No summary available.
ሰኔ 07 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ገብረ ክርስቶስ ገብረ እግዛብሓር ጠበቃ ገ/እግዚአብሓር ተስፊዬ ተጠሪ፡- ሳባ እምነበረድ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ነገረ ፈጅ አቶ ቴድሮስ ገብረ ዮሐንስ - ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የእምነ በረድ ሽያጭ ውል አፈፃፀምን የሚመለከት ነው።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በማዕከላዊ ዞን አድዋ ምድብ ችልት ነው። በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከሣሽ ተጠሪ ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ አመልካች ለሥር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ነው። አመልካች ከተጠሪ ጋር 2781 ሜትር ኩብ እምነበረድ ከቫት ውጭ በብር 939,948 /ዘጠኝ መቶ ሰላሣ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ስምንት ብር/ ለመግዛት ታህሣሥ 29 ቀን 2002 ዓ.ም ውል የተዋዋለና በዚህ ውል መሰረት ሻጭ /ተጠሪ/ 616.4 ሜትር ኩብ የእምነበረድ በብር 2ዐ5,ዐ17.47 /ሁለት መቶ አምስት ሺህ አስራ ሰባት ብር ከአርባ ሰባት ሣንቲም/ አስረክቦኛል። ገዥው /አመልካች/ ብር 661,217.37 /ስድስት መቶ ስልሣ አንድ ሺህ ሁለት መቶ አስራ ሰባት ብር ከሰላሣ ሰባት ሣንቲም/ ቅድሚያ ክፍያ ከፍያለሁ። ተከሣሽ/ ተጠሪ/ በሽያጭ ውለ መሰረት ዋጋው ከተጨማሪ እሴት ታክስ ውጭ ብር 734,93ዐ.55 የሆነ 2164.60 ሜትር ኩብ እብነበረድ አላስረከበኝም ስለዚህ በሽያጭ ውለ መሰረት እብነበረደን እንዱያስረክብ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። ተጠሪ እስጢፊኖስ አስፊው የተባለ የድርጅቱ ግዥ ዋና ክፍል ኃላፉ በክርክር ጣልቃ እንዱገባ የጠየቀ ሲሆን ከከሣሽ /አመልካች/ ጋር የተዋዋልነው የእብነበረድ ሽያጭ የለም። ከሣሽ ብር 661,217.37 አልከፈለም። በህግ ፉት የፀናና ተጠሪን የሚያስገድድ የእብነበረድ ሽያጭ ውል የለም በማለት ተከራክሯል። ተጠሪ የድርጅቱ ግዥ ዋና ክፍል ኃላፉ በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባለት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት የሥር ፍርድ ቤት በወቅቱ የድርጅቱ ግዥ ዋና ክፍል ኃላፉ የሆኑትንና በሽያጭ ውለ ላይ የፈረሙት የተጠሪ የሥራ ኃላፉ ወደ ክርክሩ እንዱገቡ አድርጓል። የሥር ፍርድ ቤት የአመልካች ምስክሮች የሰጡትን ቃልና የተጠሪን ምስክሮች ቃልና በግራ ቀኙ በኩል የፅሐፍ ማስረጃ ከመረመረና ከመዘነ በኋላ የተጠሪ የግዥ ዋና ክፍል ኃላፉ ከከሣሽ /አመልካች/ ጋር የእብነበረድ ሽያጭ ውል የተዋዋለው ሥራ አስኪያጅ በቃል ትዕዛዝ መሆኑን ገልፆ የተከራከረ ሲሆን ጣልቃ ገብ ይህንን በማስተባበል አልተከራከረም።
ከዚህ በተጨማሪ አመልካች /ከሣሽ/ ለተከሣሽ /ተጠሪ/ ብር 5ዐዐ,ዐዐዐ /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በቼክ የከፈለ ሲሆን ተከሣሹም 616.4 ሜትር ኩብ እምነበረድ ለከሣሽ /ተጠሪ/ አስረክቧል።
