No summary available.
ሀምላ 4 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገብረሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፈሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- 1/ አቶ አፅብሃ ወልዲይ አቶ ሀይማኖት ቢተው ቀረቡ 2/ አቶ ቅባቱ ግደይ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዙሪያሽ አሰግድ የክልለ ፍትህ ቢሮ ዐቃቤ ህግ ፀሐይ አበራ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በከሳሽነት ቀርባ ልጄ የሆነችው ወ/ሮ ድንቄ መኮንን በአሶሳ ዞን ኩርሙክ ወረዲ በኩሙሩክ ከተማ ውስጥ ከወ/ሮ ምስራቅ ኣንጋለ ገዝታና አስፊፍታ ስትመራው የነበረውን የድርጅት ቤት በውክልና እንዱስተዲድርላት ለአንደኛ ተከሳሽ የውክልና ሥልጣን ሀምላ 13 ቀን 1996 ዓ.ም ሰጥታው ሄዲለች። ወ/ሮ ድንቄ መኮንን ሀምላ 29 ቀን 1998 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለየች በመሆኑ የአንደኛው ተከሳሽ /አንደኛው አመልካች/ የውክልና ሥልጣን ቀሪ ሆኗል። ተከሳሾች /አመልካች/ ሟች ከሞተች በኋላ ለሁለት ዓመት የቤት ኪራይ ሲከፍለ ቆይተው ከዚያ በኋላ ቤቱን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ሆነው ስላልተገኙ ክስ ያቀረበበትን ንብረት እንዱለቁና በየወሩ ብር 2000 /ሁለት ሺህ ብር/ ሂሳብ ኪራይ እንዱከፍለ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረበችው ክስ ነው። አመልካቾች በተከሳሽነት ቀርበው የተጠሪ ክስ በይርጋ ይታገዲል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበዋል። ፍሬ ጉዲዩን በተመለከተ አንደኛ አመልካች ከወ/ሮ ድንቄ መኮንን ሀምላ 13 ቀን 1996 ዓ.ም. በተሰጠው የመሸጥና የመለወጥ የውክልና ሥልጣን መሰረት ቤቱን ሰኔ 20 ቀን 1997 ዓ.ም. ለሁለተኛው ተከሳሽ /ሁለተኛ አመልካች/ የሸጡ መሆናቸውንና ገዥው ሁለተኛው አመልካችም ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ቤቱን ተረክበው እያለሙና እያስፊፈ የሚገኙ መሆኑን በማንሣት ተከራክረዋል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ አንደኛው አመልካች ቤቱን ለሁለተኛ አመልካች ሰኔ 20 ቀን 1997 ዓ.ም. በተደረገ የሽያጭ ውል የሸጠ መሆኑንና ሽያጩም ፍትህ ቢሮ ቀርቦ የፀደቀ መሆኑን በመግለጽ የተጠሪን ክስ ውድቅ በማድረግ አመልካቾችን በነፃ አሰናብቷቸዋል።
ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርባለች። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተጠሪን ይግባኝ በፍታብሓር ስነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል። ተጠሪ የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አቅርባ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ አንደኛ አመልካች የሽያጭ ውለን ፍትህ ቢሮ ውልና ማስረጃ በመቅረብ ያስመዘገበውና ስመሃብቱም ለገዥ ለሁለተኛው አመልካች እንዱዛወር ያደረገው ወካይም ወ/ሮ ድንቄ መኮንን ከሞቱ በኋላ በ2001 ዓ.ም እና በ2003 ዓ.ም. በመሆኑ አንደኛ አመልካች የውክልና ስልጣኑ ቀሪ ከሆነ በኋላ የፈፀመው ተግባር ህጋዊ ውጤት የላለው ነው በማለት አመልካቾች ክርክር የተነሳበትን ቤት ለተጠሪ እንዱያስረክቡ በማለት በአብላጫ ድምጽ ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካቾች ለዚህ ሰበር ችልት መስከረም 23 ቀን 2004 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ሁለተኛ አመልካች የቤቱ ባለሀብት የሆነችው ወ/ሮ ድንቄ መኮንን የሰጠችው ውክልናን በሚመለከት ከአንደኛ አመልካች ክርክር የተነሳበትን ቤት ብር 4000/ አራት ሺህ ብር/ በመግዛት እስከ ብር 400,000 /አራት መቶ ሺህ ብር/ በላይ በማውጣት ገንብቻለሁ። ስለዚህ ወደ ነበሩበት ይመለሱ ቢባል የማይቻል ሆኖ እያለ ውለ ፈራሽ ነው መባለ ተገቢ አይደለም። ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል።
