No summary available.
የካቲት 30 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማዉ ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካቾች፡- አቶ አንዲርጌ እሸቱ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን ዐቃቤ ህግ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የወንጀል ክስን የሚመለከት ስሆን ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተዉ የፋ/የመጀ/ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ከላልች ግብረ አበሮች ጋር ፈጽሟል በሚል ከተከሰሰበት አጣቃላይ አራት ክሶች መካከል በላልች ሁለቱ ክሶች በነጻ ሲሰናበት በ4ኛ እና 5ኛ ክስ ስር በተመለከቱት የጉምሩክ አዋጅ ቁ.622/2001 አንቀጽ 100 ስር ለምርመራ ሳምፔል በማለት አንድ ፒኬት ባትሪ ወስድ ባለመመለሱ እና በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 95/ሀ/ ስር የተመለከተዉን በመተላለፍ ምንም ዓይነት የጉምሩክ አስተላላፉነት ፍቃድ ሳይኖረዉና ከጉምሩክ ባለሥልጣን ፍቃድ ሳያገኝ በክሱ የተመለከቱት ተሸከርካሪዎች የጫኑት የባትሪ ድንጋይ ጭነት የታሸገበትን ፔልምፔ በመበጠሱ ተከሳሹ በፈጸመዉ እሽጎችን በመፍታት እና ምልክቶችን በማንሳት የወንጀል ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ ነዉ በማለት ለሁለቱ የወንጀል ድርጊቶች በስድስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ በማለት ዉሳኔ በመስጠቱ እና የተሰጠዉም የጥፊተኝነት ዉሳኔ እና የቅጣት ዉሳኔ በፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመጽናቱ የተፈጸመዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች በማመልከቱ የቀረበ ነዉ።
አመልካች ባቀረበዉ የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል ያላቸዉን ነጥቦች ያነሳ ሲሆን የካቲት 03 ቀን 2002ዓ.ም የተጻፈ አራት ገጽ አቤቱታ ፍሬ-ሃሳብ፡- ለናሙና የተወሰደን ዕቃ አልመለሰም በማለት በበታች ፍርድ ቤቶች የተላለፈበትን የጥፊተኝነት እና የቅጣት ዉሳኔ በተመለከተ የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ አሽከርካሪዉ ላደረገለት ትብብር በስጦታ መልክ ሰጥቶት ይዞ የሄደ እንጂ መጀመሪያ ላይ ለናሙና የተወሰደትን የመለሱ ስለመሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ ያለአግባብ በመሆኑ፣ በመተላለፍ ላይ ያለ ወይም የጉምሩክ ወደብ በደረሱ የጭነት ማሸጊያ በመፍታት ወንጀልም ስር የዐቃቤ ህግ ምስክሮች በክሱ በተመለከተዉ መሰረት ያስረደት ነጥብ ሳይኖር የተወሰነብኝ በመሆኑ እና ባጠቃላይ የቀረቡብኝ ክሶች በበቂ ማስረጃ ያልተረጋገጡ ከመሆኑም በላይ በመከላለከያ ምስክሮች የተከላከልኩ በመሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች የተላለፈብኝ የጥፊተኝነት ዉሳኔ ተቀባይነት የለዉም። የቅጣት ዉሳኔን በተመለከተም ከብድ የተወሰነ በመሆኑ አግባብነት የላለዉ ነዉ በማለት የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት የጥፊተኝነት እና የቅጣት ዉሳኔ ተሸሮ በነጻ እንድሰናበት፤ ይሄ የማይቻል ከሆኑ ደግሞ የእስራት ቅጣቱ ቀልልኝ በገደብ እንድታለፍ በሚል ነዉ። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ታዞ ግንቦት 6 ቀን 2003ዓ.ም በሶስት ገጽ በተጻፈ የሰጠዉ የመልስ ፍሬሃሳብ፡- አመልካች ጥፊተኛ በተባለባቸዉ ሁለቱም የወንጀል ድንጋጌዎች ስር ባቀረብናቸዉ ምስክሮች የተረጋገጠ እና ያልተከላከለ በመሆኑ የተላለፈበት የጥፊተኝነት ዉሳኔ የሚነቀፍበት አግባብ የላለ በመሆኑ እና የተላለፈበት የቅጣት ዉሳኔም ስንመለከት እጅግ ያነሰ በመሆኑ የቀረበዉ ቅሬታ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል። የአመልካች የመልስ መልስ ቀርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ከተያዘዉ ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል።
