No summary available.
ሐምል 20 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፉሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሪት አሉያት ይማም ሙዘይን - ጠበቃ የሺጥላ አሰፊ ቀረበ መልስ ሰጭ፡- አቶ እምነቴ እንደሻው - አልቀረቡም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፣ መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የአሁን አመልካች ወኪል ናቸው በተባለት እና በአሁን ተጠሪ መካከል ተደረገ የተባለው የቤት ሽያጭ ውል አመልካችን ሉያስገድድ የሚችልበት አግባብ አለ ወይስ የለም?
የሚለውን ነጥብ ለይቶ ለመወሰን ሲባል የቀረበ ነው።
የጉዲዩም መነሻ የአሁን ተጠሪ በአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከሳሽ ሆነው በአሁን አመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ ሲሆን፤ ይዘቱም፣ የአሁን አመልካች በወኪሎ አማካኝነት በ1994 ዓ.ም በተደረገ ውል በአዋሳ ከተማ በቀድሞ ከፍተኛ 02 ቀበላ 04 ክልል በካርታ የምስክር ወረቀት ቁጥር 5045 የሚታወቀውን እና በ3000 ካ.ሜትር ያረፈውን ቤት በብር 300,000 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) ሽጠውልኛል። በዚህም የሽያጭ ውል መሰረት ብር 95,000.00 (ዘጠና አምስት ሺህ ብር) ውለ በተደረገበት ዕለት ወስደዋል። ብር 20,000.00(ሃያ ሺህ ብር) ደግሞ የካቲት 30 ቀን 1994 ወስደዋል። ስለዚህ ቀሪውን 185,000,00 ተቀብለው እንደውለ እንዱፈጽሙ ይደረግልኝ የሚል ነው። የአሁን አመልካችም በተከሳሽነት በሰጡት መልስ የቤት ሽያጭ ውል ፈጸመ ለተባለው አባቴ ውል ተፈጸመ በተባለበት ጊዜ የሰጠሁት የውክልና ሥልጣን የለም ስለዚህ በ1994 ዓ.ም.
የሰጠሁት ውክልና ስለላለ የሸጥኩትም ሆነ የተቀበልኩት ገንዘብ የለም። አይመለከተኝም የሽያጭ ውል ነው የተባለው በቅንብር እንደተመዘገበ ለማስመሰል የተደረገ እንጂ በአዋዋይ ፉት የተደረገ አይደለም። ተሸጠ የተባለው ቤት አዋሳ ከተማ ስለሚገኝ ሉመዘገብ የሚችለው በዚሁ ከተማ አስተዲደር ሥር በሚገኘው መዝጋቢ አካል እንጂ በሲዲማ ዞን ፍትህ መምሪያ ላሆን አይችልም ይህ ተመዘገበ የተባለውም የሲዲማ ዞን ፍትህ መምሪያ በቁጥር 1304/2003 በተፃፈ ደብዲቤ ይህ ውል በህጋዊ መንገድ የተመዘገበ ውል ነው ለማለት የማይቻል መሆኑን ገልፆ ማረጋገጫ ሰጥቶበታል። ስለሆነም እኔ ለአባቴ የውክልና ሥልጣን ከሰጠሁበት ከጥር 14 ቀን 1995 ዓ.ም በፉት የሽያጭ ውለ ተደርጓል ስለተባለ እኔ ባልሰጠሁት የውክልና ሥልጣን ተደረገ በተባለው ረቂቅ ውል እና በሐሰት ተመዝግቧል የተባለው ውል እኔን የማይመለከተኝ ስለሆነ ከወጭና ኪሳራ ጋር እንድሰናበት ይደረግልኝ በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ተመልክቶ በፍ/መ/ ሐምል 13 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት ተወካይና ከሳሽ በ1994 ዓ.ም የሽያጭ ውል በተዋዋለበት ጊዜ ሻጩ ህጋዊ ውክልና ያልነበረው መሆኑ ቢታወቅም፤ ተወካዩ በ1994 ዓ.ም የገቡት ውል መስከረም 25 ቀን 1998 ዓ/ም መመዝገቡ ተረጋግጧል። ውለ በተመዘገበበት ጊዜ ምስክሮች ውል አዋዋይ ፉት ቀርበው የመሰከሩ ባለመሆኑ በውለ አመዘጋገብ ጊዜ የተፈጠረው ጉድለት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ይህ ውል ከተመዘገበበት ከ1998 ዓ.ም በፉት ጥር 04 ቀን 1995 ዓ.ም ተከሳሽ ለወኪላቸው ውክልና የሰጡ ስለሆነና ተወካዩ ያለህጋዊ ውክልና በ1994 ዓ.ም የገቡት ውል የውክልና ሥልጣን ከተገኘ በኋላ በ1998 ዓ.ም በመመዝገቡ የሽያጭ ውለን ረቂቅነት ያስቀረዋል። ስለዚህ በ1994 ዓ.ም. የተከሳሽ ወኪል እና ከሳሽ ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል ተወካዩ ህጋዊ ውክልና እስካገኘበት ጊዜ ድረስ ረቂቅ ነው የሚባል ቢሆንም ረቂቅ መሆኑ በሲዲማ ዞን መምሪያ በ1998 ዓ.ም ቀርቦ ከተመዘገበ በኋላ ህጋዊነቱን ስላገኘ ተከሳሽን ያስገድዲታል። ስለሆነም እንደውለ ልትፈጽም ይገባል በማለት ወስኗል።
