No summary available.
ጥቅምት 17 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ የሰባተኛው ቀን አደቬንቲስት ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን የአቃቂ አድቬንቲስት ሚሲዮን ት/ቤት - ጠበቃ ዶ/ር ዘውድነህ በየነ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የአቃቂ ቃልቲ ክፍል ከተማ ወረዲ 01 አስተዲደር ገቢዎች ጽ/ቤት - ዐቃቤ ህግ ቶላኒ ታከለ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ፍ/ቤት የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤትና የከተማው ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የቤትና የቦታ ኪራይና ግብር አፈጻጸም የሚመለከት ነው። የክርክሩ መነሻ የአቃቂ ቃሉቲ ክፍለ ከተማ ወረዲ 1 አስተዲደር ገቢዎች ጽ/ቤት አመልካች 1968 ዓ.ም እስከ 1992 ዓ.ም ያልከፈለው የቦታ ኪራይ የከተማው ቤት ግብርና መቀጮ ብር 734,110.20 /ሰባት መቶ ሰላሣ አራት ሺህ አንድ መቶ አስር ብር ከሃያ ሣንቲም/ እንዱከፈል የግብር ውሣኔ ማስታወቂያ የሰጠው መሆኑን ገልጾ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የግብር ውሣኔውን እንዱያስፈጽም ያቀረበው የአፈጻጸም ክስ ነው።
አመልካች የበጏ አድራጏት ድርጅት በመሆኑ የቦታ ኪራይና ግብር ከመክፈል ነጻ መሆኑን በመጥቀስ ያቀረበውን ክርክር የሥር ፍ/ቤት ባለመቀበል በመወሰኑና የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤትና ሰበር ችልት የስር ፍ/ቤት ውሣኔ በማጽናታቸው ጉዲዩ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችልት ቀርቦ የስር ፍ/ቤት አመልካች ለትርፍ የተቋቋመ ድርጅት ስለመሆኑ ወይም የበጏ አድራጏት ድርጅት መሆኑን አጣርቶ እንዱወሰን ጉዲዩን ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መልሶታል። በስር ፍ/ቤት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰበር መዝገብ ጥር 18 ቀን 2002 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ በሰጠው መመሪያ መሰረት አመልካች የበጏ አደራጏት ድርጅት ስለመሆኑ የበጏ አድራጏት ድርጅቶች ማህበር ኤጀንሲ ማብራሪያ እንዱሰጥበት በማድረግና አመልካች ከተማሪዎች ወርሀዊ ወይም ዓመታዊ ክፍያና የመመዝገቢያ ክፍያ የሚያስከፍል መሆኑን አመልካች በግቢው ውስጥ ገቢ የሚያስገኙ የተለያዩ የጓሮ አትክልት ልማት የድሮ እርባታ የከብቶች ወተትና የወተት ተዋጽኦ ገቢ የሚያገኝ መሆኑን ከዚህ በተጨማሪ ከወፍጮ ቤት አገልግልት ከሱቅና ለስላሣ ሽያጭ ገቢ የሚያገኝ መሆኑን ትምህርት ቤቱ ትፍፊማ ላሆን የሚችል ቢሆንም ባለው ብልሹ አስተዲደር ምክንያት ትፍፊማ እንዲልሆነ በመግለጽ የኪራይና የቤት ግብር ከመክፈል ነጻ የሚያደርጉ የበጏ አድራጏት ድርጅት መስፈርት አያሟላም። ብር 611,798.20 /ስድስት መቶ አስራ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና ስምንት ብር ከሃያ ሣንቲም/ ለፍርድ ባለመብቱ ለተጠሪ እንዱከፍል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአዱስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት አቅርቧል።