ስለሆነም በከሣሽ /አመልካችና/ በተከሣሽ /ተጠሪ/ መካከል የፀና የእምነበረድ ሽያጭ ውል ያለ በመሆኑ ተጠሪ በሽያጭ ውለ መሰረት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ውጭ ዋጋው ብር 734,93ዐ.35 የሆነ 2164.60 ሜትር ኩብ እምነበረድ የማስረከብ ግዳታ አለበት በማለት ወስኗል። ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ ቅሬታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተጠሪን ይግባኝ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል። ተጠሪ የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት በሰጡት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ተጠሪን በኃላፉነት ሉያስጠይቅ የሚችል የሽያጭ ውጭ የመዋዋልና የመፈረም ሥልጣን ያለው የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ነው። የተጠሪ የግዥ ክፍል ኃላፉ ከሥልጣኑ ውስን ውጭ ከአመልካች ጋር የተዋዋለው የእምነበረድ ሽያጭ ውል ድርጅቱን የማያስገድድ በመሆኑ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገ የእምነበረድ ሽያጭ ውል የለም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አቶ እስጢፊኖስ አስፊው ከሥራ አስኪያጁ በተሰጠው የቃል ትዕዛዝ መሰረት የሽያጭ ውለን መዋዋለን በግልፅ በማመን መልስ ሰጥቷል። የሰው ምስክሮችም የሽያጭ ውለ ተፈፅሞ እብነበረድ እርክክብ የተጀመረ መሆኑን በማረጋገጥ አስረድተዋል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት መሰረታዊ የህግ ስህተት የማረም ሥልጣን ያለው ቢሆንም በሥር ፍርድ ቤት ያልተነሳና በማስረጃ ያልተጋገጠ ፍሬ ጉዲይ በማንሣት ውሣኔ መስጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። ከዚህ በተጨማሪ የሰበር ችልት የህሉና ግምት መሰረት በማድረግ ውሣኔ ሰጥቷል። ሥራ አስኪያጅ ባይፈርምበትም በአመልካችና በተጠሪ መካከል የሽያጭ ውል የተዋዋለ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ተጠሪን የሚያስገድድ ውል የለም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ የካቲት 27 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በሰጠው መልስ የተጠሪ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ በውለ ላይ ስላልፈረመበት ተጠሪ የሽያጭ ውለን ለማቋቋም አስፈላጊ የሆነውን ፈቃደን ሰጥቷል ለማለት አይችልም። በክርክሩ በተጠሪ ጠያቂነት ወደ ክርክር የገቡት ሰው በሥር ፍርድ ቤት የሰጡት መልስ ሽያጩ የእጅ በእጅ ስለሆነ የውል ሰነድ አያስፈልግም ነበር። የፅሐፍ ውክልና ሣይኖረኝ በቃል ተነግሮኝ በስህተት የፈረምኩት ነው በማለት ተከራክረዋል። ስለዚህ ተጠሪን የሚያስገድድ ውል አይደለም። ስለሆነም የተጠሪ ሥራ አስኪያጅ የፈረሙትና ተጠሪን የሚያስገድድ የፀና ውል አለመኖሩን በማረጋገጥ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች እኔ ስለተጠሪ ውስጣዊ አሰራር የማውቀው ነገር የለም። ከዚህ በፉት የገበያ ዋና ክፍል ኃላፉው የፈረሙበት የሽያጭ ውል ከተጠሪ ጋር ተዋውየ ውለ ተፈፃሚ ሆኖልኛል። የፅሐፍ ውክልና አልተሰጠም በሚል ምክንያት ብቻ ውለ አልተደረገም በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። ተጠሪ ገንዘቡን በቼክ ሲከፈለው ተቀብሎል። ስለዚህ ውል የለም በማለት የሚያቀርበው ክርክር የህግ መሰረት የለውም በማለት ሀምላ 7 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም. የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ተጠሪና አመልካች የተዋዋለት የእምነበረድ ሽያጭ ውል የለም በማለት የሰጠው ውሣኔ የህግ መሰረት ያለው ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲይን መርምረናል።
