No summary available.
መጋቢት 14 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡-
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው ጉዲዩን በይግባኝ ያየው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአንደኛው አመልካች ላይ የወሰነው የገንዘብ መቀጮ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአንደኛ አመልካች ላይ ያቀረባቸውን ሶስት የወንጀል ክሶችና የተጠሪን ማስረጃዎችና የአንደኛ አመልካችን የመከላከያ ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ አንደኛ አመልካች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከጥቅምት 1 ቀን 1999 ዓ.ም. ጀምሮ ከተመዘገበ በኋላ እስከ ሰኔ 2000 ዓ.ም.
ለተከናወነው ግብይት መክፈል የሚገባውን ለብር 161,870.13 ተጨማሪ እሴት ታክስ ባለመክፈለ የአዋጅ ቁጥር 255/94 አንቀጽ 49 በመተላለፍ ወንጀል የፈፀመ ጥፊተኛ ነው በማለት የጥፊተኝነት ውሣኔ ሰጥቷል። እንደዚሁም አንደኛ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 285/94 በአዋጅ ቁጥር 609/2001 አንቀፅ 50/መ/1 እና የወንጀል ሕግ አንቀፅ 34 በመተላለፍ ጥፊተኛ ነው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አንደኛ አመልካች አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 49 በመተላለፍ ጥፊተኛ ሆኖ የተገኘበት ወንጀል ለሚፈረድበት የአምስት ዓመት ፅኑ እስራት ወደ ገንዘብ በመለወጥ ብር 100,000 እንዱቀጣ፣ እንደዚሁም አዋጅ ቁጥር 285/94 በአዋጅ ቁጥር 609/2001 አንቀፅ 50/መ/1 በመተላለፍ ጥፊተኛ በሆነበት ወንጀል ከሚወሰንበት ቅጣት ብር 50,000፣ ለሁለቱ ወንጀልች ብር 150,000 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ መቀጮ እንዱከፍል ውሣኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ አንደኛ አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በተከሰሰበት ግብር ባለመክፈል ወንጀል በነፃ መሰናበት ተገቢ አይደለም። እንደዚሁም የበታች ፍርድ ቤት በጣምራ የገንዘብ መቀጮ መወሰን ሲገባው ሳይወሰን ማለፈ ተገቢ አይደለም በማለት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን አመልካቾች የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔውን በመቃወም ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የአመልካችንና የተጠሪን ይግባኝ መዛግብት በማጣመር የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ አመልካቾች ያቀረቡትን የይግባኝ ቅሬታ ውድቅ አድርጎታል።
በልላ በኩል ተጠሪ አንደኛ አመልካች ጥፊተኛ ሆኖ የተገኘበት የአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 49 የእስራት ቅጣት ብቻ ሣይሆን የገንዘብ መቀጮ የሚደነግግ ነው በማለት የቀረበውን ይግባኝ በመቀበል የአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 45 መሰረት በማድረግ የገንዘብ ቅጣቱን አስልቶ አንደኛ አመልካች ብር 604,546.74 /ስድስት መቶ አራት ሺህ አምስት መቶ አርባ ስድስት ብር ከሰባ አራት ሣንቲም/ ለተጠሪ እንዱከፍል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አንደኛ አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ችልት ወደ ይግባኙ የሚያስገባ በቂ ምክንያት የላለ መሆኑን በመግለፅ የአመልካችን ይግባኝ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት ሰርዞታል። አንደኛ አመልካች የሰበር አቤቱታው በሰበር ማጣሪያ ችልት ውድቅ ከተደረገው ከሁለተኛ አመልካች ጋር ሚያዝያ 20 ቀን 2003 ዓ.