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የአመልካችን ይግባኝ አልተቀበለውም። አመልካች የሰበር አቤቱታ ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የሰበር ችልት አቅርቦ የከተማው የሰበር ችልት የአመልካችን አቤቱታ አልተቀበለውም።
መጋቢት 9 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ የአቃቂ አድቬንቲስት ሚስዮን ትምህርት ቤት ህጋዊ ሰውነት ያለው ተቋም አይደለም። ትምህርት ቤቱ በንግድ ህግ ቁጥር 5 መሰረት የንግድ ፈቃድ ከንግድ ቢሮ አውጥቶ የተቋቋመ አይደለም። ስለሆነም ትምህርት ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 80/1968 አንቀጽ 14 መሰረት ከግብር ነጻ መሆን ሲገባው በተጠሪ የተወሰነውን ግብር እንዱከፍል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች በአፈጻጸሙ ክስ ላይ ያቀረበውን የይርጋ መቃወሚያ በማለፊ ከሀያ አራት ዓመት በኋላ የቀረበ ክስ በማስተናገድ የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 384/1/ የሚጥስ በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረምልኝ ይገባል። የስር ፍ/ቤት ይህ ጠቅላይ ፍ/ቤት ጉዲዩን ሲመልስለት እንዱጣራ ትዕዛዝ የሰጣቸውን ጉዲዮች በአግባቡ ሣያጣራ የሰጠው ውሣኔ በመሆኑ በትኩረት ላታይልን ይገባል። የበጏ አድራጏት ድርጅቶችን ማህበራት ኤጀንሲ በዚህ ጉዲይ ማስረጃ የመስጠት ስልጣን ያላለው ሆኖ እያለ በህግ የተሰጠውን ስልጣን በመተላለፍ የሰጠውን አስተያየት መሰረት በማድረግ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መስጠታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው። ስለዚህ ተቋሙ ሀይማኖታዊ ተቋም ሆኖ እያለ ተጠሪ የወሰነውን ግብር እንዱከፍል የሰጠውን ውሣኔ እንዱፈጽም የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በኩል ግንቦት 26 ቀን 2003 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው መልስ የአቃቂ አድቬንቲስት ትምህርት ቤት ከኢትዮጵያ የሰባተኛው ቀን አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን የተለየ ህልውና ያለው የትምህርት ተቋም እንጂ ሀይማኖታዊ ተቋም አይደለም።
የአቃቂ አድቬንቲስት ትምህርት ቤት ከትምህርት ሚኒስቴር ፈቃድ ተሰጥቶት ቁጥራቸው ከሁለት ሺህ በላይ ከሆኑ ተማሪዎች ከፍተኛ የሆነ ክፍያ በማስከፈል የትምህርት አገልግልት የሚሰጥ ተቋም ነው። ትምህርት ቤቱ በስሙ ካሬ ሜትር ቦታ በውል የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃ ከስራና ከተማ ልማት ቢሮ የተሰጠው ተቋም ነው። ትምህርት ቤቱ ከተማሪዎች ከሚያስከፍለው ከፍተኛ ክፍያ በተጨማሪ በይዞታው ሥር ባለ ቦታ ላይ የተለያዩ ምርት እያመረታና የንግድ ስራ እያከናወነ ከፍተኛ ገቢ የሚያገኝ ነው። ትምህርት ቤቱ የበጏ አድራጏት ድርጅት አለመሆኑ በአዱስ አበባ ፊይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የክትትልና ድጋፍ ክፍል ተረጋግጧል። ትምህርት ቤቱ ከሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በርቀት የሚገኝ ከመሆኑም በላይ ለአማኞች የተዘጋጀ የጸልት ማከናወኛ ስፍራ ሣይሆን በሚመለከተው የመንግስት አካል ፈቃድ የተሰጠው የትምህርት ግልጋልት የሚሰጥና ላልች ከፍተኛ የንግድ ስራዎችን የሚያከናውን ተቋም በመሆኑ አመልካች አዋጅ ቁጥር 80/68 አንቀጽ 14 በመጥቀስ የሚያቀርበው ክርክር የህግ መሰረት የለውም።
