No summary available.
የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- 1.አቶ አካለ አለሙ - ጠበቃ ወልደሥላሴ ብርቱ ጋር ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የገቢዎችና ጉምሩክ ዐቃቤ ሕግ - የቀረበ የለም።
መዝገቡ ከሰ/መ/ ጋር እንዱጣመር የታዘዘ በመሆኑ ሁለቱም መዛግብት ተመርምረው ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ከጉምሩክ አዋጅ ጋር የተያያዘ የወንጀል ጉዲይን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካቾች ላይ በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- 1ኛ አመልካች አቶ አካለ ዓለሙ እ.ኤ.አ ከ1990 እስከ አፔሪል 2004 ድረስ ከአሜሪካ ቆይተው ወደ አገራቸው ሲመለሱ በተሰጣቸው የቀረጥና ታክስ ነፃ መብት በመቀጠም የሰላዲ ቁጥር 2-544552 አ.አ. የሞተር ቁጥር LM7-5892294፣ የሻንሲ ቁጥር 4T23 F 13 C64 UZ 79592 ቶዮታ፣ ከጃፒን መኪና አስገብተው ለአሁኑ ሁለተኛ አመልካች አቶ ተስፊዬ ጸጋዬ አሳልፈው በመስጠት እንዱጠቀሙበት ማድረጋቸውን፣ እንዱሁም ይህንኑ ተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለበት ለግል መገልገያ የገባ በማንኛውም አገልግልት ላይ የማይውል መሆኑን እያወቁ ለብር 259,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ሺህ ብር) ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ መኪናውን በመያዣነት በመስጠት ብድር የወሰደ መሆናቸውን፣ ሁለተኛ አመልካች ደግሞ ከላይ የተገለጸውን መኪና ከቀረጥና ከታክስ ነፃ የገባ መሆኑን እያወቁ ወይም ማወቅ ሲገባቸው ከአንደኛው አመልካች ተቀብለው እየተገለገለበት እያለ ሕዲር 23 ቀን 2001 ዓ.ም. ከቀኑ በግምት 9፡00 ሰዓት ሜክሲኮ አደባባይ ከሚባለው አካባቢ ሲያሽከረክሩ የተያዙ መሆናቸውን በመዘርዘርና በኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1(ሀ(ለ)) እና የጉምሩክ ባለስልጣንን እንደገና ለማቋቋምና አሰራሩን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 60/1989 እንደተሻሻለ አዋጅ ቁጥር 368/1995 አንቀፅ 73(1(ሀ እና ለ)) ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ተላልፈዋል በሚል አመልካቾች በወንጀል እንዱጠየቁ ክስ ማቅረቡን የሚያሳይ ነው። አመልካቾች በዚህ መልኩ የቀረበባቸውን ክስ ክድው ተከራክረው አቃቤ ሕግ አለኝ ያላቸውን ማስጃዎችን አቅርቦ አሰምቷል። አመልካቾች እንዱከላከለ ተደርጎም የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በመከላከያነት አቅርበዋል። የስር ፍርድ ቤትም የአመልካቾች መከላከያ ማስረጃዎች እርስ በርሳቸው የሚጋጩ መሆናቸውን ጠቅሶ የዐቃቤ ሕጉን ማስረጃዎችን ሉያስተባብለ የሚችለ አይደለም በሚል ምክንያት ክብደት ባለመስጠት ውድቅ አድርጎ አመልካቾችን በአቃቤ ሕግ በኩል ተጠቅሶ በቀረበባቸው ክስ መሰረት ጥፊተኛ አድርጎ አንደኛውን አመልካች በዘጠኝ ወር፣ ሁለተኛውን አመልካች ደግሞ በስድስት ወር እስራት፣ እንዱሁም ብር 170,603.21 (አንድ መቶ ሰባ ሺህ ስድስት መቶ ሶስት ብር ከሃያ አንድ ሳንቲም) እንዱቀጡ የወሰነ ሲሆን የእስራት ቅጣቱን እያንዲንዲቸው በሁለት