በአሁን አመልካች የይግባኝ አቤቱታ አቅራቢነት ይግባኝ ሰሚው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩለ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በ1998 ዓ.ም ተደረገ የተባለው የምዝገባ ስራ የአመዘጋገቡን ሥርዓት ካላሟላ ቅሬታ ያለው ወገን በሰነድች ማረጋገጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 334/95 አንቀጽ 7 መሰረት ሥርዓቱን ጠብቆ መፍትሄ ማግኘት ከሚቻል በቀር የማስረጃውን ተቀባይነት ከወዱሁ ውድቅ ለማድረግ አይቻልም። በዚህም አንቀጽ መሰረት አመልካች አቤቱታ የማቅረብ መብቷ በይርጋ የታገደ ነው በማለት ከዚህ በፉት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በተመሳሳይ ጉዲይ በሰበር መ/ በሆነው በአመልካች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በወ/ሮ ዓለምነሽ ኃይላ መካከል በነበረው ጉዲይ ትርጉም የሰጠበት መሆኑን ጠቅሶ ግራ ቀኙን የሚያከራክረው እና በ1994 ተደረገ የተባለው ውል በአዋዋይ ፉት የተደረገ ሆኖ ተገኝቷል የሚለውን መሰረት አድርጎ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ በማጽናቱ የተነሣ የአሁን አመልካች በዚህ የፋዳራል ጉዲይ በሆነው የመጨረሻ ፍርድ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል የሚለበትን የመከራከሪያ ነጥቦች በመዘርዘር ለዚህ የሰበር ጉዲይ መነሻ የሆነውን የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል።
ተጠሪም ቀርቦ ለሰበር አቤቱታው ዝርዝር መልስ ሰጥቶበታል ግራ ቀኙ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ስለጉዲዩ ያቀረቡትን የፅሁፍ ክርክር እንዲየነው ሁለቱም ወገኖች በየፉናቸው በሥር ፍ/ቤቶች ያቀረቡትን ክርክር በማጠናከርና በማብራራት የቀረበ ከመሆኑ በቀር የይዘት ለውጥ ያለው አይደለም።
እንግዱህ የጉዲዩ አነሳስና አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን፤ እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል። እንደመረመርነውም ለነገሩ መነሻ የሆነው የቤት ሽያጭ ውል የተደረገው የአመልካች ወኪል የተባለት ሻጭ ከንብረቱ ባለቤት ከአሁን አመልካች ቤቱን ለመሸጥ የሚያስችል የውክልና ሥልጣን ሳይኖራቸው በ1994 ዓ.ም ከአሁን ተጠሪ ጋር ያደረጉት ስለመሆኑና ይህም ውል በአዋዋይ ፉት ያልተደረገ ለመሆኑ በሥር ፍ/ቤቶች በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። በዚህም የተነሣ በዚህ አኳኋን የተደረገው ውል እስከ 1998 ዓ.ም ድረስ የረቂቅነት ደረጃ እንደነበረውም የስር ፍ/ቤቶች በሰጡት ዲኝነት ተረጋግጧል።
ሆኖም የአሁን አመልካች ጥር 04 ቀን 1995 ዓ.ም. ሻጭ ለነበረው ወገን የውክልና ሥልጣን የሰጡ የመሆኑን እና በ1994 ዓ.ም የተደረገው ውል በሲዲማ ዞን ፍትህ መምሪያ ቀርቦ በ1998 ዓ.ም. ተመዝግቦ ተገኝቷል የሚለትን አውነታዎች (facts) በመያዝና ከዚሁም በመንደርደር በ1994 ዓ.ም የተደረገው ውል ረቂቅ መሆኑ ቢታወቅም በ1998 ዓ.ም በውል አዋዋይ ፉት የተመዘገበ ሆኖ ስለተገኘ ረቂቅነቱ ቀርቷል ህጋዊ ደረጃውን አግኝቷል። እንዱሁም ሻጭ ቤቱን በሸጠበት ጊዜ ከንብረቱ ባለቤት ከአሁን አመልካች ቤቱን ለመሸጥ የሚያስችል ሥልጣን የነበረው ባይሆንም ውለ በአዋዋይ ፉት ቀርቦ ከመመዝገቡ በፉት ሻጭ በጥር 04 ቀን 1995 ዓ.ም.
