No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 18 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፉሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የቦላ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ፅ/ቤት ተጠሪ፡- አቶ ሚሉዮን አሰፊ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ አንድ በሕጉ አግባብ ደረጃው ተለይቶ ግብሩን ሲከፍል የቆየ ግብር ከፊይ የገቢ መጠኑ ሲሻሽል የግብር ከፊይነቱ ደረጃ ለወጥ የሚወሰነው በግብር አስገቢው ባለስልጣን ነው ወይስ በግብር ከፊዩ ነው? የሚለውን ጥያቄ የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ሲሆን በዚህ አካል ይግባኝ ያቀረቡት የአሁኑ ተጠሪ ናቸው።ተጠሪ ለዚህ አካል ባቀረቡት የይግባኝ ቅሬታ በጥብቅና አገልግልት የጥብቅና ፈቃድ በደረጃ "ሐ" ከፊይነት ያወጡ መሆኑ፣የአሁኑ አመልካች መስሪያ ቤት ከደረጃ "ሐ" ግብር ከፊይነት ወደ ደረጃ "ለ" ግብር ከፊይነት እንዱሻሻል የሰጠው ውሳኔ ሳይኖር ተርን ኦቨር ታክስ አሳውቀህ አልከፈልህም፣የ ደረጃ ለ ግብር ከፊይ ሁነህ መዝገብ ሳትይዝ ቀርተሃል በሚል መዝገብ ባለመያዝ ቅጣት የጣለባቸው መሆኑንና ይህ ተግባር ከአዋጁ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 48(1)፣89(1) እና ከደንብ ቁጥር 78/1994 አንቀጽ 22(2) ድንጋጌዎች አንፃር ሕጋዊ ያለመሆኑን ገልፀው የአመልካች መስሪያ ቤት ውሳኔ እንዱሻርላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል።ጉባኤውም የአሁኑ አመልካች መልስ እንዱሰጥበት ያደረገ ሲሆን አመልካች ባቀረበው መልስም ተጠሪ አመታዊ ገቢያቸው ከብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በላይ በመሆኑ የደረጃ "ለ" ግብር ከፊይ መሆናቸውን እንደሚያሳይ፣የደረጃ ለ ግብር ከፊይ ደግሞ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እስካልሆነ ድረስ በደረጃው የሚጣለውን ማንኛውንም ታክስ መክፈል እንደሚኖርበት፣ በዚህም መሰረት በተቀመጠው የመክፈያ ወቅት ሉከፍለ እንደሚገባ ስለሚታወቅ ሉከፍለ እንደሚገባ፣ ገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤቱም በወቅቱ ባልከፈለውና ሉከፈል በሚገባው ግብር መነሻነት መዝገብ ካለመያዝ መቀጫ መጣለ በሕግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት መሆኑን፣ተርን ኦቨር ታክስ በአዋጅ ቁጥር 308/1995 አንቀፅ 3 መሰረት ከታክስ ነፃ ካልተደረገ በቀር በተጨማሪ እሴት ታክስ ያልተመዘገቡ ሰዎች ከአገር ውስጥ በሚሸጧቸው እቃዎችና አገልግልት ላይ ተርን ኦቨር ታክስ እንደሚከፈል በግልፅ የተቀመጠና ተጠሪ ቅሬታ በቀረበባቸው ዘመናት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ባለመሆናቸው የተርን ኦቨር ታክስ የመክፈል ግዳታ እንደአለባቸው፣መዝገብ ባለመያዝ የተጣለው ቅጣትም ከደረጃ "ሐ" ግብር ከፊዮች በስተቀር በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ በሙለ /በከፉል/ የሚከራዩ ሕንጻዎች ባለቤት የሆኑ የሑሳብ መዝገብና ሰነድችን የመያዝ ግዳታ በህግ የተጣለባቸው መሆኑን፣ማናቸውም የግብር ከፊይ ለአንድ የተወሰነ የግብር ዘመን መያዝ የሚገባውን ተገቢ የሂሳብ መዝገብና መግለጫ ያልያዘ እንደሆነ የተወሰነበትን ግብር 20% መቀጫ እንደሚከፍል በሕጉ መመልከቱን፣ተጠሪውም የደረጃ "ለ" ግብር ከፊይ በመሆናቸው የሂሳብ መግለጫ ለመያዝ ግዳታ ባለመወጣታቸው የተቀጡ መሆኑንና ይህንንም ለማድረግ የአሁኑ አመልካች በሕጉ ስልጣን የተሰጠው መሆኑን ዘርዝሮ ተከራክሯል። ክርክሩ በዚኅ መልክ የቀረበለት ጉባኤም ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪ የደረጃ "ለ" ከፍይነት ደረጃውን ራሱ መለወጥ ነበረበት የሚለው የአሁኑአመልካች ክርክር የሕግ ድጋፍ የላለው መሆኑንና ከ1999 እስከ 2001 ዓ.ም. ድረስ ያለውን ፍሬ ግብር አመልካች ከተጠሪ ሙለ በሙለ ከተቀበለ በኋላ መቀጫው መወሰኑ የህግ ድጋፍ እንደላለው በምክንያትነት ይዞ የአመልካችን ውሳኔ ውድቅ አድርጎ ተጠሪ መቀጫውን ሉከፍለ አይገባም ሲል ወስኗል።በዚኅ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ተጠሪ የግብር ከፊይነት የደረጃ ለውጡን ራሳቸው አውቀው የደረጃ ለ ግብር ከፊይ በሕጉ የተጣለበትን ግዳታ መወጣት ሲገባቸው የአሁኑ አመልካች መስሪያ ቤት የደረጃ ለውጥ ውሳኔ አላሳወቀኝም በማለት የሚያቀርቡት ክርክርና የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የሰጠው ውሳኔ ሕጋዊ አይደለም የሚል ምክንያት በመያዝ የጉባኤውን ውሳኔ በመሻር በመቀጫ ላይ የአሁኑ አመልካች መስሪያ ቤት በተጠሪ ላይ የሰጠውን ውሳኔ አስመልክቶ ጉባኤው የመሰለውን እንዱወስን ጉዲዩን መልሶ ልኮለታል። ከዚህም በኋላ የአሁኑ ተጠሪ የሰበር አቤቱታቸውን ለከተማው ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የደረጃ ለውጥ ውሳኔ መሰጠት ያለበት በግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት እንጂ በግብር ከፊዩ ላሆን አይገባም በሚል ምክንያት የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ተሸሮ የጉባኤው ውሳኔ በድምጽ ብላጫ ጸንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪ የደረጃ "ሐ" ግብር ከፊይ ሁነው ቆይተው ገቢያቸው ማደጉን ራሳቸው አውቀው በደረጃ ለ ፍሬ ግብሩን ሲከፍለ ከቆዩ በኋላ የደረጃ ለውጥ ስለመኖሩ አመልካች መስሪያ ወስኖ ስላላሳወቀኝ በደረጃ "ለ" ግብር ከፊይነት መዝገብ የመያዝ ግዳታ የለብኝም በማለት የሚያቀርቡትና በከተማው ሰበር ሰሚ ችልት አብላጫ ድምፅ ተቀባይነት ያገኘው ክርክር ሕጋዊ ድጋፍ የለውም በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው።አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው ስለመሆኑ ታምኖ ለዚህ ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በጽሐፍ በሰጡት መልስ የአመልካች መስሪያ ቤት ክርክር የሕግ ድጋፍ የላለው መሆኑን ያሳያለ ያሎቸውን ምክንያቶችን አንስተው ተከራክረዋል። የአመልካች መስሪያ ቤት ነ/ፈጅም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሱን አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙኝ ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።እንደመረመረውም የግብር ከፊይ ደረጃ ለውጥ መኖሩን የመወሰን ስልጣን የግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ስልጣን ነው? ወይስ የግብር ከፊዩ ነው?
የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ የተሰማሩበት የገቢ ማስገኛ ስራ 1ኛ ደረጃ የጥብቅና ስራ ሲሆን የተጠየቁትም የ1999፣2000 እና የ2001 ዓ.ም. የግብር ዘመን መዝገብ ባለመያዛቸው ቅጣት እንዱከፍለ እንዱሁም በ1999 እና 2000 ዓ.ም. የግብር ዘመን የተርን ኦቨር ታክስ ፍሬ ግብር፣ገቢን ባለማስታወቅ ግብር በጊዜ ባለመክፍል ቅጣት እንደተወሰነባቸው የአመልካች መስሪያ ቤት የውሳኔ ማስታወቂያ የሚገልጽ መሆኑን ተጠሪ የአመልካች መስሪያ ቤትን ውሳኔ እየተቃወሙ ያለት የደረጃ ሐ ግብር ከፊይ በመሆን ገቢዬን ሳልደብቅ ያስታወቅሁና የተወሰነውን ግብር የከፈልኩ ስለሆነ ግብር አስገቢው ባለስልጣን ደረጃዬን ሳይለውጥ በደረጃ ለ ግብር ከፊይ፣የተርን ኦቨር ታክስ ክፈል፣ገቢ ባለማስታወቅና በጊዜ ባለመክፈል እንዱሁም መዝገብ ባለመያዝ ልቀጣ አይገባም በማለት የሚከራከሩ መሆኑን የክርክሩ ሂደት የሚያሳይ መሆኑን፣ተጠሪ አመታዊ ገቢአቸው ብር 100,000.00 ስለመሆኑ ገልፀው በዚህ አግባብ ጥሬ ግብሩን ሲከፍለ የነበሩ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ መረጋገጡን ነው።
በመሰረቱ ግብር አስፈላጊነቱ ዘርፈ ብዙ በመሆኑ ሕጉ ይህንኑ የግብር አስፈላጊነት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባትና የግብር አሰባሰብ ስርዓቱን ውጤታማና ቀልጣፊ ለማድረግ በማሰብ በግብር ከፊዩም በአጠቃላይ፣እንደታክስ ከፊይነቱ ደረጃና እንደ ታክሱ አይነት በታክስ ከፊዩ ላይ የጣለው ግዳታ ያለ ሲሆን በግብር ሰብሰቢ መስሪያ ቤት ላይም የጣለው ግዳታ መኖሩ የሚታወቅ ነው።ሁለም የግብር ከፊይ ተገቢ በሆነው የሂሳብ አያያዝ ስርኣትና የታክስ ባለስልጣኑ በሚያስቀምጠውና በሚፈቀደው አኳኋን የሑሳብ መዛግብትንና ደጋፉ ሰነድችን አሰናድቶ በስራ ሂደቱ መጠቀም ግዳታው ተብል ከሚጠቀሱ ነጥቦች አንደ ስለመሆኑ ከገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል ከወጣው አዋጅ ቁጥር 608/2001፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል ከወጣው አዋጅ ቁጥር 609/2001፣ ከተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ ቁጥር 308/1995 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል ከወጣው አዋጅ ቁጥር 611/2001፣ከኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 307/1995 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል ከወጣው አዋጅ ቁጥር 610/2001 እንዱሁም ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 78/1994 እና በስራ ላይ ካለት ላልች አዋጆች፣ደንቦች፣መመሪያዎች ጠቅላላ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው።
ከላይ የተዘረዘሩት ሕጎችን ግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤትን ከአቋቋመው አዋጅ ቁጥር 587/2001 ጋር አንድ ላይ ስንመለከትም ግብር ሰብሰቢ መስሪያ ቤት ግብር የሚሰበሰብበትን ጊዜና ቦታ፣እያንዲንደ ግብር ከፊይ የሚከፍለውን የግብር መጠን እንዱሁም ግብር የሚሰበሰብበትን ሁኔታ የግብር መስብሰቢያ ጊዜ ከመድረሱ በፉት በማያሻያማና ግልፅ በሆነ ሁኔታ ለግብር ከፊዩቹ ማሳወቅ ያለበት መሆኑን ያስገነዝባለ።ይህ በታክስ ስርዓት ግልጽነት እንዱኖር የሚያደርግ ሲሆን በታክስ ሕግ ጽንሰ ሀሳብም ሙለ ተቀባይነት ያለውና በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 12 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ አንፃር ሲታይም በአግባቡ ሉተገበር የሚገባው ጉዲይ ነው።