አመልካች ታህሣስ 13 ቀን 2004 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ሁለተኛ አመልካች ቤቱን የቤቱ ባለሀብት ወኪል ከሆነው አንደኛ አመልካች ገዝቸአለሁ በማለት የሚከራከረው የህጉን ፍርም ሳያሟላና ሟች በሞት ከተለየችና የአንደኛ አመልካች የውክልና ስልጣን ቀሪ ከሆነ በኋላ ከቅን ልቦና ውጭ የፈፁሙት ተግባር ነው። ስለዚህ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የቤት ሽያጭ ውለ በክልለ ፍትህ ቢሮ ውልና ማስረጃ ጽ/ቤት ሟች ከሞተች በኋላ ቀርቦ የተመዘገበና አንደኛ አመልካች ይህንን ተግባር ያከናወነው ወካይዋ መሞቷንና የውክልና ሥልጣኑ ቀሪ መሆኑን እያወቀ በመሆኑ በአንደኛ አመልካችና በሁለተኛ አመልካች መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውለ ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክረዋል። አመልካቾች ጥር 1 ቀን 2004 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የክልለ ሰበር ችልት አንደኛ አመልካች በክልለ ፍትህ ቢሮ በመቅረብ የሽያጭ ውለን ያስመዘገበው ወካይዋ ወ/ሮ ድንቄ መኮንን ከሞተችና የውክልና ስልጣኑ ቀሪ ከሆነ በኋላ በመሆኑ የቤት ሽያጭ ውለ ፈራሽ ወይም ህጋዊ ውጤት የላለው ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አከራካሪው ቤት የሟች ወ/ሮ ድንቄ መኮንን ሀብት የነበረ መሆኑና ድንቄ መኮንን አንደኛ አመልካች ይህን ቤት እንዱያስተዲድር እንዱሸጥ እንዱለውጥ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2205 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ሀምላ 16 ቀን 1996 ዓ.ም የሰጠችው መሆኗንና ወ/ሮ ድንቄ መኮንን ሀምላ 29 ቀን 1998 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት የተለየች መሆኑ የሚያከራክሩ ፍሬ ጉዲዮች አይደለም።
ወካዩ የሞቱ እንደሆነ በሥፍራው አለመኖሩ የተረጋገጠ እንደሆነ ለመስራት ችልታ ያጣ እንደሆነ ወይም በንግድ መውደቅ ኪሣራ ደርሶበት እንደሆነ ለጉዲዩ ተቃራኒ የሚሆን ውል ካልተገኘ በቀር የውክልና ሥልጣኑ ወድያውኑ የሚቀር መሆኑን የፍታብሓር ሥ/ቁጥር 2232 ንዐስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል። አንደኛ አመልካች በተሰጠኝ ውክልና መሰረት ለሁለተኛ አመልካች ቤቱን የሸጥኩት ሰኔ 20 ቀን 1997 ዓ.ም. ወካይዋ ከመሞቷ በፉት ነው በማለት የሚከራከርና ሁለተኛ አመልካችም ይህንን የመከራከሪያ ነጥብ የሚያቀርቡ ቢሆንም የቤት ሽያጭ ውለ ፍትህ ቢሮ ውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ቀርቦ የተመዘገበው ሟች ወ/ሮ ድንቄ መኮንን በሞት ከዚህ ዓለም ከተለየች በኃላና የአንደኛ አመልካች የውክልና ሥልጣን በፍትብሓር ህግ ቁጥር 2232 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ መሰረት ቀሪ ከሆነ በኃላ መሆኑ ተረጋግጧል።
የአንድን ንብረት ባለሃብትነት በውል ለላላ ሰው የሚተላለፈው ባለሃብት ወይም ባለሃብቱ የንብረቱን ባለቤትነት በውል ለላላ እንዱያስተላልፍ የፀና ልዩ የውክልና ስልጣን ባለው ሰው እንደሆነ የህገ መንግስቱ አንቀጽ 40 ንዐስ አንቀጽ 1፣ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1204 ንዐስ አንቀጽ 2፣ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2005 ንዐስ አንቀጽ 2 እና የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2232 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌዎችን በጣምራ በማንበብ ለመረዲት ይቻላል። በያዝነው ጉዲይ አንደኛ አመልካች ሟች ድንቄ መኮንን በሰጠችኝ ልዩ የውክልና ሥልጣን መሰረት ቤቱን በብር 4000 (አራት ሺህ ብር) ለሁለተኛ አመልካች የሸጠ መሆኑን በማረጋገጥ በክልለ ፍትህ ቢሮ የውክልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ያስመዘገበው በ2001 ዓ.ም መሆኑ ተረጋግጧል።
