No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 20 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ዲሽን ባንክ አ.ማ - ነ/ፈጅ አዱስ ታደለ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ኑረዱን መሐመድ - ጠበቃ አብራር አደም ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በቤት ኪራይ የሚከፈለውን የታክስ ክፍያን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን የፍርድ ባለመብት የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ በመሰረቱት የአፈጻጸም ክስ በግልግል ዳኞች ታይቶ የተወሰነው የቤት ኪራይ ይከፈለኝ ጥያቄ እንዱፈጸምላቸው ጠይቀዋል። ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የፍርድ ባለእዲ የሆነው የአሁኑ አመልካች እንደፍርደ እንዱፈፅም የማይገደድበት ምክንያት ካለው ቀርቦ እንዱያስረዲ ወይም እንደፍርደ ፈጽሞ እንዱቀርብ በማዘዙ አመልካች ቀርቦ የቤቱን ኪራይ በግልግል ዳኞች ውሳኔ መሰረት ለመፈጸም ፈቃደኛ መሆኑን፣ ነገር ግን ለፍርድ ባለመብቱ ከሚከፍለው የኪራይ ገንዘብ 2% የተቀናሽ ግብር በመቀነስ ለመክፈል ቢሞክርም ተጠሪ ግብሩ ሉቀነስብኝ አይገባም በማለት ሉቀበለ ያልቻለ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ገልፆ ተከራክሯል። ፍርድ ቤቱም የግልግል ዳኞች በሰጡት ውሳኔ ተጠሪ ተቀናሽ ግብር መክፈል እንዲለባቸው አልተመለከተም ፣ ማን መክፈል እንዲለበትም አልተጠቀሰም የሚለትን ምክንያቶችን በመያዝ አመልካች ሙለውን ክፍያ ለተጠሪ እንዱፈፅሙ በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል። በዚህ ትዕዛዝ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም አመልካች በአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 53 እና በደንብ ቁጥር 78/1994 አንቀፅ 24(2) መሰረት የተጣለበትን ግዳታ ለመወጣት ተቀናሽ የኪራይ ግብር ለማስቀረት ሲንቀሳቀስ ይህንኑ ለማድረግ ውሳኔ አላረፈበትም ተብል መወሰኑ ሕጋዊ አይደለም በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የበታች ፍርድ ቤቶች በግልግል ዳኞች ውሳኔ አልተሰጠበትም በሚል ምክንያት አመልካች ተቀናሽ የኪራይ ገንዘብ ማስቀረት አይችልም በማለት መወሰናቸው ከአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 53፣ 91 እና 101 ድንጋጌዎች አንጻር ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርበው በሰጡት መልስም አመልካች በግልግል ዳኞች ዘንድ በነበረው ክርክር ተቀናሽ የኪራይ ገንዘብ መኖር ያለመኖሩን ገልፆ ባልተከራከረበትና በግልግል ዳኞች የተሰጠ ውሳኔ በላለበት ሁኔታ የተጠሪ የኪራይ ግብር ከፊይ መሆኑን የሚያሳይ የግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን ማስታወቂያ ሳይኖር ግብሩ ሉቀነስ ይገባል የሚለው የአመልካች ክርክር የፍርድ አፈጻጸም ስርዓቱን ያላገናዘበ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች ባቀረበው የመልስ መልስም የአመልካች ግዳታ ከሕግ የሚመነጭ በመሆኑ ፍርድ አላረፈበትም ተብል በአፈጻጸም መዝገብ የሚታለፍ አይደለም በማለት የሰበር አቤቱታውን አጠናክሮ ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች የተጠሪው በኪራይ ይዞ እንደተገለገለበት እንዱሁም ቤቱም ለአመልካች ጥቅም በአገልግልት ላይ በመዋለ ምክንያት አመልካች ለተጠሪ የኪራይ ገንዘብ እንዱከፍል በግልግል ዳኞች ተወስኖ ይኸው ውሳኔ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰረት እንዱፈጸምላቸው ተጠሪ የአፈፃፀም መዝገብ አስከፍተው አመልካች በፍርድ ባለእዲነቱ ቀርቦ ስለፍርድ አፈፃፀም ሲያስረዲ ለተጠሪ ከሚከፍለው ገንዘብ ውስጥ ተቀናሽ ገንዘብ ሁለት ከመቶ (2%) የሚከፈል የኪራይ ገቢ ግብር ያለ ስለመሆኑ ለተጠሪ ገልፆ ቀሪውን ገንዘብ ለተጠሪ ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ቢያሳውቅም ተጠሪ ፈቃደኛ ያለመሆናቸውን ጠቅሶ ተቀባይነት ማጣቱን ፣የስር ፍርድ ቤት ግብሩ መከፈል ያለበት መሆኑን አምኖና ተጠሪ ለታክሱ ኃላፉነት የለባቸውም ሳይል የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ ያልተቀበለው ውሳኔ አላረፈበትም በሚል ምክንያት ነው። እኛም ጉዲዩን ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
