No summary available.
የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ ንግስቲ እምነት - ቀረቡ ተጠሪ፡- ቴዎድሮስ ተክላ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የቤት ልረከብ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአፊር ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት በደብቲ ወረዲ ፍ/ቤት ነው። በዚህ ፍ/ቤት ክርክሩ ሲጀመር ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ ሲሆኑ ተከሳሽ ደግሞ አመልካች ነበሩ። ተጠሪ በወረዲ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ አመልካች በአደራ እንዱጠብቁ ከተጠሪ አባት ሟች ተክላ ኪዲኔ የተሰጣቸውንና በልጊያ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን መኖሪያ ቤት ህጋዊ ወራሽ ለሆኑት ተጠሪ እንዱያስረክቡ ሲጠየቁ ፈቃደኛ ያለመሆናቸውን በመግለፅ ቤቱን እንዱያስረክቡ ይወሰንላቸው ዘንድ ጠይቀዋል። አመልካች በበኩላቸው ቤቱን በሕጋዊ ውክልና መሰረት ለሶስተኛ ወገን በሽያጭ ያስተላለፈ መሆኑን ገልፀው ቤቱን ለማስረከብ ልገደድ አይገባም በማለት ተከራክረዋል። ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ አመልካች አቶ ተክላ ኪዲኔ ኤርትራዊ በመሆናቸው ከአገር ሲወጡ ለአመልካች በሰጡት ውክልና መሰረት ቤቱን አመልካች ለሶስተኛ ወገን በሽያጭ ማስተላለፊቸው ተረጋግጧል በሚል ምክንያት በውክልና ስልጣን የተፈፀመ ተግባር አመልካችን ቤቱን እንዱያስረክቡ አያስጠይቃቸውም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጓል። ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ለዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩና ተገቢው ማጣራትና ተጨማሪ ማስረጃዎች ከተሰሙ በኋላ ጉዲዩ የዲኝነት ገንዘብ ተከፍልበት መታየት የነበረበት ነው በሚል ምክንያት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሮ ጉዲዩ የዲኝነት ገንዘብ ተከፍልበት እንዱታይ ወደ ስር ፍ/ቤት መልሶታል። ከዚህም በኋላ ተጠሪ የይግባኝ አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን የዲኝነት ገንዘብ ሲከፈልበት የሚታይ ነው በማለት መመለሱ የስነ ስርዓት ሕጉን ያልተከተለ መሆኑን፣ እንዱሁም ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ጭብጡን ለውጦ ዋናውን ጉዲይ ሉመለከት የሚችልበት የስነ ስርዓት ሕግ ድንጋጌ መኖሩን ጠቅሶና ድንጋጌውን ከለየ በኋላ ዋናውን ጉዲይ መርምሮ አመልካች አለ የሚለትን የውክልና ስልጣንና የሽያጭ ውል ማስረጃዎች በሚመለከታቸው አካላት በተለያየ ጊዜያት የተለያዩ መግለጫዎች የቀረቡባቸው በመሆኑ የሰነድ ማስረጃዎችን አጠራጣሪ የሚያደርገው መሆኑን፣ አመልካች አለ የሚለት የውክልና ሰነድ ማስረጃ ይዘቱ ሲታይም አከራካሪውን ቤት ለማስተዲደር እንጂ ለመሸጥና ለመለወጥ የማያስችላቸው መሆኑን የሚያስገነዝብ መሆኑን ጠቅሶና የዞኑን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የአመልካችን ክርክር ውድቅ አድርጎ ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካች በአቤቱታቸው የውክልና ስልጣን ማስረጃውን የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያለመቀበለ ከሰነደ ይዘት ውጪ ነው በማለት ዘርዝረው ውሳኔው ተሸሮ ለተጠሪ በውክልና ስልጣኑ መሰረት ቤቱን የሸጡበት ዋጋ ሕጋዊ ተቀናሽ ሂሳቦች ካለ የሚቀነሱ መሆኑ ተገልፆ ውሳኔ እንዱሰጣቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። ይህ ችልት ለአመልካች የተሰጠው ውክልና ቤቱን ከማስተዲደር ባሻገር ለመሸጥ የሚያስችል አይደለም በማለት አመልካች ከውክልና ሥልጣናቸው አሳልፈው ተገልግለዋል ተብል መወሰኑ ተገቢ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረት ያደረገው በፍሬ ነገር ክርክር ላይ በመሆኑ በሰበር ችልቱ ላታይ የሚችል አይደለም በማለት የመልሳቸውን ጽሁፍ አቅርበዋል። ችልቱም መዝገቡን ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሯል።
