No summary available.
ሐምል 30 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካቶች፡- 1- ወ/ሮ ንግስት ኪዲኔ አልቀረቡም 2- አቶ ዐቁባይ ሚካኤል ገብረየሱስ ቀረቡ ተጠሪ፡- 1- አቶ በለጠ ወልደሰማያት ቀረቡ 2- አቶ ገብረ እግዚአብሓር ሐዱስ ከጠበቃቸዉ ከአቶ ሐጏስ አብርሃ ጋር ቀረቡ መዝገቡ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ በአሁን የሰበር አመልካቾች ከሣሽነት የተጀመረው በፋ/ከ/ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪዎች ደግሞ ተከሣሾች ነበሩ። ከሣሾች ሰኔ ዐ9 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ባቀረቡት ክስ በቀድሞ ወረዲ 2ዐ ቀበላ 29 በአሁኑ አጠራር በቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበላ ዐ8/09 የሚገኘውን ቁጥሩ 486 የሆነውን የግል ቤታችንን ከሣሾች በ1992 ዓ.ም. ከሀገር ስንወጣ ለ1ኛ ተከሣሽ ውክልና በመስጠት የሄድን ቢሆንም 1ኛ ተከሣሽ ቤቱን የማስተዲደር እንጂ የመሸጥና የመለወጥ ስልጣን ሳይሰጣቸው ለ2ኛ ተከሣሽ የሸጡ ስለሆነ የሽያጭ ውለ ፈርሶ ቤቱን እንዱያስረክቡን ፣ ያለአግባብ የበለጸጉበትን በወር ብር 3ዐዐዐ ስላት ብር 72,ዐዐዐ ከነወለደ እንዱከፍለ ፣ ወደፉትም የሚኖረውን ውዝፍ ገንዘብ ተከሣሾች በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ ፣ ቤቱን መመለስ የማይቻል ከሆነ ደግሞ 1ኛ ተከሣሽ ብር 1,25ዐ,ዐዐዐ እንዱከፍለ ይወሰንልን ብለዋል።
ተከሣሾችም ክሱ በፍ/ህ/ቁ 1810 መሰረት በይርጋ የሚታገድ ነው በሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በአማራጭ በፍሬ ነገሩ ላይ መልስ ሰጥተዋል። ከሣሾችም ለይርጋ መቃወሚያው በሰጡት መልስ በፍ/ህ/ቁ 1810 የተጠቀሰው ይርጋ ተፈጻሚነት ሉኖረው የሚችለው በፍ/ህ/ቁ 171ዐ/2/ መሰረት በተንኮል፣ በማሳሳት፣ በሀይል ወይም በእድሜ መግፊት እና ከመጃጀት ጋር ተያይዞ የተፈጸሙ ውልች እንዱፈርሱ በሚል ለሚቀርብ ክርክር ሲሆን የከሣሾች ክስ ግን ከዚህ የተለየ በመሆኑ ለዚህ ክርክር አግባብነት የለውም። በእኛ እምነት ለዚህ ጉዲይ ተፈጻሚነት ያለው የፍ/ህ/ቁ 1845 ይርጋ ሲሆን ሽያጩን ካወቅነው ደግሞ ሁለት ዓመት ያልሞላው ስለሆነ ክሱ በይርጋ የሚታገድ አይደለም በሚል ተከራክረዋል።
ጉዲዩን የመረመረው የፋ/ከ/ፍርድ ቤትም በሰጠው ብይን 1ኛ ከሣሽ ለ1ኛ ተከሣሽ ከሰጡት ውክልና ስልጣን ተከሣሹ አልፍ የከሣሽ ንብረት የሆነውን መኖሪያ ቤት የሸጠ በመሆኑ ለጉዲዩ ስለውልች በጠቅላላው ክፍል የተደነገጉት የይርጋ ድንጋጌዎች አግባብነት የላቸውም። በወካይና በተወካይ መካከል ለሚፈጠር አለመግባባት ወይም ከዚሁ ጋር በተያያዘ ክስ ለማቅረብ ቢፈለግ አግባብነት ያለው የይርጋ ጊዜ በፍ/ህ/ቁ 2187 የተደነገገው ሲሆን በዚሁ ድንጋጌ መሰረትም ክሱ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ ይኖርበታል። ሆኖም በተያዘው ጉዲይ ቤቱ ከተሸጠ ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ በውክልና ምክንያት በተሰራ ሥራ የሽያጭ ውለ እንዱፈርስ በሚል የቀረበ ክስ በመሆኑ በይርጋ የሚታገድ ነው ነው ብሎል።