አመልካች በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 384 በመጥቀስ ያቀረበው ክርክርም የድንጋጌውን ይዘት ያልተከተለ ነው። አመልካች በ1997 በተደረገው ግብር ማሻሻያ መሰረት ተጠሪ ግብሩን አላሻሻልንም በማለት ያቀረበው ክርክር በወቅቱ መሟላት የሚገባቸውን ሁኔታዎች አመልካች አሟልቶ ያልፈጸመ በመሆኑ ክርክሩ ተቀባይነት የላለው ነው። ስለሆነም አመልካቹ ግብር ላለመክፈል ለረዥም ጊዜ ጥረት የሚያደርግ በመሆኑና የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያላለበት በመሆኑ እንዱያጸናልን በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች ሰኔ 21 ቀን 2003 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
አመልካች ትምህርት ቤቱ የሙያ ፈቃድ ያለው መሆኑ ራሱን የቻለ ህልውና ያለው ተቋም የሚያደርገው አይደለም። ትምህርት ቤቱ በቤተክርስቲያኑ ስር ያለ ነው። ቤተክርስቲያኗ ለትርፍ ያልተቋቋመች ናት። በትምህርት ቤቱ የቅጥር ግቢ የጸልት ቤት አለ። አስር ዓመት ያለፈውን ግብር እንድንከፍል መጠየቁ በይርጋ ቀሪ የሚሆን ነው። ግብር እንድንከፍል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክቷል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ በጽሀፍ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ተጠሪ በወሰነው ውሣኔ መሰረት እንዱፈጽም የአዱስ አበባ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተገቢነው ወይስ አይደለም የሚለው መሰረታዊ ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች የቦታ ኪራይና የቤት ግብር የመክፈል ኃላፉነት የለብኝም በማለት የሚከራከረው የከተማ ቦታውንና የቤት ግብር ለማስከፈል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 80/1968 አንቀጽ 14 በመጥቀስ ነው። የአዋጁ አንቀጽ 14 ከኪራይና ከግብር ነጻ ስለመሆን የሚል ርዕስ ያለው ሲሆን በይዘቱም አንቀጽ 14 ንኡስ አንቀጽ 1 ከዚህ የሚከተለት ከኪራይና ከግብር ነጻ ይሆናለ።
ሀ/ የህዝብ መንገድች አደባባዮች መዝናኛዎችና የስፕርት ቦታዎች መካነመቃብር /ለ/ ጸልት ቤቶችና ቅጥር ግቢያቸው ለትርፍ ያልተቋቋሙ የግል ትምህርት ቤቶችና ሆስፑታልች የበጏ አድራጏት ድርጅቶች የመዝናኛና የስፕርት ቦታዎች /ሐ/ ከጠቅላይ ግምጃ ቤት በሚሰጥ በጀት የሚተዲደሩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በማለት የሚደነግግ ሲሆን የአንቀጽ 14 ንኡስ አንቀጽ 2 የዓመት ኪራይ ግምታቸው እስከ ሶስት መቶ ብር የሆኑ ቤቶች ከግብር ነጻ ይሆናለ በማለት ይደነግጋል።
ይህ አዋጅ በመጋቢት ወር 1968 ዓ.ም የወጣ ሲሆን ለጸልት አገልግልት ለመስጠት ታስበው ከተገነቡ የሀይማኖት ተቋማትና ቅጥር ግቢያቸው ውጭ በሀይማኖት ተቋማት ባለሀብት የሆኑባቸው ላልች ህንጻዎችና የንግድ ድርጅቶች የቦታ ኪራይና የቤት ግብር ከመክፈል ነጻ የማያደርግ መሆኑን የአዋጁ አንቀጽ 14 ንኡስ አንቀጽ /ለ/ "ጸልት ቤቶችና ቅጥር ግቢያቸው" በሚል መንገድ ከገለጸው አገላለጽ ለመረዲት ይቻላል። በልላ በኩል የኢትዮጵያ ሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤቱን ያቋቋመችው ትርፍ ለማግኘት አይደለም የሚል መከራከሪያ በአመልካች በኩል የቀረበ ቢሆንም አመልካች ትምህርት ቤቱ ያለትርፍ የትምህርት አገልግልት የሚሰጥ ተቋም መሆኑን የማስረዲት ግዳታና ሀላፉነቱን አልተወጣም። በአንጻሩ ትምህርት ቤቱ ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን ዕውቅና እና ፈቃድ በመጠቀም ከሁለት ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችን በአገሪቱ ውስጥ በትርፍ የተቋቋሙ የግል ትምህርት ቤቶች ከሚያስከፍለት ክፍያ የማይተናነስ ከፍያ እየሰበሰበ የሚያስተምርና ላልች ትርፍ የሚያስገኙ የንግድና የግብር ተግባራትን የሚያከናውን ስለመሆኑ ተጠሪ በቂ ማስረጃ እንዲቀረበ የስር ፍ/ቤት በውሣኔው በግልጽ አስፍሮታል።
ከዚህ በተጨማሪ አዋጅ ቁጥር 80/68 አሁን ያለውን ህገ መንግስታዊ ሥርዓት ጋር ተጣጥመው ከወጡ ህጏች ጋር ተጣምሮ መተርጏምና ሥራ ላይ መዋል አለበት። አዋጅ ቁጥር 80/68 በኢፋዱሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 49 እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየወቅቱ እያሻሻለ ባወጣው የአዱስ አበባ ቻርተር መሰረት የከተማው አስተዲደር ከተሰጠው ህግ የማውጣትና ህግ የማስፈጸም ስልጣን ባገናዘበ መልኩ መተርጏምና ስራ ላይ መዋል ያለበት የህግ ማዕቀፍ ነው።
ከዚህ አንጻር ስናየው በአዱስ አበባ ከተማ ለትርፍ ያልተቋቋሙ የበጏ አድራጏት ድርጅቶች ከአዱስ አበባ የፊይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ጋር ውል እየተዋዋለ የበጏ አድራጏት ተግባራትን የሚያከናውኑ መሆኑንና የአቃቂ አድቬንቲስት ትምህርት ቤት የበጏ አድራጏት ተግባር ለመስራት ከከተማው አስተዲደር ጋር የፔሮጀክት ውል በመዋዋል አገልግልት እየሰጠ ያለ ተቋም እንዲልሆነ በጽሁፍ ማረጋገጫ የሰጠ መሆኑን ከስር ፍ/ቤት ውሣኔ ተረድተናል።
ከዚህ በተጨማሪ አዋጅ ቁጥር 80/1968 አሁን በአገራችን ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ስለሚመዘገቡበትና ስራቸውን ሲያከናውኑ ላደረግ ስለሚገባው ክትትልና ቁጥጥር በዝርዝር የሚደነግገውና የበጏ አድራጏት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲን የሚያቋቁመው አዋጅ ቁጥር 621/2001 ድንጋጌዎች ጋር በተጣጣም መንገድ መተርጏምና ስራ ላይ መዋል ያለበት በመሆኑ የስር ፍ/ቤት ትምህርት ቤቱ በአሁኑ ወቅት በበጏ አድራጏት ድርጅትነት የተመዘገበ ወይም ያልተመዘገበ መሆኑን የበጏ አድራጏት ድርጅቶችና የማህበራት ኤጀንሲን መግለጫ መጠየቁ ተገቢና መፈጸም የነበረበት ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል።
ባጠቃላይ ተጠሪ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 80/68 አንቀጽ 14 /ለ/ ከቦታ ኪራይና ከቤት ግብር ነጻ አለመሆኑን አመልካች ተማሪዎችን ክፍያ በማስከፈል የትምህርት አገልግልት የሚሰጥና ላልች ትርፍ የሚያስገኙ ስራዎችን የሚሰራ ተቋም መሆኑን ተጠሪ አስረድቷል። አመልካች የአቃቂ አድቬንቲስት ትምህርት ቤት ንብረትነቱ የኢትዮትጵያ የሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን መሆኑን በመጥቀስ ትምህርት ቤቱ የራሱ የህግ ሰውነት የለውም ከሚል ውጭ ትምህርት ቤቱ ከላልች ለንግድ ከተቋቁሙ የግል ትምህርት ቤቶች በተለየ ሁኔታ ነጻ ወይም ትርፍ የማያስገኝ ተግባር ሲያከናውን የኖረ መሆኑን አላስረዲም።
ትምህርት ቤቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ዕውቅና ፈቃድ አግኝቶ ትውልድ በትምህርት የማነጽ ሀላፉነት እየተወጣ ባለበት ሁኔታና በትምህርት ቤቱ ካሬ ሜትር ቦታ በይዞታው ስር አድርጏ የሚያዝበትና ለዚህም የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃ ከከተማው አስተዲደር የተሰጠው መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ አመልካች ትምህርት ቤቱ የራሱ የሆነ ህልውና የላለው ተቋም በመሆኑና ትምህርት ቤቱ የተቋቋመው በኢትዮጵያ ሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በመሆኑ ከቦታ ኪራይና ከቤት ግብር ነጻ ላሆን ይገባል በማለት ያቀረቡት ክርክር የአዋጅ ቁጥር 80/68 አንቀጽ 14 /ለ/ ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማና የአዋጁን ድንጋጌ አሁን ካለው ህገ መንግስታዊ ሥርዓት ጋር ተጣጥሞ ስራ ላይ የሚውልበትን ሁኔታ ያላገናዘበ በመሆኑ አልተቀበልነውም።
ከዚህ አንጻር የበታች ፍ/ቤቶች የአቃቂ አድቬንቲስት ትምህርት ቤት የቦታ ኪራይ እና የቤት ግብር የመክፈል ግዳታ አለበት በማለት የሰጡት የህግ ትርጉምና ውሣኔ ተገቢና መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች የይርጋን መቃወሚያ ለማቅረብ የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁ. 384 በመጥቀስ የተከራከረ ቢሆንም ይህ ድንጋጌ ፍርድ ለማስፈጸም የተቀመጠ የይርጋ የጊዜ ገደብ የሚመለከት በመሆኑና ተጠሪ ለአመልካች የግብር ውሣኔ ማስታወቂያውን ከሰጠው በኋላ አስር ዓመት ከመሙላቱ በፉት ተጠሪ የአፈጻጸም ክስ ያቀረበ በመሆኑ ድንጋጌው ለጉዲዩ አግባብነት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል።
የቦታ ኪራይና የቤት ግብር በተመለከተ አዋጅ ቁጥር 80/68 እና በህግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 36/1968 በተቀመጠው ተመን መሰረት የመሬት ኪራይና የቤት ግብር የመክፈል ሀላፉነት ያለበት ተቋም ወይም ግለሰብ ግብሩን በየዓመቱ የካቲት ሰላሣ ቀን ድረስ እንደሚከፍል በአዋጅ አንቀጽ 8 ተደንግጓል። በአዋጁ መሰረት የሚከፈለውን ኪራይና ግብር በተወሰነው ጊዜ ያልከፈለ ግለሰብ ቤተሰብ ወይም ድርጅት ለዘገየበት ለእያንዲንደ ወር የኪራዩን ወይም የግብሩን አምስት በመቶ በመቀጫነት እንደሚከፍል ሆኖም መቀጫው ከዋናው ሂሣብ ከሀምሣ በመቶ መብለጥ እንደላለበት የአዋጅ ቁጥር 80/1968 አንቀጽ 16 በግልጽ ይደነግጋል። በእነዚህ ድንጋጌዎች ይዘት መንፈስና ዓላማ ስንመለከተው አመልካች የቦታው ኪራይ ወይም የቤት ግብር ጥያቄው በይርጋ የሚታገድ ነው በማለት ያቀረበው ክርክር የህግ ድጋፍና መሰረት የላለው በመሆኑ በዚህ በኩል አመልካች ያቀረበውን ክርክር አልተቀበልነውም።
በአጠቃላይ አመልካች ያቀረበው ክርክር የህግ መሰረት እና ድጋፍ የላለው በመሆኑና የአዱስ አበባ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍሬ ጉዲይ ደረጃ መጣራት የሚገባቸውን በማጣራትና አስፈላጊ ማስረጃዎችን በማስቀረብ የሰጠው ውሣኔ ተገቢ መሆኑን በማረጋገጥ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤትና የከተማው የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤትና የከተማው ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ጸንቷል።
በዚህ ፍ/ቤት የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ፍ/ቤት ያወጡትን ወጭ ግራቀኙ ይቻቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.