ይህም የሚያሣየን ከላይ የተገለፁት ፍሬ ጉዲዮችን በተመለከተ የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ተመሣሣይ መደምደሚያ ላይ የደረሡ መሆኑን ነው።
በሁለት ሰዎች መካከል የሽያጭ ውል አለ ለማለት ሻጭ የሆነው ወገን ገዥ ለሆነው ላላው ወገን ዋጋ በገንዘብ የተወሰነውን አንድ ነገር ገዥው ሉከፍለው ግዳታ በገባበት መሰረት ሉያስረክብና ባለቤትነቱን ሉያስተላልፍበት የሚገደድበት ውል ሲመሰርት እንደሆነ መሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2266 ተደንግጓል። ተጠሪ ለሽያጭ ውለ ድርጅቱን በመወከል በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1178/ሀ/ መሰረት ፈቃድና ስምምነቱን መስጠት የሚችለው የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ነው።
በውለ ላይ ሥራ አስኪያጁ ያልፈረመበት በመሆኑ በህግ ፉት የፀና የሽያጭ ውል የለም በማለት ይከራከራል። በእርግጥ ሥልጣን ያለው ሥራ አስኪያጅ በንግድ ድርጅቱ ሥም በውክልና የመፈረምና ሥራውንም ለማካሄድ እንደሚችል በንግድ ህጉ አንቀፅ 33 ንዐስ አንቀፅ 1 የተደነገገ ሲሆን ፣ ሥራ አስኪያጁ የንግድ ድርጅቱ ሥራ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ማናቸውንም ግዳታ የመፈፀም ሙለ ሥልጣን እንዲለው እንደሚገመት በአንቀፅ 35 ንዐስ አንቀፅ 1 ተደንግጓል።
ከላይ የጠቀስናቸው የህግ ድንጋጌዎች ተጠሪን በመወከል የእምነበረድ ሽያጭ ውልም ሆነ ላልች ውልችን የመዋዋል ሙለ ሥልጣን ያለው የተጠሪ ሥራ አስኪያጅ መሆኑን የሚያመለክቱ ናቸው። እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ የተጠሪን ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ያህል ሙለ ሥልጣን የላላቸው የተጠሪ የሥራ ኃላፉዎች በሚያደርጉት የሽያጭ ውል ተጠሪ በልዩ ሁኔታ በኃላፉነት የሚጠየቅበት ሁኔታ ይኖራል ወይስ አይኖርም? የሚለው ነጥብ ነው።
በያዝነው ጉዲይ የተጠሪ ውክልና ባለሙለ ሥልጣን የሆነው ሥራ አስኪያጅ አመልካችና ተጠሪ ታህሣሥ 29 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በተዋዋለት የእምነበረድ ሽያጭ ስምምነት ሰነድ ላይ ባይፈርምም፣ ተጠሪ ለአመልካች እምነበረድ በመሸጥ የገባውን የውል ግዳታ ሰነደ ከመፈረሙ በፉት ያውቀው እንደነበርና በውለ ላይ ስምምነቱን በፊርማው ያረጋገጠው የተጠሪ የግዥ ክፍል ኃላፉ በውለ ላይ የፈረመው ከተጠሪ ሥራ አስኪያጅ በተሰጠው የቃል ትዕዛዝ መሰረት መሆኑን ለሥር ፍርድ ቤት በሰጠው መልስ አረጋግጧል። ይህንን ፍሬ ጉዲይ ተጠሪ አላስተባበለም። ተጠሪ ለአመልካች የሰበር አቤቱታ በሰጠው መልስ የተጠሪ የግዥ ክፍል ኃላፉ “የእጅ በእጅ ሽያጭ ስለሆነ ውል አያስፈልግም? የፅሐፍ ውክልና ሳይኖረኝ በቃል ተነግሮኝ በስህተት የፈረምኩት ሰነድ” ነው በማለት የተከራከረ መሆኑን በግልፅ ያሰፈሩ ሲሆን የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በፅሐፍ ሣይሰጠው የተጠሪ የግዥ ክፍል ኃላፉ የፈረመው ሰነድ ምንም አይነት ህጋዊ ውጤት የለውም በማለት ተከራክሯል።