የውክልና ሥልጣን አግኝቷል። ስለሆነም በ1994 ዓ.ም የተደረገው ውል በወኪሎ በአሁን አመልካች እንደተደረገ ይቆጠራል የሚለውን አተረጓጎም በመከተል ውለ የአሁን አመልካችን የማስገደድ ኃይል አለው የሚል ዲኝነት ሰጥተዋል።
ይሁን እንጂ በአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት በተሰጠው ፍርድ እንደተገለፀው ይህ ክርክር ያስነሳው የቤት ሽያጭ ውል በ1998 ዓ.ም በሲዲማ ዞን ፍትህ መምሪያ ቀርቦ እንደተመዘገበ ገልፆ የአሁን ተጠሪ ቢከራከርም በሰነደ ላይ በእማኝነት/በምስክርነት የተጠቀሱት ምስክሮች በአዋዋይ ፉት ቀርበው ያስመሰከሩ መሆኑን በፍሬ ነገር ረገድ አረጋግጧል። ከዚህም በቀር እራሱ ውለን በእራሱ ፉት መደረጉን አረጋገጠ የተባለው የሲዲማ ዞን ፍትህ መምሪያ በቁጥር ሲ/ዞ/ፍ/መ/1304/2003 በ14/10/2003 እና በቁጥር ሲ/ዞ/ፍ/መ/1403-03 በ06/11/03 ዓ.ም በተፃፈ ማረጋገጫ ውለ የተደረገው አዱስ አበባ ወል ሰፈር፤ የምስክሮችም አድራሻ አዱስ አበባ መሆኑንና ምስክሮችም በሲዲማ ዞን ፍትህ መምሪያ ፉት ቀርበው የውለን መደረግ አለማረጋገጣቸውን አረጋግጧል። በተለይም ውል አዋዋይ ፉት መሰከሩ ከተባለት ምስክሮች መካከል ቅድስት በቀለ የተባለችውን አስቀርቦ እንዲረጋገጠው ውለ አዱስ አበባ ወል ሰፈር ተደርጎ ምስክሮች በአዋዋይ ፉት ሳይቀርቡ እንዳት ተመዘገበ ልባል እንደቻለ የአሁን ተጠሪ ቀርቦ እንዱያስረዲ ፍትህ መምሪያው ሲጠይቀው በተጠሪ ድርጅት ደብዲቤ በተረጋገጠ ተጠሪው በአዋሳ ከተማ ሉገኝ አይችልም በሚል ምክንያት ቀርቦ ሉያስረዲ ያልቻለ መሆኑንና ውለ ተመዘገበ የተባለትን ሂደት ሁለ ካጣራ በኋላ ይህ 1994 ዓ.ም. ተደረገ ተብል በ1998 ዓ.ም በሲዲማ ዞን ፍትህ መምሪያ ተመዘገበ የተባለው ውል በህጋዊ መንገድ የተመዘገበ አለመሆኑን አረጋግጧል።
በመሆኑም ከዚህ በላይ በሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ በፍሬ ነገር ረገድ እንደተረጋገጠው የውል አደራረግ ሂደትን የማረጋገጥ የመመዝገብ ሥልጣን ባለው አካል እና ክርክር ያስነሳውን ውል እንደ ሥርዓቱ በእራሱ ያልተመዘገበ መሆኑን እያረጋገጠ፣ ፍ/ቤቶችም ይህንኑ ፍሬ ነገር በማስረጃ መረጋገጡን እየተረደ የሥር የአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህ የውል አመዘጋገብ ጉድለት እንደተጠበቀ ሆኖ…. በሚል አገላለጽ በዝምታ ማለፈ፤ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ይህ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መ/ በሆነው በአመልካች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በወ/ሮ ዓለምነሽ ኃይላ መካከል ትርጉም የሰጠበት ጉዲይ ከዚህ ከተያዘው ጉዲይ ጋር የማይመሳሰል እና ተመሳሳይ ትርጉም ሉከተል የማይችል መሆኑ እየታወቀ የአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2(1) የተመለከተውን ድንጋጌ ያለቦታው በመጥቀስ ክርክር ያስነሳውና በ1994 ዓ.ም አ/አበባ ከተማ ወል ሰፈር ተደረገ የተባለው ውል በ1998 ዓ.ም በሲዲማ ዞን ፍትህ መምሪያ ቀርቦ ተመዝግቧል ከሚል ውሳኔ መድረሳቸው ፍ/ቤቶች የሚሰጧቸው ትዕዛዞች፣ ብይኖች፣ ፍርድች እና ማናቸውም ዲኝነት በተከራካሪ ወገኖች የተነሱትን ክርክሮች ከተከራካሪ ወገኖች ክርክር አንፃር በጭብጥነት በተያዙት ጉዲዮች በግራ ቀኙ የተሰማውን ማስረጃ መሰረት በማድረግና በዚህም በማስረጃ የተረጋገጠውን ጉዲይ ለመቀበልም ሆነ ውድቅ ለማድረግ የቻለበትን ምክንያትና አግባብነት ያለውን ህግ መሰረት በማድረግ ላሆን ይገባል በሚል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 182 እና 183 ስለፍርድ አፃፃፍ የተመለከተውን ሥርዓት የተከተለ ሆኖ አላገኘነውም።
