No summary available.
የሰ/መ/ ጥር ዐ2 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ቴዎድሮስ ደበላ ጠበቆች ሽፈራው ጉላና ተኮላ መሸሻ ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል አገር ውስጥ ገቢ ባለስሥልጣን የልደታ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፊዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት - ነ/ፈጅ ተወዲጅ ሲማ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን አቤቱታ አጣሪ ኮሚቴ በሚሰጠው የግብር ማስታወቂያ ውሣኔ ላይ ቅሬታ ያለው ወገን ይግባኙን ለግብር ጉባኤ ለማቅረብ የተፈቀደውን ጊዜና የጊዜውን ስላት የሚመለከት ነው። የክርክሩ መነሻ አመልካች ሚያዚያ 26 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም አሻሽለው ያቀረቡት አቤቱታ ነው። አመልካች በአቤቱታቸው ከ1998 ዓ.ም እስከ 2ዐዐ1 ዓ.ም. ድረስ ባለው የግብር ዘመን እንዱከፈል የተወሰነብኝ የንግድ ስራ ገቢ ግብር ያላግባብ እና ከአቅሜ በላይ ነው ፣ ይህንኑ ቅሬታ ለተጠሪ መስሪያ ቤት አቤቱታ አጣሪ ኮሚቴ ባቀርብም ኮሚቴው ተመሣሣይ ውሣኔ አስተላልፍብኛል በማለት ጉባኤው አመልካችን ያቀረቧቸውን ማስረጃዎችንና የግብር ማህደራቸውን በማስቀረብ ጉዲዩን በመመርመር ፍትሐዊ ዲኝነት እንዱሰጥ ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኑ ተጠሪም ቀርቦ በሰጠው መከላከያ መልስ የአመልካች ይግባኝ ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የቀረበው በሕጉ የተመለከተው የሰላሣ ቀን የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ከአለፈ በሁዋላ መሆኑን ጠቅሶ በዚህ መቃወሚያ መሰረት ይግባኙ ውድቅ እንዱሆንና ይህ የሚታለፍ ከሆነ ደግሞ ፍሬ ጉዲዩም ተቀባይነት የለውም የሚልባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝሮ ተከራክሯል። ይግባኙ የቀረበለት ጉባኤም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያውን በጭብጥነት ይዞ ጉዲዩን በመመርመር ይግባኙ አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 1ዐ7/2/1/ በሚደነግገው መሰረት በሰላሣ ቀናት ውስጥ ያልቀረበ ነው በማለት መዝገቡን ዘግቶታል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለማስማማት ይግባኛቸውን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ከአከራከረ እና የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ሬጅስትራርን በመጥራት ጉዲዩን ከአጣራ በሁዋላ የሰላሣ ቀናት ጊዜ ሳያልፍ አመልካች ይግባኛቸውን ማቅረባቸው ተረጋግጧል በማለት የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤን ውሣኔ ሽሮ በፍሬ ነገሩ ግራ ቀኙን አከራክሮ ተገቢውን እንዱወስን በማለት ጉዲዩን ለጉባኤው መልሶለታል። በዚህ ውሣኔ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለአዱስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችልት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ችልቱ የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮ የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች መጋቢት ዐ7 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በጻፊት አራት ገፅ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ በሕጉ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ የይግባኝ አቤቱታውን ለግብር ይግባኝ ጉባኤ አቅርበው አመልካች የተጠሪ መስሪያ ቤት ሃምሣ ፏርሰንት /50%/ የይግባኝ ማስያዣ እና የዲኝነት ሂሣብ እንዱከፍል የግብር ይግባኝ ጉባኤ ሬጅስትራር አመልካችን ሲያዝዙ አመልካች የተተመነውን ሂሣብ በባንክ ሲፑኦ አሰርተው ካስገቡ በሁዋላ የሲፑኦ ማስረጃ ስለማንቀበል ሲፑኦው ወደ ደረሰኝ መለወጥ አለበት በማለት አቤቱታቸውን ሬጅስትራሩ ባለመቀበላቸው ለተከሰተው የጊዜ ማለፍ አመልካች የሚቀጡበት አግባብ የለም በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች የይግባኝ ማስያዣና የዲኝነት ሂሣብ በሲፑኦ መጋቢት 1ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. አሰርተው ለፊይናንስ ቢሮ መጋቢት 13 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ብር 223,696.52 /ሁለት መቶ ሃያ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ስድስት ብር ከሃምሣ ሁለት ሣንቲም /ለዲኝነት ብር 83ዐ3.48/ ስምንት ሺህ ሶስት መቶ ሶስት ብር ከአርባ ስምንት ሣንቲም/ ከፍለው ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በወቅቱ አቅርበው እያለ የጉባኤው ሬጅስትራር ሲፑኦውን ወደ ደረሰኝ መለወጥ አለበት በማለት አቤቱታውን ባለመቀበላቸው የይግባኝ ማቅራቢያ ጊዜ አልፎል የመባለን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለትም ቀርቦ ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር በሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ይግባኝ ለማቅረብ ማስያዝ የሚገባቸውን ገንዘብ በCPO መጋቢት 1ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በማሰራት ከተጠሪ ቢሮ ሰላሣ ቀን ከማለፊ በፉት ቀርበው የነበሩ መሆኑና ተጠሪ የገቢ ግብር ይግባኝ ለማቅረብ በCPO አመልካች ያቀረቡትን መያዣ ደረሰኝ ቆርጦ 13/07/2002 ዓ.ም የሰጠ ሲሆን የገቢ ግብር ውሣኔ ማስታወቂያ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ በመያዣነት ያቀረቡትን CPO ወደ ደረሰኝ ካልተለወጠ በማለት ሬጅስትራሩ ሳይቀበለው ቀርቶ በ13/7/2002 ዓ.ም ግን ደረሰኝ ቆርጦ የሰጠ መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬ ጉዲይ ነው።
በመሰረቱ በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 107 ድንጋጌ መሰረት አንድ በማንኛውም ግብር /ታክስ አወሳሰን ቅር የተሰኘ ግብር ከፊይ በአንቀፅ ንኡስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ስር የተቀመጡትን ግዳታዎችን አሟልቶ ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ይግባኙን ማቅረብ ያለበት መሆኑ በሕጉ በግልጽ ተቀምጧል። በዚህም መሰረት በአዋጅ አንቀፅ 107/2/ ስር የተመለከቱት ግዳታዎች ግብር ከፊዩ አከራካሪ የሆነውን የግብር መጠን 50% /ሃምሣ ከመቶ/ ለግብር አስገቢው ባለስልጣን ማስያዝ እንደአለበትና ይግባኙንም የግብር ውሣኔ ማስታወቂያ ለግብር ከፊዩ በደረሰው ወይም በአቤቱታው ኮሚቴ ውሣኔ በተሰጠ በሰላሣ ቀን ወስጥ መቅረብ እንደአለበት የሚያሳዩ ስለመሆናቸው ንኡስ ድንጋጌው በፋደል “ሀ” እና “ለ” ስር ዘርዝሮ አስቀምጧል።
የአዋጅ አንቀጽ 108 ድንጋጌ ሲታይም ይግባኙ የቀረበበት ቀን የሚባለው በቀጥታ ለይግባኝ ጉባኤው የቀረበ ሲሆን ይግባኙ ለመዝገብ ቤት የተመዘገበበት ቀን ወይም በሪኮማንዳ የተላከ ሲሆን በፕስታ ቤት የተመዘገበበት ቀን እንደሚሆን አስቀምጧል።
አመልካችም ሆነ ተጠሪ በዚህ የህግ ይዘት ላይ ክርክር የላቸውም። ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው አመልካች በጊዜ ገደቡ ይግባኛቸውን አቅርበዋል? ወይስ አላቀረቡም? የሚለው ጉዲይ ነው።
እዚህ ላይ የሚነሣው ጥያቄ አመልካች ይግባኝ ለማቅረብ ማስያዝ የሚገባቸውን ገንዘብ መያዣው በሚፈፀመበት ሥርአት በCPO አሰርተው ለተጠሪ ጊዜው ከማለፈ በፉት ማቅረባቸው ከተረጋገጠ በCPO ለክፍያ ያቀረበውን ገንዘብ አወራርድ ደረሰኝ ለመስጠት ተጠሪ በአጋጠመው የአሰራር ወይም ላላ ችግር ምክንያት ቀናት ወይም ወራት ቢወሰድበት ይግባኝ ባዩ ይግባኝ ለማለት መክፈል ያለበትን ገንዘብ በጊዜው አልከፈለም ልባል ይገባዋል ወይ? የሚለው ነው። ይህ ጥያቄ ከሕጉ አጠቃላይ መንፈስና ዓላማና ሕግ አውጭው ሉያሣካው ከሚፈልገው ግብ አንፃር መመርመርና ውሣኔ ማግኘት አለበት። ሕግ አውጭው የግብር ውሣኔ ማስታወቂያ የደረሳቸው ሰዎች የውሣኔ ማስታወቂያ በደረሳቸው በሰላሣ ቀን ውስጥ ማስያዝ የሚገባቸውን ገንዘብ 5ዐ% /ሃምሣ ከመቶ/ ለግብር ሰብሳቢው መሥሪያ ቤት በማስያዝ ይግባኝ ማቅረብ እንዲለባቸው በአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 107/2ሀ/ ሲደነግግ ግብር ከፊዩ ለግብር አስገቢው መሥሪያ ቤት ገንዘቡን ገቢ እንዱያደርግ ለማስገደድ እንጅ ገንዘቡ ገቢ ግብር ሰብሳቢው መሥሪያ ቤት ደረሰኝ ሣይሰጥ ቢቆይ በመሥሪያ ቤቱ የአሰራር ችግር ምክንያት የግብር ከፊዩ ይግባኝ የማቅረብ መብቱ እንዱጣበብ በማሰብ አይደለም። ስለዚህ አመልካች ተጠሪ ክፍያ የሚቀበልበትን ሥርአት በማሟላት ማለትም በCPO መክፈል አለብህ ተብል የተወሰነበትን የንግድ ገቢ ግብር 50% የግብር ውሣኔ ማስታወቂያ በደረሰው በሰላሣኛው ቀን ማለትም 10/07/2002 ለተጠሪ ገቢ አድርጓል። ይህም አመልካች ከላይ በተጠቀሰው የሕግ ድንጋጌ የተወሰነው ጊዜ ከማለፊ በፉት ለተጠሪ ገቢ ማድረጋቸውን የሚያሳይ ነው። ተጠሪ ሰላሣ ቀኑ ከማለፊ በፉት በCPO ገቢ ለሆነለት ገንዘበ ደረሰኝ ቆርጦ የሰጠው ከሶስት ቀን በኋላ ማለትም 13/7/2002 መሆኑ ይግባኝ ለማቅረብ ማስያዝ ያለበትን ገንዘብ አመልካች ከሰላሣ ቀን በኋላ ነው ገቢ ያደረገው ከሚለው መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ አይደለም። በአጠቃላይ የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የተከሰተውን ችግር አጣርቶ ችግሩ የአመልካች ያለመሆኑን በመደምደም ይግባኝ ጊዜው ያለፈው በአመልካች ችግር አይደለም በማለት የሰጠውን ውሣኔ የከተማው ሰበር ሰሚ ችልት የተለየ ፍሬ ነገር ስለመኖሩ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በግብር ሰብሳቢው መሥሪያ ቤት በኩል ያለ የአሰራር ችግሮችና ክፍተቶች መሰረታዊ የሆነውን የአመልካችን ይግባኝ የማቅረብ መብት በማያጣብብ ሁኔታ በመተርጏም የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የሰጠው ውሣኔ የከተማው ሰበር ሰሚ ችልት መቀበለ የሕጉን ድንጋጌ አተረጋጏምና ተፈፃሚነት ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ጥር 3ዐ ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ ተሽሯል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመ/ ሕዲር 29 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
የአዱስ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አመልካች የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ከማለፈ በፉት በመያዣነት መከፈል የሚገባውን ገንዘብ ለተጠሪ ያስያዙ በመሆኑ የቀረበለትን ይግባኝ በመመርመርና የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት ውሣኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 341/1/ መሰረት መልሶ መላኩ ተገቢ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.