የተጠሪ ሥራ አስኪያጅ ድርጅቱ ከአመልካች ጋር የሚገባውን የእምነበረድ ሽያጭ ውል ግዳታ አስቀድመው አውቀውትና ተስማምተውበት ሰነደን ሉፈርሙ የማይችለ በመሆናቸው የተጠሪ የግዥ ክፍል ኃላፉ ውለን እንዱፈርሙ የቃል ትዕዛዝ የሰጡ መሆናቸውን ተጠሪ በግልፅ ክድ ካልተከራከረና ካላስተባበለ የተጠሪ የግዥ ክፍል ኃላፉ የሽያጭ ውለን የፈረመው ከሥራ አስኪያጁ በተሰጠው የቃል ትዕዛዝ ነው የሚለውን ፍሬ ጉዲይ እንዲመነ የሚቆጠር መሆኑን ከፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 234 ንዐስ አንቀፅ 2/ሰ/ እና ከፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 235 ንዐስ አንቀፅ 2 ድንጋጌዎች ይዘት መንፈስና ዓላማ ለመገንዘብ ይቻላል።
የተጠሪ ሥራ አስኪያጅ የተጠሪ የግዥ ክፍል ኃላፉ ድርጅቱን በመወከል የእምነበረድ ሽያጭ ውለን እንድዋዋል በሰጠው የቃል ትዕዛዝ መሰረት የግዥ ክፍል ኃላፉው የእምነበረድ ሽያጭ ውለን ፈርሟል። የእምነ በረድ ሽያጭ ውል በልዩ ፍርም እንዱደረግ የሚያስገድድ የህግ ድንጋጌ የለም። ስለሆነም የተጠሪን ድርጅት የመወከል ሙለ ሥልጣን ያለው ሥራ አስኪያጅ በልዩ ሁኔታ ከአመልካች ጋር የሚደረገውን የእምነበረድ ሽያጭ ውል ድርጅቱን በመወከል እንድፈራረም ለተጠሪ ግዥ ክፍል የሰጠው ውክልና የግድ በፅሐፍ መሆን እንደላለበት “ ስለውለ አፈፃፀም ሕጉ አንድ አይነት ፍርም እንዱደረግ ያስገደደ እንደሆነ ውለ የሚፈፀምበት ሥልጣን በዚሁ አይነት ፍርም ለወኪለ መስጠት አለበት ” በማለት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 218ዐ ድንጋጌ ይዘትና ይኸው ድንጋጌ በተቃራኒ ሁኔታ ሲታረጎም /acontrartio interpretation/ የሚኖረውን ውጤትና ተፈፃሚነት ወሰን በማየት ለመረዲት ይቻላል።
ስለሆነም የተጠሪ ድርጅት ወኪልና ባለሙለ ሥልጣን የሆነው የተጠሪ ሥራ አስኪያጅ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2215 ንዐስ አንቀፅ 3 እና በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2180 መሰረት በማድረግ የሰጠውን የቃል ውክልና በመቀበል የተጠሪ ድርጅት የግዥ ክፍል ኃላፉ ታህሣሥ 29 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ከአመልካች ጋር ያደረገው የእምነበረድ ሽያጭ ውል በተጠሪ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ዕውቅና ስምምነትና ትዕዛዝ የተፈፀመ የሽያጭ ውል ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ በዝርዝር ከተገለፀው በተጨማሪ ተጠሪ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በቃል የሰጠው ትዕዛዝና ውክልና የተጠሪ የግዥ ክፍል ኃላፉ ከአመልካች ጋር ታህሣሥ 29 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የተፈራረመውን ሰነድ ከተሰጠው ሥልጣንና ውክልና ውጭ ነው በማለት ውለን በመቃወም ለአመልካች የፃፈው ደብዲቤ ስለመኖሩ አላስረዲም። ተጠሪ የግዥ ክፍል ኃላፉው የተፈራረመውን ውል ያፀደቀው መሆኑን በግልፅ ባያረጋግጥም ይህንን ሰነድ መሰረት በማድረግ የተቀበለውን የብር 5ዐዐ,ዐዐዐ /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ቼክ ጥቅም ላይ ማዋለና ሰነደ ከተፈረመ በኋላ ከቫት ውጭ ዋጋው ብር 2ዐ5,ዐ17.47 /ሁለት መቶ አምስት ሺህ አስራ ሰባት ብር ከአርባ ሳባት ሣንቲም/ የሆነ 616.4 ሜትር ኩብ እምነበረድ ለአመልካች ያስረከበ በመሆኑ በሥር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። ይህም የተጠሪ የግዥ ክፍል ኃለፉ ከአመልካች ጋር ያደረገውን የእምነበረድ ሽያጭ ውል በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2214 