No summary available.
ታህሳስ 17 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡ ሒጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር ተያይዞ የተነሳን የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካቾች ላይ በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም፡- 1ኛ አመልካች የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 በአዋጅ ቁጥር 609/2001 እንደተሻሻለ በአንቀጽ 50//መ/2// ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ከጥቅምት 01 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ በወጣው የህዝብ ማስታወቂያ መሰረት የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ተጠቃሚ በመሆኑ ለሚያከናውናቸው ግብይቶች ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ በሚወጣ ፉስካል ደረሰኝ መጠቀም ሲገባው በቀን 06/05/2002 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 5፡00 ሰዓት አካባቢ ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ከሚወጣ ደረሰኝ ውጭ በሆነ ደረሰኝ ባለ 8.1 ግራም የሆነ የአገር ውስጥ የአንገት ሐብል በብር 93.15 የድርጅቱ ሰራተኞች በሆኑት ሶሰተኛ አመልካች አማካኝነት ግብይት ፈጽሟል በሚል ሲሆን የአሁኑ ሁለተኛ አመልካች ደግሞ የ1ኛ አመልካች ድርጅት ስራ አስኪያጅ ሁነው ኃላፉነታቸውን ባለመወጣት የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 በአዋጅ ቁጥር 609/2001 እንደተሻሻለው በአንቀፅ 50/መ(2)/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ 1ኛ አመልካች የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን የመጠቀም ግዳታ እያለበት ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ውጪ ግብይት እንዱከናወን አድርገዋል በሚል ነው። ሶሰተኛ አመልካችም የተጠቀሰውን አዋጅ አንቀጽ 55 እና በአዋጅ ቁጥር 609/2001 እንደተሻሻለው በአንቀጽ 50/መ/2// ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በ1ኛ አመልካች ድርጅት ውስጥ የሽያጭ ሰራተኛ በመሆን ሲሰሩ ከሽያጭ መመዝገቢያ ደረሰኝ ውጪ በሆነ ደረሰኝ ባለ 8.1 ግራም የሆነ የሐገር ውስጥ ሀብል በብር 93.15 በመሸጣቸው የወንጀል ድርጊት ፈፅመዋል በሚል ነው። የአሁኑ አመልካች ክሱ ተነቦላቸው እንዱረደት ከተደረገ በሁዋላ በክሱ ላይ ተቃውሞ ያላቸው መሆኑን ገልፀው ፍርድ ቤቱም ተቃውሞውን ውድቅ አድርጎ ስለድርጊቱ አፈፃጸም ድርጊቱ መፈጸሙን አምነው ጥፊተኛ አይደለንም በማለት በመከራከራቸው አቃቤ ሕጉ አለን ያላቸውን ማስረጃዎች አቅርቦ እንዱያሰማ ተደርጓል። የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች ቀርበው ሽያጩ ከሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ከሚወጣ ደረሰኝ ውጪ በሆነ ደረሰኝ መከናወኑን በማረጋገጣቸው አመልካቾች እንዱከላኩ ተደርጎ አመልካቾች የሰውና የሰነድ ማስረጃዎቹን በመከላከያ ማስረጃነት አቅርበው አስምተዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም አመልካቾች የአቃቤ ሕጉን ማስረጃዎችን ለማስተባበል ያለመቻላቸውን ገልፆ የመከላከያ ማስረጃዎችን ቃል ውድቅ ከአደረገ በሁዋላ አመልካቾችን በአቃቤ ሕግ በኩል ተጠቅሶ በቀረበባቸው ክስ መሰረት ጥፊተኛ አድርጎ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾችን እያንዲንቸውን በሶስት ወር ቀላል እስራት፣1ኛ አመልካችን ደግሞ በብር 7,000.00 (ሰባት ሺህ ብር) የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጣ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ጥቅምት 01 ቀን 2002 ዓ/ም የወጣው የሕዝብ ማስታወቂያ የሚመለከተው የወርቅና የብር ጌጣጌጥ የንግድ ፈቃድ ስራ ላይ የተሰማሩትን ነጋዳዎች ሁኖ አመልካቾች የንግድ ፈቃድ ደግሞ የሚመለከተው የባህል እቃዎችንና ስእልችን መሸጥ በመሆኑ ማስታወቂያው አይመለከተንም የሚል ነው። አቤቱታውም ተመርምሮ ጥቅምት 1 ቀን 2002 ዓ/ም ለሕዝብ የተሰጠ ማስታወቂያ አመልካቾችንም የሚመለከት ነው ተብል አመልካቾች ጥፊተኛ ተብለው የመቀጣታቸውን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለትም ቀርቦ በጽሐፍ መልሱ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራከሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆኑት ውሳኔዎችና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ አመልካቾች ጥፊተኞች ተብለው መወሰኑ ባግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ሲሆን ቅጣት ጋር ተያይዞ የቀረበው ክርክር በዚሁ ጭብጥ እልባት የሚያገኝ ሆኖ አግኝቶታል።
በዚህም መሰረት አመልካቾች በተጠሪ ተጠቅሶ በቀረበባቸው ድንጋጌዎች መሰረት የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈጸማቸው ተጠሪ በሕጉ አግባብ አስረድቷል? ወይስ አላስረዲም? የሚለውን ጥያቄን በማንሳት በስር ፍርድ ቤት በአቃቤ ሕጉ ማስረጃዎች ከተረጋገጡት ፍሬ ጉዲዮች እና አግባብነት ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ ተመልክተናል።
አመልካቾች ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ከሚወጣው ደረሰኝ ውጪ በልላ ደረሰኝ ግብይት መፈጸማቸውን ሳይክደ አጥብቀው የሚከራከሩት ጥቅምት 01 ቀን 2002 ዓ.ም. ለሕዝብ የተሰጠው ማስታወቂያ የንግድ ፈቃዲችንን የሚመለከት አይደለም በማለት ሲሆን ተጠሪ ደግሞ የአመልካቾች ንግድ ፈቃድ የባህል እቃዎችና የስዕል ውጤቶችን የሚመለከት ቢሆንም ድርጅቱ የባህል ጌጣጌጥና ወርቅ የሚሸጥበት እንደነበረ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ጥቅምት 01 ቀን 2002 ዓ.ም. የወጣው ማስታወቂያ አመልካቾችን ይመለከታቸዋል በሚል ነው። የበታች ፍርድ ቤቶችም አመልካቾች የሚከራከሩበት የንግድ ፈቃድ አመልካቾች የሚለትን የንግድ ስራ የሚመለከት መሆኑን፣ጥቅምት 01 ቀን 2002 ዓ.ም. ለሕዝብ የተሰጠው ማስታወቂያም የወርቅና የብር ጌጣጌጥ ነጋዳዎችን የሚመለከት መሆኑን እንዱሁም አመልካቾች የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ባይገዙም በእለቱ ለተከናወነው ግብይት ግን ከሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ውጪ በሆነ ደረሰኝ ግብይቱን መፈፀማቸውን በፍሬ ነገር ደረጃ አረጋግጠው አመልካቾች የወንጀል ተጠያቂያነት አለባቸው ወደሚለው ድምዲሜ የደረሱት ማስታወቂያው ይመለከታቸዋል፣ በሚመለከተው አካል ከተሰጠው የንግድ ፈቃድ ውጪ ስራውን ሲሰሩ የተገኙ መሆኑም ተረጋግጧል በሚል ምክንያት ነው።
