No summary available.
ታህሳስ 17 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሤ አመልካች፡- ኢንጅነር አድማሱ ገብሬ (ገብሬ አድማሱ) ጠበቃ ገንዘቡ ገ/አምላክ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ዐቃቤ ህግ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የወንጀል ክስ ሲሆን የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በተጠሪ ከሣሽነት ነው። ቀርቦ የነበረው ክስ ተከሣሽ የብሩክ ፉልምስ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ባለቤት ከሆኑት የግል ተበዲይ አቶ ብሩክ መክብብ ጋር መንተዮቹ የሚል ርዕስ ያለው የአማርኛ ፉልም ለመሥራት ተዋውለው ሳለ የግል ተበዲይ ሳያውቁ በግል ተበዲዩ (ፔሮዱዩሰሩ) የተሰራውን ፉልም ከተጠናቀቀ በኋላ ከግል ተበዲይ ሰራተኞች ጋር በመመሳጠር ከተቀበለ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በማምጣቱ እና ርዕሱን በመቀየር ‹‹ለአባቷ›› የሚል ርዕስ በመስጠት የፉልሙ ባለቤት ሳይሆን የፉልሙ ባለቤት በመምሰል ለህዝብ እይታ በማቅረብ የቅጅና ተዘማጅ መብቶችን ለመጠበቅ የወጣውን አዋጅ ቁ.
410/96 አንቀጽ 7(1)(ሀ) እና 36(1) ሥር የግል ተበዲይን የኢኮኖሚ መብት በመጣስ ተከሰዋል የሚል ነው።
ተከሣሹ የቀረበበትን ክስ በመካድ የተከራከረ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት በዚሁ በተከሰሰበት ወንጀል ሥር ጥፊተኛ ነው በማለት የጥፊተኝነት ውሣኔ ከሰጠ በኋላ አመልካች በ2 ዓመት ከ6 ወራት እሥራት እንዱቀጣ ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘቱ ይግባኙን ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ጉዲዩ ያስቀርባል በማለት ካከራከረ በኋላ የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በማጽናት ውሣኔ ሰጥቷል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ የግራ ቀኙን ክርክር በጽሐፍ ሰምተናል። ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመረውም አመልካች በተከሰሰበት የወንጀል ድንጋጌ ጥፊተኛ ተብል የተቀጣው በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ ተይዞ ጉዲዩ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ መሰረት ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ በአሁኑ አመልካች እና የግል ተበዲይ መካከል የውል ግንኙነት ያለ ስለመሆኑ፣ በዚሁ የውል ግንኙነት መሰረት የግል ተበዲይ በአመልካች የሚቀርብለትን ድርሰት ወደ ፉልም ለመቀየር የተስማሙ ስለመሆኑ፣ በዚህ ስምምነት መሰረት ለመልካች ለሥራው ብር 800,000 ሉከፍልና የግል ተበዲይ ደግሞ ፉልሙን በማጠናቀቅ ለአመልካች የሚያስረክብና አመልካችም የፉልሙ ባለቤት እንደሚሆን የተሰማሙ ስለመሆኑ በበታች ፍ/ቤቶች በፍሬ ነገር የተረጋገጡ ነጥቦች ናቸው።
በልላ በኩል በግራ ቀኙ መካከል በዚሁ የውል ግንኙነት መሰረት ያደረገ የፍትሐብሕር ክርክር እስከዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ታይቶ በመዝ.ቁ. 69247 ላይ እልባት ያገኘ ሲሆን አመልካች የፉልሙ ባለቤት ነው በማለት የግልግል ዳኞች የሰጡት ውሣኔ እና በፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት የፀደቀው የውሣኔ ክፍል በዚህ የሰበር ሰሚ ችልትም ያልተነካ መሆኑን ተገንዝበናል። በዚሁ የፍትሐብሕር ጉዲይ አከራካሪ ከሆነው ፉልም ግራ ቀኙ ያላቸው መብትና ግዳታ ምን እንደሆነ የተመለከተ ሲሆን ከሥራውም የሚገኘውን ትርፍ የሚከፊፈለበትን አግባብ በተመለከተ ውሣኔ የተሰጠበት ስለመሆኑ ተገንዝበናል።
ከላይ የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ይዘን የወንጀል ኃላፉነት ለያቋቁሙ የሚችለ ተግባራት ስለመፈፀማቸው መመልከቱ ተገቢ ይሆናል። በዚሁ መሰረት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 23(2) መሰረት አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለው ወንጀለን የሚያቋቋሙት ሕጋዊ፣ ግዙፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ እንደሆነ ይደነግጋል። በዚሁ መሰረት አመልካች የተከሰሰበት የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁ.410/1996 አንቀጽ 7(1)(ሀ) መሰረት ለሥራው ባለቤት የተሰጠን ተግባር ባለቤት ሣይሆን ባለቤት በመምሰል ፈጽሟል በሚል ሲሆን አመልካች የፉልሙ ባለቤት ስለመሆኑ የግራ ቀኙ የተሰማሙበትን ውል መሰረት በማድረግ የግልግል ዳኞች የሰጡት ውሣኔ አልተሻረም። አመልካች የፉልሙ ባለቤት በተባለበት ሁኔታ ደግሞ የዚህ የወንጀል ህግ ድንጋጌ ተጥሷል ማለት አይቻልም። በልላ በኩልም ባለቤት የሆነ ሰው ፉልሙን በእጁ አድርጎ መገኘቱ ከዚሁ ባለቤት ነኝ ከሚል ሃሣብ የተነሣ ከመሆኑ ባሻገር የወንጀል ተግባር ወይም የግል ተበዲይን የኢኮኖሚያዊ መብት በመጣስ ሃሣብ የፈጸመ ስለመሆኑ የወንጀል ሞራላዊ ፍሬ ነገር ስለመረጋገጡ የተደነገጉት የወንጀል ህግ ከአንቀጽ 57 እስከ 59 ደረስ ያለት ድንጋጌዎች አያመለከቱም። በዚሁ መሰረት አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት የወንጀል ድንጋጌ ሥር የሞራላዊም ሆነ የህግ ፍሬ ነገሮች ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በመሆኑ ጥፊተኛ ተብል መቀጣቱ አግባብነት የላለውና ወንጀለን የሚያቋቁሙ ፍሬ ነገሮች ባልተሟላበት በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ባጠቃላይ በአመልካችና በግል ተበዲይ መካከል ያለው ግንኙነት የውል አፈፃፀምን የሚመለከት የፍትሐብሓራዊ ባህሪይ ያለው በመሆኑ አመልካች በተከሰሰበት የወንጀል ድንጋጌ ሥር ሕጋዊ ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ጥፊተኛ ተብል መቀጣቱ አግባብነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ 1/ የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ. 59998
No topics extracted.