እንደመረመረዉም አመልካች ከተከሰሰባቸዉ የጉምሩክ ወንጀል ህግ ድንጋጌዎች መካከል በአዋጅ ቁ.622/2001 አንቀጽ 100 ስር ለናሙና የወሰደዉን ዕቃ ያልመለሰ ስለመሆኑ እና በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 95/ሀ/ በተሸከርካሪዉ ላይ ያለዉ ጭነት የታሸገበትን መሸጊያ ስለመፍታቱ በበታች ፍርድ ቤቶች በፍሬ-ነገር ረገድ ተረጋግጧል። አሁን በአመልካች እየተነሳ ያለዉ ክርክር የቀረበዉ የዐቃቤ ህግ ምስክር በክሱ መሰረት አላስረዲም የሚል ሲሆን ይሄ ደግሞ የፍሬ-ጉዲይ ክርክር እንጂ የመሰረታዊ የህግ ስህተት ጥያቄ ባለመሆኑ እና ማስረጃን የመመዘን እና ፍሬ-ጉዲይን የማጣራት ስልጣን ደግሞ ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተዉ ወይም በይግባኝ ያየዉ ፍርድ ቤት በመሆኑ እና የዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ስልጣን መሰረታዊ የህግ ስህተት ሲኖር ማቃናት ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዳ.ሪ.ህገ-መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና በአዋጅ ቁ.25/88 አንቀጽ 10 ስር የተደነገገ በመሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች በፍሬ-ነገር ረገድ የተደረሰበትን መደምደሚ መቀበለ ተገቢ ይሆናል ማለት ነዉ።
ከላይ እንደተመለከተዉ የተረጋገጡትን ፍሬ-ነገሮች ይዘን አመልካች ጥፊተኛ የተባለበትን የወንጀል ህግ ድንጋጌ ስንመለከት በአዋጅ ቁ.622/2001 አንቀጽ 95/ሀ/ መሰረት ማንኛዉም ሰዉ አግባብ ካለዉ የባለስልጣኑ ሹም ፉቃድ ሳያገኝ በመተላለፍ ላይ ያለ ወይም የጉምሩክ ወደብ በደረሱ ወቅት የዕቃዎች መያዣ ላይ የተደረገዉን ማሽጊያ የፈታ ወይም ያላቀቀ እንደሆነ በዚህ ድንጋጌ ስር የወንጀል ኃላፉነት የሚያስከትል ስለመሆኑ ተመልክቷል። በበታች ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠዉን ፍሬ-ነገር ስንመለከት የአመልካች ድርጊት የወንጀል ኃላፉነቱን ሉያቋቋም የሚችል ተግባር የፈጸመ ስለመሆኑ ከድንጋጌዉ ይዘት መገንዘብ ስለሚቻል በዚህ የወንጀል ህግ ስር አመልካች ጥፊተኛ መባለ በአግባቡ ነዉ ብለናል። ላላኛዉን የወንጀል ኃላፉነት በተመለከተ አዋጅ ቁ 622/2001 አንቀጽ 100 ን ስንመለከት ማንኛዉም ሰዉ ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለማግኘት ወይም ለላላ ሰዉ ለማስገኘት ወይም በልላ ሰዉ ላይ ጉዲት እንዱደርስ በማሰብ ለናሙና የወሰደዉን ዕቃ ያልመለሰ ወይም በዕቃዉ የተገለገለ ወይም ዕቃዉ እንዱጠፊ ያደረገ እንደሆነ በማለት የሚደነግግ ሲሆን አመልካችም በዚሁ መልኩ ለናሙና የወሰደዉን ዕቃ ሳይመልስ የቀረ ስለመሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች በፍሬ-ነገር ረገድ የተረጋገጠ ነጥብ በመሆኑ የወንጀል ኃላፉነቱን ሉያቋቁሙ የሚችለ ተግባራትን የፈጸመ ስለመሆኑ ከተረጋገጡት ፍሬነገሮች እና የወንጀል ድንጋጌዉ ይዘት መገንዘብ ይቻላል። በዚሁ መሰረት በዚህ ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ መባለ በአግባቡ ነዉ ብለናል። በአመልካች ላይ የተላለፈዉን የቅጣት ዉሳኔ በተመለከተም በቅጣት አጣጣለ ሂደት የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለመኖሩ የሚያመላክት ነጥብ ባለመኖሩ በዚህ ዙሪያ የተነሳዉን ቅሬታም አልተቀበልነዉም።
ባጠቃላይ በአመልካች ላይ የተላለፈዉ የጥፊተኝነት እና የቅጣት ዉሳኔ በአግባቡ እና የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም ብለናል።በመሆኑም ቀጥል የተመለከተዉን ዉሳኔ ሰጥተናል።
የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝ ቁ.91025 ጥር 20 ቀን 2003ዓ.ም በዋለዉ ችልት እና የፋ/የመጀ/ደ/ፍርድ ቤት በመዝ.ቁ. 155110 በቀን 8-6-2002ዓ.ም እና በቀን 22-6-2002 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጡት ዉሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.195(2(ለ(2))) መሰረት ጸንቷል።
በአመልካች ላይ የተላለፈዉ የጥፊተኝነት እና የቅጣት ዉሳኔ በአግባቡ ነዉ ብለናል።
የበታች ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ የጸና ስለመሆኑ ለሚመለከተዉ ማረሚያ ቤት ይተላለፍ ብለናል።
No topics extracted.