ከፍ ሲል እንደተገለፀው የተጠሪ አባት ሟች ተክላ ኪዲኔ የሰጡት ፈቃድና ውክልና ሳይኖር አመልካች አከራካሪውን ቤት ለ3ኛ ወገን ማስተላለፊቸው ተረጋግጧል ተብል ነው በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔ ላሰጥ የቻለው። የተጠሪ ክስ ሲታይም አመልካች ቤቱን በአደራ ለመጠበቅ ተረክበዋል የሚል ነው። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከላይ ከተገለፀው ድምዲሜ ሉደርስ የቻለው አመልካች አለ የሚለት የነሐሴ 19 ቀን 1990 ዓ.ም. የውክልና ስልጣን ማስረጃ ትክክለኛ ስለመሆኑ የውክልና ውለን መዝግቧል የተባለው የክልለ ፍትሕ ቢሮ መግለጫ እንዱሰጥበት በፍርድ ቤት ሲታዘዝ ሰነደ በቢሮው ሉገኝ አልቻለም ብል ደብዲቤ ለፍርድ ቤቱ ከሰጠ በኋላ በድጋሚ በፃፈው የማስተካከያ ደብዲቤ የውክልና ሥልጣን ማስረጃው በቢሮው ተረጋግጦ የተመዘገበና በተገቢው ማህበር ውስጥ ተያይዞ የሚታወቅ መሆኑን መግለፁና በሽያጭ ውለ ላይ ማጣራት አድርጎ መግለጫ እንዱሰጥበት የታዘዘው የአስተዲደር አካልም መጀመሪያ በሰጠው መግለጫ ውለ የማይታወቅ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ከገለፀ በኋላ በድጋሚ ማስተካከያ ነው ብል በፃፈው ደብዲቤ የሽያጭ ውለ በሕጉ አግባብ የሚታወቅ መሆኑን ማስታወቁ የሰነድ ማስረጃዎቹ አጠራጣሪ መሆናቸውን ያሳያል፣ የውክልና ስልጣን ሰነደም ቤትን ለመሸጥ ለመለወጥ የሚያስችል አይደለም የሚለትን ምክንያቶች ዘርዝሮ ነው።
በቅድሚያ ተጠሪ ጉዲዩ የፍሬ ነገርና የማስረጃ ምዘና ክርክር በመሆኑ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የሚታይ አይደለም በማለት ያቀረቡትን መቃወሚያ ተገቢነት ተመልክተናል። በእርግጥ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በኢ.ፉ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(39ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ማረም እንጂ ፍሬ ነገርን ማጣራት ወይም ማስረጃን መመዘን ያለመሆኑ ግልፅ ነው። ይሁን እንጂ አመልካች የክልለን ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔን በመቃወም የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት የውክልና ሰነደ በመንግስት መስሪያ ቤት የተረጋገጠ ሆኖ እያለና የሰነደ ይዘትም ልዩ ውክልና ልባል የሚችል ሆኖ እያለ ማስረጃው ተቀባይነት ማጣቱ ያለአግባብ ነው በሚል መሆኑን ከቅሬታቸው ይዘት ተገንዝበናል።
እንዱህ ከሆነ ቅሬታቸው በውክልና ማስረጃው ተቀባይነት ማጣቱ ላይ በመሆኑና የሰነድ ማስረጃ ተቀባይነት ደግሞ የሕግ ጥያቄ በመሆኑ በሰበር ሰሚ ችልት ስልጣን ስር የሚወድቅ እንጂ የፍሬ ነገር ወይም የማስረጃ ክርክር ነው ልባል የሚችል አይደለም። በመሆኑም በዚህ ረገድ የቀረበው የተጠሪ ተቃውሞ የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልፈነዋል።