በመሰረቱ ፍርድ የሚፈጸመው በሕጉ አግባቡ ፍርድ ያረፈበት ስለመሆኑ ተረጋግጦ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 378 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ይዘት የምንገነዘበው ጉዲይ ነው።
አመልካች ለተጠሪ ከሚከፍለው የኪራይ ገንዘብ ውስጥ ተቀናሽ ማስቀረት አለብኝ በማለት የሚከራከረው ለአፈጻጸሙ መሰረት በሆነው የግልግል ዲኝነት ፍርድ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ውሳኔ አርፍበታል በሚል ምክንያት ሳይሆን በአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 53 እና በደንብ ቁጥር 78/1994 አንቀፅ 24(2) ድንጋጌዎች በሕግ የተጣለብኝ ግዳታ አለ በማለት ነው። አመልካች በአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 53(1) በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 78/1994 አንቀፅ 24(2) ድንጋጌዎች መሰረት ግብር ተቀንሶ ቀሪ እንዱደረግበት ከተወሰነ ማናቸውም ክፍያ ላይ ግብሩን የማስቀረት ግዳታ (Duty of withholding of Income Tax on payments)ግዳታ አለበት። ይህን ግዳታ ያለመወጣት ደግሞ በወንጀል ተጠያቂነትን ሉያስከትል እንደሚችል የአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 91 እና 101 ድንጋጌዎች ይዘት ያሳያል። ግብር ተቀንሶ ቀሪ እንዱደረግበት በሕግ ከተለዩት ክፍያዎች መካከል ደግሞ የህንጻ ኪራይ ገቢ ስለመሆኑ የደንብ ቁጥር 78/1994 አንቀፅ 24(2(ሸ)) ድንጋጌ ያሳያል። ከተከፊይ ሂሳቦች ላይ ግብርን ቀንሶ እንዱያስቀር በሕግ ግዳታ የተጣለበት ሰው ግዳታውን ለመወጣት በአፈጻጸም መዝገብ በቀረበው ክርክር ቢያነሳ ተቀባይነት ሉያጣ ይችላል ወይ? የሚለው ጥያቄ ሲነሳ ደግሞ ይህንኑ የሚከለክል ሕግ የለም። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 386(2) ስር የተመለከተው ድንጋጌ ሲታይም የፍርድ ባለእዲ የሆነ ሰው እንደፍርደ የማይፈጽምበት ሕጋዊ ምክንያት ካለው ይህንኑ እንዱያስረዲ እድል እንዱሰጠው የሚያደርግ መሆኑ ሲታይ የፍርድ ባለእዲው በሕግ የተጣለበትን ግዳታንም ቢያስረዲ እንደፍርደ ላለመፈጸም በቂና ህጋዊ ምክንያት ነው ተብል ሉወሰድ የሚገባው መሆኑን የሚያስገነዝበን ነው። ከሁለም በላይ የግዳታ ምንጭ ሕግ ፣ በሕጉ አግባብ የተቋቋሙ ውልችና የፍርድ ቤት ውሳኔ መሆኑ የሚታመን በመሆኑ በሕግ የተጣለውን ግዳታ የፍርድ ቤት ወይም ጉዲዩን ለመዲኘት ስልጣን ባለው አካል ታይቶ ፍርድ አላረፈበትም በሚል ምክንያት ውድቅ ለማድረግ የሚቻልበት አግባብ የለም። በሕግ በተጣለበት ግዳታ መሰረት ከተከፊይ ሂሳብ ላይ ግብርን ቀንሶ ያስቀረን አካል ከግብሩ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት ካለው ገቢ ጋር ተያይዞ በተነሳው ክርክር ከገቢው ግብሩን ለመቀነስ እንዱችል የተሰጠ ውሳኔ የለም በማለት በአፈጻጸም መዝገብ ግብሩን ሳይቀንስ ሙለውን ገቢ እንዱከፍል ማስገደድ በሕጉ የተጣለበትን ግዳታውን ለመወጣት በእጁ ያስገባውን ገንዘብ እንዱለቅ የሚያደርግና በውጤቱ ደግሞ ባለግዳታውን ለአላስፈላጊ ውዝግብ የሚዲርግ ነው።ሲጠቃለልም አመልካች በሕግ የተጣለበትን ግዳታ ለመወጣት ሲል ያቀረበው ጥያቄ በአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 53 እና ደንብ ቁጥር 78/1994 አንቀጽ 24(2) ድንጋጌዎች ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 386(2) ድንጋጌ ጋር ተጣምሮ ሲታይ ሕጋዊ በመሆኑ በአፈጻጸም መዝገብ ላይ ፍርድ ሳያርፍበት ሉያነሳ አይችልም በማለት የተሰጠው የበታች ፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 11 ቀን 2003 ዓ.ም.
በትዕዛዝ የፀናው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች በአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 53 እና በደንብ ቁጥር 78/1994 አንቀጽ 24(2) የተጣለበትን ግዳታ ለመወጣት የተቀናሽ ሂሳብ ጥያቄን በአፈፃጸም መዝገብ ላይ ቢያነሳ የሚከለከልበት የሕግ ምክንያት የለም ብለናል። በመሆኑም አመልካች ለተጠሪ ከሚከፍለው የኪራይ ገንዘብ ውስጥ 2% (ሁለት ከመቶ) ተቀናሽ ገቢ ማስቀረት ይችላል ብለናል።
በዚህ ችልት በተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻቻለ ብለናል።
No topics extracted.