልግልት አላማ የሚባዙና የሚሰራጩ ከሆነ በስራው ባለቤት በወጡበት መንገድ ከሚሆን በቀር በመጽሐፍ መልክ ታትመው የሚባዙበት አግባብ የላለ መሆኑን ከአዋጁ አንቀጽ 13/1/ ድንጋጌ ከህዝብ ስለማሰራጨትና ስለማዛባት ሕጉ ከሰጠው ትርጓሜ ጋር ተዲምሮ ሲነበብ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው።
በአዋጁ አንቀፅ 13/1/ ስር “……. መፅሓት….” የሚለው ቃል “ Periodical ” የሚለውን የእንግሉዝኛ ቃል የሚተካው መሆኑን ሕጉ የሚያሳይ በመሆኑ ይኸው ቃል በማንኛውም መለኪያ መፅሐፍ የሚለውን ቃል አይተካም። ስለሆነም አመልካቾች አዋጅ ቁጥር 410/1996 አንቀጽ 13/1/ ድንጋጌን በመጥቀስ የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የላለው ሁኖ አግኝተናል።
በመሆኑም የተጠሪዎች አባት በድንጋጌው በፉደል “ ሀ ” “ ረ ” እና “ ቀ ” የተመለከተው ወጥ( “ኦርጅናል” ) ሥራን የማባዛት ፣ የማሳተም ወይም በልላ መንገድ የማሰራጨት መብት ተጥሷል። ይኸውም የፈጠራ ስራቸው ከአውራሾች ፈቃድ ውጪ በመጽሐፍ መልክ ታትሞ በገበያ ላይ ውል በሕዝብ መነበቡ ነው። የሟቹ የፈጠራ ስራ ከወራሾቹ ፈቃድ ውጪ በ1ኛ አመልካች አሳታሚነት በመጽሐፍ መልክ ገበያ ላይ ውል መነበቡ ኦርጅናል ሥራውን ወይም ቅጅውን ለሕዝብ ማሳየት/public display of original or copies of the work/ የሚለው በሕጉ የተመለከተው የሟች ወራሾች መብት ተጥሷል ማለት ነው። ይህ መብት ተጥሶ የሞራል ጉዲት በደረሰ ጊዜ የካሣው መጠን በአዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 34/4/ መሰረት ከ1ዐዐ,ዐዐዐ/አንድ መቶ ሺህ ብር / የማያንስ የገንዘብ ካሣ ሉከፍል እንደሚገባ ተመልክቷል። በዚህ መሰረት በተጠሪዎች ላይ የደረሰውን የህሉና ጉዲት ሞራል ካሣ 1ኛ አመልካች በተጠቀሰው አዋጅ መሰረት 1ዐዐ,ዐዐዐ/አንድ መቶ ሺህ ብር / የመክፈል ግዳታ ይኖርበታል።
ሁለተኛው አመልካች ከላይ የጠቅስናቸውንና ተቀባይነት የላላቸው የሕግ ክርክሮችን ከማንሳቱም በተጨማሪ በአታሚነቱ የሚጠየቅበት አግባብ የላለ መሆኑን ጠቅሶ ተከራክሯል። የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ አመልካችን ለክሱ ኃላፉ ያደረገው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 27 ፣ 29 ፣ 2027 ድንጋጌዎችን በመጥቀስ ነው። ይኸው ፍርድ ቤት ሁለተኛ አመልካች በአከራካሪው መፅሐፍ የሟች አለቃ አያላው ታምሩን ፍቶ ግራፍ ለጥፍ ማውጣቱን ፣ አሳታሚው አንደኛው አመልካች የሟቹን ፍቶ ግራፍ አትሞ ለማውጣት በቅድሚያ ስለመወከለ ወይም ይህንን ለማድረግ ስልጣን ያለው መሆኑን ሁለተኛ አመልካች ያለማጣራቱን ፍቶውን የያዘው መፅሐፍ በገበያ ላይ መሰራጩቱን በፍሬ ነገር ደረጃ አረጋግጧል። ሁለተኛ አመልካችም እነዚህን ፍሬ ነገሮችን አልካደም። እንዱህ ከሆነ ሁለተኛ አመልካች በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 27/ ፣ 29 እና 2ዐ27 ድንጋጌዎች የማይጠየቅበት የሕግ አግባብ የለም። በመሆኑም አመልካቾች ለጉዲዩ በአንድነትና በነጠላ ኃላፉ ናቸው ተብል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአሁኑን አንደኛ አመልካችን በተመለከተ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 16 ቀን 2ዐዐ3 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ የካቲት ዐ4 ቀን 2ዐዐ3 ዓ/ም በትዕዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
ሁለተኛ አመልካችን በተመለከተ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ሚያዚያ 12 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
አመልካቾች ብር 6ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ /ስልሳ ሺህ/ ለቁሳዊ ጉዲት ካሣ ፣ ብር 1ዐዐ,ዐዐዐ.ዐዐ /አንድ መቶ ሺህ / ለሞራል ካሣ ፣ በድምሩ ብር 16ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ/አንድ መቶ ስልሳ ሺህ/ እንዱከፍለ፣ የሟች አለቃ አያላው ታምሩን ስራ እንዲያሳትሙና መብቱን ከመጣስ ተግባር እንዱቆጠቡ፣ የታተሙትና ወደፉት የሚታተሙት መፅሐፍት እንዱወገደ ተብል መወሰኑ ባግባቡ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ ብለናል።
በዚህ ችልት በመ/ ሐምል 2ዐ ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል። ለሚመለከታቸው አካላት ይፃፍ ብለናል።
መዝገቡን ዘግተናል፣ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.