No summary available.
ሕዲር 5 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- 1- አቶ ስሻህ ክፍላ - አልቀረቡም 2- አቶ ሰጡኝ በቀለ ጠበቃ ጌትነት ያሻነህ ቀረቡ ተጠሪ፡- 1- ወ/ሮ አፀደ ደቤ - አልቀረቡም 2- ወ/ሮ አዛለች ደቤ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ ከውክልና ሥልጣን ውጭ የተፈፀመ የቤት ሽያጭ ውልን የሚመለከት ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ በመሆን የተከራከሩ ሲሆን ሁለተኛ አመልካች የተከሣሽ ከሣሽ ተጠሪዎች የከሣች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክራቸው ይዘትም የአንደኛ ተጠሪ ልጅና የሁለተኛ ተጠሪ ወንድም የሆነው አንደኛው አመልካች የማይንቀሣቀስ ንብረት እንዱሸጥ ፣ እንዱለወጥ ፣ ለሶስተኛ ወገን እንዱያስተላለፍ የተሰጠው ልዩ የውክልና ሥልጣን የለም። በአደራ እንዱያስተዲድር የሰጠነውን በመተሀራ ከተማ የሚገኝ ቤት ለሁለተኛው አመልካች በመሸጥ ስመሃብቱ የተዛወረ መሆኑን ገልፀው ውለ እንዱፈርስ እንዱወሰንላቸው ክስ አቅርበዋል። አመልካቾች በተከሣሽነት ቀርበው ሁለተኛ ተከሣሽ የነበሩት ሁለተኛው አመልካች ቤቱን ውክልና ካለው ሰው የገዛሁት ነው የሽያጭ ውለ ሉፈርስ አይገባም የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል።
በልላ በኩል የአሁን ሁለተኛ አመልካች በሥር ፍርድ ቤት የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ አቅርበዋል።
ቤቱን ከገዛሁ በኋላ ብር 15ዐ,ዐዐዐ /አንድ መቶ ሃምሣ ሺህ ብር/ ወጭ በማድረግና በማሻሻል ገንብቻለሁ። ስለዚህ የገነባሁት ቤት ባለሀብት ነህ ተብል እንዱወሰንልኝ ይህ የሚታለፍ ከሆነ ገንዘቡን በጋራና በተናጠል እንዱከፍለ ይወሰንልኝ በማለት የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ አቅርቧል።
ተጠሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ እና ላልች የመከራከሪያ ነጥቦች በከሣሽ ተከሣሽነት ቀርበው አንስተዋል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አንደኛ ተከሣሽ ለሁለተኛ ተከሣሽ ቤቱን የሸጠው በተሰጠው የውክልና ሥልጣን መሰረት በመሆኑ ውለ የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት ወስኗል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪዎች ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት የተጠሪዎችን ይግባኝ አልተቀበለውም። ተጠሪዎች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አቅርበዋል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ተጠሪዎች አንደኛ አመልካች የማይንቀሣቀሥ ሀብት እንዱሸጥ ልዩ የውክልና ሥልጣን ያልሰጡ በመሆኑ አንደኛው አመልካችና በሁለተኛው አመልካች መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል ፈራሽ ነው። ሁለተኛ አመልካች ከፈለገ አንደኛ አመልካችን ከሚከስ በስተቀር በተጠሪዎች ላይ የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ ማቅረብ አይችልም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካቾች ታህሣሥ 6 ቀን 2002 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1000/1/ በመጥቀስ ያቀረብነውን ክርክር አላግባብ አልፍታል። ተጠሪዎች ለአንደኛ አመልካች የሰጡት ውል አንደኛ አመልካች እንደነሡ ሆኖ እንዱከራከርላቸው ፣ ማናቸውም አቤቱታ አቅርቦ እንዱያስፈፅምላቸው ቃለመሃላ ፉርሞ እንዱያቀርብ እነሡን በሚመለከት ማስረጃ እንድቀበል በእነሡ ስም ውል እንዱዋዋል ዕርቅ እንዱደራደር ገንዘብ እንዱቀበል እና በተጠሪዎች ስም የሚዛውር ንብረት ፍርማሉቲ እንዱያሟላ እንዱያዛውር የሚል ይዘት ያለው ነው። አንደኛ አመልካች ውል እንዱዋዋል በተሰጠው የውክልና ሥልጣን ተጠቅሞ የተዋዋለውን የቤት ሽያጭ ውል እንዱፈርስ መወሰኑ ተገቢነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። ውለ አይፈርስም