ስለሆነም በ1994 ዓ.ም የተደረገው ውል ረቂቅ ሆኖ እስከ 1998 ዓ.ም የቆየ ቢሆንም በ1998 ዓ.ም ውል አዋዋይ ፉት ቀርቦ የተመዘገበ ሆኖ ስለተገኘ ህጋዊነቱን አግኝቷል የሚለው የፍርድ መነሻ ሀሳብ ህጋዊ መሰረት ያለው አይደለም። ሻጭ የተባለው ወገን ንብረቱን በ1994 ዓ.ም ሸጧል ከተባለ በኋላ የአሁን አመልካች ጥር 04 ቀን 1995 ዓ.ም ንብረቱን ሸጠ ለተባለው ወገን የውክልና ሥልጣን የመስጠታቸው ተግባር በእራሱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1678(ሐ)፣ 1719(2) እና 1723 በተደነገገው መሰረት ህጉ የሚጠይቀውን ማሟያ አሟልቶ ባለመገኘቱ ምክንያት በህግ ፉት ሉፀና የሚችል ውል የለም፤ ውለ ረቂቅ ነው የተባለበትን ማናቸውም ክንውን ለመቀበል ህግ አያስገድዲቸውም። ይህም ብቻ ሳይሆን አመልካች በ1995 ዓ.ም. የሰጡት የውክልና ሥልጣን አገልግልት የውክልና ሥልጣን ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ለሚከናወኑ ህጋዊ ተግባራት ተብል የተሰጠ መሆኑን ከሚያመለክት በቀር የውክልና ሥልጣን ከመስጠቱ በፉት ወኪለ የፈፀመውንም ማናቸውም ተግባር ለመቀበል እንደፈቀደ፣ እንደፈለጉ ያስቆጥራቸዋል ለማለት የሚያበቃ የህግ መሰረት የለውም።
ምናልባትም ይህ ዘግይቶ የውክልና ሥልጣን የመስጠት የአመልካች ተግባር ቀደም ሲል ወኪል የተባለው ሰው ፈፀመ የተባለውን የሽያጭ ተግባር ለማፅደቅ መፈለጋቸውን ያሳያል በማለት መተርጎም እንዲይቻል ለዚሁ አግባብነት ባለው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2190 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ሉሆኑ የሚችለት የውክልና ሥልጣን ኖሮ ተወካዩ ከውክልና ሥልጣኑ በላይ አሳልፍ ለፈፀመው ተግባር እና የውክልና ሥልጣን ዘመኑ ካበቃ በኋላ ወኪል የነበረው ሰው ለፈፀማቸው ተግባሮች እንጂ አሁን እንደተያዘው ላለው ፈፅሞ የውክልና ሥልጣን ባልተሰጠበት ጉዲይ ሆኖ አላገኘነውም።
በዚህ ሁለ ምክንያት ክርክር ያስነሳውና የቤት ሽያጭ የተባለው ውል የአሁን አመልካችን ሉያስገድድ የሚችል የህግ መሰረት በላለበት ሁኔታ የስር ፍ/ቤቶች ውለ አመልካችን ይመለከታል፤ እንደውለ እንዱፈፅሙ ይገደዲለ በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስለተገኘ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል፤
የሰበር አቤቱታ የቀረበበት እና የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በይግባኝ መ/ በ19/12/2003 ዓ.ም የሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ ተሽሯል።
ሀጂ ይማም ሙዘይን በውክልና ሥልጣን ከተጠሪ ከአቶ እምነቴ እንደሻው ጋር በ1994 ዓ.ም ተፈፀመ የተባለው የቤት ሽያጭ ውል ወካይ ናቸው በሚል ምክንያት የአሁን አመልካችን ወ/ሪት አሉያት ይማምን ሉያስገድድ የሚችል አይደለም ብለናል።
በዚህ ሰበር ችልት ለተደረገው ክርክር ግራ ቀኙ ያወጡትን ወጪና ኪሣራ በየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.