ጉዲዩን በይግባኝ የመረመረው የፋ/ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም የግራ ቀኙን ወገን ካከራከረ በኋላ የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ብይን በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት አጽንቷል።
የሰበር አቤቱታም የቀረበው በከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይንና በፋ/ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን አመልካቾች የጠቀሱት የቅሬታ ነጥብም፡- ከ199ዐ ዓ.ም. ጀምሮ ከአገር ውጪ ስንኖር የነበርን ሲሆን ቤቱ መሸጡን ያወቅነው 2ኛ አመልካች ከወጪ ሀገር ከተመለስኩ ከሰኔ ዐ7/2002 ዓ.ም. ጀምሮ ሆኖ እያለና ይህን ጊዜ ተጠሪዎች ሳያስተባብለ አግባብነት የላለውን በፍ/ህ/ቁ 1810 የተደነገገውን የሁለት ዓመት ይርጋ በመጥቀስ ክሱ በይርጋ ይታገዲል በሚል የክስ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን ከፍተኛው ፍርድ ቤትም ተጠሪዎች ያላነሱትን በፍ/ህ/ቁ 2187 የተደነገገውን የሁለት ዓመት ይርጋ በመጥቀስ ክሱ በይርጋ ይታገዲል ሲል መዝገቡን በብይን የዘጋውና የፍደራል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም ያጸናው ያለአግባብ ነው የሚል ነው።
1ኛው ተጠሪ በሰጡት መልስ በጊዜው በነበረው አጠራር የክልል 14 መስተዲድር በ18/08/1992 ዓ.ም ከአገር የወጡ ኤርትራዊያን ንብረት በሰጡት ውክልና መሰረት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተወካዮቹ መሸጥ እንደሚችለ ለውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ባስተላለፈው የመንግስት መመሪያ መሰረት ከራሴ ፈቃድ ውጪ ሽያጩን የፈጸምኩ ስለሆነና ሽያጩም ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ 11 ዓመታት ስላለፈት ፍርድ ቤቶች ክሱ በይርጋ የሚታገድ ነው ሲለ የወሰኑት ተገቢ ነው በከፍተኛው ፍርድ ቤት የይርጋ መቃወሚያ ሳቀርብ ጠቅሼ ያቀረብኩት በፍ/ህ/ቁ 1810 የተደነገገውን የሁለት ዓመት ይርጋ ቢሆንም በ1ኛ አመልካችና በእኔ መካከል የነበረውን የወካይና ተወካይ ግንኙነት መነሻ በማድረግ አመልካቾች ቤቱን የሸጠው ቤቱን ለመሸጥ የሚያስችለው ውክልና ሳይሰጠው ነው በሚል ላቀረቡት ክርክር ፍርድ ቤቶቹ አግባብነት ያለው ይርጋ በፍ/ህ/ቁ 2187 የተጠቀሰው የሁለት ዓመት ይርጋ ነው በሚል ክሱ በዚሁ በሁለት ዓመት ጊዜ ወስጥ ያልቀረበ ነው ሲለ ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢ ነው፣ አመልካቾች ሽያጩን ያወቅነው ሰኔ ዐ7 ቀን 2ዐዐ2 ነው ቢለም ይህን አባባላቸውን በማስረጃ አስደግፈው ለፍርድ ቤቶች ስላላቀረቡ ተቀባይነት የለውም ሲለ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ብይን/ ውሣኔ እንዱጸና ጠይቀዋል።