ይህም የሚያሣየው ሁለተኛው አመልካች በፍትህ ቢሮ ውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት በኩል በ2001 ዓ.ም የሟች ወ/ሮ ድንቄ መኮንን ቤት ለመግዛት ያደረጉት ውል የቤቱን ባለሃብትነት ለማስተላለፍ የፀና የውክልና ስልጣን ከላለው ከአንደኛው አመልካች ጋር የተደረገ በመሆኑ ህጋዊ ውጤት የላለው ነው። ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አንደኛ አመልካች ለሁለተኛው አመልካች የድንቄ መኮንንን ቤት ለመሸጥ ያደረገው ውል ፈራሽና ህጋዊ ውጤት የላለው ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ ከላይ የዘረዘርናቸውን የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገና የህግ ስህተት የላለበት ነው።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አነስተኛው ድምጽ የአንደኛው አመልካች ሟች ከሞተች በኃላ በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት በኩል ውለን ማስመዝገቡ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2232 ንዐስ አንቀጽ 2 የሚሸፈን ተግባር እንደሆነ ትንታኔ ሰጥቷል። አመልካችም የሽያጭ ውለ የተደረገው ሰኔ 20 ቀን 1997 ዓ.ም ተደርገ ውለ በክልለ ፍትህ ቢሮ ውልና ማስረጃ በ2002 ዓ.ም የተመዘገበ መሆኑን ጠቅሰው የአንደኛው አመልካች አድራጎት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2232 ንዐስ አንቀጽ 2 የሚሸፈን ነው የሚል ክርክር አቅርበዋል። ሆኖም በመጀመሪያ ደረጃ አንደኛ አመልካች ሁለተኛ አመልካች የቤት ሽያጭ ውል የፈፀመበት እርግጡን ቀን ተብል የሚያዘው እነርሱ ውለ የተደረገበት ቀን ነው ብለው በውለ ሰነድ ላይ የፃፈት ቀን ሣይሆን የሽያጭ ውለን የክልለ ፍትህ ቢሮ ውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ተቀብል የመዘገበበት ቀን እንደሆነ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2015(ሀ) በግልጽ የተደነገገ በመሆኑ የአመልካቾች ክርክር የህግ ድጋፍ ያለው ሆኖ አላገኘነውም። ከዚህ በተጨማሪ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2232 ንዐስ አንቅጽ 2 ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ ወካዩ ከሞተ በኃላ ተወካዩ የቤት ሽያጭ ውል እንዱያከናውን ወይም የቤት ሽያጭ ውለን ለመፈፀም የውክልና ስራውን እንዱቀጥል ለማድረግ ታስቦ የተቀረፀ ድንጋጌ አይደለም። ስለዚህ አመልካቾች የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2232 ንዐስ አንቀጽ 2 ድንጋጌን በመጥቀስ ያቀረቡትን ክርክር አልተቀበልነውም።
ሁለተኛ አመልካች ገዝቸዋልሁ የሚለትን ቤት ባለሃብትነት ለማስተላለፍ መብት ወይም የፀና የውክልና ስልጣን ከላለው ሰው ጋር ያደረጉት ውል ከጅምሩ ፈራሽና ህጋዊ ውጤት የላለው ነው። በመሆኑም በዚህ መዝገብ ከቀረበው ፍሬ ጉዲይ በእጅጉ የተለየውንና ይህ ሰበር ችልት በሰበር መዝገብ ሰጥቶት የነበረውን የህግ ትርጉም በመጥቀስ ያቀረቡት ክርክር ለጉዲዩ አግባብነት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም። በአጠቃላይ ከላይ በዝርዝር በገለጽናቸው ምክንያቶች የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት በአብላጫ ድምጽ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የቤንሻጉል ጉምዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
ሁለተኛ አመልካች ተጠሪ የማይገባትን ብልጽግና አግኝታለች የሚል ከሆነ አግባብነት ያላቸው የህግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ በተጠሪ ላይ ክስ የማቅረብ መብቷን ይህ ውሣኔ የሚገድበው አይደለም በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
በዚህ ፍርድ ቤት ህዲር 25 ቀን 2004 ዓ.ም. የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል ይፃፍ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.