ከላይ የተጠቀሱት ሕጎች፣ደንቦችና በስራ ላይ ያለ መመሪያዎች በአጠቃላይ ሲታዩ ለግብር ሰብሰቢው መስሪያ ቤት ስልጣን ሰጪ ሲሆኑ መስሪያ ቤቱ ግብርን በወቅቱ የማስከፈል፣ግብር ከፊዩቹ የገቢና ወጪ ሰነድ ካልያዙ የግብር ክፍያ መጠንም ተምኖ የማስከፈልን፣ግብር ከፊዩ በግብሩ አከፊፈል ስርኣት የግብር ህጎችን፣ደንቦችንና አግባብነት ያላቸውን መመሪያዎችን ጥሶ ከሆነ በሕግ እንዱጠየቅ ማድረግን፣የግብር ከፊዩን ንብረት መያዝንና የመሳሳለት ስልጣንና ተግባራት ያለት መሆኑን ያስገነዝባለ።እነዚህን ስልጣንና ተግባራት ለመወጣት ደግሞ ግብር ከፊዬችን ደረጃውን የመለየት እና በተገቢው መንገድ ማሳወቅ ያለበት መሆኑ ይታመናል። ሕጉ በግብር ከፊዩ ላይ ከጣላቸው መሰረታዊ ግዳታዎች መካከል ገቢን ማሳወቅና በሕጉ አግባብ ግብሩን መክፈል ነው።ገቢን የማሳወቅ ተግባር ለግብር ከፊዩ ደረጃ አወሳሰን ወሳኝ ሂደት ሲሆን ግብርን ለመክፈልም ቀድሞ መሟላት ያለበት ሁኔታ ነው።ይህ የማሳወቅ ተግባር ደግሞ በሕጉ አግባብ ለእያንዲንደ የግብር አይነት በሕግ በተቀመጠለት ጊዜና ባለስልጣኑ ተገቢ ነው ባለው መንገድ ተገቢውን ማስረጃ /ቅፅ /በመሙላት መካሄድ ያለበት ጉዲይ ነው።በአግባቡ ያልተያዘ መዝገብም ሆነ በሕግ በተወሰነው ጊዜ ያልተከናወነ ገቢውን አሳውቆ ግብር መክፈል ድርጊት መቀጫን የሚያስከፍል ከመሆኑም በላይ በወንጀል ጭምር ሉያስቀጣ የሚችል ነው።
በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 11፣ 14 እና 17 ድንጋጌዎች ስር እንዱሁም በደንብ ቁጥር 78/1994 አንቀጽ 18 ስር የግብር ከፊዮች ደረጃ ተዘርዝሯል።እነዚህ ድንጋጌዎች ለግብር ከፊዮች ደረጃ መሰረት ያአደረጉት አንደ መነሻ የግብር ከፊዩን የአመታዊ ገቢ መጠን ነው።የደንብ ቁጥር 78/1994 የእያንዲንደ ደረጃ ግብር ከፊይ ስላለበት ግዳታ በግልጽ ያሳያል።በዚህም መሰረት የደንቡ አንቀፅ 19 መዝገብ የመያዝ ግዳታ ያለባቸው ግብር ከፊዮች ደረጃ "ሀ" እና ደረጃ "ለ" መሆናቸውን የሚያሳይ ሲሆን የአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 48(1) ድንጋጌ የደረጃ "ሐ" ግብር ከፊዮች መዝገብ የመያዝ ግዳታ የላለባቸው መሆኑን ሲደነግግ የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ ቀጥር 308/1995 አንቀፅ 10 ደግሞ የተርን ኦቨር ታክስ ማስታወቂያ ማቅረብና ታክሱን የመክፍል ግዳታ የተለያየ መሆኑን ያሳያል።አንድ ግብር ከፊይ በወጣለት ደረጃ መሰረት ግብር የመከፍለ ሁኔታ ሉቀጥል ወይም ሉለወጥ የሚችልበት አግባብ ስለመኖሩም ደንብ ቁጥር 286/1994 በአንቀፅ 22(2) ስር ተደግንጓል።በዚህ ድንጋጌ አግባብ የግብር ከፊይ ደረጃ በነበረው ደረጃ እንዱቀጥል ወይም እንዱለወጥ የሚደረገው ግብር ከፊዩ የሚያቀርበውን መግለጫ፣መረጃዎችንና የአከባቢ ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ ሲሆን ይህ ተግባር በግብር አስገቢው ባለስልጣን መስሪያ ቤት ሉከናወን የሚችለው ለጉዲዩ ያገኛቸውን ማስረጃዎች በመመርመርና ክብደታቸውን በመመልከት ስለመሆኑ የድንጋጌው ይዘትና መንፈስ ያሳያል።ሕግ አውጪው በደንቡ አንቀፅ 18 ስር ለግብር ከፊዮቹ ደረጃ ከአወጣላቸው በኋላ በዚሁ አግባብ ደረጃው ቀጣይነት ሉኖር የማይችልበት አጋጣሚ እንደሚኖር በመገመት የደረጃ ለውጡን ባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ሉወስን የሚችበትን አግባብ በደንቡ አንቀፅ 22(2) ስር በግልፅ አስፍሯል።ይህ ድንጋጌ ግብር አስገቢው መስሪያ ቤት የደረጃ ለውጡን ሉወስን ይችላል ብል ፈቃጅነት ባለው ሁኔታ መደንገጉ ግልፅ ሲሆን ይኸው የድንጋጌው ቅርፅና ይዘት ግን የደረጃ ለውጡ በግብር አስገቢው ባለስልጣን ሳይወሰን ቢቀር ግብር ከፊዩ በራሱ የደረጃ ለወጡን መወሰን ያለበት ስለመሆኑ አያስገነዝብም።ግብር ከፊዩ በራሱ ጊዜ የደረጃ ለውጡን መወሰን አለበት ከተባለ በግብር አሰባሰብ ስርዓት ላይ የራሱ የሆነ አለታዊ ተእፅኖ ሉያስከትል እንደሚችል የሚታመን ነው።