2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው የኤርትራዊያን ቤት ለኢትየጵያዊያን እንዱሸጥ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት በመወሰኑ የኤርትራ መንግስት ሚዱያዎች ፣ የሰብአዊ መብት ተቋማት ፣ የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን እና ላልች ወገኖች በግልጽ ሲሟገቱበት የቆየ የአደባባይ ሚስጥር ስለሆነና አመልካቾችም ይህን የአካባቢ ሁኔታ በግልጽ የሚያውቁት ጉዲይ ነው። በመሆኑም የሚያከራክረውን ቤት ሚያዚያ 1992 ዓ.ም ገዝቼ ስመ ሀብቱም ተዛውሮልኝ ይዤ የምገኝ ሲሆን ይህንኑ ቤት ለመረከብ አመልካቾች ያቀረቡት ክስም በሁለት ዓመት ውስጥ ያልቀረበ በመሆኑ ክሱ በፍ/ህ/ቁ 2187 መሰረት በይርጋ ይታገዲል ሲለ ፍርድ ቤቶቹ የሰጡት ብይን/ውሣኔ ተገቢነት ያለው ነው፣ ይህ ቢታለፍ ቤቱ ከተሸጠበት ጊዜ አንስቶ ክስ እስከቀረበበት ያለው ጊዜ ሲቆጠር 1ዐ ዓመት ያለፈው በመሆኑ ክሱ በፍ/ህ/ቁ 1845 መሰረት በይርጋ የሚታገድ ነው ሲለ ተከራክረዋል። በዚህ ችልት ደረጃም የግራ ቀኙ ወገኖች በቃል ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከዚህ በላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም፡- አመልካቾች ያቀረቡት ክስ በይርጋ የሚታገድ ነው ሲለ ፍርድ ቤቶቹ ክሱን ወድቅ ያደረጉት በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም?
የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
ከክርክሩ መገንዘብ የተቻለው የሚያከራክረው ቤት የተመዘገበው በ1ኛ የሰበር አመልካች ስም መሆኑንና 1ኛ አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ ቤቱን እንዱያስተዲድሩ ውክልና ሰጥተው ከ2ኛ አመልካቾች ጋር ወደ ኤርትራ ሀገር በ199ዐ ዓ.ም. ሄደው እያለ 1ኛ ተጠሪ ለ2ኛ ተጠሪ ሚያዚያ ዐ5 ቀን 1992 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ውል ቤቱን መሸጣቸውን ነው። አመልካቾችም በክሳቸው ሽያጩን በመቃወም እንዱፈርስ ሰኔ ዐ9 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ክስ ያቀረቡት 1ኛ ተጠሪ ቤቱን የማስተዲደር እንጂ የመሸጥና የመለወጥ ስልጣን ሳይሰጣቸው ለ2ኛ ተከሣሽ ሸጠዋል በሚል ነው። አመልካቾች ቤቱ የተሸጠ መሆኑን ያወቁት 2ኛ አመልካች ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሱ በሰኔ ዐ7/2002 ዓ.ም መሆኑን በክሳቸው ከመጥቀሳቸውም በላይ በቃል ክርክር ጊዜም በዚሁ በተጠቀሰው ቀን ሽያጩን እንዲወቁ በመግለጽ ተከራክረዋል። ተጠሪዎችም ክሱን ለመቃወም በዋናነት የጠቀሱት የይርጋ ህግ የፍ/ህ/ቁ 181ዐ ሲሆን ፍርድ ቤቶቹ ግን በወካይና በተወካይ መካከል ለሚፈጠር አለመግባባት ወይም ከዚሁ ጋር በተያያዘ አግባብነት ያለው የይርጋ ጊዜው በፍ/ህ/ቁ 2187 የተደነገገው ነው በሚል ክሱ በሁለት ዓመት ይርጋ ይታገዲል ማለታቸውን ከክርክሩ መረዲት ይቻላል። በመሆኑም የግራ ቀኙን ወገኖችን ለሚያከራክረው ጉዲዩ አግባብነት ያለው የይርጋ ህግ ድንጋጌ የትኛው እንደሆነ መለየት ተገቢነት ያለው ነው።