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌዎች መሰረት ፈቅድ እንደተቀበለው የሚያስቆጥረው ነው። ስለሆነም የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ከላይ ከገለፅናቸው አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር ሣያገናዝብ በውለ ላይ የተጠሪ ሥራ አስኪያጅ አለመፈረማቸውን ብቻ መሰረት በማድረግ በተጠሪና አመልካች መካከል የተደረገ የእብነበረድ ሽያጭ ውል የለም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪና አመልካች ታህሣሥ 29 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የእምነበረድ ሽያጭ ውል ተዋውለዋል።
በህግ አግባብ የተቋቋሙ ውልች በተዋዋይ ወገኖች መካከል ህግ መሆናቸውና የህግ ያህል አስገዲጅነት ያላቸው መሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1731 ንዐስ አንቀፅ 1 ተደንግጓል። ተጠሪ ውለ ከተደረገበት ቀን አንስቶ በአንድ መቶ ሰማኒያ ቀን ውስጥ 2781 ሜትር ኩብ እብነበረድ በብር 939,948 ለአመልካች ለመሸጥ በገባው የውል ግዳታ መሰረት ዋጋው ብር 2ዐ5,ዐ17.47 ሣንቲም ከቫት ውጭ የሆነ 616.40 ሜትር ኩብ የእምነበረድ ብቻ ያስረከበ መሆኑ ተረጋግጧል።
ከዚህ አንፃር ስናየው ተጠሪ 2164.60 ሜትር ኩብ እብነ በረድ የማስረከብ ግዳታና ኃላፉነት ያለበት መሆኑን ከፍትብሓር ህግ ቁጥር 2274 ድንጋጌዎች ይዘት መንፈስና ዓላማ ለመገንዘብ ይቻላል።
በልላ በኩል አመልካች ተጠሪ ለሚስረክበው እብነበረድ በውለ መሰረት ዋጋውን የመክፈልና የገዛውን ዕምነበረድ የመረከብ ግዳታ ያለበት መሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 23ዐ3 ንዐስ አንቀፅ 1 ተደንግጓል። አመልካች ውለን በተዋዋለበት ቀን የብር 5ዐዐ,ዐዐዐ በቼክ ለተጠሪ ክፍያ የፈፀመ መሆኑ በሥር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ችልት ተረጋግጧል። ስለሆነም አመልካች በውለ መሰረት ሉከፍል የሚገባውን ብር 439,948 /አራት መቶ ስላሣ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ስምንት ብር / መክፈል ቀሪውን 2164.60 ሜትር ኩብ እብነበረድ ተረክቦ የመውሰድ ኃላፉነት አለበት ። ስለሆነም የስር ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡትን ውሣኔ በመሻር በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገ የእምነበረድ ሽያጭ ውል የለም በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን የአድዋ ምድብ ችልትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
ተጠሪና አመልካች ታህሣሥ 29 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ያፀናና ህጋዊ ውጤት ያለው የእምነበረድ ሽያጭ ውል ተዋውለዋል በማለት ወስነናል።
በውለ መሰረት ተጠሪ 2164.60 ሜትር ኩብ እምነበረድ የማስረከብ ኃላፉነት አለበት በማለት ወስነናል።
በውለ መሰረት አመልካች ከዚህ በፉት በቼክ ለተጠሪ ከከፈለው ብር 5ዐዐ,ዐዐዐ /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በተጨማሪ ብር 439,948 /አራት መቶ ሰላሣ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ስምንት ብር/ ለተጠሪ የመክፈል ግዳታ አለበት በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.