እንጅ ይፈርሳል ቢባል ብር 25ዐ,ዐዐዐ በማውጣት አሻሽዬ የገነባሁት ሲሆን ስመሀብቱም ወደ ሁለተኛ ተጠሪ የዞረ በመሆኑ ተጠሪዎች ላይ ያቀረበው የተከሣሽ ከሣሽነት ታይቶ ውሣኔ ላሰጥበት የሚገባው በመሆኑ ይህ ነጥብ መታለፈ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት አመልክተዋል። ተጠሪዎች በቃል ባቀረቡት ክርክር አንደኛ አመልካች የማይንቀሣቀሥ ንብረት በተጠሪዎች ስም እንዱያዛውር እንጂ በተጠሪዎች ስም ያለን የማይንቀሣቀሥ ንብረት ለላላ ሰው እንዱያስተላልፍ የተሰጠው ልዩ ውክልና የለም። ስለዚህ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ የህግ ስህተት የለበትም። ሁለተኛ አመልካች ብር 15ዐ,ዐዐዐ እንድንከፍለው ያቀረበው ክስ የህግ መሰረት የለውም በማለት ተከራክረዋል። አመልካች በቃል ክርክር የሥር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ ሣያጣራና ማስረጃ ሣይመዝን ሁለተኛ አመልካች ያቀረበውን የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ አልፍታል ስለዚህ የሁለተኛ አመልካች የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ በአግባቡ ታይቶ ውሣኔ አልተሰጠበትም በማለት ተከራክሯል።
ከሥር የቀረበው ክርክርና በሰበር የቀረበው የሰበር አቤቱታና በግራ ቀኙ የተደረገው የቃል ክርክር ከላይ በአጭሩ የተገለፀው ሲሆን አንደኛ አመልካችና ሁለተኛ አመልካች ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል ፈራሽ ነው ተብል የተሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? ሁለተኛው አመልካች ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ የሥር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ታይቶ የመጨረሻ ውሣኔ ተሰጥቶበታል ወይስ አልተሰጠበትም? የሁለተኛው አመልካች የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ በሥር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሣኔ አልተሰጠበትም የሚባል ቢሆን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ሁለተኛ አመልካች አንደኛ አመልካችን እንጂ ተጠሪዎችን መክሰስ አይችልም በማለት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም ? የሚለትን ጭብጦች በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ተወካዩ ከአስተዲደር ሥራ በቀር ላላ ሥራ ለመስራት የሚያስፈልግ ሲሆን ልዩ ውክልና እንዱኖረው አስፈላጊ መሆኑንና ተወካዩ ልዩ የውክልና ሥልጣን ከላለው በቀር የማይንቀሣቀሡ ንብረቶችን ለመሸጥ ወይም አስይዞ ለመበደር የማይችል በመሆኑ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2205 ንዐስ አንቀፅ 1 እና ንዐስ አንቀፅ 2 ተደንግጓል። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው ተጠሪዎች አንደኛ አመልካች ወደ ተጠሪዎች ሉዛወር የሚችል ማናቸውም ንብረት አስፈላጊውን ፍርማሉቲ በማሟላት በተጠሪዎች ሥም ለማዛወር የሚችል የውክልና ሥልጣን የሰጡት ሲሆን አንደኛ አመልካች ወደ ተጠሪዎች ሥም ያዛወረውን የማይንቀሣቀሥ ንብረት እንዱሸጥ ፣ እንዱለውጥ ፣ በማያዣነት አስይዞ እንዱበደር ለሶስተኛ ወገን እንዱያስተላልፍ የሚል ልዩ የውክልና ሥልጣን በግልፅ ያልሰጡት መሆኑ ተጠሪዎች ለአንደኛ አመልካች ከሰጡት የውክልና ሰነድ ይዘት ለማረጋገጥ ይቻላል።
አመልካቾች ተጠሪዎች ለአንደኛ አመልካች መጋቢት 13 ቀን 1985 ዓ.ም. በሰጡት የውክልና ሰነድ “ በስማችን ውል እንዱዋዋል ” በማለት የገለፀ በመሆኑ ይህ አገላለፅ ተጠሪዎች አንደኛው አመልካች የማይንቀሣቀሥ ሀብት ለመሸጥ ለመለወጥ የሚያስችለው ልዩ ውክልና እንደሰጡ ሉተረጎም ይገባል የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል። በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2205 መሰረት የሚሰጥ ልዩ ውክልና በይዘቱ በልዩ ውክልና የሚፈፀሙ እያንዲንዲቸውን ተግባሮች በግልፅ የሚያመለክት መሆን ይገባዋል። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው ተጠሪዎች አንደኛ አመልካች “ በስማችን ውል እንዱዋዋል ” በማለት የሰጡት ውክልና አንደኛ አመልካች በፍታብሓር ህግ ቁጥር 22ዐ4 የተዘረዘሩትን የአስተዲደር ተግባራት ለመፈፀም የሚያስችለትን ውልች በተጠሪዎች ስም ሉፈፅም እንደሚችል የሚያመላክት እንጂ የማይንቀሣቀሥ ንብረት ለመሸጥ ለመለወጥ የሚያስችለው ልዩ የውክልና ሥልጣን እንደተሰጠው ተደርጎ የሚተረጎምበት አግባብ የለም።
