No summary available.
ጥር 2 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ አበበ ገ/እግዚአብሓር ጠበቃ ዮሐንስ ዘለቀ ቀረበ ተጠሪ፡- አራዲ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ዐቃቤ ህግ ተወዲጅ ሲማ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የአዱስ አበባ አስተዲደር የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ፤ የአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የንግድ ሥራ ገቢ ግብርን የሚመለከት ነው።
የክርክሩ መነሻ አመልካች የ2000 ዓ.ም የበጀት ዘመን ብር 472,594.89 /አራት መቶ ሰባ ሁለት ሺህ አምሥት መቶ ዘጠና አራት ብር ከሰማኒያ ዘጠኝ ሣንቲም/ ያልተጠራ ትርፍ ያገኘ መሆኑን የሚያሣይ የሑሣብ መዝገብ አቅርቦ ብር 83,507.02 /ሰማኒያ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ሰባት ብር ከዜሮ ሁለት ሣንቲም/ የንግድ ሥራ ከፍሎል። ተጠሪ አመልካች በአመቱ ውስጥ ያገኙት ጠቅላላ ገቢ ብር 5,647,298.90 /አምስት ሚሉዮን ስድስት መቶ አርባ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ሥምንት ብር ከዘጠና ሣንቲም/ መሆኑን አመልካች ያቀረበው የሂሣብ መዝገብ የሚያሣይ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ አመልካች የተሰማራበት የፅሕፈት መሣሪያ አስመጭነት ሥራ ዘርፍ ዕቃዎች የጉምሩክ ፍርማሉቲ አሟልተው ከገቡበት አሥራ አምስት ፏርሰንት ያልተጣራ ትርፍ የሚገኝ መሆኑ በአዱስ አበባ አስተዲደር ገቢዎች የተጠና ጥናትና የተዘጋጀ ቼክ ሉስት ያለ መሆኑን በመግለፅ በዚሁ ስላት አመልካች ብር 3ዐ3,61ዐ.71 / ሶስት መቶ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ አስር ብር ከሰባ አንድ ሣንቲም /ያልተጣራ ትርፍ ስላለ በዚሁ ስላት ግብር እንዱከፍል የግብር ውሣኔ ማስታወቂያ ተጠሪ ለአመልካች ሰጥቷል።
አመልካች ተጠሪ በሰጠው የግብር ውሣኔ ማስታወቂያ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአዱስ አበባ ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ አቅርቧል። የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤው የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ተጠሪ የሰጠውን የገቢ ግብር ውሣኔ አፅንቶታል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቧል።
አመልካች የሰበር አቤቱታውን ለአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አቅርበው አቤቱታቸው ተቀባይነት አልተገኘም።
አመልካች ሰኔ 1ዐ ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ አመልካች ያቀረብኩት የሂሣብ መዝገብ የዋጋ ማሣነስ ወይም underinvocing የላለው ነው። አመልካች የሑሣብ መዝገቡን ተቀብልታል። ይህ ከሆነ ተጠሪ ተጨማሪ ግብር እንዱከፍል የሰጠው ውሣኔ የአዋጅ ቁጥር 286/94 ድንጋጌዎችን የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ ጥቅምት 14 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም በተፃፈ ለሰበር አቤቱታ በሰጠው መልስ ተጠሪ አመልካች ባቀረቡት የሑሣብ መዝገብ ላይ ያለትን ጥቃቅን ስህተቶች በማረም ውሣኔ የሰጠው የአዋጅ ቁጥር 286/94 ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ በመሆኑ የፈፀመው መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት መልስ ሰጥተዋል።
