No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዚያ 9 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገብረሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ዘመነ ዮሐንስ ጀኔራል ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጠበቃ ሙለጌታ ፀጋዬ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ዲውድ ኢብራሂም ጠበቃ ክፍላ ታደሰ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የመጋዘን ኪራይ ውል አከፊፈል የሚመለከት ነው። አመልካች ከተጠሪ ለተከራየው መጋዘን የስድስት ወር ኪራይ ብር 78,000 (ሰባ ስምንት ሺህ ብር) እንዱከፍለው ተጠሪ ክስ አቅርቧል። አመልካች ይህንን ገንዘብ የምከፍለው፣ የመንግስት ግብር ቅናሽ ተቀንሶ መሆን ይገባዋል በማለት ተከራክሯል። ተጠሪ ግብር ሣይቀንስ ሉከፍለኝ ይገባል በማለት ተከራክሯል። የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ግብር ሣይቀንስ የቤቱን ኪራይ ብር 78,000 (ሰባ ስምንት ሺህ ብር) ለተጠሪ ይክፈል በማለት ውሣኔ ሰጥተዋል።
አመልካች የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የውሣኔ አዋጅ ቁጥር 286/1994 ድንጋጌዎችን የሚጥስና በእኔም ላይ የወንጀል ተጠያቂነት እና አስተዲደራዊ ቅጣት የሚያስከትል ስለሆነ በሰበር ይታረም በማለት የካቲት 10 ቀን 2003 ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ የግብር እዲውን እኔ ከፍያለሁ። እሱ የኪራይ ውለን አስመዝግቤያለሁ። ስለዚህ አመልካች የሚቀነስበት ምክንያት የለም በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች በበኩለ ከጠቅላላ ግብር መክፈላቸው አመልካች ቀንሶ እንዱያስቀር በሕግ የተጣለበትን ግዳታ የሚያስቀር አይደለም በማለት የመልስ መልስ ሰጥተዋል። ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረቡት የጽሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች የተጠሪን መጋዘን በወር ብር 13,000 (አስራ ሶስት ሺህ ብር) የተከራየ መሆኑና አመልካች ለተጠሪ የሚከፍለው የስድስት ወር ኪራይ ብር 78,000 (ሰባ ስምንት ሺህ ብር) እዲ ያለበት መሆኑ አከራካሪ አይደለም።
አመልካችና ተጠሪን የሚያከራክራቸው አመልካች የኪራይ ገንዘቡን በጥቅለ ለተጠሪ የመክፈል ግዳታ አለበት ወይስ በአዋጅ ቁጥር 286/1994 መሰረት መቀነስ የሚገባውን ግብር ቀንሶ ቀሪውን ሉከፍል ይገባዋል የሚለው ነጥብ ነው።
አመልካች ማናቸውንም የአገልግልት ግዥ ሲፈፀም ሻጩ የግብር ከፊይ መለያ ቁጥር ካለው የገዛውን አገልግልት ወይም እቃ ዋጋ ሁለት ፏርሰንት፣ሻጭ የግብር ከፊይ መለያ ቁጥር ከላለው ሰላሳ ፏርሰንት ቀንሶ በማስቀረት ለግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት የመክፈል ግዳታ ያለበት መሆኑ በአዋጅ 286/94 አንቀጽ 83 እና አንቀጽ 91 በግልጽ ተደንግጓል። ተጠሪ ከአመልካች ጋር ባደረግሁት የኪራይ ውል፣ ግብር የመክፈል ኃላፉነት ያለበት ተከራይ ሣይሆን አከራዩ መሆኑ በግልጽ ተመልክቷል የሚል ክርክር አቅርቧል።
ተዋዋይ ወገኖች የሚዋዋለበትን ጉዲይ እንደመሰላቸው የመወሰን መብት (የመዋዋል) ነፃነት የሚኖራቸው ህግ ከወሰናቸውና ከከለከላቸው ነገሮች ውጭ ባለ ጉዲዩች እንደሆነ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1711 በግልጽ ይደነግጋል። በያዝነው ጉዲይ የተጠሪን መጋዘን የተከራየው አመልካች ለተጠሪ ከሚከፍለው የኪራይ ገንዘብ የመንግስት ግብር ቀንሶ የማስቀረት ግዳታ እንዲለበት በአዋጅ ቁጥር 286/1994 በአንቀጽ 56 እና አንቀጽ 91 በግልጽ ተወስኗል። አመልካችና ተጠሪ ህግ በአስገዲጅነት የደነገገውን ግዳታ ለማስቀረት የሚችል ውል የመዋዋል መብት የላቸውም።
አመልካችና ተጠሪ በህጉ በአስገዲጅነት የተደነገገውን በመተላለፍ ውል ተዋውለው ቢገኙ ውለ ህግን የሚቃረን በመሆኑ ፈራሽና ሕጋዊ ውጤት የላለው መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 56 እና አንቀጽ 91 ድንጋጌዎችና ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 1716 ድንጋጌዎች ጋር በማጣመርና በማገናዘብ ለመረዲት ይቻላል።
ስለሆነም ተጠሪ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 286/1994 ዓ.ም የተጣለበትን ህጋዊ ግዳታ በመተላለፍ ለተጠሪ ከሚከፍለው የኪራይ ገንዘብ ግብር ሣይቀንስ እንዱከፍለው ተጠሪ ያቀረበውን ጥያቄ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1718 ድንጋጌ መሰረት ተቀባይነት የላለው መሆኑን በመግለጽ ውድቅ ማድረግ ሲገባቸው አመልካች በአዋጅ ቁጥር 286/1994 አስገዲጅ ድንጋጌዎች መሰረት የግብር ገንዘብ ሣይቀንስ የስድስት ወር የቤት ኪራይ ብር 78,000 (ሰባ ስምንት ሺህ ብር) የመክፈል ግዳታ አለበት በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሎል።
አመልካች ተጠሪ የግብር ከፊይ መለያ ቁጥር ካቀረበ ሁለት ፏርሰንት ተጠሪ የግብር ከፊይ መለያ ቁጥር ካላቀረበ ሰላሣ ፏርሰንት በመቀነስ የስድስት ወር የመጋዘን ኪራይ ለተጠሪ የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.