የኸውም ግብር ከፊዩ ገቢውን አሳንሶ በማቅረብ ሉከፍል የሚገባውን ግብር ሳይከፍል እንዱቀር የማድረግና በታክሱ ስርዓቱ ላይ የማጭበርበር ድርጊት እንዱስፊፊ ሰፉ በር የሚከፍት መሆኑ ይታመናል።የግብር ሰብሳቢ ባለስልጣኑን ከአቋቋመው አዋጅ ቁጥር 587/2001ም ሆነ ከገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 38 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው የግብር አስገቢው ባለስልጣን በግብር ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የቁጥጥር ስራ በማድረግ የግብር ስርዓቱን ውጤታማና ቀልጣፊ የማድረግ ሃላፉነት ና ተግባር የተሰጠው መሆኑን ሲሆን ይህንኑ የባለስልጣኑን ሃላፉነትና ተግባር ውጤታማ እንዱሆን ከግብር ከፊዩ የሚጠበቀው ግዳታ በሕጉ የተጣለበትን ግዳታ መወጣት ነው።በግብር ከፊዩ ላይ በሕጉ የተጣለበት ግዳታዎች በባለስልጣኑ መስሪያ ቤት በወጣለት ደረጃ መሰረት ግብሩን በወቅቱ፣በተገቢው ቦታና ሁኔታ መክፈል እንጂ ደረጃውን ጭምር ግብር ከፊዩ አውጥቶ ግብርን እንዱከፍል አይደለም።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪ የደረጃ "ሐ" ግብር ከፊይ ሁነው ከ1999 እስከ 2001 ዓ.ም.
ድረስ ያገኙትን ገቢ ሳይደብቁ ገቢያአቸውን ለአመልካች መስሪያ ቤት ማሳወቃቸው፣ግብር ባለመክፈል ወይም አሳንስው በማሳወቃቸው የተወሰነባቸው ቅጣት የላለ መሆኑ፣በአዋጅ ቁጥር 308/1995 አንቀፅ 10(2(ሐ)) መሰረት ተጠሪ ግዳታቸውን አልተወጡም የሚል ክርክር በአመልካች በኩል ያለመቅረቡን ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያለው ጉባኤው ያረጋገጠው ጉዲይ ነው። እንዱህ ከሆነ አመልካች አሁን አጥብቆ የሚከራከረው ተጠሪው ገቢያቸው ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ መሆኑን እያወቁ የግብር ከፊይነት ደረጃቸውን ከደረጃ "ሐ" ወደ ደረጃ "ለ" ራሳቸው ከፍ አድርገው በመወሰን የደረጃ "ለ" ግብር ከፊይ ያለበትን መዝገብ የመያዝ ግዳታ መወጣት ነበረባቸው በማለት ነው።ይሁን እንጂ ከላይ በዝርዝር ከተመለከትናቸው የሕግ ድንጋጌዎች ይዘትና አላማ አንጻር ሲታይ አንድ ግብር ከፊይ ገቢውን በሕጉ አግባብ ለግብር አስገቢው መስሪያ ቤት ከማሳወቅ ውጪ ደረጃውን ራሱ ሉወስን እንደሚገባ በሕጉ ግልጽ ግዳታ የተጣለበት ባለመሆኑና የግብር ከፊዩን ደረጃ ለውጥ የመወሰን ስልጣን የግብር አስከፊዩ መስሪያ ቤት በመሆኑ አመልካች ተጠሪ ላይ መቀጮ የሚጥልበት ሕጋዊ መሰረት የለም።የአመልካቹ ክርክር የግብር ከፊዩን መብትና ግዳታ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ሃላፉነትና ተግባር ጋር ያላገናዘበና ለታክስ ስርዓቱ ውጤታማነትና ቀልጣፊነትም አለታዊ ውጤት ያለው በመሆኑ ተቀባይነት የላለው ሲሆን የአዱስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ በአንፃሩ የአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 38፣የደንብ ቁጥር 78/1994 አንቀፅ 18 እና 22፣የአዋጅ ቁጥር 308/19995 አንቀፅ 10(2(ሐ)) እንዱሁም አዋጅ ቁጥር 587/2001 እና ተቀባይነት ያላቸውን የታክስ ህግ መርሆችን ያገናዘበ ሁኖ አግኝተናል።በዚህም ምክንያት በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመ/ ሐምል 20 ቀን 2003 ዓ.ም. በአብላጫ ድምፅ የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
የአንድ ግብር ከፊይ ደረጃ ለውጥ ሉወሰን የሚገባው በግብር ከፊዩ ሳይሆን በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ነው ብለናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል
No topics extracted.