እንደራሴው በፈጸመው ውል ምክንያት የሿሚውና የእንደራሴው ጥቅሞች የሚቃወሙ የሆኑ እንደሆነ ይህን ውል የፈረመው 3ኛ ወገን ይህን ሁኔታ ያወቀና ሉያውቀው የሚገባ የሆነ እንደሆነ በሿሚው ጥያቄ መሰረት ውለ ሉፈርስ እንደሚችል በፍ/ህ/ቁ 2187/1/ የተመለከተ ሲሆን በሿሚውም ውለን ለማፍረስ ክስ ሉያቀርብ የሚችለው የዚሁ አካባቢ ሁኔታ ስለመኖሩ ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ መሆን እንዲለበት የዚሁ ቁጥር ንዐስ ቁጥር 2 ይደነግጋል። ውክልና ተወካዩ ለወካዩ እንደራሴ ሆኖ አንድ ወይም ብዙ ህጋዊ ስራዎችን በወካዩ ስም ለማድረግ የሚደረግ ስምምነት ስለመሆኑ የፍ/ህ/ቁ 2198 የሚስገነዘብ ሲሆን ይህም ስምምነት ወካዩ የውክልና ስራ በሚፈጽምበት ጊዜ የወካዩን ህጋዊ ሁኔታዎች የመለወጥ ስልጣን የሚሰጠው በመሆኑ ተወካዩ የውክልናውን ስልጣን ተጠቅሞ ሲሰራ ለወካዩ ጥቅም ፍፁም ታማኝና በስራው ሁለ የወካዩን ጥቅም ብቻ የማስጠበቅ ግዳታ አለበት። ስራውን በሚያከናውንበት ጊዜም ይህንን ለወካዩ ፍፁም የሆነ ታማኝነትና ሙለ ለሙለ ለወካዩ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚከለክለው ፍላጎት ወይም ታማኝነቱን የሚከፊፍል ሁኔታ የሚያስከትል የጥቅም ግጭት ሲፈጠር ተወካዩ ለስራው አፈጻጸም ጥንቃቄ ሉያደርግ ይገባል። በመሆኑም እንደራሴው የውክልና ሥልጣኑን በሚያከናውንበት ጊዜ ተቃዋሚ ጥቅሞችን የማስወገድ ግዳታ አለበት።
በዚህ በተያዘው ጉዲይ ግን በወካይና በተወካይ መካከል የጥቅም ግጭት ያለ ስለመሆኑ አመልካቾች በክሳቸው ከላመግለጻቸውም ላላ በቃል ክርክር ወቅትም በ1ኛ ተጠሪና በሿሚዋ መካከል የጥቅም ግጭት ስለመኖሩ ያለት ነገር የለም። በመሆኑም ፍርድ ቤቶቹ 1ኛ ተጠሪ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በፈጸመው ውል ምክንያት የሻሚውና የ1ኛ ተጠሪ የጥቅም ግጭት ስለመኖሩ አመላካች ነገር ባልተገኘበት ሁኔታ ከጉዲዩ ጋር አግባብነት የላለውን የፍ/ህ/ቁ 2187/2/ የተመለከተውን ይርጋ ለብይኑ / ለውሣኔ መሰረት ያደረጉት ተገቢነት ያለው አይደለም።
ተጠሪዎች በዋናነት ወዲነሱት የፍ/ህ/ቁ 181ዐ ይርጋ ስንመለስ አንድ ውል በሚመሰረትበት ጊዜ የችልታ ወይም የፈቃድ ጉድለት ያለበት ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ ችልታ አልነበረኝም ወይም ፈቃዳን በአግባቡ አልሰጠሁም በሚለው ተዋዋይ ወገን ጠያቂነት ብቻ ውለ ሉፈርስ እንደሚችል፣ እንደዚሁም ውለ የተደረገበት ጉዲይ ለህግ ወይም ለሞራል ተቃራኒ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜና የውለ አጻጻፍ ሥርዓትም ባልተጠበቀበት ወቅት ከተዋዋይ ወገኖች መካከል ወይም በሙለ ጥቅም አለኝ በሚል 3ኛ ወገን አማካይነት የውል ይፍረስልኝ ጥያቄ ቀርቦ ሉፈርስ እንደሚችል በፍ/ሕ/ቁ 18ዐ8/1/ ተደንግጓል። የውል ይፍረስልኝ ክስ ማቅረቢያ ጊዜን በተመለከተ ውለ የማይረጋበት ምክንያት ከቀረበት ጊዜ አንስቶ በሁለት ዓመት ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን በፍ/ህ/ቁ 181ዐ ተጠቅሷል። ይህን የይርጋ ድንጋጌ በተመለከተ ይህ ችልት በሰበር መ/ በሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም ተፈጻሚነቱ ውለ የማይረጋበት ምክንያት ቀሪ በሚሆንበት ጊዜ ሲሆን ይህም የሚመለከተው ከአንደኛው ተዋዋይ ወገን ችልታ ወይንም ፈቃድ ጉድለት ጋር ተያያዘ መሆኑን በፍርደ ላይ አስፍሯል። በዚሁ መሰረትም ውለ በችልታ ማጣት ወይንም በፈቃድ ጉድለት እንዱፈርስ የሚጠይቅ ወገንም በሁለት ዓመት ውስጥ ክሱን ካላቀረበ በዚሁ በተጠቀሰው የፍ/ህ/ቁ 181ዐ ይርጋ መሰረት የሚታገድ ይሆናል።
በዚህ በተያዘው ጉዲይ ግን አመልካቾች ውለ እንዱፈርስ የጠየቁት 1ኛ አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን በሙለ እንዱጠብቁ ፣ እንዱቆጣጠሩ ፣ ክፍያዎችን ተሳስበው እንዱከፍለ በአጠቃላይ ንብረቶቹን በተመለከተ በመንግስታዊ መ/ቤቶችና በህዝባዊ ድርጅቶች እየቀረቡ ጉዲዮችን እንዱፈጽሙና እንዱያስፈጽሙ እንጂ ንብረቹን እንዱሸጡ ሥልጣን ሳይሰጣቸው በህገወጥ መንገድ ለ2ኛ ተጠሪ ሽጠዋል በሚል ነው። በመሆኑም አመልካቾች ውለ እንዱፈርስ ዲኝነት የጠየቁት የችልታ ወይም የፈቃድ ጉድለትን መሰረት አድርገው ሳይሆን የውለን ሕገ ወጥነት በመጥቀስ ስለሆነ ተጠሪዎች ለክርክራቸው መሰረት ያደረጉት በፍ/ህ/ቁ 1810 የተደነገገው የሁለት ዓመት ይርጋ አግባብነት የለውም።
ለዚህ ጉዲይ የፍ/ሕ/ቁ 1810 እና 2187/2/ ይርጋ አግባብነት የላቸውም ከተባለ ጉዲዩን ስለውልች በጠቅላላው በተደነገገው ክፍል በሚገኘው በፍ/ህ/ቁ 1845 መሰረት መመርመር ተገቢ ይሆናል።
በፍ/ህ/ቁ 1845 ድንጋጌ መሰረት ህግ በልላ አኳን ካልወሰነ በቀር ውለ እንዱፈጸም ወይም ከላመፈጸሙ የተነሳ ስለሚደርስ ጉዲት ወይም ውለ እንዱፈርስ መብት ያለው ወገን መብቱን በ1ዐ ዓመት ውስጥ ካልጠየቀ መብቱ ቀሪ እንደሚሆን በግልጽ የተጠቀሰ ሲሆን አመልካቾችም የሽያጭ ውለ 1ኛ ተጠሪ ቤቱን ለማስተላለፍ በፍ/ህ/ቁ 2205 መሰረት ልዩ ውክልና ሳይሰጣቸው የፈጸሙት ውል በመሆኑ ውለ ህገ ወጥ ነወ እስከሚለ ድረስ ይህንኑ ህገወጥ ነው የሚለትን ውል እንዱፈርስ ክስ ማቅረብ የሚችለት በ1ዐ ዓመት ጊዜ ውስጥ ስለሚሆን የግራ ቀኙን ተከራካሪዎች የይርጋ ክርክር ለመወሰን አግባብነት ያለው ይሄው የ1ዐ ዓመት የይርጋ ጊዜ ነው።