ለዚህም ምክንያቱ የውክልና ሥልጣን የሚተረጎመው ሣይስፊፊ በጠባቡ መሆን እንዲለበት የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2181 ንዐስ አንቀፅ 3 የሚደነግግ ከመሆኑም በላይ ተጠሪዎች ለአንደኛ አመልካች የሰጡት ውክልና ሙለ ይዘት አንደኛ አመልካች በልላ ሰው ስም ያለን ንብረት በተጠሪዎች ስም ለማዛወር የሚያስፈልጉ ፍርማሉቲዎች በማሟላት ወደ ተጠሪዎች ሥም እንዱያዛውር የተወከለ መሆኑን እንጂ አንደኛ አመልካች በተጠሪዎች በተሰጠው ውክልና ተጠቅሞ በተጠሪዎች ስም ያዛወረውን የማይንቀሣቀሥ ሀብት ለላላ ሶስተኛ ወገን እንዱሸጥ እንዱለውጥ ያልተወከለ መሆኑን የሚያሣይ በመሆኑ ነው። ስለሆነም አንደኛ አመልካች ቤቱን ለመሸጥ የሚያስችል የውክልና ሥልጣን ሣይኖረው የተጠሪዎችን ቤት ለሁለተኛ አመልካች ለመሸጥ ያደረገው ውል ተጠሪዎችን የማያስገድድ ፈራሽ ነው በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ የፍሬ ጉዲይ ወይም የህግ ስህተት የላለበት መሆኑን በመግለፅ የተጠሪዎችን ይግባኝ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት የሰረዘው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ሁለተኛው አመልካች ባቀረበው የተከሣሽነት ክስ ላይ የሰጡት ውሣኔ የለም። በመሆኑም ሁለተኛው አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረበው የተከሣሽነት ክስ ጉዲዩን በመጀመሪያ ባየው በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ በይግባኝ ሰሚ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሣኔ ያልተሰጠበት መሆኑን አረጋግጠናል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ ተሻሽሎል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አንደኛ አመልካች የተጠሪዎች ወኪል ነኝ በማለት ከሁለተኛው አመልካች ጋር ሰኔ 11 ቀን 1994 ዓ.ም የፈፀመው የቤት ሽያጭ ውለ ተጠሪዎችን የሚያስገድድና ፈራሽ ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል። በአንደኛ አመልካች የተጠሪዎች ወኪል ነኝ በማለት ከሁለተኛ አመልካች ጋር የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል ተጠሪዎችን የሚያስገድድና ፈርሽ ነው በማለት ወስነናል።
የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ሁለተኛ አመልካች በተጠሪዎች ላይ የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ ለማቅረብ አይችልም በማለት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ አመልካች በተጠዎች ላይ ያቀረበውን የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ ፣ ተጠሪዎች ሁለተኛው አመልካች ባቀረበው የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ ላይ ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያዎችና ላልች የፍሬ ጉዲይና የህግ ክርክር ፣ የግራ ቀኙን ማስረጃ በመስማትና በመመርመር ውሣኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት 341/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ጥር 19 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. የሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል ይፃፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.