ም. በጋራ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የሥር ፍርድ ቤት ጥፊተኛ ሆኖ ባልተገኘበት የሕግ ድንጋጌ ቅጣት የወሰነበት መሆኑን የገለፀ ሲሆን በተለይ ይግባኝ ሰሚው የከፍተኛው ፍርድ ቤት የአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 49 በመተላለፍ ጥፊተኛ ሆኖ የተገኘ ሰው በእስራት ቅጣት ብቻ እንደሚቀጣ የሕጉ ድንጋጌ በግልፅ ደንግጎ እያለ ድንጋጌው በጣምራነት ገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ አድርጎ የተረጎመው መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ግልፅ የሆነውንና ትርጉም የማያስፈልገውን የሕግ ድንጋጌ በመተርጎም በአስተዲደራዊ ቅጣት ሉወስን የሚገባውን የገንዘብ መቀጮ በወንጀል ጥፊተኛ ሆኖ የተገኘ ሰው ሉከፍለው የሚገባው የወንጀል መቀጮ ነው በማለት የገንዘብ ቅጣቱን የአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 45 መሰረት በማስላት የሰጠው ውሣኔ የሕጋዊነት መርህን የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ የአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 49 ድንጋጌ በአቀራረፅም ሆነ በይዘቱ ጥፊተኛው በእስራት ቅጣት ብቻ ሣይሆን በመቀጮ የሚቀጣ መሆኑን የሚደነግግ ነው በማለት ሰኔ 9 ቀን 2003 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ ሰጥቷል። አመልካች ሰኔ 21 ቀን 2003 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የፅሐፍ ክርክር ከላይ በአጭሩ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩ ለሰበር ሲቀርብ የተያዘውን ጭብጥ ማለትም አንደኛ አመልካች በእስራትና በመቀጮ እንዱቀጣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 49 በመተርጎም የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
የተጨማሪ እሴት ታክስን ተግባራዊ ለማድረግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 285/1994 አስራ ሶስት ክፍልችና 66 አንቀፆች ያለት መሆኑን የአዋጁን ድንጋጌዎች በማየት ለመረዲት ይቻላል።
የአዋጅ ቁጥር 285/94 አቀራረፅና አደረጃጀት ስንመለከት አዋጁ በአስራ ሶስት ክፍልች የተደራጀ ነው። የአዋጁ ክፍል አንድ ትርጓሜና ላልች ጠቅላላ ድንጋጌዎችን የያዘ ሲሆን የአዋጁ ክፍል ሁለት ታክስ ስለመጣልና ከታክስ ነፃ ስለሚሆኑ ግብይቶች ይደነግጋል። የአዋጁ ክፍል ሶስት ታክስ የሚከፈልባቸው አቅርቦቶች የሚከናወኑበት ቦታ ጊዜና ዋጋ ገዥነት ያላቸውን ድንጋጌዎች የያዘ ነው። ክፍል አራት ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች እሴትና የገቡበትን ጊዜ የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን የያዙ ሲሆን ክፍል አምስት ስለምዝገባ የሚደነግጉ ድንጋጌዎችን የሚደነግግ ነው።
የአዋጁ ክፍል ስድስት ስለታክስ ስላት የሚደነግጉ ድንጋጌዎችን የያዘ ሲሆን ክፍል ሰባት ስለተጨማሪ እሴት ታክስ አስተዲደራዊ ሥርዓት ገዥነት ያላቸውን ድንጋጌዎች ያካተተ ሆኖ እናገኘነዋን። የአዋጁ ክፍል ስምንት የታክስ አሰባሰብና አፈፃፀም የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን፣ በክፍል ዘጠኝ ስለ ሂሳብ ሰነድች በክፍል አስር ይግባኝ ስለሚቀርብበት ሥርዓት ገዥነት ያላቸውን ድንጋጌዎች ይዟል። የአዋጁ ክፍል አስራ አንድ ስለ አስተዲደራዊ ቅጣቶች በሚደነግጉ ድንጋጌዎች የተዋቀረ ሲሆን ክፍል አስራ ሁለት የወንጀል ጥፊቶችን የሚዘረዝር ድንጋጌ ነው።
የአዋጁ ክፍል አስራ ሶስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችን የሚደነግግ ነው።
አከራካሪው አንቀፅ 49 በአዋጁ በአስራ ሁለተኛው ክፍል ውስጥ የተደነገገ ድንጋጌ ሲሆን ይዘቱን ስንመለከተው “ሕጉን በመጣስ ታክስ ስላለመክፈል” የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል። ድንጋጌው “ሕግን በመጣስ የተሰበሰውን ታክስ ያላሳወቀ ወይም የሚፈለግበትን ታክስ ያልከፈለ ወይም መንግስትን ለማጭበርበር በማሰብ የማይገባውን ተመላሽ ታክስ የጠየቀ ማንኛውም ሰው ወንጀል እንደፈፀመ ይቆጠራል። ስለሆነም በዚህ አዋጅ ክፍል አስራ አንድ መሰረት ከሚጣልበት በተጨማሪ ጥፊተኛ መሆኑ ሲረጋገጥ ከአምስት ዓመት በማያንስ እስራት ይቀጣል” በማለት ይደነግጋል።
የአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 49 ድንጋጌ የእንግዚኛ ቅጅ A person who evades the declaration of payment of tax, or a person who, with intention to defraud the government; applies for refund he is not entitled to, commits an offence and, in addition to any penalty under section 11, may be prosecuted and on conviction, be subject to a term of imprisonment of not less than five/5/ years” የሚል ይዘት ያለው ነው።
ከላይ የተገለፀው የአዋጅ አንቀፅ 49 ድንጋጌ ሕግን በመጣስ የሰበሰበውን ተጨማሪ እሴት ታክስ ያላሳወቀ፣ ወይም የሚፈለግበትን ታክስ ያልከፈለ ወይም መንግስት ለማጭበርበር በማሰብ የማይገባውን ተመላሽ ታክስ የጠየቀ ሰው በክፍል አስራ አንድ የተዘረዘረውን አስተዲደራዊ ቅጣት የሚያስቀጣ ፍታብሓራዊ ጥፊት የፈፀመ መሆኑ በተጨማሪ ወንጀል እንደፈፀመ የሚቆጠርና በወንጀልም ተጠያቂ እንደሚሆን የሚደነግግ ድንጋጌ ነው። ሆኖም አንቀፅ 49 ድንጋጌን በመተላለፍ በወንጀል ጥፊተኛ ሆኖ የተገኘ ሰው ላይ የሚጣለው የወንጀል ቅጣት ከአምስት ዓመት የማያንስ የእስራት ቅጣት መሆኑን ድንጋጌው “በመሆኑም በዚህ አዋጅ ክፍል አስራ አንድ መሰረት ከሚጣልበት በተጨማሪ ጥፊተኛ መሆኑ ሲረጋገጥ ከአምስት ዓመት በማያንስ እስራት ይቀጣል” በማለት የደነገገውንና በእንግሉዝኛ ቅጅ “in addition to any penalty under section 11, may be persecuted and on conviction to subject to the term of imprisonment not less than five years” ከሚለው የድንጋጌው አቀራረፅና ይዘት ለመረዲት እንችላለን።
የታክስ አሰባሰብ ሥርዓቱን በሚያስተዲድረው ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት በአዋጁ ክፍል አስራ አንድ ከአንቀፅ 45 እስከ አንቀፅ 47 የተደነገጉትን አስተዲደራዊ ቅጣቶች ለመወሰንና ለማስከፈል ግብር ከፊዩ በአዋጁ የተመለከቱትን ግዳታዎች ያልተወጣ መሆኑን በማረጋገጥ የሚወስነው ሲሆን አስተዲደራዊ ቅጣቱን ለመወሰንና ቅጣቱን ለማስፈፀም የግብር ከፊዩ በወንጀል መከሰሱና በፍርድ ጥፊተኛ ሆኖ መገኘቱ አስፈላጊ አይደለም። በልላ በኩል ግብር ከፊዩ የተጨማሪ እሴት ታክስ አስተዲደር ሥርዓት የሚደነግጉ ድንጋጌዎችን በመተላለፍ ሥልጣን ባለው የመንግስት መሥሪያ ቤት በአዋጁ በክፍል አስራ አንድ ከተደነገጉት አስተዲደራዊ ቅጣቶች በአንደኛው ወይም በሁለም የተቀጣ መሆኑ፣ በዚያው ጉዲይ የሚቀርብበትን የወንጀል ክስና ቅጣት የማያስቀርለት መሆኑን አንቀፅ 49 ግልፅ የሚያደርግ ድንጋጌ ነው።
አዋጅ ቁጥር 49 ግብር ከፊይ በአዋጅ ክፍል አስራ አንድ ከተደነገጉት አስተዲደራዊ ቅጣቶች በአንደኛው ወይም በሁለም መቀጣቱ በወንጀል ከመከሰስና ተጠያቂ ከመሆን የማያስቀር መሆኑን ከሚደነግግ ውጭ በአንቀፅ 49 ጥፊተኛ ሆኖ በተገኘ ሰው ላይ የወንጀለን ጉዲይ ያየው ፍርድ ቤት ጥፊተኛውን ከአምስት ዓመት በማያንስ የእስራት ቅጣትና በአዋጅ ክፍል አስራ አንድ የተደነገገውን የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጣ ውሣኔ መስጠት የሚችል መሆኑን የሚደነግግ የሕግ ድንጋጌ አለመሆኑን ከላይ በዝርዝር ያየነው የአዋጁን አወቃቀር የድንጋጌውን አቀራረፅና ይዘት በመመርመር ለመረዲት ይቻላል።
ፍርድ ቤት በሕግ በግልፅ ከተደነገገው በቀር የወንጀል ቅጣቶችንና የጥንቃቄ እርምጃዎችን መወሰን እንደማይችል በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 2 በሁለተኛው ፒራግራፍ ተደንግጓል። ችልቱ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 3 በሚደነግገው መሰረት ድንጋጌውን አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 49 ሲያውጅ ሕግ አውጭው ሉደርስበት ያሰበውን ግብና የድንጋጌውን መንፈስና ዓላማ ለመረዲት የኢፋዱሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 