አመት ገደብ ሁነው በውጪ እንዱጨርሱ፣ በኢግዚብትነት የተያዘው መኪና ደግሞ ለመንግስት እንዱወረስ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። አመልካቾች የሰበር አቤቱታቸውን በተለያዩ መዛግብት ያስከፈቱ ቢሆንም ጉዲዮቹ አንድ ላይ ተጣምረው እንዱታዩ ተደርጓል። የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም አንደኛው አመልካች በውጪ አገር ባፈሩት ገንዘብ በአገር ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ በሕጉ አግባብ ፈቃድ ወስደው አከራካሪውን መኪና በመያዣነት በባንኩ መመሪያና አሰራር መሰረት ያስያዙ መሆኑና ለጥገና ለሁለተኛው አመልካች አሳልፈው የሰጡ መሆኑ በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች ተረጋግጦ እያለ ጥፊተኛ መባላቸው ያላግባብ መሆኑን፣ 2ኛ አመልካችም ተሽከርካሪውን በወቅቱ ይዘው የተገኙት ባላቸው ሙያ የተሸከርካሪ ጥገና አገልግልት ለመስጠት ሁኖ እያለ ጥፊተኛ መባላቸው ያላግባብ መሆኑን ዘርዝረው የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ እንዱሻር ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበት ተጠሪን ያስቀርባል ተብል ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ክሱን ሉመሰርት የቻለው 1ኛ አመልካች ያለቀረጥ መብት ተጠቃሚ በመሆን ከውጪ ያስገቡትን የቤት መኪና በሕግ ላልተፈቀደለት ሰው አገልግልት ላይ እንዱውል አድርገዋል፣ እንዱሁም ተሽከርካሪውን ለግል መገልገያ የገባና ለላላ ማናቸውም አገልግልት ላይ የማይውል መሆኑን እያውቁ ከባንክ ለወሰደት ብድር መያዣ ሰጥተው ተገኝተዋል በሚል ሲሆን 2ኛው አመልካችም የ1ኛ አመልካች መኪና ከቀረጥና ከታክስ ነፃ የገባ መሆኑን እያወቁ ወይም ማወቅ ሲገባቸው ከ1ኛ አመልካች ተቀብለው እየተገለገለበት እያለ ተይዘዋል በሚል መሆኑን ነው። 1ኛ አመልካችም ሆነ 2ኛ አመልካች መኪናው በሕጉ (አዋጅ ቁጥር 60/89 በአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 73(2) እንደተሻሻለ) ቤተሰብ ተብለው ከተቀመጡት ውጪ በሆነ ሰው ሲሽከረከር በተጠሪ መያዙን ሳይክደ መኪናው በተያዘበት ወቅት መኪናውን ሲያሽከረክሩት የነበሩት የአሁኑ 2ኛ አመልካች መኪናውን በወቅቱ ይዘው የተገኙት ለጥገና ወደ ጋራዥ ለመውሰድ ነው የተያዘው በማለት የሚከራከሩ መሆኑን ነው። በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካቾችን ክርክር የበታች ፍርድ ቤቶች ውድቅ ያደረጉት የግራ ቀኙን ማስረጃዎችን መርምረው የአመልካቾች መከላከያ ማስረጃዎች ቃል እርስ በርሱ የሚጋጭ በመሆኑ ሉታመን የሚችል አይደለም በሚል ነው። በልላ አገላለፅ የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካቾችን ክርክር ውድቅ ያደረጉት ፍሬ ነገርን አጣርተውና ማስረጃቸውን መዝነው ነው።
የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በግልፅ የሚያሳየው አመልካቾች የመከላከያ ጭብጣቸውን ለማስረዲት የአቀረቧቸው ማስረጃዎች ታይተው ክብደት የሚሰጣቸው ባለመሆኑና የአቃቤ ሕጉን ማስረጃዎች ሉያስተባብለ ያልቻለ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በመገንዘብ ውሳኔ መስጠቱን ነው። እንግዱህ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮችን መሰረት በማድረግና ማስረጃን በመመዘን የተሰጠ ነው ከተባለ የአመልካች የሰበር ቅሬታ የሚያሳየው የስር ፍርድ ቤት ፍሬ ነገርን በማጣራትና ማስረጃን በመመዘን ረገድ ስህተት ሰርቷል የሚል ይዘት ያለው መሆኑ ግልፅ ነው። እንደሚታወቀው ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ))እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 10 መሰረት የተሰጠው ስልጣን በማናቸውም የመጨረሻ ፍርድ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መፈጸሙ ሲረጋገጥ ይህንኑ ስህተት ማረም ነው። በመሆኑም የማስረጃ ምዘና ጉዲይ የመሰረታዊ ሕግ ስህተት መመዘኛን ሉያሟላ የሚችል ባለመሆኑ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የሚታይበት አግባብ የለም። አመልካች መኪናው ለቤተሰብ አገልግልት ሲውል የነበረ መሆኑን ባላስረደበት ሁኔታ የሕግ ጥያቄ የሚነሳበትን ምክንያት አላገኘንም። እንዱሁም ለግል መገልገያ ከቀረጥና ከታክስ ነፃ የገባ መኪናን ከባንክ ብድር ለመውሰድ የባንኩን መመሪያና ስርዓት መሰረት በማድረግ በመያዣ መስጠትም ከአዋጅ ቁጥር 280/1994 እና የአዋጅ ቁጥር 60/1989 ማሻሻያ ከሆነው አዋጅ ቁጥር 345/1995 የተፈፃሚነት ጊዜ ቅደም ተከተል አኳያ ከሚኖረው የሕጎቹ አተረጓጎም መርህ አንፃር ሲታይ 1ኛ አመልካችን ከወንጀል ተጠያቂነት ነጻ ሉያደርጋቸው የሚችል ሕጋዊ ምክንያት አይደለም።
እንዱሁም 1ኛ አመልካች የተከሰሱት ለቤተሰብ አግልግልት እንዱውል ከቀረጥና ከታክስ ነፃ የገባ መኪና ለብድር መያዣነት ሰጥተዋል በሚል እንጂ ለኢንቨስትመንት የተፈቀደላቸውን መኪና ለብድር መያዣ ሰጥተዋል በሚል ባለመሆኑና አቃቤ ሕጉም እንደክሱ ያረጋገጠ በመሆኑ 1ኛ አመልካች አዋጅ ቁጥር 280/1994ን መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡት ክርክር ሕጋዊ መሰረት ያለው ሁኖ አልተገኘም።
ላላው አመልካቾች ያቀረቡት ቅሬታ የገንዘብ መቀጮን በተመለከተ ሲሆን የአመልካቾች የቅሬታ ይዘት አመልካቾች እያንዲንዲቸው ብር 170,603.21 ሉከፍለ ይገባል ተብል በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ነው። የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካቾች ይህንኑ ገንዘብ እያንዲንዲቸው እንዱከፍለ የወሰነው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በጥቅለ አመልካቾች ብር 170,603.21 የገንዘብ መቀጮ ሉከፍለ ይገባል በማለት በሰጠው የውሳኔ ክፍል የአሁኑ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኙን በማቅረቡ ነው። ከዚህ ከፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ መገንዘብ የሚቻለው የገንዘብ መቀጮው አመልካቾች እያንዲንዲቸው እንዱከፍለ የተወሰነ መሆኑን ነው። እኛም የውሳኔውን ሕጋዊነት ተመልክተናል። አመልካቾች በወንጀል ህግ ቁጥር 32/1/ሀ እና አዋጅ ቁጥር 60/89 በአዋጅ ቁጥር 345/1995 እንደተሻሻለ አንቀጽ 73(1) በመተላለፍ ወንጀል የፈፀሙ ጥፊተኞች መሆናቸውን ተረጋግጧል። አመልካቾች ጥፊተኛ የተባለበት ድንጋጌ በእስራትና በገንዘብ መቀጮ በጣምራ የሚያስቀጣ የወንጀል ድርጊት ነው። ቅጣት የሚወሰነው የእያንዲንደን ጥፊተኛ ግላዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነና ወንጀልና የወንጀል ቅጣት ግላዊ መሆናቸውንና ከአንደ ወደ ላላው የማይተላለፍ መሆኑ በ1996 በወጣው የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 41 ስር ከተደነገገው መሰረታዊ መርህ ለመረዲት የምንችለው ጉዲይ ነው። ከዚህ አንፃር የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአመልካቾች ላይ የገንዘብ መቀጮ የወሰነው የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት በመቀበል አመልካቾች ያላቸውን የቅጣት ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶችና በህጉ የተቀመጠውን ዝቅተኛ የገንዘብ መቀጮ መነሻ በማድረግና በማገናዘብ ነው። ስለሆነም እያንዲንዲቸው ጥፊተኛ ሆነው የተገኙበት የህግ ድንጋጌ በወቅቱ ለመንግሥት ይከፈል የነበረውን ቀረጥና ታክስ ገንዘብ መነሻ በማድረግ ፍርድ ቤቱ ሉወሰን የሚችል መሆኑን የሚደነግግ ነው።
በመሰረቱ ወንጀል በመፈፀሙ የሚወሰነው የገንዘብ ቅጣት በወንጀል ሕጉ የቅጣት አወሳሰን መርሆችን መሰረት በማድረግ የሚወሰን ነው። በወንጀል ጥፊተኛ በተባለ ሰዎች ላይ የሚጣለው የገንዘብ መቀጮ በፍታብሓር ለመንግሥት ሣይከፈለው የቀረውን ቀረጥና ታክስ በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍል ለማድረግ ከሚቀርብ ክስና ከሚሰጥ ውሳኔ በእጅጉ የተለየ ነው። በተያዘው ጉዲይ አይነት ለሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶች በአጥፉዎች ላይ የሚጣለው የገንዘብ መቀጮ በፍታብሓር ክርክር ጊዜ በአንድነትና በነጠላ ኃላፉነት ጋር ተመሳሳይነት የላለውና በእያንዲንደ አጥፉ ላይ ሉጣል የሚገባው መሆኑን ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ በቀረበው ጉዲይ ላይ በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) ድንጋጌ መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። ይህ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም በሕጉ አግባብ አልተለወጠም። በመሆኑም በአመልካቾች ላይ የተጣለው የገንዘብ ቅጣት ከሰ/መ/ የሕግ ትርጉም አንፃር ሲታይ የሚነቀፍ ሁኖ አልተገኘም። በአጠቃላይ አመልካቾች ለድርጊቱ በወንጀል ጥፊተኛ መሆናቸውም ሆነ እያንዲንዲቸው ለመኪናው ይከፈል የነበረውን ቀረጥና ታክስ መከፈል ያለበት ገንዘብ ለፈፀሙት ወንጀል በመቀጫነት እንዱከፍለ ተብል የተሰጠው ውሳኔ ቀደም ሲል በተመሳሳይ ሁኔታ በሰ/መ/ እና በላልች በርካታ መዛግብት ከተሰጡት ውሳኔዎች ጋር የተጣጣመ በመሆኑ ውሳኔው የወንጀል ህጉን መሰረታዊ የማስረጃ አመዛዘንና የቅጣት አወሳሰን መርሆች የተከተለና መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 09 ቀን 2003 ዓ.ም.
የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ፣ ይኸው ፍርድ ቤት በተጠቃሹ መዝገብ ህዲር 03 ቀን 2003 ዓ.ም. የሰጠው የቅጣት ውሳኔ፣ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 17/08/2003 ዓ.ም. በመ/ ሚያዚያ 19 ቀን 2003 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195(2(ለ-2)) መሰረት ፀንተዋል።
No topics extracted.