ወደ ዋናው ስንመለስም፤ በመሰረቱ የአስተዲደር መ/ቤት አንድ ጊዜ የሰጠው የደብዲቤ መግለጫ ትክክለኛ ያለመሆኑን በልላ ጊዜ ከደረሰበት በዚሁ ላይ ላላ ማስተካከያ ደብዲቤ ቢጽፍ መ/ቤቱ ሁለት ጊዜ የተለያየ ይዘት ያላቸውን ደብዲቤዎች በመጻፈ ብቻ ደብዲቤዎቹ ለማስረጃነት ዋጋ ሉሰጣቸው አይገባም ብል ሁልጊዜ መደምደም የሚቻልበት የሕግ አግባብ የለም። ዋናውና ቁልፈ ነገር ከተፃፈት ደብዲቤዎች መካከል የትኛው ነው ትክክለኛ የሚለውን በተገቢው መንገድ ማጣራት ሲሆን ትክክለኛነቱ የተረጋገጠው ደብዲቤ ካለ ለዚሁ ተገቢው የማስረጃነት ዋጋ ላሰጥ ይገባል።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች አለ የሚለትን የውክልና ስልጣንና የሽያጭ ውለ በሚመለከታቸው አካላት ስለመኖራቸው በድጋሚ በተፃፈት የማስተካከያ ደብዲቤዎች ተረጋግጠዋል። እነዚህ ማስተካከያ ደብዲቤዎች ትክክለኛ ያለመሆናቸው ወይም ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ የተሰጡ ስለመሆኑ ተጠሪ ያነሱት ክርክር ካለመኖሩም በላይ ፍሬ ነገሩን ያጣሩት ፍ/ቤቶችም በዚህ ረገድ ያለት ነጥብ የለም። በመሆኑም የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰነድ ማስረጃዎችን ዋጋ ያልሰጠበት ምክንያት ሕጋዊ ካለመሆኑም በላይ የውክልና ማስረጃውን በተመለከተም ማስረጃው ዋጋ የላለው መሆኑን በውሳኔው ላይ ከአሰፈረ በኋላ ይዘቱን ተመልክቶ የደረሰበት ድምዲሜ ሕጋዊ አይደለም። ምክንያቱም ነሐሴ 19 ቀን 1990 ዓ.ም. የተደረገ የተባለው የውክልና ስልጣን ማስረጃ የተጠሪ አባት ለአመልካች አከራካሪውን ቤት እንዱጠብቁላቸው፣ እንዱያስተዲድሩላቸውና ሽጠው ገንዘቡን በመቀበል እንዱልኩላቸው በሚል የተቀመጠ ስለመሆኑ ይዘቱ ያሳያል። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በዚህ የውክልና ስልጣን ለአመልካች የተሰጣቸው ስልጣን ቤቱን የማስተዲደር ነው፣ እንዱህ ከሆነ ደግሞ አመልካች ማከናወን የሚችለት በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2203 እና 2204 ስር በተመለከተው መሰረት የማስተዲደር ተግባራት የሚባለትን እንጂ ቤቱን የመሸጥ የመለወጥ ተግባርን ጭምር አይደለም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ በውክልና ስልጣኑ አመልካች ቤቱን ከማስተዲደር በተጨማሪ መሸጥና መለወጥ የሚችለ ስለመሆኑ የሚያሳየውን የዓረፍተ ነገር ክፍል በመተው የተያዘ በመሆኑ ሕጋዊ ተቀባይነት የሚሰጠው አይደለም። በእርግጥ ለአመልካች በተሰጠው ውክልና ስልጣን ላይ አመልካች ምን ምን አይነት ተግባራትን ማከናወን እንደሚችለ ከተዘረዘረ በኋላ የተጠቀሰው የፍትሒ ብሓር ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 2199 ነው። የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለመሸጥ ለመለወጥ የሚያስችል ስልጣን ልዩ ውክልና እንደሚያስፈልገው የፍ/በ/ሕ/ቁጥር 2205 በግልፅ ያስቀመጠው ጉዲይ ነው። የዚህ ቁጥር ንዐስ አንድ ድንጋጌ ተወካዩ ከአስተዲደር ስራ በቀር ላላ ስራ ለመስራት የሚያስፈልግ ሲሆን ልዩ ውክልና እንዱኖረው አስፈላጊ መሆኑን ሲያስቀምጥ ንዐስ ሁለት ድንጋጌ ደግሞ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን መሸጥ ወይም አስይዞ መበደር የሚችለው ልዩ የውክልና ስልጣን ሲኖረው ስለመሆኑ ያስገነዝባል።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች አከራካሪውን ቤት ለመሸጥ የሚያስችላቸው ልዩ ውክልና የላቸውም የተባለው በውክልና ሰነደ የተዘረዘሩት የተወካዩ ኃላፉነቶች ሙለ በሙለ ይዘታቸው ሳይታይ ከመሆኑም በላይ በሰነደ ላይ የተጠቀሰው ድንጋጌ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2199 መሆኑ ለአመልካች የተሰጣቸው የውክልና ስልጣን ጠቅላላ ውክልና ስለመሆኑ ያሳያል በሚል ምክንያትም ጭምር ነው። ይሁን እንጂ የውክልና ሰነደ ይዘት በግልፅ ውክልና ተቀባዩ የተሰጠው ስልጣን የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ለመሸጥ የሚያስችል ስለመሆኑ እየገለፀ ስለልዩ ውክልና አስፈላጊነት የተቀመጠው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2205 በውክልና ስልጣን ሰነደ ያለመጠቀሱ ውክልናው ልዩ የውክልና ስልጣን አይደለም ብል ለመደምደም የሚያስችል ስለመሆኑ የሚያሳይ የሕግ ድንጋጌ የለም። ዋናውና ቁልፍ ነገር ለውክልና ተቀባዩ የተሰጡት ተግባሮች በዝርዝርና ግልጽ ሁኔታ ተጠቅሰው በውክልና ሰነደ ላይ መገኘት እንጂ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች ያለመጠቀሳቸው አይደለም። የሰነደ ይዘት ግልጽ መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች በውክልና ስልጣን ሰጪውና በውክልና ስልጣን ተቀባዩ አልተጠቀሱም ተብል ሰነደ ዋጋ እንዱያጣ ማድረግ የተዋዋዮችን ሐሳብ ውጤት እንዲይኖረው የሚያደረግ በመሆኑ በውል አተረጓጎም ደንቦችም ተቀባይነት የላለው አካሄድ ነው የሚሆነው። ስለሆነም የአፊር ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የውክልና ሰነደን ይዘት ሙለ በሙለ ሳይመለከትና በሰነደ ላይ ስለልዩ ውክልና ሥልጣን የሚደነግገው የፍትሒ ብሓር ሕግ ድንጋጌ አልተጠቀሰም በሚል እምነት አመልካች ከተጠሪ አባት ቤቱን ለመሸጥ የተሰጣቸው የውክልና ስልጣን የለም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2179 ፣ 2205 እና 2ዐዐ5 /1/ ድንጋጌዎችን ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል።
የተጠሪ አባት ቤት በአመልካች የተሸጠው በሕጉ አግባብ በተሰጣቸው ስልጣን መሰረት ነው ከተባለ ቀጥል መታየት ያለበት ተጠሪ ያላቸው መፍትሓ ምንድን ነው? የሚለው ነው። ተጠሪ ለአመልካች የውክልና ስልጣን ሰጡ የተባለት ግለሰብ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ መሆናቸው ከመረጋገጡም በላይ አመልካች ቤቱ የተሸጠበትን ገንዘበ ለተጠሪ ወይም ላልች ሕጋዊ የሟች አቶ ተክላ ኪዲኔ ወራሾች ሰጥቼአለሁ የሚል ክርክር በበታች ፍርድ ቤቶችም ሆነ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የላቸውም። ይልቁንም በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ባቀረቡት የጽሐፍ መልስ ቤቱ የተሸጠበትን ገንዘብ ለተጠሪ ከመክፈል ውጪ ቤቱን ለመመለስ የሚገደደበት አግባብ የላለ መሆኑን ግልጽ አድርገው ጠቅሰዋል። ስለሆነም ተጠሪ በሕጉ አግባብ በተሰጠ የውክልና ስልጣን የተሸጠውን ቤት አመልካች እንዱያስረክቡ መጠየቅ የሚችለበት ሕጋዊ ምክንያት ባይኖርም ቤቱ ተሸጠ የተባለበትን ገንዘብ ግን በወራሽነት መብታቸው ልክ መሰረት ከአመልካች ከመጠየቅ አይታገደም። በመሆኑም ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአፊር ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 2310 ነሀሴ 12 ቀን 2003 ዓ.ም አመልካች አከራካሪውን ቤት ከማስተዲደር ባሻገር ለመሸጥ የሚያስችላቸው የውክልና ስልጣን የለም ተብል የተሰጠው የውሣኔ ክፍል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች በተጠሪ አባት ነሐሴ 19 ቀን 1990 ዓ.ም. የተሰጣቸው የውክልና ስልጣን ማስረጃ በማስረጃነት ተቀባይነት የማይሰጥበት ሕጋዊ ምክንያት የላለ ሲሆን የሰነደ ይዘት ሲታይ አመልካች አከራካሪውን ቤት ለመሸጥ የሚያስችላቸው በመሆኑ ሽያጩ የተከናወነው አመልካች በተጠሪ አባት በተሰጣቸው የውክልና ስልጣን ስለሆነ አመልካች ለተጠሪ ቤቱን እንዱያስረክቡ ሉገደደ አይገባም ብለናል።
አመልካች ቤቱን የሸጡበትን የሽያጭ ገንዘብ ተጠሪ ካላቸው የወራሽነት መብት መጠን አንጻር ሉከፍለ ይገባል ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.