285/94 ከማወጁ በፉት በረቂቅ አዋጁ ላይ ውይይት ያደረገበትን ቃለጉባኤ በማስቀረብ ተመልክቷል። የሕግ አውጭ ምክር ቤት ውይይት ቃለ ጉባኤ የሚያስረዲው ሕግ አውጭው በፍርድ ቤት የሚወሰኑ ቅጣቶችና አስተዲደራዊ ቅጣቶችና ውሣኔዎችን የማጣመር ሀሳብና ፍላጎት የላለው መሆኑን ነው። ሕግ አውጭው ሕጉን ሲያወጣ ባደረገው ውይይት አስተዲደራዊ ውሣኔዎችና ቅጣቶች በተጨማሪ እሴት ታክስ አስተዲደር ሥርዓት ውስጥ የራሱ የሆነ ድርሻና ዓላማ ያለው፣ በፍርድ ቤቶች ከሚወሰኑ ውሣኔዎችና ቅጣቶች ጋር ሳይያያዝ መታየት የሚገባው መሆኑን የሚያከራሩ ሀሳቦች እንዲለበት ተረድተናል። ስለሆነም አንቀፅ 49 “በዚህ አዋጅ ክፍል አስራ አንድ መሰረት ከሚጣልበት በተጨማሪ” የሚለው ቃል ወይም በእንግሉዝኛው ‘’in addition to any penalty under section 11’’ የሚለው አገላለጽ ግብር ከፊዩን በአዋጁ ክፍል አስራ አንድ ከተዘረዘሩት አስተዲደራዊ ቅጣቶች በአንደ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ ቅጣቶች መቀጣቱ በወንጀል ከመከሰስና ጥፊተኛ ሆኖ ከተገኘ ከአምስት ዓመት በማያንስ እስራት መቀጣቱን የማያስቀርለት መሆኑን ለማሣየት የገባ እንጅ፣ በወንጀል ጥፊተኛ ሆኖ የተገኘ ሰው ከአምስት ዓመት በማያንስና በአዋጁ ክፍል አስራ አንድ መሰረት እየተሰላ በመቀጮ የሚቀጣ መሆኑን ለመደንገግ የገባ አለመሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል።
ከላይ የገለፅነውን አተረጓጎም ሕግ አውጭው የገንዘብና የእስራት ቅጣትን በጣምራ ሲደነግግ፣ ድንጋጌዎቹን ለመቅረፅ የተጠቀመባቸውን የሕግ አቀራረፅ ጭብጦች የሚያጠናክሩ ናቸው። ሕግ አውጭው በአዋጅ ቁጥር 50 ንዐስ አንቀፅ 2/ሀ/….ከአንድ ሺህ ብር በማያንስ ከብር ሃያ ሺህ በማይበልጥ መቀጫና ከአንድ ዓመት በማያንስ ከሶስት ዓመት በማይበልጥ እስራት ይቀጣል።
በአንቀፅ 50 ንዐስ አንቀፅ 2/ለ/…ከብር ሃያ ሺህ በማያንስና ከብር መቶ ሺህ በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮና ከሶስት ዓመት በማያንስና ከአምስት ዓመት በማይበልጥ እስራት ይቀጣል” በማለት የገንዘብ መቀጮውንና የእስራት ቅጣቱን በጣምራ የሚወስኑ ቅጣቶች መሆናቸውን በግልፅ በማስቀመጥ ከተጠቀመባቸው የሕግ አቀራረፅ ጥበቦች ለመረዲት ይቻላል።
በአጠቃላይ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 49 ከእስራት ቅጣት ጋር በጣምራ ጥፊተኛው በገንዘብ መቀጮ እንዱቀጣ የሚደነግግ ድንጋጌ ነው በማለት የሰጠው የሕግ ትርጉም የወንጀል ሕጉን አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀጽ 2 የድንጋጌውን አቀራረፅ ይዘት፣ መንፈስና ዓላማ እንደዚሁም ሕግ አውጭው ሉያሣካው የፈለገውን ግብ ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰራውን የሕግ ስህተት ሳያርም ማለፈ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። በመሆኑም የከፍተኛው ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ለአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 49 የሰጡት የሕግ ትርጉምና ለሕጉ የሰጡትን ትርጉም መነሻ በማድረግ የወሰኑት የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በአንደኛው አመልካች ላይ የሰጡት ውሳኔ ተሻሽሎል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በአንደኛው አመልካች ላይ የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ፀንቷል።
አንደኛው አመልካች ጥፊተኛ ሆኖ ለተገኘባቸው ወንጀልች ብር 150,000 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ መቀጮ ይክፈል በማለት ወስነናል።
አንደኛው አመልካች በቁጥር 3 ከተወሰነው መቀጮ ውጭ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ጨምሮ የወሰነውን ብር 454,546.74 /አራት መቶ ሃምሳ አራት ሺህ አምስት መቶ አርባ ስድስት ብር ከሰባ አራት ሣንቲም/ የመክፈል ኃላፉነት የለበትም በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.