አመልካች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ያቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ተጠሪ ቀደም ብል በተዘጋጀ መመሪያና ቼክ ሉስት መሰረት በማድረግ አመልካች ተጨማሪ ግብር እንዱከፍል መወሰኑ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ተጠሪ ያቀረብኩትን የሑሣብ መዝገብ ከተቀበለ በኋላ በተሰማራሁበት የፅሕፈት መሣሪያዎች አስመጭነት ንግድ ዘርፍ ሉገኝ ይችላል ተብል በግምት የተዘጋጁ የትርፍ ተመን መሰረት የግብር ውሣኔ መስጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ተከራክረዋል።
በአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀፅ 69/1/ ግብር ከፊዩ ምንም አይነት የሂሣብ መዝገብና ሰነድ ያልያዘ እንደሆነ ወይም በማናቸውም ምክንያት የሂሣብ መዝገቡንና ሰነደን የግብር አስገቢው ባለሥልጣን ያልተቀበለው እንደሆነ ወይም ግብር ከፊዩ በዚህ ህግ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ገቢውን ያላሣወቀ እንደሆነ የግብር አስገቢው ባለሥልጣን የግብሩን ልክ በግምት ሉወስን ይችላል በማለት ይደግጋል። ተጠሪ አመልካች በዓመት ውስጥ አስገብቸዋለሁ በማለት በሑሣብ መዝገብ ያሣወቀውን ብር 5,647,298.9ዐ እና ላልች የወጪ መግለጫዎች የተቀበለ መሆኑ ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ባቀረበው ክርክር አረጋግጧል። በልላ በኩል አመልካች በበጀት ዓመቱ አግኝቻለሁ በማለት መግለጫ ያቀረበበት ያልተጣራ ትርፍ በዘርፈ ይገኛል ተብል በጥናት ከተረጋገጠው እና በመመሪያ ከተወሰነው አማካኝ ያልተጣራ ትርፍ በታች መሆኑን በማገናዘብ ይህንን የሑሣብ ስህተት በማስተካከል የግብር ውሣኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ የአመልካችን የሑሣብ መዝገብ በከፉል በመቀበልና በከፉል በማስተካከል አመልካች ተጨማሪ የገቢ ግብር እንዱከፍል መወሰኑ የአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀፅ 71 ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘት መንፈስና ዓላማ ጋር የሚቃረን ሆኖ አላገኘነውም። ምክንያቱም የህጉ ድንጋጌ ተጠሪ አመልካች ያቀረበው የሑሣብ መዝገብ ሙለ በሙለ የማይቀበልበት በቂ ምክንያት ካገኘ የአመልካችን የሑሣብ መዝገብ ሙለ በሙለ ውድቅ በማድረግ ግብሩን በግምት የመወሰን ሥልጣን ለተጠሪ ይሰጠዋል። እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ አመልካች ያቀረበው የሑሣብ መዝገብ በከፉል ተቀባይነት ያላቸው የሑሣብ መግለጫዎችን የያዘ በከፉል ደግሞ የሑሣብ አያያዝና የአሰራር ስህተት ያለበት ሆኖ ቢገኝ ተጠሪ በሂሣብ አያያዝ የተፈጠሩ ስህተቶችን በማስተካከል የግብር ውሣኔ ከመስጠት የአዋጅ አንቀፅ 69 ድንጋጌዎች የሚገድቡ /የሚከለክለ/ አይደለም።
ከዚህ አንፃር ስንመዝነው ተጠሪ አመልካች በ2ዐዐዐ ዓ.ም የበጀት ዓመት የፅህፈት መሣሪያዎችን በማስመጣት ስላገኘው ጠቅላላ ገቢና ስለላልች ወጭዎች ያቀረበውን የሂሣብ መግለጫ ተቀብሎል። ሆኖም አመልካች በበጀት ዓመቱ ወደ አገር ውስጥ ያስገባውን የፅሕፈት መሳሪያ በመሸጥ አግኝቸዋለሁ ብል በሑሣብ መዝገቡ መዝግቦ የያዘው ያልተጣራ ትርፍ የፅሕፈት መሣሪያዎችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት እንደሚገኝ በጥናት ተለይቶ ከተያዘው አማካኝ ያልተጣራ የትርፍ መጠን ዝቅተኛ ሆኖ በመገኘቱ አመልካች በዓመት ውስጥ ስላገኘው ያልተጣራ ትርፍ ሰርቶ ያቀረበውን የሂሣብ መግለጫ ተጠሪ ሙለ በሙለ ትክክል ነው ብል አልተቀበለውም። ስለሆነም ያልተጠራ የትርፍ መጠን ለመወሰን የወጣውን መመሪያና ቼክ ሉስት መሰረት በማድረግ የአመልካችን ያልተጣራ የትርፍ መጠን የሑሣብ መግለጫ በማስተካከል አመልካች ተጨማሪ የገቢ ግብር እንዱከፍል የሰጠው ውሣኔ የአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀፅ 69 ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገና መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለው ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ የአዱስ አበባ ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ፤ የአዱስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.