ይርጋው የሚቆጥርበትን መነሻ ጊዜን በተመለከተም አመልካቾች የቤቱን ሽያጭ ያወቅነው ሰኔ ዐ7 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ነው በሚል የሚከራከሩ ሲሆን ተጠሪዎች ደግሞ ቤቱ የተሸጠው በሚያዚያ ወር 1992 ዓ.ም በመሆኑ ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ ምንም እኳን አመልካቾች ከሀገር በ199ዐ ዓ.ም የወጡ ቢሆንም ከነበሩበት ከኤርትራ መንግስት ሚዱያዎች ፣ የሰብአዊ መብት ተቋማት ፣ የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን እና ላልች ወገኖች በግልጽ ስለንብረታቸው የሚያውቁት ጉዲይ ነው ብለዋል። ሆኖም እነዚህ የተጠቀሱት ምንጮች 1ኛ ተጠሪ ቤታቸውን የሸጡባቸው ስለመሆኑ ያሣውቃለ ወደሚለው ድምዲሜ የሚያደርሱ አይሆንም። በመሆኑም ተጠሪዎች በዚህ ረገድ ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም።
በልላ በኩል 1ኛ የሰበር አመልካች እስካሁን ድረስ በውጪ ሀገር የሚኖሩ ስለመሆናቸው ክርክሩ የሚያመለክት ሲሆን 2ኛ ተጠሪም ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ሰኔ ዐ7 ቀን 2002 ዓ.ም መሆኑን የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች በከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ካደረጉት ክርክር የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። በመሆኑም ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ ሲቆጠርም አመልካቾች ውለ እንዱፈርስ ክስ ያቀረቡት በፍ/ህ/ቁ 1845 የተደነገገው የ1ዐ ዓመት የይርጋ ጊዜ ከማለፈ በፉት ነው። ይህ ሆኖ ሳለ ፍርድ ቤቶቹ ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን በፍ/ህ/ቁ 2187/2/ የተደነገገውን የይርጋ ጊዜ በመጥቀስ አመልካቾች ያቀረቡት ክስ በሁለት ዓመት ውስጥ ያልቀረበ በመሆኑ በይርጋ የሚታገድ ነው ሲለ የሰጡት ብይን /ውሣኔ ይህ ችልት በሰበር መ/ በፍ/ህ/ቁ 181ዐ እና 1845 የተደነገጉትን የይርጋ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት በተመለከተ የሰጠውን አስገዲጅ የህግ ትርጉም መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ብይኑ/ ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ በማግኘታችን ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
በዋለው ችልት የሰጠውን ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ሽረናል።
ለጉዲዩ አግባብነት ያለው የይርጋ ጊዜ በፍ/ህ/ቁ 1845 የተደነገገ ሲሆን በዚሁ የይርጋ ድንጋጌ መሰረት አመልካቾች ያቀረቡት ክስ የክስ ማቅረቢያ 1ዐ ዓመት ከማለፍ በፉት የቀረበ ስለሆነ ክሱ በይርጋ የሚታገድ አይደለም ብለናል። በመሆኑም የፋ/ከ/ፍርድ ቤት በፍሬ ጉዲይ ላይ የግራ ቀኙን ወገን በማከራከርና ማስረጃዎችን ሰምቶ በመመዘን የበኩለን ፍርድ እንዱሰጥበት ክርክሩን በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 341/1/ መሰረት መልሰናል።
የዚህን ፍርድ ቤት ወጪና ኪሣራ የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.