በመሰረቱ የአንድ ሰው በወንጀል ተጠያቂነት የሚኖረው ሕጋዊ፣ ግዙፊዊ እና ሞራላዊ ነገሮች በአንድነት ተጣምረው ሲገኙ ብቻ ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ የወንጀል ሕግ በአንቀፅ 23(2) ስር በግልፅ አስፍሯል። በተያዘው ጉዲይ የአመልካቾች የሐሳብ ክፍል እና ሕጋዊ ተዋጽኦዎች በሚገባ የተሟለ መሆን ያለመሆኑን መመልከት አስፈላጊ ነው። ከላይ እንደተገለጸው አመልካቾች የተከሰሱት ሽያጩን ከሽያጭ ማሽን በሚወጣው ደረሰኝ መሸጥ ሲገባቸው ከማሽኑ ባልወጣው ደረሰኝ ሽጠዋል በሚል ነው። ለዚህም ተጠሪ ተጥሷል የሚለው የሕግ ማዕቀፍ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው ደንብ ቁጥር 139/1999 ሲሆን ለጉዲዩ ቀጥተኛ አግባብነት ያለው ድንጋጌም በደንቡ በአንቀጽ 5(1(ለ)) ስር የተመለከተው ሁኖ ይዘቱም የሽያጭ መሳሪያውን ጥቅም ላይ ሉያውል የሚችለው በመሳሪያው ለመጠቀም የሚያስችለው ፈቃድ ላይ በተመለከተው የንግድ ስራ ብቻ ነው በሚል በግልጽ ተቀምጧል። በዚህ ደንብ ድንጋጌ መሰረትም የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያውን ገዝተው የመጠቀም ግዳታ ያለባቸው ታክስ ከፊዮች በየምድባቸው መሳሪያውን ገዝተው መጠቀም የሚጀምሩበትን የሚያሳይ የጊዜ ሰላዲ በሕዝብ ማስታወቂያ እንዱወጣ እንደሚደረግ በአስገዲጅነት ደንግጎ ይገኛል። የድንጋጌው ይዘት ሲታይም የሽያጭ መሳሪያውን የመጠቀም ግዳታ ያለባቸው ታክስ ከፊዮች ማስታወቂያው ሲነገራቸው የንግድ ፈቃድ የስራ ዘርፍ በግልፅ ተለይቶ የሚነገራቸው መሆኑን ነው። ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካቾች በወንጀለ ተጠያቂ የሆኑት የንግድ ፈቃዲቸው ወርቅና የብር ጌጣጌጥ በሚመለከት ጥቅምት 01 ቀን 2002 ዓ/ም የወጣው የህዝብ ማስታወቂያ ይመለከታቸዋል ተብል ቢሆንም የንግድ ፈቃደ የሚያሳየው ግን የባህልና የስእል ውጤቶቹን የመሸጥ የንግድ ስራ ፈቃድ መሆኑን ነው።
ስለሆነም ጥቅምት 01 ቀን 2002 ዓ/ም የወጣው የህዝብ ማስታወቂያ የአመልካቾችን የንግድ ዘርፍ ይመለከታል ለማለት የሚቻል ያለመሆኑን ከደንብ ቁጥር 139/1999 አንቀጽ 5(1(ለ)) እና ከወንጀል ሕጉ አንቀፅ 23(2) ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ሁኖ አግኝተናል። የተጠሪ ማስታወቂያ የአመልካቾችን የንግድ ፈቃድ የሚመለከት ካለመሆኑም በላይ አመልካቾች ሽያጩን የፈፀሙት ከማሽን ባልወጣ ደረሰኝ መሆኑ ሲታይ ደግሞ አመልካቾች ድርጊቱን ለመፈፀም የነበራቸው የሒሳብ ክፍል ከድርጊቱ አፈጻጸም አንፃር ላታይ የሚገባው እና ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23(2) ድንጋጌ ይዘትም አኳያ ሲታይም ሕጉ የሚጠይቀው መመዘኛ ያልተሟላ መሆኑን የሚያሳይ ነው። በመሆኑም አመልካቾች ከሃሳባቸው በላይ ሉቀጡ የሚችለበት አግባብ የለም። ሲጠቃለልም ሕጋዊና ሞራላዊ ነገሮች ባልተሟለበት ሁኔታ አመልካቾች በወንጀለ ተጠያቂ መደረጋቸው ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23(2) ድንጋጌ ይዘት ውጪ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመ ሁኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ፣እንዱሁም ሰኔ 24 ቀን 2003 ዓ.ም. የተሰጠው የቅጣት ውሳኔ እና በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ህዲር 20 ቀን 2004 ዓ.ም. የጸናው ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 195(2(ለ-1)) መሰረት ሙለ በሙለ ተሽሯል።
No topics extracted.